Monday, November 1, 2021

ወያኔን አግቶ እየተዋደቀ ያለን ሕዝብና የአብይ አሕመድ እይታ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 11/1/2021

 

ወያኔን አግቶ እየተዋደቀ ያለን ሕዝብና የአብይ አሕመድ እይታ

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay)

11/1/2021

ህጻኑ አብይ አሕመድ ጦርነቱን አስመልክቶ ትናንት አሽከሮቹን ሰብስቦ ባነጋገረበት ወቅት በኢቲቪ ያስተላለፈው ንግግሩን በመጥቀስ ልጀምር። እንዲህ ይላል፦

 “ኢትዮጵያዊ ዝርያ የሌላቸው “ነጭም ጥቁርም” የውጭ ዜጎች ከወያኔ ጋር ወግነው ወሎ ድረስ በመምጣት ኢትዮጵያን ለማፍረስ  “መስዋእትነት ከፍለዋል” ጥያቄው  “ኢትዮጵያዊ  የሆነ ሰው አገሩን ለማዳን ምን ያሕል ዝግጁ ነው?” ምን ያህል ተግቶ እየሰራ ነው? የሚለው ጉዳይ ለሁላችን የሚተው ጉዳይ ይሆናል።”

በማለት እራሱ ስለ ጦርነቱ ያለው ትኩረት ከመመርምር ይልቅ ሕዝቡን የመውቀስ ሱሱ ዛሬም ሕዝቡ ምንም ትኩረት እያደረገ እንዳልሆነ ይናገራል።

ሰሚ የለም እንጂ ይህ ህጻን መታከም ይገባዋል ብለናል። ባለፈው ሁለት  ሳምንት “ዝመት ታጠቅ ማለት አያስፈልግም፡ እናንተ የክልል መሪዎች ሕዝቡን ታጠቅ ዝመት ተደራጅ አትበሉት ፤ ይህን አያስፈልገንም ፤ወደ ጎመን ቲማቲም ችግኝ ተከላ ነው ዝመት ማለት ያለባችሁ” እያለ ሕዝቡ ለጦርነቱ እንዳይታጠቅ፤ እንዳይዘምት ሲናገር ቆይቶ አሁን ሕዝቡ ምን ያህል ዝግጁ ነው? እያለ ሕዝቡን ሲተች መስማት ይህ ሰው በተደጋጋሚ እንዳልው “ጤኛ አይደለም” ወደ ሕክምና መወሰድ አለበት።

በጦፈ ጦርነት ውስጥ ባለበት ከሁለት ሳምንት በፊት ”አትዝመቱ ፤አትሰልጥኑ፤ አትደራጁ” በማለት  የክልል መሪዎቹን ሲወቅስና ስያስጠነቅቅ ቆይቶ አሁን ሕዝቡ ጫንቃ ላይ ወጥቶ ሃላፊነቱን ያልተወጣ መስዋእትንት መክፍል የማይፈልግ እያለ ሕዝቡን በሽርደዳ ማንኳሰስ በሽታ ካልሆነ ምን ትሉታላችሁ?

ሕዝቡን ከማበረታታትና እኔም ሥልጣኔ እንዳላጣ እንዳልማረክ ማድረጋችሁ አመሰግናለሁ ከማለት ይልቅ ወደ ማሾፍ ገብቷል። ሕዝቡ ባይዘምት ኖሮ፤ መስዋእት ባይከፍል ኖሮ ይኸኔ ወያኔ አዲስ አበባ ገብታ “አብይ እመድ ከነ ባለቤቱ ትማርከው ነበር”። ወይንም ወደ መቃዲሾ ወይ አስመራ ይፈረጥጥ ነበር።

ሕዝቡ አስታጥቁን አታስጨርሱን እያለ ሲጮህ ፤ “ውዥምብር አትፍጠር” እየተባለ ሲታሰር ኖሯል። |”ወሎ እና ጎንደርም ስንቅ አንፈልግላችሁም ብቻ ትጥቅ ጠስጡን ጥይት ስጡ”| ሲል አብይ አሕመድ  መሳርያ ሊሰጣቸው አልፈለገም። አሳምነውን የገደለ ይህ ወንጀለኛ ሰው አሁን ደርሶ ሕዝቡን የመውቀስና የመምራት ሞራል የለውም። በሕዝቡ ላይ ከማማረር ይልቅ ከአሳምነው ጽጌ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ብለህ ያሰርካቸው 23 ወታደራዊ መኮንኖችን “አገራችን ለማዳን ፍታን እና ወደ ጦር ግምባር እንዝመት” ብለው ሲጠይቁህ “እምቢ ብለህ አሁንም ያሰርካቸው መኮንኖችን ሳትፈታ ሕዝቡን ለመውቀስ ቁጢጥ ማለት ቂመኛ እና የመምራት ችሎታ ቢስ መሆንህን ያሳያል!!  

ይልቁኑ ከሕዝቡ ጫንቃ ውረድና በየክልሉ ያደራጃሃቸው፤ በተለይ አንተ ያስታጠቅሃቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአሮሙማ ታጣቂዎችህ “ኢትዮጵያዊነታቸው እንዲቀበሉ አድርገህ” ወደ ከምሴ እና ወደ ሌላ ቦታ አዝምታቸው። እንዳትማረክ እየተከላከለልህ ያለውን ሕዝብ ለቀቅ አድርግ! ኢትዮጵያን የመሰለች አገር አብይ አሕመድ በመሰለ “ማሰብ ያቆመ” በሽተኛ ሰው መመራትዋ ይበልጥ ለአደጋ ተጋልጣለች።

     ጌታቸው ረዳ

    (Ethio Semay)