የትግሬ
ፖለቲከኞች ገለባ ማስረጃ ፍለጋና የአበረ አዳሙ የጦርነቱ መጀመር
ንግግር
ጌታቸው
ረዳ
Ethiopian
Semay
4/21/2023
ዱቄቶቹ የትግራይ ፖለቲከኞች (የፋሺስቱ የአብይ አሕመድ አባባል አይደለሁም
እየተጠቀምኩ ያለሁት ፤ ግን ከዱቄትም ብናኝ የፖለቲካ አመድ መሆነቻውን ለመግለጽ ነው) የወያኔ መሪዎች ሥልጣን ለምን ለቀቅን ከሚለው
ባሻገር በዋናናት <<፡ሥልጣን ከተነጠቅን ወደ እየ መንደራችን እንበታተናለን>> ብለው እንደተናገሩት መሠረት
(ሰብሓት ነጋን ያስታውስዋል) “የሃገረ ትግራይ” የምስረታ አጀንዳቸው
እውን ለማድረግ ጥቅምት 24 ማክሰኞ ዕለት ጦሩን አዘናግተው የጀመሩት የሰሜን ዕዝ ጭፍጨፋ ሽፋን አገኘን ብለው የአብይ አሕመድ
አሽከር የነበረው በወያኔ/ኢሕአዴግ ጊዜ “መቶ አለቃ” የነበረ ከዚያም ኔዘርላንድ ሲኖር የግንቦት 7 አመራር አባል የነበረ፤አገር
ገብቶም የአማራ ክልል ፖሊስ “ኮሚሽነር” ሆኖ ተሹሞ ብዙ ሰው ሲያሰቃይ የነበረ፤ አሳምነው ጽጌን “ዕብድ በሽተኛ” ብሎ የዘለፈው
የከንቱ ከንቱ የነበረው የኮሚሽነር አበረ አዳሙ “የጦርነቱ ተጀመረ” ንግግሩ ትግሬዎቹ ለወንጀላቸው መሸፈኛ ለማድረግ እንደ መከራከርያ
አድርገው በየመድረኩ ሲጠቅሱት እየሰማን እኛም እሳቅንባቸው ነው።
ሰሞኑን አንድ ጅላጅል የትግሬ ብሔረተኛ (ትግራይ ፕሬስ የሚባል የሚዲያ
አዘጋጅ) የወያኔ ሽጉጥ ታጣቂ የነበረውን “ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌውን”
ጋብዞ ጦርነቱ አማራዎች ናቸው የጀመሩት እያለ ልደቱን ለማሳመን ሲከራከር ሲዘላብድ ከተጠቀመበት ማስረጃ በዚህ ጽሑፌ ውስጥ ቃል
በቃል ከታች የምጠቅሰው የአበረ አዳሙ ንግግርን ነው።
ይህ የአበረ አዳሙ ንግግር የትግራይ ፖለቲከኞችና ተንታኞች እንዲሁም ጀሌዎቻቸው 100% ዕርግጠኞች ሆነው ጦርነቱ “አማራዎች፤ልዩ ሃይሎች” (በነሱ አጠቃቀም) እንጂ የወያኔ መሪዎች እንዳልጀመሩት እየጠቀሱ መስማት ስለሰለቸኝ ይህ ለናንተው ፍርድ አቅርቤዋለሁ።
መጀመሪያ የአበረ አዳሙ ቃል በቃል ንግግሩን ላቅርብ እና ከንግግሩ አንድ ባንድ ምን ማለት እንደሆነ የራሴን ግንዛቤ አቀርባለሁ፡ ከዚያ እናንተም ጨምሩበት።
የሚገርመው ደግሞ አበረ አዳሙ ጦርነቱ ተጀመረ ያለበት ቀን መች እንደሆነ ዕለት አይጠቅስም፡ ዝም ብሎ ብቻ ተጀመሯል ብሎ የልዩ ሃይሉ ነገረኝ በሚል ነው እንጂ ጦርነቱ “<<እኛ ጀመርነው>”> አይልም። ያ ጦርነት ለመጀመር በምሽጉ ላይ ተመድቦ የነበረው የልዩ ሃይሉ አዛዥ ጦርነት ማዘዝ መብት የለውም። ጦርነት ጀምር ተብሎ ሲታዘዝ ብቻ ነው ጦርነቱን የሚጀምረው እንጂ፤ በዚህ መንገድ አዛዦቹ ዜና ሰሚዎች ሲሆኑ የሚገርም ነው። ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ያሉት ክላሽ ብቻ የያዙ “ፖሊሶች ናቸው”። እስኪ ደምጹን በጽሑፍ ላስነብባችሁ እነሆ፤-
እንዲህ ይላል፡
<< ያቺን ክስተት ትንሽ ላሳያችሁ፦የአማራ ክልል ፖሊስ፤ የአማራ ክልል መንግሥት አቶ ተመስገን ነበሩ ፕረዚዳንት። ይሄ ነገር እንደሚከሰት ቀደም ብለን እናውቅ ነበርና በተለይ ደግሞ የወያኔዎች ዝግጅት አጠገባችን ስለነበረ፤እኛ “ኦል ረዲ/all ready ስራችንን ሰርተን ነበር። ምደባ ተካሂዷል፤በየድምበራችን፤ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ዝግጅት ላይ እያለን፤ ዝግጅታችን ጨርሰን እየተጠባበቅን እያለን ነበር ምሽት ላይ ጦርነት የተጀመረው።
እናም ረዳት ኮሚሽነር ይባላል “ቢሰጥ” ይባላል የልዩ ሃይል አዛዥ ነው።ደወለልኝ፡ “አቤ” ነው የሚለኝ፡ እኔ ደግሞ ብዙውን ጊዜ “አምበሳየ” ነው የምለው፡ወታደሮች ወይንም መሪዎችን ብዙ ጊዜ አምበሳየ እያልኩ ነው የማዛቸውና፤ “አምበሳየ” ስለው፤ “ጦርነቱ ተጀምሯል አለኝ!” እናስ? አልኩት፡ “እናማ ገጥመናል አለኝ”።
የተነጋገርንባቸው ብዙ ወታደራዊ ቋንቋዎች ስለነበሩ በተነጋገርነው ቀጥል አልኩት “እሺ” አለ። እኔም ወዲያው ለፕረዚዳንታችን ደወልኩ፤ “በቃ እንግዲህ መግጠም ነዋ” ነው ያለኝ አቶ ተመስጌንም። “ያዝ በለው” አለኝ፡ “አዎ ብየዋለሁ አልኩት”። “አዎ ገጥመናል አልኩት”። ከዚያም በኋላ ሁላችንም ሥራ ላይ ነን፡ ትንሽ ቆይቶ ‘ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ (ረደት ኮሚሽነር ማለት በፖሊስ ብርጋዴር ጀነራል ማለት ነው) እና ብርጋዴር ጀኔራል እያልኩ ብጠራው ደስ ይለኛል፡የተለመደ ሥም እሱ ስለሆነ።እንደገና መልሶ ደወለ፡ “በተነጋገርነው መሰረት እየሆነ ነው አለኝ”።
የተነጋገርነው ዛሬ ስላለፈ ግልጽ ላድርግላችሁ “እዛው ውስጥ ያሉ ከኛ ጋር ቀርበት የነበራቸው፤ በተለይ ደግሞ በሑመራ አካባቢ የነበረው ሜከናይዝ ክ/ጦር አባሎች ከኛ ጋር ግንኙነት ነበረን።እናጠና ነበር። አንድ ነገር ቢፈጠር እንዴት ከዚያ ወደ እኛ ሃይል መሳብ እንዳለብን አጥንተን የጨረስነው ስለነበር፤ “በተነጋገርነው መሠረት ስንባባል እኔ እና ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ (እንግባባለን)፡ “በተነጋገርነው መሰረት እየሆነ ነው ምን ላድርግ? አለኝ”፤ ይህ ምን ማለት ነው? ብረት ለበስ ነበሩ እዛው የነበሩ በኛው ልዩ ሃይሎች ሽፋን እየተሰጣቸው ወደ እዚህ እንዲመጡ ማድረግና ከመጡ በኋላ/እኛ ጋር ከደረሱ በኋላ አዙሮ ወደ ጠላት መደገን ስለነበረ፤ “እየመጡ ነው ምን ላድርጋቸው አለኝ”፡ “አዙርና ወደ ጠላት ደቅን” አልኩት። “አደረገው”።
መጀመሪያ ሽፋን እየሰጠን ያወጣናቸው ብረት ለበሶች ከዚያ በኋላ እንደገና ለኛ ልዩ ሃይል “ሽፋን እየሰጡን እግረኛው ገባ”።ኪዚያ በኋላ የሆነውን የምታውቁት ነው። ጦርነቱ የተጀመረው በዚያ መንገድ ነበር ፤ዕለትዋ ይህች ናት”።
በዚህ ሂደት ውስጥ ጦርነቱ እንደተጀመረና ብረት ለበሶቹ ከኛ ጋር በማስሰለፍ
“ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ዘንድ ደወልኩ”። ጀኔራል የናንተ ልጆች ወደ እኛ ስበን አውጥተናቸዋልና ከኛ ጋር አስሰልፈናቸዋል፤ በመከላከያ
እና በኛ ልጆች መካካል ትስስር እንዲኖር መመሪያ ኣውርድ አልኩት።” በጦርነት ጊዜ ትስስር የሚባል ቋንቋ ኣለ፡አለበለዚያ ዕርስበርስ
መማታት ይመጣል።አንዱ ማን እንደሆነ ካላወቀ፤ያን ማድረግ ስለነበረብን፤ ለጀኔራል ብርሃኑ ስነግረው፤ጀኔራል ብርሃኑ የመደሰትና የመጠራጠር
ስሜት ነበር ሲናገር፡ መደሰቱ በዛው መንገድ አምጥተን (ለጸረ) ጠላት ማስሰለፋችን ነው፡መጠራጠሩ
ደግሞ ይመስለኛል “እንዴት ሊሆን ቻለ?” በሚል ነበር “ከቶኑ” ‘ካነጋገሩ’ የተረዳሁት ያ ነው። በል የሆነ ሆኗል መመሪያ አውርድ
አልኩት፤እሺ ኣለ” በዚያው መንገድ ነው ውግያው የቀጠለ” >> ይላል ሟቹ አበረ አዳሙ።
እንግዲህ ይህ ንግግር አማርኛ ለሚገባው ግልጽ ነው።
በዚህ ልጀምር፡
<<ዝግጅታችን ጨርሰን እየተጠባበቅን እያለን ነበር ምሽት ላይ ጦርነት የተጀመረው።>> አማርኛው ግልጽ ነው። አደለም?
“እየተጠባበቅን እያለን ነበር ምሽት ላይ ጦርነት የተጀመረው ሲል” የሚጠባበቀው ሁለት ነገር ነው፡ ጦርነት ለመጀመር የበላይ ጠቅላይ አዛዥ መኖር አለበት፡ እነ አበረም ሆነ ምክትልም ሆነ የክልሉ ፕረዚዳንት ጦርነት ለመጀመር መብት የላቸውም (ሲተኮስባቸው ብቻ ነው አጻፋ መስጠትና መታኮስ የሚጀምሩት ያም ሆኖ አበረ እንዳለው ምክትሉ (ም/ኮሚሽነር ቢሰጥ) ጦርነት እንደተጀመረ ለአበረ አሳወቀ (“ጦርነቱ ተጀምሯል አለኝ!” እናስ? አልኩት፡ “እናማ ገጥመናል አለኝ”።) “እሺ” “እንግዳውስ ያዝ በለው አልኩት” አለ አበረ። ከዚያም በተዋረድ ለተመስገን ጥሩነህ አስተላለፈ፤ ተመስገንም “ያዝ በለው” አለኝ፤ “እኔም ያዝ በለው ብየዋለሁ አልኩት”። ይላል አበረ አዳሙ። በተጨማሪም “በመጠባበቅ ላይ እንደነበርን” የሚለው ኮሚሽነር ቢሰጥ “ቢተኮስብን ለመተኮስ ወይንም ከበላይ ትዕዛዝ ቢተላለፍብን ጦርነቱን ለመጀመር “ ነው በመጠባባቅ ላይ እያለን እያለ ያለው። ወታደር ሁሌም በመጠባባቅ (አለርት) ንቃት ዝግጁነት ላይ መሆን አለበት፡ ደምብ ነው።
እንግዲህ የዕዝ ሰንሰለቱን እዩት። ቢሰጥ (ታዛዥ ነው) ለአለቃው ለፖሊስ ኮሚሽነሩ ለአበረ አዳሙ አስተላለፈ፤ አበረም ታዛዥ ነውና ለአለቃው ለተመስገን ጥሩነህ አስተላለፈ፤ አበረ ለብርሃኑ ጁላ ስልክ ደወለ፤ ብርሃኑም እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ በመጠራጠር “እሺ” በማለት የጦርነት ትዕዛዝ ለማስተላለፍ እሺታው ገለጸለት (ምክንያቱም ጦርነቱ እንዲጀመር ስላላዘዘ ወይንም የሚያውቀው ነገር ስለሌለ) ።
ይህንን ስትመለከቱት በወታደራዊ ሕግ እነዚህ የተጠቀሱ ባለሥልጣኖች (ፖሊሶቹ (መከላከያ ጦርም አይደሉም፤ ከባድ ብረት ለበስ መካናይዝ/ታንክ/ ተዋጊ ሃይል የላቸውም፤ “ፖሊሶች ናቸው”፡ አንዲሁም ስቪል ለበስ የሆነ የክልሉ ተጠሪ ሆነው በራሳቸው ክልል ተሻግሮ ድምበር ዘለል ጦርነት ማወጅ መብት የላቸውም (በተለይ በፌደራሉ ዓይን በጎሪጥ እና ጥንቃቄ ሲታይ የነበረው ይዞ ይሆናል ተብሎ ሲጠረጠር የነበረው ሚሳይልና መካናይዝ ጦር የነበረው ወያኔ) ፖሊስ ጦርነት ሊጀምር አይፈቀድለትም (ድጋፍ ሰጪ ነው፤ ስለነበርም ነው አብይም ሆኑ ጀኔራሎቹ የአማራ ከልል ልዩ ሃይና ሚሊሺያ እንዲሁም ፋኖ በድጋፍ ሰጪነት አስገራሚ ውጤት ማስገኘታቸው ሲያሞግሱት የሚደመጡት))። ስለሆነም በጠላት በኩል ተተኩሶባቸው ስለነበረ ሁኔታው በተዋረድ ለበላይ አለቆች በሰንሰለት አስተላለፉ ማለት ነው። ግልጽ ነው አይደለም እንዴ?
ዝግጅት ቢያደርጉም ፖሊሶች ስለሆኑ ጦርነት መጀመር አይችሉም፤ ድጋፍ ሰጪዎች ናቸው (ከትጥቅና ሃይል ሚዛን አኳያም ቢሆን አያዋጣም) ስለዚህም ተኩስ ቢተኮስባቸው “ተዘጋጅተው ሲጣበበቁ ነበር” እንጂ ቶከስ ከፈትንባቸው አላለም (ጦርነት ተጀመረ ነው የሚለው፤ ለአለቃው ሪፖርት እያደረገ ነው እንጂ ጦርነት እንጀምር ወይ የሚልም ጥያቄ አልቀረበም፤ወይንም ጦርነቱን ጀምረነዋል አላለም። አዛዦቹም “ጦርነቱን ጀምሩት አላሉም)። ጦርነቱ ተጀመረ ሲለው አበረ አዳሙ “እናስ?” እያለ በጥያቄ እና በአግራሞት አበረ የጠየቀው ለዚህ ነው።
አበረ አዳሙም በግልጽ እንደሚናገረው “ጦርነቱ ተጀምሯል አለኝ!” እናስ? አልኩት፡ “እናማ ገጥመናል አለኝ”። “እሺ” “እንግዳውስ ያዝ በለው አልኩት” አለ አበረ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ጦርነቱ ተጀምሯል ሲለው አበረም በድንጋጤ “እናስ?” አልኩት “እናማ ገጥመናል” አለኝ ይላል። ይህ አማርኛ ግልጽ ይሆን? ይህ የሚያሳየው ወያኔ ጦርነት ትንኮሳ መግባቱ ግልጽ ነው። አለቃ ሳያዝ ጦርነት አይጀመርም። “እናስ?” ብሎ ሲጠይቅ የሚያሳየን “የመከላከል ዝግጅት ቢጠናቀቅም ጦርነት ጅምሩ የሚል ስላልተላላፈ ”አዲስ ክስተት መሆኑነ ነው “እናስ?” ብሎ የጠየቀው።
ሌላው ነጥብ እዩልኝ።
አበረ አዳሙ እየተቀሰው ያለው ቦታ በውል ባይታወቅም ፖሊሶቹ (ልዩ ሃይሎቹ) የሰው ሃይልም ሆነ “ታንክና መድፍ” ስለሌላቸው ጦሩ በየቀጠናው አቅራቢያ በየማዓዝን ተመድቦ ጥበቃው ላይ ስለነበር “ድንገት ወያኔ በፖሊሶች ላይ ቶከስ ቢከፍትባቸውም ሆነ በመከላከያው ላይ ወያኔ ጥቃት ቢያደርስ” መከላከያዎቹ ከሚተኮስባቸው የጠላት አቅጣጫ አፈትልከው ወደ ፖሊሶቹ እንዲቀላቀሉና እንዲታገዱዋቸው ተነጋግረው ስለነበር (ሁለቱም ለጥቃት እንዳይጋለጡና እርስ በደርስ እነዳይገዳደሉ ትብብር ስለነበራቸው) ፤ አበረ አደሙ በዚህ ምክንያት ነበር <<መጀመሪያ ሽፋን እየሰጠን ያወጣናቸው ብረት ለበሶች ከዚያ በኋላ እንደገና ለኛ ልዩ ሃይል “ሽፋን እየሰጡን እግረኛው ገባ”>> በማለት የጦርነቱ ሁኔታ የገለጸው ሽፋን ሊሰጥዋቸው የተገደዱበት ምክንያት ወያኔዎቹ ወደ ፖሊሶቹ ዕራዳታ ለመስጠት ሲሳብ ጠላት መከናይዙ ላይ ቶከስ እየከፈተ መኖሩን ያሳያል።ከተቀላቀሉ በኋላ ግን ሁለቱም በማበር ወደፊት ገቡና ጦርነቱ ቀጠለ። ጠላት በፖሊሶቹ (ልዩ ሃይሎቹ) ላይ ባይቶክስ ኖሮ መካናይዙ ለዕርዳታ አይደርስም ነበር።ልዩ ሃይሉ ጦርነት ፈለግኩኝ ቢል እንኳ ጦርነት መክፈት አይችልም፤ መሳሪያም ፤የሰማይ ድጋፍም የአየርና ማአከላዊ የመገናኛ ግንኙነትም የሰው ሃይልም የለውም። በቃ!
ከተመቸኝ ክፍል ሁለት ከአበረ አዳሙ የተለየ ወያኔዎች ጥቅምት 24 ቀን ማክሰኞ በሰሜን ዕዝ ላይ ጭፍጨፋ ከማካሄዱ በፊት የሰሜን ዕዝ ወታደሮች ዕንቅስቃሴ ፌደራሉ የማዘዝ አቅሙን እንዴት እንዳሳጣው፤ እገልጻለሁ። እስኪያ ግን በዚያው ወቀት መስከረም የሰሜን ዕዝ አዛዥ “ጀኔራል ደሪባ መኮንን” ምሳ ግብዣ ጋብዘዋቸው በመርዝ እንዴት እንደተመረዙና ከዚያም ለሕክምና ሄደው በምትካቸው መስከረም ወር ሜ/ጀኔራል ጀማል መሐመድ ካዲስ አባባ መቀሌ ሲገቡ መቀሌ አየር ማረፊያ የክልሉ ልዩ ሃይል አላስገባም ብሏቸው ተመለሱ። ከዚያም ለጭፍጨፋው ሁለት ሳምንት ሲቀረው ወዲ ነጮ የተባለ መሰሪ ወንጀለኛ (ዛሬ በህይወት የለም) በየ አውራጃው እየዞረ ወታደራዊ መገናኛዎቹ ኮድ ለውጦ (ከ9 ኙ ራዲዮ መገናኛ ሃላፊዎች 8 ቱ ትግሬዎች ነበሩ) አንደኛው ሰውየ “ወላይታ ይመስለኛል) አፍኖ ወስዶ ለጭፍጨፋው ቀን ጦሩ እንዳይገናኝ በማድረግ፤ ሴራ ተፈጸመ። ጠቅላላ ጦሩ ለዘብ ጥበቃ ብቻ ካልሆነ ጠመንጃ እንዳይዝ ባዶ እጁ እንዲሆን ተደረገ (የሚገርም ተንኮል ነው አደለም?)፤ በዚህ ሴራ ወታደሩ ግራ ይገባው እንደነበርና፤ ደሞዝ ዘገየን ብሎ ጦሩ ሲናገር “ገንዘብ ምን ያሰራልሃል ሰሞኑን ትሞታለህ፤ ግድ የለህም” እያሉ ትግሬዎቹ ወታደሮቹን በጎንዮሽ እየቀለዱ ሲነግሯቸው እንደነበር እና አንዳንድ ቦታም ነገሮች ደስ እንደማይሉ ጥንቃቄ አድርጉ እያሉ ደግ የሆኑ ትግሬ ወታደሮች ምስጢር ያስልፉላቸው እንደነበር ….ወዘተ..ወዘተ…..ሴራዎችና የጭፍፋ መጀመር ምልክቶች እንደበሩ የተከዳው የሰሜን ዕዝ ደራሲ የሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው (ቻቻው) ይገልጻል።
አንዲህ ይላል፡
ከጥቅምት 24 ቀደም ብሎ በነበሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ ወለጋ ላይ በኦነግ ሸኔ ንጹሐን አማራዎችን ለሰብሰባ ኑ ብሎ ጠርቶ ከ200 በላይ ሰዎችን ጨፈጨፋቸው። ጥቅምት 24 ቀን ማክሰኞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድርጊቱን እያለቀሱ አወገዙ።የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ድርጊቱን አወገዙ። ኦሮሚያ ክልል ፕረዚዳንትም ድርቱ የኦነግ ሸኔ እና የህወሓት ጥምረት ድርጊት እንደሆነ በመግለጫ አሳወቀ። የትግራይ ም/መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካልም << ጦርነት እየመጣብን ነው ለሁሉም ነገር የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ ይሁን..” በማለት መልዕክት አስተላለፈ። መልዕክቱም እንደማንኛውም ሰው ሰማነው። “የተለመደ ጉራ ነው ከማለት ያለፈ የተለየ ትርጉም የሰጠው ሰው አልነበረም”። ለካ ለእነሱ ግን የመጨረሻ የጦርነት ማወጃ መግለጫቸው ኖሯል። ጥቅምት 24 ዕለተ ማክሰኞ “ዱብ ዕዳ” ሆናብን ይህች ዕለት የተመረጠች ቀን ነበረች፤ ለሰሜን ዕዝ ድግሞ “ጥቁር ቀን”። በዚያው የጁንታው አመራሮችና አሮጌ ጀኔራሎች መቀሌ ሀውልት ሆነው ፊሽካውን ለመንፋት ተዘጋጅተዋል። የቀጠሮአቸው ሰዓት ደረሰና የክሕደት ፊሽካቸው ተነፋ!!!!!!!!”>>
በማለት ጭፍጨፋው እንዴት እንደተጀመረ በሰፊው ይተነትነዋል። የትግሬ ፖለቲከኞች ወያኔ የመላዕክት ስብስብ አድረገው ቢራቀቁም አፈርና ድንጋይ ቢቆፍሩም የጦርነቱ ጀማሪዎች እነሱ እንደሚወነጅሉት በአማራ ክልል ታጣቂዎች ሳይሆን ጀማሪዎቹ ወያኔዎች ናቸው።
ጽሑፉ አስፈላጊ ሰነድ ስለሆነ እንደ ወያኔዎች እናንተም የኛን ትንታኔ
ተቀባበሉት “ሼር” አድርጉት፡ (አለመታደል መቸም ልማና ነው ምን ይደረግ!)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)