Sunday, May 22, 2022

አስቸኳይ ደብዳቤ ፣ ይድረስ ለአቢይ አህመድ ከደብሩ ነጋሽ (ሃኪም) ሕትመት -Ethiopian Semay- 5/19/2022

 

አስቸኳይ ደብዳቤ ይድረስ ለአቢይ አህመድ

ከደብሩ ነጋሽ (ሃኪም)

ሕትመት -Ethiopian Semay-

5/19/2022

ለዛሬ “ከትውስታ ማህደር” ውስጥ መርጬ  ኦትዮ ሰማይ  ላይ ታትሞ የነበረ ሰነድ በማቅረብ በአብይ አሕመድ አገዛዝ ሥር የተፈጹ አሰቃቂ ወንጀሎችን ባጭር ደብዳቤ የተጠቃለለ የሚያስረዳ ሰነድ ከሕሎናችን እንዳይጠፋ የሚያሳስበን ሰነድ እነሆ ያንብቡ!!

የኦሮሞው ሹማምንቶችህ ህጋዊ ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የጦርነት አዋጅ ነው።

ለዘመናት ሲያሰቃይ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወራሪ ወያኔን በአመጽ አፍረክርኮ፣ አንተንና መሰሎችህን ስልጣን ሲያስጨብጥ፣ ፈንጥዟል። ክስተቱ የመለኮት ስራም ነው ያሉ የዋሆች ነበሩ። በተለይ አንተንና ለማ መገርሳን፣ ሲያወድሱ የነበሩት ጥቂት አልነበሩም። ባደባባይ ትናገሩ የነበረው፣ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን ነበር። የብዙ ህዝብ ደም በግፍ ካፈሰስው ኦነግ፣ የምትለዩ ስለመሰለው ነበር።    በህዝብ አመጽ ልስልጣን በቅተህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን በመናገርህና፣ በርካታ በግፍ የታሰሩን በማስፍትታትህ፣ ህዝብ ተደሰተ።  እመነት የጣለብህ፣ በከንቱ እንደሆነ ያለፉት ሁለት ሶስት ወራት ክስተቶች ያመለክታሉ። ለነገሩ የግንዛቤ እጥረት ካልሆነ የስራዐት እንጂ የሹማምንት መቀያየር እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር።

ስልጣን ከያዝክ ጀምሮ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት ይፋ ሆኗል።  የሰሞኑ የመግስትህ ድርጊት ግን በእትዮፕያውያን ላይ ጦርነት እንዳወጅክ ግልጽ ነው። ‘’ጅብ እስኪነክስ ያነከስ’ ‘እንዲሉ፣ ያንተና የለማ፣ ቃላት ፍሬከርስኪነት ታውቋል። ድርጊታችሁ፣ ከጅብ ትክክለኛ ባህርይ ያመሳስላችኋል። ላብነት ከዚህ የሚከተሉትን እንዘርዘር።

    ‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ

ታልንት በወለጋ አያሌ ባንኮች ኦነግ በተሰኘው የኦሮሞ ቡድን  ሲዘረፉ ንጹሃን ሲፈጁ፣ አዛዣቸውም መንግስት እያንደላቀቀ ሆቴል እያኖረው፤ እርሱም ሆነ ከምንዝሮቹ አንድ ሰው ተይዞ ለፍርድ አልቀረበም በርካታ ሚሊየን የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ሳንቲም አልተመለሰም።  አንድ ሚሊየን ህዝብ ሃረርጌ ሲባረር፣ ወደተወለደበት ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ቁጥር በአዲስ አበባ ለማግዘፍ በሚመስል መልክ፣ አዲስ አበበ እየሰፈረ ነው።  እንግዲያው ገጠርና ቆላማ በሆነው ሃረር፣ በእርሻና ከብት ርቢ ይተደደር የነበረውን ህዝብ፣ ከኖረበት መልሶ፣ በሙያው እንዲተዳደር ያለመደረጉ፣ ለእኩይ አላማ መሆኑ ግልጽ ነው። የስራ እድል በሌለበት ነባር ነዋሪዎች በመብራት፣ የውሃ ችግር ሲሰቃዩ፣ የአማራና የሌሎች ዜጎችችን ቤቶች፣ ለገዳዲና ለገላፍቶ በግፍ እያፈረሱ፣ ከሃረር ኦሮሞዎችን ማስፈር አንተም ሆንክ፣ ቡድንህ ከመጠየቅ አይድንም።

ከወራት በፊት፣ በትግራይ ድንበር ላይ የነበረ ሰራዊት ወደ ማህል አገር በመንቀሳቀስ ላይ ባለበት ግዜ ደጋግሞ ታግቷል። ለቀናት መንገዱን በዙጉበት ዜጎች አንዲት ጥይት አልተተኮሰም። ይህም ተገቢ ነበር። ግን ይህ በሆነ በሳምንት ግዜ ጎንደር አካባቢ ይሀው   ኢትዮጵያ ሰራዊት 29 ሰላማዊ ሰልፍ የወጡን አማሮችን በግፍ በጥይት ደብድቦ 9 ውድያው ገድሏል። የወያኔን የመንገድ ስራ ድርጅት ተሽከርካሪዎች በፍርድ ቤት ማዘዣ ለመፈተሽ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በነበሩ አማሮች የጥይት ናዳ ያወረደባቸው የወያኔን ግል ድርጅት ያጀበ ሰራዊት ነው። በትግራይ ውስጥ ጠጠር ሳይወረወር፣ በአማራው ላይ ጥይት ያዘነበው ሰራዊት የጦር አበጋዝ፣ ለዎያኔ ያደረ ምርኮግኛው ኦሮሞ መሆኑን ልብ ይሏል።

የድንበርን ውዝግብ ይፈታ ዘንድ በሚል ምርህ፣ በተቋቋመው ቡድን በሃይል የወልቅይትና ራያን ወደ ትግራይ የከለለውን የወያኔ የቀድሞ መሪ ሳይቀር አካተሃል። ወሎን፣ ሸዋን ቆራርጦ ኦሮምያ ለተባለው ግዛት ለደለደለውና  ለበርካታ ሚሊዎን  አማራ እልቂትም ሆነ፣ ባገርቷ ለደረሰው መከራ ከሚጠየቁት መሃል አንዱን፣ ነጋሶ ጊዳዳን  ጭምር ሰይመሃል። ለድንበር ዳኝነት ያሰባስብካቸውን አላማውን የሚዋጅ ስብዕና የሌላቸውን ጭምር ናቸው። ግማሹ ከኦሮሞ ነገድ ነው።የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥአደል?   እሪ በይ አይ እትዮጵያ ያሰኛል።

በመጨረሻ፣ የባለቤትነት ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ሰዎች ቤቶች፣ ከማፍረስ የባሰ የጦርነት አዋጅ የለም።  በለገዳዲና ለገጣፎ መሬቱን የቸበቸቡ የኦሮሞ ሹማምንትና አፍራሽ ግብረሃይል፣ እንደወራሪ፣ ቤቶቹን ሲያፈርሱ፣ ኡኡ ይሉ የነበሩን ባለቤቶች  ‘መጤበማለት እየተሳደቡም፣ነበር። እንኝህ ለህግም ሆነ፣ ለስረአት ባይተዋር የሆኑ፣ የኦሮሞ ሹማምንት፣መጤየሚሉት ያን የፈረደበትን አማራ ብቻ አደለም። ከድፍን ኢትዮጵያ የመጡ ወገኖቻችን ሁሉ ነበር። ይህ የፈሪዎችና የአይምሮቢስ ኦነግ ልሂቃን ድርጊት የጨዋና የደጉ ኦሮሞ ህዝብ ሊያውግዘው ይገባል። ይህ ግፍ ከቀጠለ፣ የኦሮሞን መንግስት ወረራ  የማይቋቋም የለም።

የኢትዮጵያውያን ለአንድ ትውልድ፣ የግፍ ግፍ የፈጸሙባቸውን የወራሪ ወያኔዎች ቡድን ሲንገዳገድ ተገንዝቦ ህዝቡ ስራዐቱ የተገረሰሰ መሰሎት ነበር። ከጅምሩ፣ ረዥም እድሜውን በወያኔ ሞግዚትነት ላደገ ዜጋ፣ ለኢትዮጵያዊነት ባዕድ ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያን ጥንታዊነት፣ ተረትና የቅርብ ግዜ ፈጠራም እንደሆነች ሲሰማ ለኖረ በወያኔው ግብረ፟_አበር በኦነግ ትርክት ምንሊክ 5 ሚሊየን ኦሮሞን ፈጅቷልየሴቶች ጡት ቆርጧል እየተባሉ በደረቅ የሃሰት ታሪክ ላደጉ ኦሮሞ ሹምምንት፣  ይህ የተፈጸመው ግፍ ከመጤፍ አይቆጠር ይሆናል። የአቢይና ለማ ማንነት ከዚህ አይዘልም።  ‘’ከወርቁ’’ የትግሬ ነገድ የተፈጠረውን አለቃህን ይመስል፣ መቀሌ ሄደህ፣ እንደበቀቀን፣ያንን ስትደግም፣ አልተቸገርክም። ባንጻሩ አሜሪካ በሄድክበት ወቅት፣ አለም ያወቀውን ጸሃይ የሞቀውን ፣በአማራ ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅት፣ በአደባባይ የካድክ ጎበዝ ነህ።

በአኖሌው የጥፋት ሃውልት ግንባታ፣ ግዙፍ ተሳትፎ እንደነበረህ አይካድም።

በሃሰት ትርክት በተመሰረተ ወንጀል፣ ያልታጠቀ፣ያልጠረጠርንራ እልቆ መሳፍርት የሌለውን አማራ እልቂት ያስከተለን ሃውልት፣ ከመቅጽበት መናድ ሲገባህ፣  አስካሁን ተገትሯል።  ስልጣን እንደያዝክ ኦሮምያ በሚባለው የደባ ክልል የሚኖረውን 15 ሚሊዎን ህዝብ ሰቆቃ ፣ቀጥለህበታል በአማርኛ እንዳይማር፣ እንዳያስተምር በመንግስት ተቋማትም እንዳይገለገል የሚያደርገውን ፣የግፍ እግድ እንኳን አላነሳህም። እነኝህን ከማንሳት ይልቅ፣ ኦሮሞ ያልሆኑን ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ቤቶች ማስፈረስ፣ አጣዳፊ ልምን እንደሆነብህ ትጠየቅበታለህ!!

አንድ በሰሞኑ ለገጣፎ ቤቷ የፈረሰባት እናት፣ ያንተን ከኤርትራን ጋር እርቅ መሻት ስትደሰት እትዮጵያውያንን በግፍ በመንቀልህ የደም እምባ እያለቀሰች ነበር ለውጭ ስደተኛ የሚሳሳ መንግስትህ፣ በእትዮጵያውያን ላይ ይህን ግፍ በማስፈጸምህ ይቅር የምትባልበት አደለም።

ይህ ኦሮምያ በሚሉት መስተዳደር የተጧጧፈው የሌሎችን ዜጎች በህግ የተሰሩና ለአመታት ይገበርባቸው የነበሩን መኖርያ በቶችን በነዋሪዎቹ ላይ የማፍረስ ዘመቻ ያንተንም ሆነ የምትወክለውን ህዝብ ስነልቦና ምንነት ጠንቅቆ ያሳያል። ኢላማ የተደረጉት የከተማዋ አብዛኛ ነዋሪ የሆነው በህግ ከለላ የሚፈጀውና የሚፈናቀለው አማራ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ ቦታዎችህ የመጡ ነባር ኢትዮጵያውያን ናቸው።

                                                   ‘ትኩስ እረሳ፣የደረቀን አስነሳ

ይባስ ብለህ አማራንም ሆነ ለሎችህ ኢትዮጵያውያንን  ቤቶች አፍርሶ በሺዎች የሚቆጠሩን ወገኖቻችንን ለቀን ሃሩር፣ ለሌሊት ቁር መዳረግህ፣ መልዕክቱ ግልጽ ነው። ልክ በፋሽስት ጣልያን ግዜ ተሞክሮ እንደከሸፈው ሁሉ፣ የሸዋ ኦሮሞ፣ በወገኑ አማራውም ሆነ ለሌሎች፣ አጋር ወንድምነቱን በመግለጽ፣ ልዕልናውን እንደገና አስመክሯል።

የአቢይ መንግስት  ግንትኩስ እሬሳ፣የደረቀውን አስነሳአስኝቶናል።  የኦሮሞው መንግስት ድርጊት፣ የትላንቱን የከፋውን አባጆቢርና፣ መሰሎቻቸው፣ በወለጋ በኢሉባቦር፣ በሃረር ፣በጣልያን ሃይ ባይነት፣ የተፈጁትን፣ ያልታጠቁ አማሮች ሰቆቃ ያስታውሳል። ዛሬ መሳቂያ ባደረገውአዲስ አበባን የኦሮሞ ናት የሚለው ቅዠት፣ የሚናውዘው የኦሮሞው መንግስት፣ አቅም ቢኖረው፣ ከፋሽስቱ ወያኔና  ከጣልያን ያልተለየ ግፍ ባማራውና በሌሎች ወገኖች ከመፈጸም የምይመለስ መሆኑን ነው።   በህዝብ አመጽ ልስልጣን በቅተህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን በመናገርህና፣ በርካታ በግፍ የታሰሩን በማስፍትታትህ፣ ህዝብ ተደሰተ።  ህዝቡ እመነት የጣለብህ፣ በከንቱ እንደሆነ ያለፉት ሁለት ሶስት ወራት ክስተቶች ያመለክታሉ። ለነገሩ የግንዛቤ እጥረት ካልሆነ የስራዐት እንጂ የሹማምንት መቀያየር እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር። ዘመቻህ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት ይፋ አድርጓል።

የአዲስ አበባን በረራነት አትስተውም። በትንሹ 1500 ዘመናት በፊት የአማራ፣ የጉራጌና ጋፋቶችና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ከተማ መሆኗን አታውቅም አይባልም ነባርቹ ኢትዮጵያን እንክዋን የኛ ብቻ ከተማ ናትብለው አልቀለሉም።

ማንኛውም ነገር ገደብ አለው። ያንተን አመራር ጨምሮ። ዛሬ አንተ የምትመራው በሚመስለው የወያኔ መንግስት የሚፈጸመው ግፍ አንድ እና  ሁለት የለውም። ያለአንዳች ሃፍረት፣ ይሉኝታ፣ ፈሪሃ እግዚብሄር፣  ህዝብን ለርስበርስ ለጦርነት የሚገፋፋ ድርጊት መፈጸሙን መገንዘብ የሚሳንህ አይመስልም። ምናልባትም የትም አይደርሱበሚል የትዕቢት ከሆነ ተሳስትሃል።

ስለዚህ አንድ ነገር ልብ አድርግ።  ለግብር ይውጣ የሚደረግ  ማንኛውም  ነገር ዘለቄታ አይኖረውም   ዛሬ የሚፍጸመው ግፍ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ ነው። እዳው ከባድና ከነአራጣው  መከፈል ስለሚኖርበት አበው  ‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱእንዲሉ። ከመቅጽበት ይህንን የህዝብ ሰቆቃ ካላቆምክ፣ የተፈጥሮ ህግ ነውና፣ የተገፋው ይነሳል። አታቆመውም።

በመጨረሻ፣ የግራኝን ወደር የለሽ ገድል በመጥቀስ ልሰናበት ጥሎበት አማራውን እጅግ ይፈራው ነበር። ስለሆነም   ሃይማኖት ሳይለይ፣ እስላምና ክርስቲያኑን አማራ እኩል ነበር ይፈጀው የነበረው። ብዙ ከተዋጋቸው አማራ መሃል ከአስሩ ነዋሪ፣ አንድ ብቻ የተረፈበት ግዜ ነበር። ዛሬ ወያኔና ኦነግ በአማራው ህዝብ ላይ ተመሳሳይ የጥፋት ዘመቻ የተያያዙ ይመስላል። በሁለቱ ጣምራ ጦር የተፈጀው ህዝብ፣ ሂትለር ከፈጃቸው አይሁዶች ቁጥር ይበልጣል። ግፍ ዘለቄታ አይኖረውምና   ይቅናሃ!!

Posted - Ethiopian Semay