Tuesday, January 7, 2020

ክፍል -2- ዩቱበሩ አቤል ብርሃኑ ታምራት ነገራን እና እኛ አጋሮቹን ጌታውን አብይ አሕመድ እንዲያስረን ጠይቋል።ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) 01/06/2020


ክፍል -2-
ዩቱበሩ አቤል ብርሃኑ ታምራት ነገራን እና እኛ አጋሮቹን ጌታውን አብይ አሕመድ እንዲያስረን ጠይቋል።ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
01/06/2020


አቤል ብርሃኑ “Abel Birhanu ዩ ቱብ” የተባለው ይህ የአብይና የሻዕቢያ ቀንደኛ  አምላኪ የሆነው “ኤርትራ ዘመዶች” አሉኝ እያለ የሚዘላብደው አቤል ብርሃኑ *የወይንዋ  ልጅ” (ወዲ ወይኒ) የተባለ ያላደገ ጮርቃ ምሁሩን ጋዜጠኛን ታምራት ነገራን “ወያኔ ነው” ከማለቱ አልፎ ታምራትን የምንደግፍ ሁሉ አብይ አሕመድ እስር ቤት እንዲያስረን ሲማጸን መስማት ፖለቲካው የነዚህ መምቦጫረቂያ ሆኖ ማየት እጅግ ይገርማል። እኛ ትግሬዎች ከመገርም አልፎ ያለው መገርም “መርመም” የምንለው እርከን አስገርሞኛል።

አብይ አሕመድ እንዲያስረን የመማጸኑ የዚህ ጮርቃ ተማጽኖ ያስታወሰኝ ነገር አሜሪካ የሚኖሮው ትግሬው የወያኔው ካድሬ ‘አሉላ ሰለሞን’ ከሦስት አመት በፊት የፖለቲካ ተንታኙ ‘ሥዩም ተሾመን’ ወያኔ እንዲያስረው በፌስ ቡኩ ላይ ወያኔን የተማጸነበትን ትውስታችን ወደ ላ መለስ ብለን ስናስታውስ ዛሬ ባለተራዎቹ ሲተኩዋቸው እኛ እንድንታሰር አብይ አሕመድን የተማጸነበት የወጣት “አቤል ብርሃኑ” አንደበት ስናነጻጽረው የዚህ ልጅና “የሰለሞን አሉላ” ተመሳሳይነት ሳሰላስለው የሚገርም ተመሳሳይነት ነው።

ኤርትራኖችን ይቅርታ ይጠይቅ ካልሆነ ፌስቡኩን አስዘግተን አብይ እንዲያስረው እናደርጋለን እያለ “ተጠንቀቅ” ብሎ ሲያስጠነቅቀው ተማጽኖነ ማስተንቀቂያ የሚያሳየን አንድ ነግር ‘የወያኔ ተከታዮች እና የአብይ አሕመድ አምላኪዎች አደገኛነትና ተረኛነት እንዴት እንደተሸጋገረ በዚህ ጮርቃ ልጅ መምዘን ትችላላችሁ።  


ታምራትም ሆነ እሱን የሚደግፉ መሳዮቹ ኤርትራኖችን አስቆጥተዋልና እሰራቸው ብሎ አብይ አሕመድ እንድያስረን ውሳኔ ያሳለፈውን ተማጽኖ ጌታው የሚያስረን ከሆንም እየጠበቅን ነው። ታምራት ነገራን እንዲታሰር መወትወቱ ብቻ ሳይሆን ታምራትን በጋጠወጥ ምላሱ ሲዘልፈው መስማት ለጀሮ ይዘገንናል። የዩቱብ ቀባጣሪው የጮርቃው አቤል ብርሃኑ ያልተገረዘው ጋጠወጥ ምላሱን ለማድመጥ 
ኤርትራዊያንን ያስቆጣው የኢትዮጵያዊው አቶ ታምራት ነገራ ብልግና የኤርትራ ህዝብን ይቅርታ ይጠይቅ | Ethiopia | Eritrea 

የሚለውን ርዕስ በመጻፍ (ኮፒ & ፔስት) በማድረግ ዩ ቱብ ላይ ጉጉል አድርጉትና ጌታው አብይ አሕመድ እስኪያስረን ድረስ እንጠብቃለን።

ኤርትራውያን የሥጋ ዘመዶቼ እንዴት ሲሆን በዘመዶቼ ላይ ፖለቲካዊ ትንተና ተደረገባቸው ለምንስ ተነኩብኝ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ባዩ  ጮርቃው የአቤል ብርሃኑ “ጌታው አብይ አሕመድ አሜሪካ ድረስ መጥቶ ወይንም በወኪሎቹ በኩል  ተመክቶ ካልታሰርን” እንደነገርኳችሁ ክፍል 3 ስለ ኤርትራ ጉዳይ በስፋት በምለጥፈው ሰፊ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ሰነድ ጠብቁኝ። ወይ ጉድ ወያኔ ለበርካታ አመታት ሲያስፈራራን የነበረው እንዳይበቃን ዛሬ ደግሞ ስለ ኤርትራ ተናገራችሁ ብሎ ታምራት ነገራና መሰሎቹ ይታሰሩ ብሎ የሚማጸን ጮርቃ ማየት የሚያስደንቅ “መጽኣት። ነው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)