የሰለመ ንጉሥ አልነበረንም
መልስ ለወንድወሰን ተክሉ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)
እንደመን ሰነበታችሁ? አንድ ርዕስ ለመስራት ስዘጋጅ አንባቢን የሚበክል ዓይን ያወጣ ውሸት ሲሰራጭ ሕዋሳቶቼን ይፈታተኑትና ርዕሴን ትቼ ያላሰብኩበትን ትችት ውስጥ ተጎትቼ እገባለሁ። ባለፉት ወራቶች ውስጥ እየሆነ ያለው እንዲህ ያለ የብከላ ጥበብ /ሳብቨርስ/ ብዛት እየተሰራጪ ነው።
ትንናንት June 17, 2017 አቶ ወንድወሰን ተክሉ የተባሉ ንጉስ ነጋሽ [አል-ነጃሺ]እና የእስልምና አነሳስ በኢትዮጵያ [በወንድወሰን ተክሉ] June 17, 2017 | by ethioexploreradmin Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/30763 በሚል ርዕስ አባይ ሚዲያ በተባለ በግንቦት 7 የመናፍሕ ማሰራጫ ድረገጽ ላይ ያሰራጩትን በምንም መልኩ “አገራዊ ማስረጃ” የማይገኝለትን የታሪክ ብከላ አስነብበውናል።
ጸሐፊው የብከላ ጹፋቸው የጀመሩት ንጉሥ ነጋሽ (አል-ነጃሲ) (ዓረቦች የሚጠቀሙበት ዓረባዊ ቃል ለምን እንደሚጠቀሙ ባይገባኝም) በኢትዮጵያ የነገሥታት ታሪክ ውሰጥ ተዘግቦ የማይታወቅ ስም ነው። ይህ ብከላ አሁን አልጀመረም። የቆየ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስላም የነበረ ወይንም ክርስትያን ኖሮ ወደ እስልምና የተከተለ ንጉሥ በፍጹም በታሪካችን፤በቅርጻችን፤ በነበሩ የወቅቱ ገንዞቦቻችንና ቤተመንግሥቶቻችን ወይንም በነብዩ መሐመድ እና “በንጉሥ አድርአዝ” መካከል የተለዋወጠጧቸው ደብዳቤዎች ውስጥም ይሁን እስላማዊ ንጉሥ እንደነበረ በተላለፉልን ቅሬቶች ላይ ምልክት/ምንጭ አናገኝም።
ወያኔ ከመጣ ወዲህ፤ግብረሰዶማዊያንም ሆኑ ጽንፈኛ እስላሞችና የተለያዩ ጽንፈኛ ጸረ ኦርቶዶክሶች፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የታሪክ ባለቤትነትም ሆነ ማንነት ለመጻረር፤ለመንጠቅ፤ለመበከል ሲሉ ብዙ ሙከራዎች እየተከሰቱ ነው። እስላማዊ ንጉሥ ነበረ አልነበረ ለኔ ትርጉም የለውም። ለብከላ፤ ለክፋት ተብሎ የሚሰነዘር የታሪክ ነጠቃ መፍቀድ የለብንም። ግን ታሪክ በታሪክነቱ መመዝገብ አለበት። ማወቅ ያለብን ግራኝም ነግሦ ነበር’ኮ (አነጋገሡ ግን ያው ክርስትናን ለማጥፋት ነበረ እንጂ። ስለነበረም - አሁን ያለው ብዙውን ያገራችን እስላም የግራኝ የሰይፍ ውጤቶች ናቸው።) ሆኖም የተጠቀሱ ጽንፈኞችና የመሳሰሉ ተገንጣዮችና ግራ ዘመም ፖለቲከኞች፤ እንዲሁም የውጭ ሃይላት፤ የተለያዩ ብከላዎችና ነውሮችን በማስፋፋትና በመበከል የተዋህዶ ቤተክርስትያንን ታሪካዊ ባለቤትነት “ማኦይስቱና ማሌሊቱ” ጸረ ኦርቶዶክሱ ወያኔ ከነገሠ ጀምሮ ብከላው በድብቅ ሳይሆን በአደባባይወጥቷል። በብከላው ዘመቻ አስፋፊዎች በኩል የተበከሉት አንዱ እኝህ ከእኛ እምነት የሆኑ ክርስትያናዊ (? ካልሆኑ ይቅርታ) ከላይ የተጠቀሱ ጸሐፊ ናቸው።
ወቅቱ ረዘም ያለ (ባለስታውሰውም) ቢሆንም ፤ ይህ ነገር በአሜሪካ ድምፅ ቪ ኦ ኤ ትግርኛ ክ/ጊዜ በስፋት ውይይት ተደርጎበት እንደነበረ አስታውሳለሁ። በዚያው ወቅት የቀረቡትን ምሁራን ባስታወስኳቸው ነገሮች እየቀነጨብኩ ላቀርብላችሁ ነኝ። እኔም የማምንበት አቅጣጫ ስለነበረበት።
ከጥቂት አመት በፊት ግርማይ ገብሩ የተባለ የአሜሪካ ድምፅ የትግርኛ ዘጋቢ፤ ይህንን በሚመለከት በፕሮግራሙ ዝግጅት ያቀረበው ላስታውሳችሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክረስትያን፤ብከላ ሲበዛባት “ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባ እውነታ” የሚል መግለጫ አውጥታ እንደበር እናስታውሳለን። በዚያው መግለጫ ውስጥ እንዲህ ይላል።
“በ6ኛው/7ኛው ክፍለ ዘመን እስላምና የተቀበለ ንጉሥ እንደነበረ ባሁኑ ወቅት በተደጋጋሚ እየተነዛ ያለ ጉዳይ ስለሆነ ይህ ደግሞ ያልተፈጠረና የማይታሰብ ጉዳይ መሆኑን ሕዝብ እንዲያውቀው ያስፈልጋል። በተጠቀሰው ወቅት፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እስላም የነበረ ንጉሥ ወይንም ክርስትያን የነበረ ያሰለመ ንጉሥ እንደነረ በጉምጉምታ ይነገር እንደነበር ቢታወቅም፤ ባሁኑ ባለንበት ወቅት ግን በግልጽ ከተለያዩ ወገኖች በጽሑፍ መግለጫና ተቃውሞ እየተሰጠ ነው።
ኦርቶዶክሲያዊት ኢትዮጵያ ከ3ኛ ከ/ዘመን እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ነግሠው የነበሩ ነገሥታቶች ሥም ዝርዝራቸው በጽሑፍ በመመዝገብ ማቆየቷ የታሪክ እውነታ ነው። በዚያው ወቅት “አልነጋሺ” ወይንም “አሕመደል ነጋሽ” የተባለ ንጉሥ እንዳልነበረም። ነበረ ብሎ ማመን የተፋለሰ ታሪክ መሆኑ አዲሱ ትውልድ መረዳት አለበት።” ብላለች።
ዓረቦች የኤርትራን ምድራዊ ቀጠና ዓረባዊ ነው ብለው በካርታቸው እንዳስገቡት ሁሉ (ዛሬም በካሃዲው በትግራይ ተወላጁ በኢሳያስ አፈወርቅ ዛሬም ያንን ለማስቀጠል የዓረብ ሊግ አባል እንደሆነው ሁሉ፤ የዓረብ ጸሃፊዎችም በሃይማኖት ጣልቃ ገብነትም በቆየው ጥንታዊ ሴራቸው ለእንዲህ ላሉ “ተበካዮች” ሲገልጹ አሰለመ ወይንም እስላም ነበር የሚባለው “አስሓማ ኢቡር አድሑር” የሚባል ንጉሥ ነው። ይሉዋቸዋል (እንደ እነ ኢትዮጵያዊው ቡሽራ ሸኽ ያሕያ ዓይነቶቹ ያንን “የፈጠራ” ስም ከዓረቦች ቀድተው ተጠቅመውበታል)። ማን ነው “አስሓማ ኢቡር አድሑር” የሚባለው? ሲባሉ ደግሞ እነ ቡሽራ ሸኽ ያሕያ “ንጉሥ አድርአዝ” ብለው የሚጠሩት ንጉሥ ነው “አስሓማ ኢቡር አድሑር” ማለት ሲሉ ጽፈዋል። ከላይ የተጠቀሱት አቶ ወንድወሰን የተባሉ ጸሐፊ “አሕመደል ነጋሽ” የሚል ባይጠቀሙም (አልነጋሺ) የሚበላውን ነው እስላም ነበር የሚሉን። ያውም ጸሐፊው ያለ ምንም ሰቀቀን አሰለመ ወይንም እስላም ነበር የተባለው ንጉሥ ብዙዎቹ ነገሥታት ከነገሡበትና ከሚቀበሩበት መናጋሻ ከተማው ከአክሱም ውጭ እንደነበረ ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፤
“በትግራይ ክልል በውቅሮ ወረዳ ከውቅሮ ከተማ 11 ኪሎሜትር ርቅት ላይም ከተሰደዱት 15 እስላም ስደተኖች ሬሳ አብሮ ከእስላሞቹ ጋር ሬሳቸው ተቀብሯል።” ሲሉ ብከላቸውን አሰራጭተዋል። ያውም ጸሐፊው ‘እስላማዊ የዓረብ/የመካ/ ስደተኞችን” ያስተናገዱ ንጉሥ ከማለት ይልቅ “እስልምና” ወደ ኢትዮጵያ “እንዲመጣ የፈቀደ” ንጉሥ ነጋሽ እያሉ፤ በዕቅድ አቅደው እስልምና እንዲመጣ እንዳደረጉ ነው የጻፉት”። ንጉሡ መጠለያ ስለተጠየቁበት ነበር የፈቀዱት እንጂ እስላሞች ስለሆኑ ወይንም ስላልሆኑ አይደለም የፈቀዱት፡ ወይንም እስልምና ለማስፋፋት ፈቃድ ለመጠየቅ አይደለም የመጡት/የተፈቀደላቸው። ሃይማኖት ባይሆንም ማለትም፤ ሌላ መነሻ ኖሮ ቢሆንም ከመፍቀድ አይቦዙኑም ነበር። ስለሆነም ከሃይማኖት ጋር የመፍቀድ አለመፍቀድ ባይያያዝ ጥሩ ነው (በነብዩ ደብዳቤዎች ውስጥ ሃይማኖት ነክ አይጠቅስም)። ይህ ንጉሥ (አድርአዝ) ነው አሕመደል ነጋሽ (አል ነጋሺ/ንጉሥ ነጋሽ) የሚባለው እያሉ የጻፉትን በዝርዝር ቆይተን እንገባበታለን።
ይህ ብከላ ወያኔዎች ሆን ብለው በሚዲያቸው በቴ/ቪዥን፤ራዲዮና በጋዜጦቻቸው፤በ7ኛው ክ/ዘመን አሕመደል ነጋሽ (አል ነጋሺ) የሚባል እስላማዊ ንጉሥ ነበር የሚሉ ብከላዎች በአክራሪዎቹ በኢትዮጵያዊው በእነ ዑስታዝ አሕመድ በኩል (ዛሬ ክርስትያን ይጥፋ እያለ ካሰውዲ በእስላሞቹ ፓልቶክ የሚሰብከው ሽብርተኛ) ተዋናይነት በኩል በማሰራጨት ብከለው ሲያበረታታ እንደነበር የምናስታውሰው ነው (ሌላ ቀርቶ ቢላል የሚባለው ቲቪ/ራዲዮን (“እዚህ ውጭም አገር ያንኑ ያሰራጭ ነበር” ከኢትዮጵያ ሚዲያ ባገራችን ካርታ አናት ላይ ኮከብ እና ጨረቃ ምልከት በማስቀመጥ “ወያኔ” ብከላቸውን ሲፈቅድ እንደነበር ይታወቃል)። ይህ ወደኋላ ስለምመጣበት አሁን ወደ አቶ ወንድወሰን ተክሌ ስመለስ፤ ኦቶ ወንድወሰን እንዲህ ይላሉ፡
“እንደ ዜና መዋእለ ነጋሽ ታሪክ ከሆነ ከዓረቢያ ምድር የመጡት 15ቱ ዓረብ እንግዶች እምነት በአንድ ክፍላተ ዓለሙን [ዩኒቨርስ] በፈጠረ እማይታይ፣እማይጨበጥ ፈጣሪ አምላክ እንደሚያምኑ መግለጻቸውን ያትታል።” ይላሉ።
“መዋእለ ነጋሽ” የሚባል እኔ ለመጀመሪያ ጆሮየ ነው እየሰማሁ ያለሁት። በቤተክርስትያኒቷ የታሪከ ነገሥት/የነገሥታት ታሪክ በየትኛው እንደተገኘና ጸሐፊው ማን መሆኑን ቢገለጹልን እንማርበታለን።
ቀጥለውም እንዲህ ይላሉ፤’
“በ613 ዓ.ም ነቢዩ መሀመድ የእስልምናን እምነት ባወጁበት ወቅት ወገኖቻቸው ጣኦት አምላኪዎች አልተቀበላቸውም ነበርና ከመካ መዲና ለመባረር ቻሉ። የመካ መዲና ሕዝብም በተከታዮቻቸው ላይ ጦርነት በማወጁ እሳቸውና ተከታዮቻቸው ጭንቅ ውስጥ ገቡ ። ……….በትግራይ ክልል በውቅሮ ወረዳ ከውቅሮ ከተማ 11 ኪሎሜትር ርቅት ላይም ይህንን የእስልምናን ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን የፈቀደን ንጉስ ነጋሽ ለማስታወስና ለመዘከር አል-ነጃሺ መስጊድ ተገነባ። መስጊዱ በእስልምና እምነት ተከታዩች ዘንድ ከኢትዮጵያ ከአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ ከዓለም ከመካ መዲና እና ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ በ3ኛነት ደረጃ ላይ ያለ ቅዱስ ስፍራ እንደሆነ ይታመንበታል።” ብለዋል።
እኔም ቦታው በደምብ አውቀዋለሁ። ስለ ንጉሡ በዚች እጅግ በጣም ትንሽ ገጠር ሬሳው አብሮ ከእስላሞቹ ጋር መቀበር እጅግ አስገራሚ ነው። ንጉሡ እዛው ሥፍራ ይኖር ነበር? ወይስ አክሱም ከተማ? አክሱም ከሆነ (ሁሉም ነገሥታቶች መዲናቸው እንደሚያደርጉት ሁሉ) ንጉሡ ሲሞት ወዲያውኔ ይቀበራል እንጂ ከሁለት/ሦስት ቀን የእግርና/የጋማ/የአጋሰስ ጉዞ ወደ እሚፈጅ አድካሚ ርቀት ወደ “ውቅሮ” ከተማ ለቀብር ተጉዟል ለማለት ከሃይማኖታቸው ሕግ አንጻር አያስኬድም። ነበር ከተባለስ እዚያው አካባቢ ተመሳሳይ መስጊዶች ሌሎች መስጊዶች ለምን አልተገነቡም? ንጉሡ አልነጋሺ ከተማ/ውቅሮ/ ነበር የሚኖሮው ከተባለ ደግሞ፤ እንደ ንጉሥ ሲኖርበት የነበረ ቅሪት /ቤተመንግሥት/ገንዘብ/ እስላማዊ የንጉሡ ማመላከቻ አሰር/ኮቴ/ አንዲት ነገር የለም። ጸሐፊው የንጉሡ “አድራዝ” (ንጉሥ ነጋሽ ብለው የሚጠሩት ጸሐፊው) ሬሳ መኖሩን መስጊዱ ይነግረናል ብለዋል። ምን ተብሎ እንደተጻፈ እና ጸሐፊውንም ሆነ በመቃብሩ ላይ ምን እንደሚል አልነገሩንም፤የተጻፈውስ መቸ ነው? 15ቱ ሬሳዎች በአንድ ጉድጓድ ናቸው የተቀበሩት? ወይስ ለየብቻ? ለየብቻ ከሆኑ “የንጉሡ” መቃብር አቶ አስፋወሰን ተክሉ ወይንም አቻዎቻቸው በፎቶግራፍ ቀርጸው ያሳዩን።
ይህች ትንሽ ዳገት ላይ ተጠግታ የተገነባች መስጊድ (ገጠር) እንኳን የጊዜው ገናና ንጉሥ የሚያክል ሊኖርባትና ሊቀበርባት ቀርቶ ‘ዛሬም’ እጅግ ትንሽ የሆነች ብቸኛ የገጠር መንደር ነች። በስፍራው ንጉሳዊም ሆነ ጥንታዊ ቅርስ የሚባል ተፈልጎ አይገኝባትም። ለብቻዋ ተነጥላ በመኪና መጠምዘዣ ትንሽ ዳገት ዳር ተጠግታ የምትታይ አንዲት “ትንሽዬ” መስጊድ ብቻ ነች (አሁን በቀለም በግንብ አሳምረዋታል)። ከዓለም ሦስተኛ የሚያደርጋት ቅዱስ ስፍራ ነገር ሊኖራት ይችል ይሆናል። ሆኖም እስላማዊ ንጉሥ የተቀበራበት አካባቢ ሆና ብትሆን ኖሮ ልክ ሐረር 4ኛ እስላመዊ ቅዱስ ሥፍራ እንደምትባለዋና እንድታበልም ምክንያት የሆነው (the greatest concentration of Mosques per Square Kilometer/ km2/) ሐረር ውስጥ የሚገኙ የመስጊዶቹ እጨቃ/መጨናነቅ ከሌለው እስላማዊ/ዓረባዊ አገሮች ሲወዳደር (መረጃየ ካንድ የፊልም ዘጋቢ “በደርግ አስተዳዳር ዘመን” የተሰራ የፊልም ዘገባ ያገኘሁት ነው) እጅግ የታጨቁ መሆናቸውን የሚያሳየን ምክንያት፤ከሌሎቹ ከተሞቻችን ብዙ እስላም ተከታዮችና መሪዎች ስለሚኖሩባት ነው (ከሌሎች ምክንያቶች ተጨምረው)። ወደ ትግራይ አልነጋሺ መስጊድ ስንመለከት ግን ይህንን መሳይ የመስጊዶች እጨቃ/ብዛት/ ቀርቶ ካጠገቡም ሌላ መስጊድ አልታየም፤አለነበረም። ንጉሡ እስላም ከነበረ፤ ቤተክረስትያናትና ገዳማት ልክ እንደ ክርትያን ንጉሦች በብዛት በርካታ መስጊዶች መግንባት ይችል ነበር። ንጉሥ እስላም ከነበረ የተቀበረበት አካባቢም ሆነ ባገሪቱ ላይ እንደ መስጊዷ የመሳሰሉ በርካታ መስጊዶችና ተከታዮች እንመለከት ነበር። ግን ያ የለም። \
ስለሆነም፤ አቶ ወንድወሰን ተክሉ፤--
“በዚህ ታሪካዊ እና ጥንታዊ መስጊድ ውስጥ የንጉስ ነጋሽ እና የ15ቱ የነቢዩ መሀመድ ተከታይ ሱሀባዎች አጽም በክብር ተቀብሮ እንዳለ የጥንታዊው መስጊድ ታሪክ ይናገራል።”
የሚሉት አባባል ጸሐፊው የንጉሡ ሬሳ የተቀበረበት ስፍራ ነው የሚል “የጥንታዊ መስድ ታሪክ” ሥፍራ በሚል አጠቃላይ እንጂ የንጉሡ ሬሳ በተለይ የተመለከተ መቃብር ማስረጃው አላቀረቡልንም። በስፍራው የተመራመሩ ታሪክ አጥኚዎችም ይህንን አላየንም ነው የሚሉት።
አስገራሚው የአቶ ወንድወሰን ተክሉ አስተምህሮ ደግሞ የሚከተለው ነው፡
“በዘመነ ነጋሽ የነበረችው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ክርስትና እና በከፊል ደግሞ ጁደይዝም[የአይሁድ እምነት] እንደነበረ በታሪክ መዛግብት ተጽፎዋል።” ይላሉ እና ትንሽ ሳይቆዩ አከታትለው፤ ( ቢጫ ቀለም የኔ)
“ኢትዮጵያም ከመካ በፊት እስልምናን በይፋ በ615ዓ.ም ላይ የተቀበለች የመጀመሪያ አገር ሆነች።” ይሉናል። (ቢጫ ቀለም የተጨመረ)
በጣም አስገራሚ!! ስደተኞቹ በመጡ በሁለት አመታቸው፤ወይንም ወዲያውኑ እንበለው ኢትዮጵያ “በይፋ” እስልምና የተቀበለች የመጀመሪያ አገር ሆነች? እንዴት እንዲህ በቀላሉ ሊሆን ቻለ? ይፋ ማለት ምን ማለት ነው? በአዋጅ ነው? አዋጅ ከሆነ ከየትኛው ንጉሥ? በ613/615 የተገነቡ መስጊዶች ስንት ነበሩ / የትስ ነበሩ? በማንስ ፈቃድ ነው ሕዝቡ እስልምና የመከትል መብት አላችሁ ብሎ ፈቃድ የሰጠ? አዋጅ/ይፋ/ ሲሆን ክርስትናም ሆነ አይሁዳዊ እምነት በማን እና በየትኛው ወቅት እንደተሰበከና ፈቃድ እንዳገኘ ማረጋገጥ ይቻላል። ያ ከሆነ፤ እስላማዊ እምነትም ይፋ አንዲሆን የፈቀደ ንጉሥ እናውቅ ነበር? እስልምና ይፋ የሆነው የአረቦች የአክሱም ከበባ ወቅት ነው (እንደ ግራኝ አህመድ የመሰለ በሰይፍ የተደገፈ ዘመቻ!!)። በወቅቱ ክርስትያኑም ሆነ አይሁዳዊው ለመሰለም “ሰይፍ” እንጂ ሰበካ እንደማይለውጠው የታወቀ ነው። ክርስትያኑ ግራኝ አሕመድን የታገለው “ላለመሰለም ነው”።
የተበከሉት ሊቃውንቶቻችን ለማሳመን እንደሚጥሩት እና ኢትዮጵያ የእምነት ዲሞክራት ነበር ለማለት፤ እንደሚነገረው ሁሉ፤ ለማሳመር የተቀረጸ ዲስኩር ካልሆነ፤ እስላማዊ ሃይማኖት በየትኛውም የጥንት ክርስትያነዊ ንጉሥ በሕዝቡ ላይ እንዲገባ በቸልተኛነት ያለፈ ንጉሥ እኔ አላውቅም (መሐመድ የከተበለትን ንጉሥ ጭምር)። ስደተኞችን ማጥለል/ማስተናገድ እና እስልምናን እንዲስፋፋ ማድረግ ለየቅል ነው። እንኳን በእስልምና ሊፈቀድ ቀርቶ በክርስትና እና አይሁድ ተከታዮች ውስጥም ስንት ፍጨትና ፍጅት እንደተደረገ የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያ በ615 እስልምናን በይፋ ተቀበለች የሚባል ወሬ ለፖለቲከኞች መጠቀሚያ ዘዴ (ኤክስፕሎይተቲቭ-ታክቲክ) እንጂ በእኛ በተራ ዜጎች ተቀባይነት የለውም።
ጸሐፊው ይህ ሁሉ ሲተነትኑ፤ የትኛው የታሪክ መጻሕፍት እየጠቀሱ እንደሆነ አልነገሩንም። ሆኖም መሐመድ ተከታዮቹን የላካቸው ጸሐፊው እንደሚጠሩት “ዘመነ ነጋሽ” የሚባለው ከላይ እንደጠቀስኩት ንጉሡ ወደ እሚያስተዳድረው ወደ ነበረው ወደ አክሱም እንጂ ንጉሡ ተቀብሮበታል ወደ እሚሉን ወደ “ውቅሮ መስጊድ አይደለም”። ስለሆነም፤ ንጉሡ እዛቺው “ገጠር ውስጥ” የሚኖርበት ምክንያት/ጣጣ/ቢዝነስ/ የለውም። እስላማዊ ዐረቦቹ የመጡት እንደ ጸሐፊው እምነት በ613 ከሆነ ‘እስልምና’ ተከታዮች የተባሉት ስደተኞች ወዲያውኑ ንጉሱን የማስለም አቅም ሊኖራቸው አይችልም። ሆነ ከተባለም ንጉሡ (በእኛ መጽሐፍ የሚታወቅ ንጉሥ ‘አድርአዝ’ ) የነገሰው ከ600 እስከ 622 ነው። ዓረቦቹ ከመጡ ወዲህ “አድርአዝ” ሥልጣን ላይ የኖሮው 9 አመት ብቻ ነው። እሱ የፈቀደላቸው እምነታቸው በሰላም መከተል እንደሚችሉ እና ለተጠየቀው ጠላቶቻቸው መልሶ እንደማያስረክባቸው እንጂ “ህዝቤን የመስበክ” መብት ሰጥቻችኋላሁ የሚል አይገኝም።ከዚያ አገር ሰላም ሲሆንላቸው ተመልሰው ወደ ሳውዲ አገራቸው ሄዱ።
መተማመን ያለብን ከሜካ የመጡ ዓረባዊ ስደተኞች/የመሓመድ ተከታዮች ጥገኝነት የፈቀደላቸው ንጉሥ “አድርያዝ” መሆኑን በእኛው የነገሥታት መጽሐፍ አለ (ወቅቱን ስናስተያየው)። በተጠቀሰው ዘመን የነበረው ንጉሥ ማን እንደነበር ሊቃውንቱ ሲገልጹ “አድርአዝ” እንደነበር ነው፤በ622 አካባቢ የነበረ ማለት ነው። ይህ ነጉሥ ነው እስላም ነበር የሚሉን። ዓረቦቹ (መራግሕሽ) ጥገኝነት ጠየቁ የተባለበት ውቅት የነበረው ንጉሥ ‘አድርያዝ’ እንጂ “አልነጋሺ/ንጉሥ ነጋሽ/አሕመደል ነጋሽ/ የሚባል ንጉሥ አይታወቅም። ባጭሩ የኛ ሊቃውንት የሚነግሩን፤ አል ነጋሺ የሚል መረጃ እስካሁን ድረስ የለም። አልነጋሽ፤የሚባል እኛ የምናውቀው አፈታሪክ “እንደ መስጊድ” ወይንም “ትልቅ “የሃይማኖት አባት” ወይንም “የሃይማኖት ቦታ” እንጂ በወቅቱ በኛ በኩል የሚገኙ ጥንታዊ መረጃዎች እንደ ንጉሥ የተገለጸ ጽሑፍ የለም።
አቶ ምትኩ የተባለ አዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ ወጣት ምሁር ከትግርኛው የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኛ ከግርማይ ገብሩ ጋር ከጥቂት አመታት በፊት በትግርኛ ያደረገው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ይላል።
“የኔ ጥናት ያደረግኩት ይህንን ለመመርመር በርካታ መጽሐፍቶችን ተመልከቼአለሁ፤ እንዲሁም በሁለቱ ማለትም በንጉሡ እና በነብዩ መሐመድ በኩል የተለዋወጧቸው ደብዳቤዎች ሁሉም አንድ ባንድ ተመልከቼአቸዋለሁ።የደብዳቤዎቹ ይዘቶች የሚገልጹት በወቅቱ የነበሩ ስደተኞች ስለ ማስተናገድና ጥገኝነት ስለመስጠት በሚመለከቱ ጉዳዮች ካልሆነ በቀር፤ በሃይማኖታዊ ነክ የተመሰረቱ ወይንም የተመለከቱ ክርክሮች ወይንም የሃሳብ ልውውጦች በደብዳቤዎቹ ውስጥ አይታዩም።
እስካሁን ድረስ በመረመርኳቸው መረጃዎች ውስጥ አህመደል ነጋሽ ወይንም አልነጋሺ የሚባል ንጉሥ ወይንም ከክርስትና ወደ እስለምና ያሰለመ ንጉሥ ነበር የሚል ፈጽሞ አላገኘሁም። ብዙዎች ጥናቶች አልነበረም ነው የሚሉት። ምክንያቶቻቸውን ሲዘረዝሩ
‘የወቅቱ ሁኔታ /መሬቱ ላይ/ የነበረው ሁኔታ የሚፈቅድ ኣልነበረም። ሌላው በደብዳቤዎቹ በግልጽ እንደሚነበቡ የስደተኞቹ መስተንግዶ ጉዳዮች ብቻ ነቻው ያተኮሩት እንጂ፤ ነብዩ መሐመድ ወደ ሌሎቹ አገሮች እንደላካቸው ሃይማኖታዊ ነክ ደብዳቤዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተለዋወጣቸው ደብዳቤዎች አታገኝም።
ማለትም ወደ ግብፅ፤ሶርያ፤ሮማ ደብዳቤዎች ተጽፈዋል። ወደ ተጠቀሱት አገሮች የታለኩ እና ወደ አክሱም ንጉሥ የተላኩ ደብዳቤዎች የተለዩ ናቸው። ምን ይላል “ተቀበላቸው አስተናግዳቸው” የሚል ሃሳብ እንጂ አዲስ ሃይማኖት አለን፤ ተቀበል፤እመን ..የሚል ጽሑፍ የለውም። የደብዳቤዎቹ ዋና ይዘት “እነዚህ ስደተኞች /እንግዶች እባክህን ተቀበላቸው” ነው የደብዳቤው ትኩረት። ብዙዎቹ በአገር ውስጥ ጸሐፊዎች እንደ እነ ቡሽራ ሸኽ ያሕያ እንደ እነ ዶ/መሐመድ የመሳሰሉ የተጻፉ ክርክሮች ፤መጽሐፍቶች እና በውጭ ሰዎች የተጻፉም አይቻቸዋለሁ። ከዳረግኩዋቸው ጥናቶች ምንም መረጃ የላቸውም።” ሲል ጥናቱ ግልፅ አድርጓል። ምርምሩም በቅርብ እንደሚታተም ገልጿል።
ሌላም ልጨምርላችሁ፤- መቀሌ ክሳቴ ብርሃን የቤተክህነት ሊቅ እና መምህር የሆኑት መቀሌ ያለው የ ቪ ኦ ኤ ትግርኛ ወኪል ግርማይ ገብሩ ስለ ጉዳዩ አነጋግሮአቸው፤ መልሳቸው እንዲህ ነበር፡
“እየተጠቀሰ ያለው ዘመን ክርስትና ገና በጣም ትኩስ በነበረበት ወቅት ነው። በ6ኘው ክ/ዘመን ማለት ነው። መሐመድ በ570 ዓ.ም ነው የተወለደው፤ከዚያ በ40 አመቱ በ610 ዓ.ም ነው እንቅስቃሴው የተጀመረው። እየተጠቀሱ ያሉት ንጉሥ አድሪያዝ ደግሞ ከ600 እስከ 623 ዓ.ም ነው የነበሩት።
መረዳት ያለብን። እንኳን አንድ ንጉሥ ከክርስትና ወደ እስልምና የሚያከል ሲያሰልም፤ አንድ ኗሪም በወቅቱ ሲሰልም ያለተቃውሞ በሰላም የሚሰልምበት ህዋ የሚፈቅድ አይደለም። ወቅቱ ማየት፤መገመት አለብን። ንጉሡ አክሱም ውስጥ ነው መኖርያቸው፡ ሲሰልሙ፤ ከነ ሠራዊታቸው ነው? ከመላ አካባቢው ሕዝብ ጋር ነው የሰለሙት? ከነ ልጆቻቸው ጭምር ነው የሰለሙት? ሕዝበ ክርስትያኑስ ምን አላቸው? ተቃዉሞ ነበር? ከነበረስ ለምን አልተመዘገበም? የሚሉ ነገሮችን መጠየቅ አለብን። በሰላምም ቢሰልሙ አንዲት ነገር የሚያመላክት አሳማኝ ነገር አላገኘንም። ለሕሊናም መቀበል ይከብዳል። …’’
“ …በታሪካችን እስልምና የተቀበለ ወይንም የሰለም ንጉሥ አልነበረም። ጭራሽኑ ንጉሥ ነጋሽ የሚባል ነጉሥም አልነበረም። በአክሱም ዘመነ መንገሥትም ሆነ በአክሱም ከተማ እስላም የነበረ ንጉሥ ጭራሽኑ አልነበረም፤ የማይታሰብም ነው።
ኦርቶዶክስ ቤተክረስትያን ስለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጪ ማን አደረጋት ስለሚሉ ወገኖች እንዲህ ይላሉ፤-
“የግንዛቤ ጉድለት ያለ ይመስለኛል።ተወደደም ተጠላም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ ከቤተክርስትያኒቷ ጋር የተያያዘ መሆኑን መታወቅ አለበት። ጠብቃ ያቆየቺው እርስዋ ነች። እስከ ቅርብ ጊዜም ቤተከርስትያኒቷ እና መንግሥት አንድ አካላዊ ግንኙነት የነበሩ ናቸው። እስከ ቀ/ሃ ዘመን ድረስ። ስለዚህ ጥልቅ ማለት ሳይሆን፤ ታሪኳ ስለሆነ ነው! የረሷ ታሪክ ነው። ታሪኳ ስለሆነ አሁንም እንዲጠበቅ ሐላፊነት አለባት።ለሚሰነዘረው አግባብ የሌለው ፈጠራ የመከላከል ሐላፊነት አለባት።” ሲሉ የመቀሌ ክሳቴ ብርሃን ሊቅ ገልጸዋል።
የትግርኛው ዘጋቢ ግርማይ ገብሩ በማስከተል እንዲህ ይላል። ማሕበረ ቅዱሳን መቀሌ ከተማ ውስጥ አዘጋጅተውት በነበረው አወደራዕይ (አግዚብሽን) የነብዩ መሐመድ የተላኩ ስደተኞች የተቀበለ እንጂ እስልምና የተቀበለ ንጉሥ አንዳልነበረ በወቅቱ የቀረቡት ማስረጃዎች ለጎብኝዎች ቀርበዋል።
በቅርቡ ይላል ጋዜጠኛው። ዐለም አቀፍ እስላማዊ የዜና አግልግሎት ማእከል በመባል የሚታወቀው ‘ዩኒሴፍን’ ምንጭ በማድረግ ያስተላለፈው ሰርጭት ከ1400 አመታት በፊት ከነቢዩ መሐመድ የተላኩ ስደተኞች እስላሞች የተቀበላቸው “አሕመድ ነጋሽ” የተባለ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ነበር፡ ሲል አስተላልፎ ነበር።
የቤተክርሰትያን ሊቃውንት የሚሉት ፤
“በዚህ ወቅት እየታየ ያለው ነገር መቻቻል ሳይሆን መደበላለቅ ነው። ይላሉ”። መቻቻል ማለት ሁሉም የዬራሱ ሃይማኖት ይዞ ተቻችሎ ተደማምጦ ተስማምቶ መኖር ማለት ነው። አንዱ ወዳንዱ ክርስትያን ኖሮ እስላም ሆነ የሚል የመቻቻል ምልክት ሳይሆን ፤መደበላለቅ፤መዋሃድ፤መነካካት፤መነቅነቅ ይባላል። የያራሳችን ታሪካችንን ይዘን ተከባብረን ብንዋሃድ ጥሩ ነው፤ታሪካችንም ያምራል፤ ትክክል ይሆናል።እንዲህ ስንል ግን ይጠቅመኛል የሚለውን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች እንደ እየሰው አግልግሎት ይጠቀመብቻዋል። ከጠቀመው ይሂድበት፤ ነገር ግን ነጠቃ መኖር የለበትም፤ መደበላለቅ የለበትም። በማለት ተቃውሞአቸውን ይገልጻሉ።
ጨረስኩ!
አመሰግናለሁ
ጌታቻው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ- Ethio-Semay) getachre@aol.com