መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
እመኛለሁ!!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
እኔ እንደ ትግሬነቴ ለበርካታ
አመታት የኢትዮጵያ ጠላቶችን በተቻለኝ ጉልበት እና እውቀት እልክ አስጨራሽ በሆነ ትግል ታግያለሁ።ተኝቶ የነበረውን የአማራ ወጣት
እና ምሁር ተንሰቶ ወያኔን ፥ ሻዕቢያን እና ኦነጎችን እንዲታገል እዚህ አፋፍ ድረስ አድርሻለሁ።
ቢያንስ 85% አሁን ያለው ምሁር እና ተቃዋሚ ወጣት እኛ ጥቂቶች 15% ወያኔን ስንታገል 85% ያክል በትግሉ ሜዳ ላይ ያልነበረ ፥ የራሱን ኑሮ ሲያደላድል የነበረ ፥ ወያኔን በአሽከርነት ሲያገለግል የነበረ ፥ ከሩቅ ሆኖ እኛን ሲያሳንስ ወይንም ሲያሽማጥጥ የነበረ ፥ መሃል ሰፋሪ የነበረ ፥ ገለልተኛ ታዛቢ የነበረ… ነበር አሁን 85% ተቃዋሚው ወደ
ትግሉ እንዲቀላቀል በቁጥር ከፍ እንዲል ያደረግነው።
እንዲያም ሆኖ ይህ አዲስ
ሃይል ወደ እኛው ጎራ ተቀላቅሎም ቢሆን ጤና አልሰጠንም። አንዳንዱ ጭራሽኑ ከወያኔ አፈና ወይንም ከወያኔ እና ኦነግ ፖሊሲ ጋር
የሚሄድ ባህሪ ያለው ተቃዋሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እንዲያም ሆኖ እኔ አንደ ግለሰብ ከፍተኛ ትግል አድርጌአለሁ። ከታላላቅ መምህራኖቼ
እና ወዳጆቼ በፖለቲካው መስምር ምክንያት ተቀያይሜአለሁ፤ ወላጆቼን ሳልቀብር፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ ወደ ፋሺሰቱ ሜዳ ወደ ወያኔ ድርጅት
ተቀላቅለው የወያኔ ታጋዮች ሆነው ሲዋጉ የቆሰሉ ፥ የሞቱ ፥ የደኸዩ ወንድሞቼ እና እህት ዘመዶቼ አብሮ አደግ ጓደኞቼ በሙሉ ሳላይ፤ትምህርቴ እና ኑሮየን ወደ ኋሊት በማቆየት
ለእናት አገሬ ስል ሕሊናየ እና መንፈሴ
ለፋሺሰቱ ለወያኔ ሳላስረክብ ከፋሺሰቱ ወያኔ ጋር ታግየ፤ በሃያሉ ጦረኛው ብዕሬ አምበርክኬአቸዋለሁ። ታሪክ፤ ሰንደቃላማ እና ሉኣለዊነት
እንዲከበር የጎላ አስተዋጽኦ አድረጌአለሁ።ይህ ቃል በጉራ የምናገረው ሳይሆን ታሪክ የዘገበው እውነታ ነው። ሆኖም ተቃዋሚው (ሕዝቡ)
ከዛሬ ዛሬ ይሻለዋል ብየ በትዕግስት ትግሉን ለመቀጠል ብበረታታም፤ እያደረ ወደ ኋሊት እየተጎተተ መጨረሻ ላይ የቀንደኛ ጠላቶቹን ባንዴራ እያውለበለበ
‘ኢሳያስን’ ጎንድር እና በመሳሰሉት አከባቢዎች ትያትር ይመስል ኢሳያስ አፈወርቅ ከአይሮፕላን ወርዶ የጎንደር መሬት ሲረግጥ “አዋጅ”!“አዋጅ!” እያለ እግሩ ላይ ሰግዶ በመቀበል
አሳፋሪ ታሪክ እያስመዘገበ በማየቴ ከዚህ ወዲያ ይህ ሕዝብ ጠላት እና ወዳጅ ለይቶ መታገል የማያውቅ ሆኖ ስላገኘሁት፤ ትዕግሱቱን
የሰጣችሁ በአብይ አሕመድ እየተመራ ያለው “የትግሬዎች እና የኦሮሞዎቹ ፋሺስቶች ጥምር መንግሥት” ተከታዮች የአማራን ሕዝብ ከተቸነከረበት
ምስማር እንደምታላቅቁት መልካሙን እመኝላችኋለሁ።
በረዢም የትግሉ ጊዜ ከተቃዋሚም
ከወያኔም ከኦነጎችም፤ከኤርትራ ሻዕቢያኖችም በርካታ ጠላት አፍርቻለሁ። ያ መሰዋእትነት ለናት አገሬ ኢትዮጵያ የከፈልኩት መስዋእት
ስለሆነ አይቆጨኝም። ጠላቶቼም በዚህ እንደሚረዱልኝ አምናለሁ። ከንትርኩ ከመሰናበቴ በፊት የኔን ድምፅ በማፈን ከወያኔዎች እኩል
በማይተናነስ እኩይ አፈና ያደረጉብኝ የተቀዋሚ ሚዲያዎች (ዛሬ የፋሺስቶችን ጥምር መንግሥት በማገልገል እና የዜና ወኪሎቻቸው ሆነው
እየሰሩ ያሉት የዜና እና የትችት ማሰራጫ ድረገፆች) ምን እየተሸረበ እንዳለ እየተረጎሙ የማይነግሩዋችሁ ከወደ ትግራይ እየተፋፋመ
ያለው አደገኛ ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ላካፍላችሁ እና ልሰናበታችሁ።
ሰሞኑን ወያኔዎች በእንደርታዊው
ደ/ር ጎይተኦም (አዲስ ማንነት ለመላበስ የሚጥር እውቀተ ቢስ ‘ገለባ’ እና የእንደርታን ማንነት እና ታሪክ ያዋረደ አሳፋሪ
የ “አሽዓ” ምልምል ወጣት) ፥ እንዲሁም ህወሓትን እና ደርግን በማፈራረቅ ያገለገለ
ሽማግሌው አድርባይ እና ዘረኛው ፥ ሽሬታው (ሽሬ/ዛና) ተወላጅ መምህር ገብረኪዳን ደስታ ፥ እንዲሁም አድዋዊው የድሮ ኢሕአፓ የዛሬው ወያኔ ‘አጋኣዚያን
(ሰብ ሕድሪ) ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም ፥ እንዲሁም ይህ የወያኔ ሰልፈኛ ነው ስል እሱን በመወከል እኔን መስደብ ሲቀናቸው የነበሩት
የተቃዋሚዎች ጀግና የነበረው ‘ቢከፍቱት ተልባ እና ገለባ’ አብርሃ ደስታ እና የመሳሰሉት “አጋአዚያኖች”
ትግራይ መገንጠል አለባት በማለት በግልጽ ሕዝብን እና ወጣቱን የሚቀሰቅሱበት ነፃነት በወያኔዎች እውቅና እና አበረታችነት
በየአደራሹ እየተሰበሰቡ “ሚዲያ” ተፈቅዶላቸው ግንጠላውን እየሠሩበት ነው።
ይህንን እውን ለማድረግም
ሰብ ሕድሪ እና አጋአዚያን የተባሉ የግንጠላ እና ጸረ እስላም ድርጅቶችን መስርቶ ትግራይ ትግርኚ የተባለ
ጽዮናዊት የሆነች የክርስትያኖች አገር ለመመስረት በወያኔ የተደገፈ መድረክ ይፋ ሆኗል። አጋአዚያን እና ሰብ
ሕድሪ.. የተባሉ እነዚህ ድርጅቶች የተለያዩ ድርጅቶች ይምሰሉ እንጂ ባንድነት እየሰሩ ላንድ ለወያኔ ግብ ለማሳካት በመነሳት ”አክሱም የትግሬዎች ሥልጣኔ እና መንግሥት ብቻ ነበር” በሚል “ቅዠት” እና “ልብ ወለድ ተረት” ወደ እውነታነት አስመስለው ለመለወጥ
ሌት ተቀን እየሰሩ “አክሱም” ለመላው ኢትዮጵያ ምኑ ነው?
በሚል የመለስ ዜናዊ መርሆ በመከተል ትግራይ ሌላ አገር አሁን ያለቺው ኢትዮጵያ ደግሞ ሌላ አገር ስለሆኑ ፤ በግድ በሚኒሊክ ስለተቀላቀልን
እንለያለን በሚል መርሆ እየሰሩ ይገኛሉ።
በዘመነ አክሱም ትግራይ ወይንም ተጋሩ/ትግራዎት/ትግርኛ የሚል መጠሪያ ወይንም ሕዝብ ስላልነበረ ያቺን ወደ ኋላ የተከሰተች “ስም እና ሕዝብ” ለመሸፈን ሲሉ “አጋዚያን” የሚል በመለጠፍ “ወያኔ አጋዚያን ማለት ከየመን/ ደቡባዊ አረብ የመጡ የአረብ ዝርያዎች ናቸው” ብሎ በማኒፌስቶው ያወጣውን ስም በመጠቀም “አጋዚያን” ማለት ትግሬዎች ማለት ነው የሚል በጥንታዊ ሰነድ ያልተደገፈ ፤ በሃውልት ጽሑፍ እና ማስረጃ ያልተነገረ ፤ ትግሬዎች የጥንት ሰዎች የአክሱም ብቸኛ መስራቾች በማስመሰል ዛሬ “የማንነት ፍለጋ እንቆቁልሽ” የተጠናወታቸው ግብዞች አዲስ ስም ለትግሬዎች በመስጠት “አጋዚያን (ሰብ ሕድሪ/የአደራ ሰዎች)” በሚል መጠሪያ እየተንቃሰቀሱ ናቸው። ትግራይ/ ተጋሩ/ ትግሬ/ ትግርኛ/ ትግራዋይ የሚባሉ ቃላቶች/ መጠሪያዎች በዘመነ አክሱም ጭራሽ የማይታወቅ በመሆኑ ያቺን የበታችነት ስሜት ለመሸፈን ሲሉ ያልሆነ ስም አጋዚያን በማለት ለትግሬዎች በመስጠት አዲስ ስም ሊሰጡን እየሞከሩ ነው። የኢትዮጵያ የጋላ ነገዶች ወደ ኦሮሞ እና ኦሮሚያነት ስም የለወጡት ያህል አስገራሚ ክስተት ስንታዘብ በተመሳሳይ ትግሬዎች ወደ አጋአዚያንነት የመለወጥ ትግሉ ስናነጻጽረው ከውስጥ መፈተሽ ያለበት የስነልቦና ተመራማሪዎች ሊያስተምሩን የሚገባ አስገራሚ አዲስ ክስተት ነው።
በዘመነ አክሱም ትግራይ ወይንም ተጋሩ/ትግራዎት/ትግርኛ የሚል መጠሪያ ወይንም ሕዝብ ስላልነበረ ያቺን ወደ ኋላ የተከሰተች “ስም እና ሕዝብ” ለመሸፈን ሲሉ “አጋዚያን” የሚል በመለጠፍ “ወያኔ አጋዚያን ማለት ከየመን/ ደቡባዊ አረብ የመጡ የአረብ ዝርያዎች ናቸው” ብሎ በማኒፌስቶው ያወጣውን ስም በመጠቀም “አጋዚያን” ማለት ትግሬዎች ማለት ነው የሚል በጥንታዊ ሰነድ ያልተደገፈ ፤ በሃውልት ጽሑፍ እና ማስረጃ ያልተነገረ ፤ ትግሬዎች የጥንት ሰዎች የአክሱም ብቸኛ መስራቾች በማስመሰል ዛሬ “የማንነት ፍለጋ እንቆቁልሽ” የተጠናወታቸው ግብዞች አዲስ ስም ለትግሬዎች በመስጠት “አጋዚያን (ሰብ ሕድሪ/የአደራ ሰዎች)” በሚል መጠሪያ እየተንቃሰቀሱ ናቸው። ትግራይ/ ተጋሩ/ ትግሬ/ ትግርኛ/ ትግራዋይ የሚባሉ ቃላቶች/ መጠሪያዎች በዘመነ አክሱም ጭራሽ የማይታወቅ በመሆኑ ያቺን የበታችነት ስሜት ለመሸፈን ሲሉ ያልሆነ ስም አጋዚያን በማለት ለትግሬዎች በመስጠት አዲስ ስም ሊሰጡን እየሞከሩ ነው። የኢትዮጵያ የጋላ ነገዶች ወደ ኦሮሞ እና ኦሮሚያነት ስም የለወጡት ያህል አስገራሚ ክስተት ስንታዘብ በተመሳሳይ ትግሬዎች ወደ አጋአዚያንነት የመለወጥ ትግሉ ስናነጻጽረው ከውስጥ መፈተሽ ያለበት የስነልቦና ተመራማሪዎች ሊያስተምሩን የሚገባ አስገራሚ አዲስ ክስተት ነው።
በራሱ በወያኔ ማኒፌሰቶ
አባባል ደግሞ “አጋዚያን” ማለት ይላል እንደሚከተለው እቅጩን ሲነግራቸው፡ እንዲህ ይላል።
“The people of Tigray have a
rich history of thousands of years. In the past, they were known by various
names such as Axumites, Habeshas, etc. Before 1000 BC, present day Tigray was
inhabited by Nilotic and Hametic peoples of African origin, who led a primitive communual life.....the tribes
of South Arabian origin known as the Sabean, Agazeans,Habeshats, and Himyarites began to cross the Red
Sea and settle in the areas which are todayTigray and Eritrea. These tribes
were at a more advanced stage of development than the indigenous people. /
People's Democratic programm of TPLF, May 1983)
ወያኔ እራሱ አጋዚያን
ማለት የደቡብ አረቦች ዝርያ ነገዶች ወደ አክሱም የፈለሱ ናቸው ሲል ነግሮናል። እንዲህ ከሆነ ትግሬዎች ወደ አረባዊ ነገድነት እንድንለወጥ
ለምን እየጣሩ እንዶሆነ የኔ ብቸኛ ጥያቄ ነው። ትግሬ እና አጋዚያን ለየብቻ ናቸው። አመጣጣቸውም ከሁለት ተቃራኒ ስፍራዎች እንደፈለሱ
የታሪክ ጸሐፍቶች ይጠቅሳሉ። አንዱ የቤጃዎች ጎሳ ነው የአሁኑ ትግሬዎች ስም እና ቋንቋ ከግዕዝ ጋር ቀላቅሎ የፈጠረ ወይንም
የአክሱም ነገሥታትን ተዋግቶ ከሥልጣን ያባረረ፤ የአክሱም ስልጣኔ የናደ በትግሬ ስም አካባቢውን የሰየመ የሚባለው) ሌላው ወያኔ እንደሚለው “ደቡባዊው አረቦች
ጎሳ “አጋአዚያን”።
በዚህ ታሪክ እየተጓዙ
ነው ዛሬ “ወያኔ/አጋዚያኖች/ሰብ-ሕድሪ” እያሉ ከግራ ቀኝ ስም እየቀያየሩ ሕብረተሱብን በማንነት ፍለጋ ቁፋሮ እንዲገባ እያደረጉት
ያሉት። ለዚያ አዲስ ማንነት መፈለጊያ ማምለጫ መስኮት የሚጠቀሙበት ደግሞ "አማራን
እና ኢትዮጵያ የምትባል የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደ ቀዳሚ ጠላትነት” ዛሬም
ለሕዝቡ በግልጽ እያስተማሩት ነው። ማስረጃውም በቪዲዮ ከወደ ታች አሳያለሁ።
አጋዚያን /ሰብ ሕድሪ ከተመሰረተ ዓድዋ፤አክሱም ሽሬ (አጋሜ(?) 8 አመት ሆኖታል። እንደርታ ውስጥ በሽታው ተጋብቶባቸው ከተመሰረተ ደግሞ 2 አመት ሆኖታል። ወያኔ ሲመሰረት ልክ እንደ አጋዚያኑ በእነዚያ አውራጃዎች ብቻ ተወስኖ ነበር። እንደርታ እና ተምቤን ራያ ኋላ ነው መቆጣጠር የጀመረው። አጋዚያንም የወያኔዎቹ ቅድ በመመርኮዝ የተመሰረተው በነዚህ አውራጃዎች ሲሆን እንደርታ እና የመሳሰሉት ደግሞ በወረርሺኝ በቅርብ ጊዜ ተጋብቶባቸዋል።
አጋዚያን /ሰብ ሕድሪ ከተመሰረተ ዓድዋ፤አክሱም ሽሬ (አጋሜ(?) 8 አመት ሆኖታል። እንደርታ ውስጥ በሽታው ተጋብቶባቸው ከተመሰረተ ደግሞ 2 አመት ሆኖታል። ወያኔ ሲመሰረት ልክ እንደ አጋዚያኑ በእነዚያ አውራጃዎች ብቻ ተወስኖ ነበር። እንደርታ እና ተምቤን ራያ ኋላ ነው መቆጣጠር የጀመረው። አጋዚያንም የወያኔዎቹ ቅድ በመመርኮዝ የተመሰረተው በነዚህ አውራጃዎች ሲሆን እንደርታ እና የመሳሰሉት ደግሞ በወረርሺኝ በቅርብ ጊዜ ተጋብቶባቸዋል።
በነገራችን ላይ ትግራይ
ውስጥ “የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባል የለም” ያለው የትግሬዎች የወያኔ መንግሥት ነው። ስለሆነም ትግሬዎችን ወደ እውነታው ለመመለስ
(ከቅዠታቸው ለመቀስቀስ) ‘የምጣኔ ሃብቱ እና እህል ሸቀጥ የጫኑ የጭነት መኪኖች መጓጓዣ እና የመሳሰሉ ማዕቀቡ በትግራይ ላይ እንዲቀጥል
እና ዝግ እንዲሆን መቀጠል አለበት። እንዲህ የምለውም “የመገንጠል
አባዜአቸው እና ኢትዮጵያን የመዝለፍ እና ቂጣቸውን ካልሸፈኑ ደናቁርት ኢትዮጵያውያኖች ጋር ትግራይ መኖር መቀጠል የለባትም ስለሚሉ”:: ይህ ቅዠት እና ጉራ በማዕቀቡ ትምህርት ወስደው “ሁለቴ” እንዲያስቡ” ስለሚያደርጋቸው “ማዕቀቡ” መቀጠል አለበት።
ትግራይ ብትገነጠል እንዲህ ተንደላቅቆ መኖር እንደማይቻል መማር አለባቸው። ሕዝቡ በስሜት የሚያሳስቱት “ደናቁርት” ሳይገነጠል በፊት በማዕብ በኩል “በግብር ስያየው” ችግር ውስጥ እንዴት እንደሚገቡ ሲረዳው ‘ግንጠላው ለመቃወም ስለሚረዳው” ወያኔን እንዲታገል ሕዝቡ ከወያኔ ደጋፊነት እንዲላቀቅ በር ይከፍታል “ወይንም በደጋፊ እና በተቃዋሚ ጎራ ይከፈል እና ለውጡ በትግራይ ካምፕ ውስጥ እንዲገባ ስለሚረዳ ማዕቀቡ መቀጠል አለበት።
ትግራይ ብትገነጠል እንዲህ ተንደላቅቆ መኖር እንደማይቻል መማር አለባቸው። ሕዝቡ በስሜት የሚያሳስቱት “ደናቁርት” ሳይገነጠል በፊት በማዕብ በኩል “በግብር ስያየው” ችግር ውስጥ እንዴት እንደሚገቡ ሲረዳው ‘ግንጠላው ለመቃወም ስለሚረዳው” ወያኔን እንዲታገል ሕዝቡ ከወያኔ ደጋፊነት እንዲላቀቅ በር ይከፍታል “ወይንም በደጋፊ እና በተቃዋሚ ጎራ ይከፈል እና ለውጡ በትግራይ ካምፕ ውስጥ እንዲገባ ስለሚረዳ ማዕቀቡ መቀጠል አለበት።
1)
እኔን ጸረ ትግራይ ነው ሚሉኝ ሊኖሩ ነው። ያ ለኔ ደንታ አይሰጠኝም። ጸረ ትግሬ መባል ያለባቸው ግንጠላን እና ጸረ
አማራነትን የሚሰብኩት እዛው ትግራይ ውስጥ ተቀምጠው በሚዲያ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚዘልፉ እና የትግራይን ታላላቅ አባቶች በእሳት
እያቃጠሉ የሚገርፉ እና የሚገድሉ ናቸው “ጸረ ትግራይ መባል ያለባቸው”። ዋናው
ቁም ነገሩ “ከደንቆሮዋ እና ካልሰለጠነች ኢትዮጵያ የሚፈልጉት ነገር ከሌለ፤ ትግሬዎች ለብቻቸው ያለ ኢትዮጵያ መኖር ከቻሉ እና
አክሱማዊ ሥልጣኔ ማምጣት የሚችሉ “ሃያልን ትግሬዎች” ብቻ ከሆኑ ማዕቀቡን እንዴት መቋቋም እንደሚችሉት በግብር እንዲያሳዩን ሁለቴ
እንዲያስቡ ማስተማርያ ፈተና ስለሚሆንላቸው ማዕቀቡ እንዲቀጥል እጠይቃለሁ።
በእግረ መንገዱም ወያኔዎች ትግራይ ሜዳ በትግሉ ዘመናቸው ሲዘምሩት የነበረው “ሓቢርና ንሕሰብ ብዛዕባ ናብራ ሎሚስ ይአኽለና ግዝኣት ናይ አምሓራ “
በእግረ መንገዱም ወያኔዎች ትግራይ ሜዳ በትግሉ ዘመናቸው ሲዘምሩት የነበረው “ሓቢርና ንሕሰብ ብዛዕባ ናብራ ሎሚስ ይአኽለና ግዝኣት ናይ አምሓራ “
(ባንድነት እናስብ ስለኑሮአችን ፤ዛሬስ ይበቃናል የአማራ አገዛዝ) (ምንጭ ጌታቸው ረዳ መጽሐፍ “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነ?” ገጽ 393)
የሚለው
ጉረኛ መፈክራቸው እውን ለማድረግ እንዲመቻቸው ያለ ኢትዮጵያ በአንድነት አስበው ስለኑሮአቸው ካውጠነጠኑ
እንዴት እና በምንስ ሜላ መኖር እንደሚችሉ እንዲያስመሰክሩ ዕደሉን እንስጣቸው። “ ስለሆነም ማዕቀቡ መቀጠል አለበት’
የምለው ለዚህ ነው።
ትግሬዎቹ ሁለት ነጥቦችን
በሰሞኑ ስብሰባቸው ይፋ አድርገዋል።
ትግሬዎች
ብለህ በጅምላ ለምን ትፈርጃለህ የሚሉ ይኖራሉ። የኔ መልስ ይህ ሁሉ ሴራ ትግሬዎች ፊት በመሃል ትግራይ ቁጭ ብለው በይፋ እየተነጋሩ
እና እየተደራጁ ስለሆነ የትግራይ ሕዝብ ተቃውሞውን ሲያሳይ አላየሁም። ይባስኑ
“የኛ ሰዎች አይዟችሁ” እየለ በመፈክሩ እያበረታታቸው ስለሆነ በዚህ ተረዱልኝ። ወይንም በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ብልህ አባባል “““የትግራይ ሕዝብ ተነስቶ ወያኔን ይጥላል ማለት ቅዠት ስለሆነ
እንደየ አግባቡ ትግሬዎች እያልኩ በወል መጥራቴን እቀጥላለሁ። ሁለቱን
ነጥቦቻቸውን እንመልከት
(1)-“ከአክሱም ዘመነ
መንግሥት ጀምሮ እስከ አጼ ዮሓንስ ዘመነ መንግሥት ድረስ ሃብታም እና የሠለጠነቺው ትግራይን በጉልበት “ምኒልክ” የተባለ ሸዌው አማራ አሁን ካለቺው
“ኢትዮጵያ ከምትባል አገር ከቀላቀላት በኋላ” የትግራይ ሕዝብ ሥልጣኔ እና ከተደላደለው የትግራይ ሕዝብ ኑሮ ወደ ድህነት እና ድንቁርና እንድትገባ ሆነ፦
(2)- የትግራይ ሕዝብ
ወደ ኋሊት የገባበት ምክንያት “የተቀደደው ቂጣቸው ለመጣፍ/ለመሸፈን/ ትንሽዋን አውቀት የሆነቺው ሸማኔነት እንኳ በማያውቁ ኋላ ቀር ደናቁርት (ሚኒሊኮች/ አማራዎች/ኢትዮጵያውያኖች) ትግራይን መግዛት ሲጀምሩ ነው ትግራይ ወደ ድንቁርና እና ድህነት የገባቺው…… ወዘተ
እያሉ
አዳራሹን እያስጨበጨቡ
ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ከኤርትራኖች በባሰ መልኩ እየዘለፉ የትግራይን ሕዝብ ለግንጠላ እያዘጋጁት ነው። በአንጻሩ “ጎንደሬዎች’
ኢሳያስብ ለመቀበል “አዋጅ!! አዋጅ!! ” እያሉ
በሚያስገርም አሳፋሪ አዋጅ ጸረ አማራውን ኢሳያስ አፈወርቂን “የጎንደር ሕዝብ በክብር አንዲቀበለው ሲያሽቃብጡ መስማት ከሚገርምም
የሚገርም መስደመም ነው። ሰለሆነም አማራው እንቅልፉን ጠግቦ እራሱ
ተነስቻለሁ እስኪል ድረስ “ተነሳ ታገል” ማለቴን ለጊዜው ጋብ እድሬርጌ
እስኪነቃ ድረስ ትንሽ እረፍት አውስዳለሁ። እስከዛው ግን ቢሉት፤ቢሉት ስለሆነ
ዘንጋዳ ነጭ ነው ሲፈጩት ይነጣል
ተለወሰ
እዛው
ተመለሰ!!! የሚሉት ዓይነት
ስለሆነብኝ
መልካም ዕድል ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ግራ ለተጋባው ለወጣት ኢትጵያውያን በሙሉ መልካሙን እመኛለሁ። እኔ ራሴን
ነፃ አውጥቻለሁ። እያንዳንዱ ራሱን ነፃ ያውጣ! በመጨረሻ የትግሬዎች
ሴራ ለማድመጥ ይህንን ቪዲዮ አድምጡ፦
ብ ዶ/ር ጎይቶኦም ዋዕላ ሰብ ሕድሪ ተጋሩ ወርቂ ዘረባ ። ብምቅጻ ከኣ መምህር ገብረኪዳን ዋዕላ ሰብ ሕድሪ ተጋሩ ወርቂ ዘረባ ። ምንቅስቃስ ኣግኣዝያን
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)