Tuesday, April 8, 2008

One day “Alula Jr.” will born from Temben!


Please read it with Ge’ez Unicode (download it from “Ge’ez Unicode.com”. It is free and easy to use with MS Words.

አንድ ቀን “ዳግማዊ አሉላ” ከተምቤን ይወለዳል!
በግደይ ባሕሪሹም
(ከ አሞራ መጽሃፋቸዉ የተገኘ- ገጽ 197)

ከዚህ ገጽ በስተ’ግርጌዉ መጨረሻ በኩል በትግርኛ ለትግርኛ አንባቢዎች ተርጒሜ ያቀረብኩትን ተሐህቶችን የተቃወመ የትግራይ ተወላጅ አንዳንዴ በሕይወቱ እያለ መቃብር ጉድጓድ ዉስጥ በመክተት የቁም ስቃዩን እያሳዩ እንዴት እንደሚገድሉት የሚገልጽ ነበር። በዚህ ገጽ ግን ለአማርኛ አንባቢዎቼ የማቀርበዉ ለየት ያለ በመሆኑ ሁሉም እነዲያነ’በዉ እጋብዛለሁ።

<< …ሴቶች ለማገዳ እንጨት ለቀማ ከሠፈራቸዉ ወጣ ብለዉ ወደጫካ ሲሄዱ፤በክረምት ወራት በጎርፍ የተጠራቀመዉን በደረቀዉ ወንዝ አፋፍ ላይ ዳሰሳ ጭራሮዉንና ጉቶዉን መምዘዝ ሲጀምሩ፤ጎርፍ ካጠራቀመዉ ቅርፊትና ግንድ ጋር የተቀላቀለ፤ የሰዉ አጽምና ያልፈረሰ የራስ ቅል፤ደጋግመዉ ያገኛሉ። በተለይ በትግራይ ክፈለ ሃገር፤በሽሬ አዉራጃ፤ በሰየምት አድያቦ ወረዳዎች ዉስጥ፤የሰዉ አጽም ያልተበተነበት በረሃ’ና ቋጥኝ የለም። ከሰላሳ ሁለት ጊዜ የወያኔ እና ኢዲህ ጦርነት እልቂት ልላ፤አካባቢው በወያኔ ቁጥጥር ከዋለ በሗላ፤ የኢዲህ ደጋፊ ነበርክ፤ነበርሽ ተብለዉ በወያኔ ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በሗላ ፤በተሓህት አፈሙዝ እየተረሸኑ፤ በየፈፋዉና በየጋምስቱ የተደፉት፤ አፈር ተነፍጓቸዉ ፤ ፀረ ትግራይ “<ኮራኹር አምሐሩ”> ( የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ ቀለብ የሆኑትን፤ የወለደና የተወለደ፤ተሸማቅቆ ያየ ቤት ጎረቤት ይቁጠረዉ።

በእርስ በርስ ጦርነት ካለቀዉ ይለቅ፤ በጥርጠራና በጥቆማ ተይዘዉ፤ ለዘርና ለታሪክ እንዳይተርፍ፤ በስዉር (በሻዕቢያ ባንዳዎች) ያለቀዉ የትግራይ ሕዝብ እጥፍ ድርብ ነዉ።

ከክፍለሃገርዋ ከመቀሌ ከተማ ጀምሮ፤ በስምንቱ አዉራጃዎችና በአምሳ ሁለት ወረዳዎች ያለዉ ሕዝብ፤ፈጠን ብሎ ለእነሱ በርከክ ካላለና “ትግሬና አማራ” ወይም “ኢትዮጵያና ትግራይ” በሚለዉ መሰረታዊ መፈክራቸዉ ላይ፤ ጥያቄ ያቀረበ ሰዉ ሁሉ “ኢዲህ” ነዉ፤ እየተባለ ወላጅ በልጁ አጅ እንዲመታ እና አንዲረሸን ያደረጉት የሻዕቢያ ባንዳዎች፤ በግማሽ ከኤርትራ ክፍለ ሃገር በመወለዳቸዉ፤ለነገዉ ትዉልድ ጥቁር ታሪከና የማይደርቅ ደም አተረፉ እነጂ፤ በተተኪዉ የትግራይ ትዉልድማ ለልጆቻቸዉ ቂም አትርፈዉ፤አመላቸዉን ይዘዉ በተራቸዉ ማለፋቸዉ አይቀርም። ደግ ይሁን ክፉ ሰዉ መቸም እንደ ድንጋይ ለዘላለም አይኖርም። ከናዚ ጀምሮ የነበረ አረመኔ ሁሉ አላለፍም ብሎ ዛላለም የኖረ ሰዉ የለም። ይህች የአረመኔዎችና የካሃዲዎች የትምክህተኞችና የቂመኞች ዘመን በተራዋ ሳትወድ በግዷ ታልፋለች። ትዉልድና ታሪክ ግን ይቀየራሉ።

“ቁጥቋጦና ታሪክ ከመቃብር በላይ ነዉ” ይባል የለ!። ደርግ በቀይ ሽብር የከተማዉን ወጣት ሊጠርግ ፤ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሆነዉ ወየኔም፤ ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነ ገበሬዉንና ወዛደሩን <ኮራኹር አምሐሩ፤ ሽዋዉያን ተጋሩ> (ያማራ ቡችሎች - የሸዋ ትግሬዎች) እያለች የ “ኢዲህ” ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፤በሬና ላሙን፤በግ አና ፍየሉን፤ አህያዉን በቅሎዉን፤ ደሮዉንና ጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤዉን፤እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ፤ ለሐማሴኖች መደሰቻ ተብሎ፤ላሻዕቢያ ያልሰገደ’ምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፤ “ዘር ማንዘሩ” ከምድር እነዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድና በጎረቤት እንዳይቀበር፤ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረዉ የቤትና ጎረቤት ሰዉ ታዝቢ ይቁጠረዉ።

ሻዕቢያ የተባለዉ የኤርትራዉ ድርጅት፤ በግማሽ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ዘመዶቹን፤ ወየኔ ትግራይ ድርጅት “ቁንጮ” ላይ አስቀምጦ፤በንጹህ የትግራይ ዘርና ትዉልድ ላይ ግፍ የፈጸመበት “በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጊዜ” እነደነበር፤ ለተተኪዉ የትግራይ ትዉልድ ታሪክ መጥቀስና ማዉረስ የተቆርቋሪ ወገን ግዴታ ነዉ።

ሻዕቢያ በወያኔ ትግራይ ስም ተሰይመዉ፤አመራሩን በወኪሎቻቸዉ ተቆጣጥረዉ፤ገበሬዉንና አገር ወዳዱን የትግራይን ሕዝብ፤ወጣቱንና ሕጻናቱን አሰባስበዉ (ትገራይ ዓደይ በል!!) <ላገሬ ለትግራይ በል!!> እያሉ፤ የራሳቸዉን ፍላጎት ለማሟለት የጦርነት ምሽግና ተገን እነዲሆንላቸዉ አታልለዉና አሞኝተዉ፤ ባልተወለደ አንጀታቸዉ በገዛ ጓሮዉ ኢትዮጵያዊነቱንና አነድነቱን በሚያስከብር የጠራናፊት ሠራዊት (ኢዲህ) እግር እነዳይተክል ትግራይ ወጣት እርስ በርሱ ወንድም በወንድሙ ላይ ሰይፍ እነዲማዘዝ አደረጉ።

ትግርኛ በመናገራቸዉና ወላጆቻቸዉ ትግራይ ዉስጥ ተወልደዉ የትግራይን መሬት ፍሬና እህል በልተዉ በማደጋቸዉ፤ትግሬዎች ነን በማለት፤ትግራይን ህዝብ <<ለነጻነትህ ብርሃን ነዉ>> እያሉ፤ በዘር ወገናቸዉ ለሆነዉ ለሻዕቢያ በተንኮል ተወክለዉ፤የትግራይን ሕዝብ የወገኑ የመሃል አገር ያማራና የኦሮሞ ወዳጅ ለዘላለም እነዳይኖረዉ ፤በኤርትራዊያን ተጨቁኖ፤ በአማራዉም ተጠልቶና ተራርቆ እነዲኖር፤ በተንኮል ወደ ገሃነም ጨለማ መሩት።

በነሱ - <ዓጋሜ የአማራ ሰላይ>
በአማራዉም - <ባንዳ አስገንጣይ ተገንጣይ ታሪክ ሻጭ> እየተባለ እነዲወቀስ፤ ዘላለም እነዲከሰስና በታሪክ እነዲኮነን አደረጉት። በሻዕቢያ መሠረተ ዓላማ የተጠመቁ ሃማሴኖች፤ የትግራይ ሕዝብ በመሀል አገር ህዝብ እነዲሞገስና እነዲመሰገን አይፈልጉም። ይልቁንም በትግሬዉና በአማራዉ መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ የትግራይ ሕዝብ ከመሀል አገር ያኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እየተጋጨና እየተነጫነጨ እነዲኖር፤እነሱ ግን <ግፋ በል -ጠቡን አታብርደዉ> እያሉ የዳር ድነበር ጠያቂ ሳይኖራቸዉ በሰላም ሊኖሩ ህልማቸዉ ነዉ። <ድንቄም ሰላም ትኑር!>

ቀን የጣለዉ የትግራይ ሕዝብ ቂሙን ይረሳል ማለት መሽቶ አይነጋም ነዉ። አንድ ቀን <ዳግማዊ አሉላ ይወለዳል> ቀይ ባሕር ራሱ የኢትዮጵያ ድንበር መሆኑን የሚያረጋግጥ <ከተንቤን> ሰዉ ይወጣል፡ ታሪክ ይደገማል!>-/-/

ለአቶ ግደይ ባሕሪሹም በአንባቢዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። ጌታቸዉ ረዳ ፤ San Jose, California USA