Thursday, June 11, 2009

ስብሓት ነጋ “የወያኔዉ ማሞ ቂሉ!

ስብሓት ነጋ “የወያኔዉ ማሞ ቂሉ! ጌታቸዉ ረዳ (www.ethiopiansemay.blogspot.com) ‘የራስን ዕድል በራስ መወሰን’ ምን ማለት ነዉ? ጎሳስ ማለትስ ምን ማለት ነዉ?
ስብሓት ነጋ ለማያዉቀዉ በእዉነቱ አዋቂ እና የዋህ ገራገር ሰዉ ይመስለዋል። በጣም “ጎጠኛ” ፤ “ቂመኛ” እና “ማሃይም” ቢኖር ስብሓት ነዉ (አስከ ዚህ ድረስ ባሕሪዉ ከጥንት ጀምሮ አዉቀዋለሁ)። ስለ ጭካኔዉ አብረዉት የነበሩት እነ መኮንን ዘለለዉ- ግርማይ ባህሊ እና ሌሎቹ በሚገባ ያዉቁታልና ለነሱ ልተወዉ። በማሌሊት የጎሳዎች አተናተን እና፡ “ራስን በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል” ለሚለዉ ዕዉቀቱ ግን ስብሃት ነጋ “አህያን ያህል ከባዱ እንስሳ እራሱ ላይ ተሸክሞ ገበያ ለገበያ ከሚዞሮዉ “ከማሞ ቂሉ” አይለይም። በዚህ ዓምድ ልተነትን ወደ አነሳሳኝ መነሻ-ልግባ።ስብሓት ሰሞኑ- በየፓልቶኩ. በየቪኦኤዉ ስለ “ጎሳ” “ስለ ብሔር/ብሔረሰቦች/ሕዝቦች….” ራስ ዕድል በራስ የመወስን እስከመገንጠል መብት”-በወያኔ ሕገ መንግሥት እንደተከበረ በጮርቃ ላሃጩ ሲለፋደድ አሽከሮቹ (ካድሬዎቹ)“አስደናቂዉ ዕዉቀቱን”አዳምጡልን ብለዉ በየሰሌዳዉ የለጠፉትን ዲስኩሩን ሳዳምጥ፤ በተለይም የወያኔ ፓል-ቶክ አሽከሮች ስለዚህ ጉዳይ ሲያስተምራቸዉ ሲያሞግሱት፤ አባባ ሲበትኑለት ሳዳምጥ “ፎከታሙ ሕሊናቸዉ”-እጅግ ይገርማል። ስብሓት እና ድርጅቱ ለኢትዮጵያ አመጣንላት ብሎ የሚለፋደደዉ ‘ራስን በራስ የመወሰን እስከመገንጠል” ፖለቲካ ምን ያህል “የቂሎች ፖለቲካ” እንደሆነ በጥልቅ የምሁራን አንደበት የተነገሩትና የተፃፉት ማንበብ ይኖርብናል። በዚህ ጉዳይ ብዙ የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ብዙ ያሉበት ቢሆንም - በቀላሉ ሊገባ በሚችል አቀራረብ ለመጪዉ ትዉልድ የተዉልንን ከሕሊናየ የማይረሳ የክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “የክህደት ቁልቁለት”መጽሃፋቸዉ -በዚህ “ራስን በራስ የመወሰን አስከ መገንጠል” የወያኔ ፋሺስቶች እና ኮሚኒስቶች ፖለቲካ ርዕየተ ዓለም ምንኛ “የቀልድ ፖለቲካ” እነደሆነ በዚህ ጉዳይ ምስጋና ይግባቸዉና በሚገባ አሳይተዉናል። ይህን “አስከ መገንጠል”የሚለዉ “የፋሽስቶች እና የኮሚኒሰቶች ፖለቲካ” ፕሮፌሰር መስፍን ካሁን በፊት በቃለ መጠይቅ እንደገለፁት እንዲህ ያለ ፖለቲካ “የልጆች- ጨዋታ” መሆኑን አብራርተዋል። ለማንኛዉም የስብሓት የወያኔ “ራስን በራስ የመወሰን አስከ መገንጠል መብት”ፖለቲካ ትንተና ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ። ‘የራስን ዕድል በራስ መወሰን’ ምን ማለት ነዉ? “የወያኔ ሕገ መንግሰሥት አንቀጽ 39 (1) ‘ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለዉ መብቱ በማንኛዉም መልኩ ያለገደብ የተጠበቀ ነዉ፣፣ ይላል። ለራሳቸዉ ግልጽ ያልሆነላቸዉን ሀሳብ በተገማመደ ጨቅላ አስተሳሰብ ለሌላዉ ሰዉ ለማስተላለፍ በመሞከር አዋቂ መስሎ ለመታየት የተደረገ ሙከራ ነዉ። ድንቁርናን ወደ አዋቂነት፣ዉሸትን ወደ እዉነት ለመለወጥ ባይቻልም ግራ ገብቶአቸዉ ግራ የሚያጋቡ ሰዎች የባሕርይ ጥረት ነዉ። በመጀመሪያ ደረጃ በሕገ መንግሥቱ ዉስጥ የተደረደሩት ቃላት-ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ በትከክል ምን ማለት እንደሆኑና በመሀከላቸዉስ ያለዉ ልዩነት ምን እንደሆነ ቢጠየቁ አያዉቁትም። ከነሱ የባሰዉን ሰዉ ለማደናበር የሚጠቀምባቸዉ ቃላት ናቸዉ.። ሌኒንም ሆነ ስታሊን የጻፉት በትክክል አልገባቸዉም። በቀላሉ ጎሳ ብለዉ እንዳያልፉት ቃሉ ለሁሉም ሰዉ ግልጽ ስለሚመስል ለማደናገር አያመችም። የሚደንቀዉ ነገር አዲስ ቋንቋ እፈጠሩ ሰዎችን ማደናገር የአዲስ ኮሚዩኒሰት ካድሬዎች (አሽከሮች) ጠባይ ነዉ። ሌኒንም ማኦም እንደዚህ ያሉ ካድሬዎች ተቸግረዉ ስለነበረ በሰፊዉ ጽፈዋል። (በወያኔዎች የጎሳ ትንታኔ-) በጎሳዎች-መሃከል አንድ ዓይነት ደረጃ ለማዉጣትም ፍላጎት ያለ ይመስላል። ብሔር ትልቅ ጎሳ. ብሔረሰብ አነስ ያለ ጎሳ፤ ሕዝብ ደግሞ ምኑም ያልታወቀና ዝቅተኛ ጎሳ ብለዉ እንዳያቀርቡት የሚደረገዉ ልዩነት ብዙዉን የሚያስቀይም ሊሆንባቸዉ ነዉ፤ስለዚህም ማንም ሳይለይ ቃላቱን ደርድረዉ የፈለገህን አድርግ ማለታቸዉ ነዉ። ሌላዉ ማደናገርያ ደግሞ “የኢትዮጵያ ህዝቦች”የሚባለዉ ነዉ። በዚህ አባባል ደረጃ የተሰጠዉ ‘ሕዝቦች” ቃል እንደ (ደቡብ ሕዝቦች) ወደ ከፍተኛ ደረጃ ይወጣና ሰፍቶና አድጎ ለአገር ደረጃ ይበቃል። ወይም ሁሉም ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ይወርድና “የኢትዮጵያ ሕዝቦች’-ይባላል።ስለዚህም “የኢትዮጵያ-ሕዝቦች” ሲባል“መዉጣታችን ይሁን መዉረዳችን አይታወቅም። ገዢዎቻችን የሚነግሩትን ያዉቃሉ ወይ? የሚያሰኘዉ ለዚህ ነዉ። የማደናገሪያዉም ቃላቱን አልፈን ወደ ሀሳቡ ስንገባ፤ሀሳቡም የሞተና መነሻ የሌለዉ ሆኖ እናገኘዋለን። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን”የሚባለዉ ብዙ ተብሏል። ይህ ሃሳብ ሁለት መነሻ መሰረቶች አሉት አንደኛዉ በ1ኛወ የዓለም ጦርነት የአሜሪካ ፕረዚዳንት የነበሩት “ዉድሮዉ ዊልሰን” ያነሱትና በሗላም የተባበሩት መንግስታት ተቀብሎ በቅኝ ግዛት ስር ላሉ ሕዝቦች ያዋለዉ ሀሳብ ነዉ። 2ኛዉ ደግሞ- የኮሚኒስቶች የትግል ስልት ነዉ። ሃሳቡ እኛ አገር የገባዉ ፊደል የቆጠረዉ ሁሉ፤ሳር ቅጠሉ ሳይቀር ኮሚኒስት በነበረበት ጊዜ ስለሆነ ሃሳቡ የኮሚኒስቱ እንደሆነ ኣያጠራጥርም። ነገር ግን የዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች የኮሚኒሰት የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚባለዉ ሀሳብ “ስልት”እንጂ “ቁምነገር” እንዳለሆነ አልገባቸዉም። በደርግ ዘመን የነበሩት በመከራ ተማሩ፤ ያልተማሩት መጡና ሕግ አደረጉት። (……ይሉና ሰፊ ሀተታ ካብራሩ በሗላ- እንዲህ ይላሉ-- የራስን በራስ የመወሰን ኢትዮያ ወይንም ነፃ አገር አይመለከትም (ማለት በተባቡሩት መንግስታት ዓላማ)። ለቅኝ ግዛቶች ተብሎ የወጣ መመሪያ ነዉ። ስለዚህ ያንን ሃሳብ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት አንድ የኢትዮጵያ ክፍል ቅኝ ግዛት ነዉ እንዲባል በግድ አስፈላጊ ይሆናል። ሻዕቢያም ጀብሃም ያደረጉት ይህንን ነዉ። የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ)የሚለዉም ይህንኑ ነዉ። ለጊዜዉ እዚህ የታሪክ ክርክር ዉስጥ አንገባም። ሆኖም ጉዳዩ ከሁት በአንድ መንገድ መፈታት አለበት። ወይ በፖለቲካ (ማለትም በሕዝብ ዉሳኔ)አለዚያ በጦርነት። የኤርትራ ለጊዜዉ አልቆለታል፤ እንዲያዉም የማግደርደሪያዉን በር የዘጋዉ ይመስላል። የኦነግ ጥያቄ ገና በ እንጥልጥል ያለ ነዉ። ሁለተኛዉ መነሻ የኮሚኒስት ስልት መሆኑን ገልጫለሁ። ይህንን በሚገባ ለመረዳት የፈለገ ሰዉ ማርክስ ወይም ኤንግልስ ስለ ጀርመን የጻፉትን በ አንድ በኩል፤ ስለ እንግሊዝ አገር የጻፉትን በሌላ በኩል እያነፃፀራችሁ አንብቡት። ከዚያም በላይ እነዚህ ሰዎች “ስልት”እንጂ ቋሚ የሆነና ሁልጊዜም ለሁሉም አገር የሚሰራ አለመሆኑን በማያሻማ ቋንቋ ገልጸዉታል። 3ኛ--- የዚህን ሀሳብ መሰረት ፈጽሞ የሚንድ የሊቃዉንት ትንተና አለ። የራስን ዕድል በራስ መወሰን ሲባል መነሻዉና መድረሻዉ ምንድነዉ? ማነዉ “ራስ”? ብለዉ መጠየቅ ይጀምራልሉ። (1)ራስ ማለት አንድ ሰዉ ነዉ? ያለምንም ጥርጥር ስለ ራሱ መናገር የሕግም ሆነ የተፈጥሮ ችሎታ ያለዉ ግለሰቡ ነዉ።ነገር ግን ዕድሜዉ ትንሽ ሆኖ የሌላ ሰዉ ጥገኛ ካልሆነ ፤ በሕጋዊ ስርዓት በወንጀል ተከስሶ የተፈረደበትና በወህኒ ቤት ያለ -እነዚህ ሁሉ ወንድም ሆነ ሴት ራስ ለሚለዉ ብቁ አይደሉም፡ (2) ራስ የሚለዉ ለአንድ ቤተስብም ይሰራል? የቤተሰብ “ራስ” ነኝ ብሎ የሚቀርበዉ ማን ነዉ? ሚስት ወይስ ባል? ለልጆችስ የሚወስንላቸዉ ማነዉ? በባልና ሚሰት መሃከል የራስን ዕድል በረስ “መወሰን”ማለት “መፋታት” ማለት ነዉ። ለዚህም በመብት ደረጃ ባልም ሚስትም እያንዳንዳቸዉ “ራስ “ በመሆን የመፋታት ዉሳኔን መወሰን ይችላሉ፤ አብረዉ ካሉ ሃብታም ከነበሩ ሲፋቱ የዕኩልነት ስርዓት ካለ ዕኩል ስለሚካፈሉ (ሴቶች በበታችነት በሚኖሩበት ማሕበረሰብ ባዶ እጃቸዉን ይወጣሉ) ሁሉም ይደኸያሉ። ሁለቱም ደሃዎች ከሆኑ ሁለቱም የባሰ ደሃ ይሆናሉ። (3)- “ራስ” ለአንድ ቀበሌ ይሰራል ወይ? የአንድ ቀበሌ ነዋሪዎች ተሰብስበዉ፤ እያንዳንዱ ነዋሪ በነፃነት አስተያየቱንና ምርጫዉ ገልፆ ተስማምተዉ ለመገንጠል ቢፈልጉ ምንም የሚከለክላቸዉ ነገር አይኖርም። ከዚህ በላይ በጥቂቱ ለማሳየት እንደተሞከረዉ የራስ ዕድል በራስ መወሰን እንደቁም ነገር ከተወሰደ-ከ እያንዳንዱ ግለሰብ ጀምሮ እያንዳንዱ ቀበሌ-፤ወረዳ-፤_ሊጠይቅ ይችላል።ከዚህ ብቻ የራስን ዕደል በራስ የመወሰኑ ምክንያት በቋንቋ ብቻ ነዉ ከተባለ ይኼዉ ብቻ “ቁም ነገር”የተባለዉን ያፈርሰዋል። የራስን በራስ የመወሰን የምትችለዉ “በቋንቋ” ብቻ ነዉ እንጂ “በሃይማኖት ወይም በሌላ” መነሻ አድርገህ መገንጠል አትችልም ከተባለ ዕድል የተባለዉ መብት “በቅድሚያ”ተወስኗል። “ራስ”ለራሱ የሚወስነዉ “ጌቶች በፈቀዱለት” መንገድ ነዉ እንጂ ‘ራስ” እንደፈለገ አይደለም ማለት ነዉ። አንድ ወገን የሃይማኖት ልዩነትን መሰረት አድርጎ መገንጠል ቢሻ እና ቢገነጠል፤ በሗላ ደግሞ በቋንቋ ልዩነት መሰረት አንዱ ክፍል ለመለየት ቢፈልግ ቀጥሎ በዘር፤ ቀጥሎ ወደ ቤተሰብ፤ቀጥሎ ወደ ግለሰብ ደረጃ ለመዉረድ ምንም የሚያግደዉ ነገር የለም። የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚለዉን ሃሳብ እንደ ቁም ነገር ከተቀበልነዉ ለመገንጠል ሚፈልገዉን ሁሉ ማስተናገድ አለብን። በሃይማኖትም ሆነ በቋንቋ ወይም በዘር ሆነ በጎሳ ወይም በቀየ- ሆነ በታሪክ፤ ወይም በፐለቲካ አመለካከት ልዩነት ያለዉ ሁሉ መገንጠልን ከመረጠ መገንጠል መቻል አለበት። ቁጥሩ አነሰ ብሎ መገንጠልን መከልከል አይቻልም። “ቁም ነገር”-ከሆነ ለግለሰብም ቢሆን መስራት አለበት። ይህ ካልሆነ እንደ ወያኔ የጎሳ ክልል በምንም ዓይነት ቁም ነገር ላይ ሳይሆይን በዘፈቀደ የሚሰራ ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ክልል ይለያያል ከሚል ቁም ነገር ከተነሳን እያንዳንዱ ጎሳ፤ ትልቅም ይሁን ትንሽ፤ የራሱ ክልል ሊኖሮዉ ይገባል። ጎሳ የሰዉ ማንነት መግለጫ ነዉ ከተባለ፤ ክልል የጎሳ መግለጫ ነዉ ከተባለ፤ ጎሳ ከጎሳ የሚለየዉ በቁጥር አይደለም። (አማራ?)፤ ኦሮሞ፤ሶማሌ፤ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሲዳሞ፤ ወላይታ ከምባታ፤ ሀድያ፤ ጊዴዎ፤አፋር፤አገዉ፤ጋሞ፤ ጎፋ፤ ሻኪሶ፤ኩሎ፤ ኮንታ ሌሎቹም ሁሉ የክልል ባለቤቶች መሆን አለባቸዉ። ይህ ካልሆነ “ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” እኩል ናቸዉ እየተባለ የሚለፈፈዉ ባዶ ማታለያ ይሆናል። ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀዉ አንዱን ጎሳ የክልል ማለትም የከፍተኛ አስተዳደር ደረጃ ባለቤት አድርጎ ሌላዉን ጎሳ የዞን ማለትም የዝቅተኛ የአስተዳደር ደረጃ ባለቤት (በክልል ስር) ማድረግ ይባስ ብሎም ሌላዉን ጎሳ የወረዳ ወይም የመጨረሻዉ ዝቅተኛ የአስተዳደር ደረጃ ባለቤት ማድረጉ ነዉ። የሕዝቡ ቁጥርም እንኳን ሚዛን ዉስጥ እንዳልገባ ከሰንጠረዡ መረዳት ይቻላል።…… (የክህደት-ቁልቁለት-ገጽ115-116-117) www.Ethiopiansemay.blogspot.com