Thursday, September 12, 2019

በ2011 የተዋወቅናቸው ሦስቱ ታዋቂ ባንዳዎች ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Ethio Semay መስከረም 1/2012


በ2011 የተዋወቅናቸው ሦስቱ ታዋቂ ባንዳዎች
ከጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Ethio Semay መስከረም 1/2012
ታማኝ በየነ
ፕሮፌሰር እና የሕግ ጠበቃ አለማዮህ ገብረማርያም
የአብይ አሕመድ ልዩ ቱልቱላ ባንዳው ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት
ብርሃኑ ነጋ 
ብርሃኑ ነጋ 
ብዙ ሰዎች ታማኝ በየነን ለኦሮሞው የፋሺሰቶቹ መሪ ለአብይ አሕመድ  ለባንዳነት ስንሰይመው የሚገረሙ ወይንም የሚደነግጡ ደናቁርቶች እንደሚኖሩ አውቃለሁ። የተለያዩ እስስታዊ የታማኝ ባሕሪያዊ ማንነት ለበርካታ አመታት ከግንቦት 7 መሪዎችም ሆነ ከእስላማዊ ቡድኖችና ኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር ሆኖ ያደረጋቸው ንግግሮቹና ተግባራቶቹ በተለያዩ ጊዜያት በድረገጾቼ እንደገለጽኩት ተከታታዮቼ የሚያውቁት ጉዳይ ነው።

ስለ አማራ መጠቃት አሳስቦኣቸው ወደ ግምባር መድረክ በመምጣት ድምጻቸውን ያስሰሙት ሁሉ እንደ “ኢጎ” (በደንቃራነት) በመሳል ባደባባይም ሆነ ከግለሰቦች ጋር ያደረጋቸው ልሳኖቹ ምስክሮች ናቸው። በዋሺንግተን ዲሲ አደባባይ ወጥቶ አማራዎችን “ከኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር በማነጻጻር” በኢጎ እንደተጠቁ አስመስሎ የተናገረበትን ንግግሩ እንዳለ ሆኖ፤ አማራን ለማዳን ድምጽ ሁንልን ብለው ለጠየቁት ሁሉ “እጅግ ሲጠላቸው እንደነበረና በወያኔነት” እንደሚያያቸው የወልቃይቷ ተወላጅ ወ/ሮ ርስቴ ከአንደበትዋ በሬከርድ ስትናገር የቀዳሁዋትን ምስክርነትዋን አንዲህ ትላለች።

“ከጥቂት አመታት በፊት ነው። አበበ በለው አለ፤ ሻምበል በላይነህ አለ፤ ታማኝ በየነ አለ። እኔ ወልቃይት አማራ እንጂ ወልቃይት ጎንደር ነው የሚባል አልቀበል አልኩኝ። እነዚህ ደግሞ አስታራቂ ሆነው መጥተው ነበር። አማራ ማለት ያን ጊዜ በጣም “አማራ ለማለት” (የሚያሰቅቅ አማራ ነኝ ለማለት ደፍረህ ለመናገር አካባቢው/ድባቡ/ትንሽ የሚያጠራጥርህ ነበር)፡ ታዲያ እነ ታማኝ በየነ እኔን “ይህቺ ወያኔ የላካት ነች” አሉኝ።  ወያኔ እኔን ሊጥለኝ የሚችል ሁኔታ ካለ የአማራ ጉዳይ ነው የሚል ስጋት ስለነበረው ፤ተቃዋሚዎቹ ያኔ አማራ ለማለት የሚደፍሩ አልበሩም። ያኔ እኔ “ቲ ፒ ኤል ኤፍ” ለማሸነፍ ከፈለጋችሁ የአማራን ትግል ደግፉ፡ አማራ ብለን መነሳት አለብን ብየ ተናገርኩኝ። ያኔ ጊዜ ሁሉም አበበ በለው፤ታማኝ፤ ሻምበል በላይነህ  በጣም ነው የጠሉኝ! በጣም! በጣም! ወያኔ የላካት ትግሉን ለማፍረስ ወያኔ የላካት ምናምን ተባልኩ።

ያኔ አማራ ብለው ቢነሱ ዛሬ የተጫነብን ሃይለኛ ፈተና ይቀል ነበር። ታማኝ ንጸህ ሰው ነው። ሰው አልገደለም፤ጥፍር አልነቀለም፤ ነገር ግን ታማኝ በየነ አብይ አሕመድ የሚባል ጥፈር ሲያስነቅል የነበረ፤ ሰው ሲያስገድል የነበረ አንድ ‘የኢንሳ’ ወንጀለኛ እግሩ ላይ ወድቆ እግሩ ላይ ሲሳለም በጣም ነው ያመመኝ! በጣም!...” በማለት ታማኝ በየነ በአማራ ትግል ላይ የቆሙ ዜጎች የሚጠላ ምን ያህል ርቀት ርቆ እንደነበር ርሰቴ በራስዋ የገጠማትን መስክራለች።

በአናርኮ ፋሺሰቱ አክራሪ ጴንጤአዊ እስላማዊው አብይ አሕመድ ጫማ ስር መደፋቱ ሳይሆን ዋናው ቅሬታ ዛሬም ጫማው ስር ወድቄ መሳለሜ ቅር አለይኝም ብሎ አሁንም ራሱን ያሳምናል) ፤ ታማኝ በየነ ሙሉ አመት ማለትም በ2011 ዓ.ም ድፍን 360 ቀናት ጫማ እግሩ ላይ ተነጥፎ የተሳለመው አብይ አሕመድ በሰራቸውና በተናገራቸው በጣም ዘግናኝ ስራዎች እና ንግግሮች “ትንፍሽ” ላላማለት ቃል ገብቶ 360 ቀኖች ምላሱን አስሮ ቆይታል። ዜጎች ሲያለቅሱ አመት ሙሉ የበበውን ምላሱን ለመሸፈኛ/ለማካካሻ ሲባል መሪው አብይ አሕመድና የጎንዮሽና የግሃድ ጓዶቹ ያደረስዋቸው ሕዝባዊ ጥቃቶችን በመጠገን “አላያንስ” በሚባል ድርጅት ታቅፎ “በፈረሱ ተቁዋማት/ወይንም በሚያለቅሱና በተፈናቀሉ ወገኖች ላይ የጥገና መርሃ ግብር” ተሰማርቶ የአብይ አስተዳዳር ያደረሳቸው ብሔራዊ ጥቃቶች በመጠገን እና አብይ ያስለቀሳቸው እና ያስራባቸው ዜች ላይ በማባባልና በመመገብ ስራ ተሰማርቶ ወዲያ ወዲህ ሲል እንደነበረ ይታወቃል።

ይህ ስራ በመስራቱ ለምን ትነቅፈዋለህ ብለው የሚቃወሙኝ ዜጎች እንዳሉ አውቃለሁ። ሥራው ‘በጎ ነው በጎ አይደለም’ የሚለው ሳይሆን እንዲህ ያለ ስምሪት  የሚያስታውሰኝ በደርግ ጊዜ ሲደረግ የነበረውን ነው። የችግሩ መነሻ “ሻዕቢያን እና ወያኔን የማስወገጃ ንድፍ አጥንቶ አፍራሹን ቡድን ከማስወገድ ይልቅ” ትኩረቱ የነበረው “ሁለቱም ጸረ ሃይላት ሲያፈርሱዋቸው የነበሩዋቸው መዋቅሮችን ፤በመጠገን ላይ ሙሉ ሃይሉ ተረባርቦ ትኩረት ይሰጥ እንደነበርና በሳምንቱ ተመልሶ ያ ተመሳሳይ ችግር እየተደጋጋመ ይከሰት አንደነበረው ሁሉ፤ ዛሬም በ2011 ዓ.ም ታማኝም ለጥቃቱ ዋና መነሾ የሆነው አፍራሹ አብይ አሕመድን ከመቃወም ይለቅ አብይ እና ተላላኪዎቹ ባፈረስዋቸው ብሔራዊ ተቁዋማት እና ዜጎች ሲያነቡ፤ ሲጮሑ በዜጎች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ለማስቆም ሳይሆን ለመጠገን የተሯሯጠበትን ተመሳሳይ ታሪክ ነው ታማኝ የደገመው።

ታማኝ ለዘብተኛ ብቻ ሳይሆን ዝግምታዊ የሆነ ባንዳዊ ባሕሪ እግሩ ላይ ተጎንብሶ ለተሳለመው ለፋሺሰቱ እና ቅጥረኛ አብይ አሕመድ ዓሊ ማጎብደዱ የ2011 ዓ.ም አሳዛኝ ክስተት ካደረጉት አንዱ የታማኝ መሞዳሞድ ባሕሪ ይፋ ወጥቶ ማየታችን ነው።በዚህ አጋጣሚ ወንድሙ ተወልደ በየነን (ተቦርነ) አመሰግነዋለሁ። እጅግ ሃቀኛ ሃገራዊ ነው!

ሁለተኛው የ2011 ዓ.ም ሌለው አዲሱ ባንዳ ፕሮፌሰር እና የሕግ ጠበቃ አለማዮህ ገብረማርያም ነው። ባጭር የስም አጠራር “አል ማርያም”። ይህ ሰው ወያኔ ሲገባ ጀምሮ እናቶች እና አማራዎች እየታረዱ ጥቂት ምሁራን እና ጥቂት ዜጎች አብረን በጋራ ወያኔ ስንታገል የነበርን ሰዎች የምናስተጋባውን የዜጎች ጩኸት ከምንም ሳይሰማው 10 አመት ሙሉ ተንደላቅቆ ተኝቶ ሲዝናና ቆይቶ “በቅንጅት” (ከ13 አመት በፊት) ወቅት ከተኛበት ባንኖ ወያኔን በመቃወም ወደ ትግሉ የተቀላቀለን ሰው ነው።

ቅንጅት ሲፈርስ ተጨማሪ የማፍረስ ጨዋታ ከተጫወቱት ከነታማኝ በየነ፤ ከነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ከነ አበበ በለው፤ ንአምን ዘለቀ አንጃ በመፍጠር በዲያስፖራው ዓለም ቡድን በመለየት “አፍራሽዋ” ብርቱካን መዲቅሳን እየተንከባከቡ በውጭ አገር አንድነታችን ፈርሶ በብርቱካን ቡድን እና በሃይሉ ሻውል ጎራ በቡድን እንድንከፋፈል ንትርክ ውስጥ ከከተቱን ዋናው ሚና ከነበራቸው አል ማርያም እንደነበር ይታወሳል። ያ መከፋፋል እስከዚቺው ደቂቃ ድረስ ሊድን አልቻለም።

ያ በእንድያ እንዳለ ወያኔን በመቃወም ግምባር ቀደም ተሰልፎ ሲቃወም ቆይቶ ያንን የቡድንነት ሚና እና አፍራሽ ባሕሪው በመቀጠል ዛሬም ወደ አብይ አሕመድ ቡድን ተጠቃልሎ በመግባት ግምባር ቀደም አወዳሽ እና ዘማሪ ሆኖ በየ ዜና ማሰራጫዎች አሳፋሪ የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎችን ሲነዛ እያየን ነው። ይህ ሰው አልተማርም እንዳይባል የሕግ መምህር እና የሕግ ጠበቃ ነው። ከሚያንጸባርቀው አምባገነኖችን የማወደስ ተግባሩ ሲነጻጸር በዩኒቨርሲቲው ምን እሚሉት ትምህርት እንደሚያስተምር ግራ ቢገባኝም፤ ለሕግ መምህርነት የማይገባ “የፋሺሰቶችን ፍልስፍና እና አስተዳዳርን” የሚያሞግስ ሰው ሆኖ ማግኘታችን እጅግ የሚያስገርም ዘመን ሆኖ አግኝቼዋለሁ።   

ከጅምሩ የአማራዎችን ማሕበር በመቃወም ያሳየው ባሕሪ ለመሪው ለአብይ አሕመድ ስጦታ እንዲሆነው በማለት ወይንም በቀጥታ መረጃው ከየት እንዳገኘው ያልታወቀ ጸረ አብን (አማራ ብሔራዊ ብቅናቄ) በውሸት የነዛው ጸረ አብን ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ያነበቡ ዜጎች እንዲህ ሲሉ ተችተውታል።

ከጅምሩ የአማራዎችን ማሕበር በመቃወም ያሳየው ባሕሪ ለመሪው ለአብይ አሕመድ ስጦታ እንዲሆነው በማለት ወይንም በቀጥታ መረጃው ከየት እንዳገኘው ያልታወቀ ጸረ አብን (አማራ ብሔራዊ ብቅናቄ) በውሸት የነዛው ጸረ አብን ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ያነበቡ ዜጎች እንዲህ ሲሉ ተችተውታል።
In his recent commentary, Mariam indicated that the TPLF old guards have masterminded a plot against the “reformists” or in his own words – the “non-violent change”. Accordingly, TPLF is forgoing a tactical alliance with Arena Tigray, NaMA and OLF, so as to wage a scorted earth opposition against his romance party, EPRDF.
ትርጉም፦

በቅርቡ አል-ማሪያም ባሰራጨው ጽሑፉ የህወሓቶች አስተባባሪዎች “አመፅ አልባው ለውጥ” ላይ ሴራ እንዳሳዩ አመልክቷል ፡፡ በዚህ መሠረት ህወሃት ፓርቲው በኢሕአዲግ ላይ ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ተቃውሞ ለማምጣት ከአርና ትግራይ ፣ ከአብን እና ከኦነግ ጋር የትግል ጥምረት እየፈጠረ ይገኛል ፡፡

”ምንጭ
(Prof. Alemayehu Gebremariam is engaged in a defamation and false propaganda campeign against the National Movement of Amhara (NaMA)(By Dessalegn Chanie Dagnew, NaMA chairman)

ምንጭ- ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ላይ የስም ማጥፋት እና የውሸት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄደ ነው ፡፡
(በደስአለኝ ጫኔ የአብን ሊቀመንበር)


ባጭሩ ከላይ እንዳያችሁት አል ማርያም እንዲህ ያለ ውሸት በአብን ላይ ሲነዛ አንብበናል። ካንድ የሕግ ምሁር የውሸት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ነውር ነው። 

ይህ ሰው ኢትዮጵያን ዲያስፖራ ትራስት ፋንድ በመባል የሚታወቀው ለአብይ አሕመድ አሳሳቢነትና ጥያቄ ከውጭ አገር ኢትዮጵያውያን የሚሰበሰብ ገንዘብ ከነታማኝ በየነ ጋር ሆኖ በሊቀመንበርነት የሚመራ ለፋሺስቶቹ አስተዳዳር የሚያጎበድድ እጅግ አሳፋሪ ምሁር ነው። ማፈሪያ መሪዎችን ማድነቅ በኢሉሙናቲው መሪ “ኦባማ” የጀመረው ማድነቅ ዛሬም በሌላው የውጭ አገር ቅጥረኛ የሆነው አብይ አሕመድ ላይ ማድነቁን ተያይዞታል። አል ማርያም እና ታማኝ በሚሳተፉበትት ይህ ድርጅት በመላ ኢትዮጵያውያን እንዳልተደገፈ እራሱ አል ማርያም እንዲህ ሲል ላጎበደደለት ለአብይ አህመድ የምስጋና ደብዳቤ በጻፈለት ደብዳቤ እንዲህ ይላል።     

When you have been doing all of the heavy lifting over the past 8 months, and millions of us in the diaspora could not lift a dollar a day to support the EDTF, I am not sure we deserve such overwhelming gratitude from you. ትርጉም- (ባለፉትን 8 ወራት ከባድ ጭነት ትከሻሕ ላይ ተሸክመህ ስትሰራ በሚሊዮኖች የምንቆጠር እኛ ዲያስፖራዎች ‘ኢዲቲ ኤፍን’ ለመደገፍ በቀን አንድ ዶላር ለማውጣት ለግመናል። ስለሆነም አመስግናለሁ ስላልከን ምስጋና እንደዚህ ያለ የላቀ አድናቆት የሚገባን መሆናችንን እርግጠኛ አይደለሁም።” ሲል ኢትዮጵያውያን በቀን አንዲት ዶላር ለፋሺሰቶቹ ለዘመነ ኦሮሞዎቹ ለነ አብይ አሕመድ አስተዳዳር ለማዋጣት እንደለገመ አል ማርያምም ሳይሸሽግ ሃቁ ከምላሱ አምልጦት ተናግሯል።

የአብይ አሕመድ የውጭ አገር ፐሮፐጋንዳ ሰባኪው አዲሱ ባንዳው አልማርያም እንዲህ ይላል፡
 "There are those who are quick to criticize you and insist that you walk on water before they even acknowledge your work let alone express their appreciation." (የተሸከሙትን ሓላፊነት) በቅጡ ሳይመለከቱ አድናቆትን ለመግለጽ ቀርቶ እርስዎ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ እና በውሃ ላይ እንዲራመዱ የሚከራከሩ አሉ:::"

 የባንዳው አል ማርያም የበሰበሰ የማስተዋል ብቃት የሚመዘነው እዚህ ላይ ነው። ከላይ እንደተመለከታችሁት (የተሸከሙትን ሓላፊነት) በቅጡ ሳይመለከቱ አድናቆትን ለመግለጽ ቀርቶ እርስዎ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ እና በውሃ ላይ እንዲራመዱ የሚከራከሩ አሉ:::"  የሚለው ስንመለከት በዚህ ሰውየ አንድ አመት አስተዳዳር በአገራችን የደረሰው ውድመት እና የተደመጠው የእናቶች ዋይታ፤የቤተክርስትያናት ውድመት እና የቀሳውስት መታረድ በግራኝ አሕመድ ዘመን የታየው እልቂትና ዋይታ የሚመሳሰል እና ክፉ አደጋ እንዲጎለብት ያደረገ አደገኛ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውን አክራሪ ኦሮሞው አብይ አሕመድ የተጠየቀው አልማርያም እንደሚያጋንነው “እንደ እየሱስ በውሃ ላይ እንዲራመድ ሳይሆን ሕዝባችን የጠየቀው” “እየደረሰብን ያለው አገራዊ እና ሰብአዊ ውድመት ተሎ አስቁምልን ሲል ነበር የጠየቀው (አሁንም ጥያቄው አልተመለሰም)። ስርዓተ አልበኛውን አብይን ሥርዓት አስፍን ብሎ መጠየቅ በባንዳው አልማርያም ትርጉም “አብይ አሕመድ በውሃ ላይ እንደ እየሱስ ለምን አልተራመድክም’ እያሉህ ነው እያለ ሕዝባዊውን ጥያቄው ፈር እንዲስት ተርጉሞታል። እንዲህ  ዓይነቱ ታገሱ፤ … ጫማ ሳሙ፤ ስግኑ፤ አሞግሱ…ዝም በሉ…ወዘተ..ወዘተ. የማሽቃበጥ ባህሪ የተማሩ ባንዳዎች ለአዳዲስ ጌቶቻቸው ጥላ ላትጥል ዕንቁላል ለመጣል እያስካካች መንደሩን እንደምትረብሽ ዶሮ የሚያስደምጡት ድምፅ አንዱ እንዲህ ዓይነቱ ማስካካትን ነው።

I must tell you that it really bothers me why your compatriots, particularly those in the learned and professional communities, withhold their gratitude and appreciation for your extraordinary accomplishments. "የተማሩ እና የባለሙያ ማህበረሰቦች ያሉዎት ልዩ ለሆኑት ግኝቶችዎ ምስጋናቸውን እና አድናቆታቸውን የማይሰጡበት ምክንያት በእውነቱ የሚረብሸኝ ግኝት መሆኑን ልነግርዎት እፈልጋለሁ።" ሲል የተማረው ክፍል እንደ አል ማርያም ለምን ለጥ ብሎ ለፋሺት ኦሮሞ አስተዳዳሪዎች ቱልቱላቸውን አልነፉም ሲል የተረበሸው ሕሊናው ለጌታው ቅሬታውን አስደምጦታል። ባጭሩ ፕሮፌሰር አል ማርያም ለአናርኮ ፋሺሰቱ ለአብይ አሕመድ ማሽካካቱ የወያኔው ባንዳ እንድርያስ እሸቴን ገጸ ባሕሪ እንድናስታውስ አድርጎናል።

ከላይ በእንግሊዝኛ የተጠቀስኩዋቸው ጥቅሶች ምንጩ Thank You PM Abiy Ahmed for All You Have Done for Ethiopia! Posted in Al Mariam's Commentaries (By almariam On December 31, 2018) PM Abiy Ahmed ለኢትዮጵያ ላደረጉት ሁሉ አመሰግናለሁ! ታህሳስ 31, 2018)። ከሚል ሳምንታዊ ኪመያሰራጫቸው ባንዳዊ ሐተታዎቹ ያገኘሁት ምንጭ ነው።

ሦሰትኛው ባንዳ፤ ያው የምታውቁት ከባንዳ በሕሪ መላቀቅ የማይሆንለት ብርሃኑ ነጋ ነው። ስለ ብርሃኑ ማንንት መዘርዘር ለቀባሪ ማርዳት ስለሆነ ስለ ብርሃኑ ጊዜ ሳላጠፋ ፎቶግራፎቹን ብቻ አቅርቤ ልሰናበታችሁ። መልካም አዲስ አመት አንዲሆንላችሁ ስመኝ በፋሺስቱ አብይ አሕመድ አንድ አመት አገዛዝ ቤቶቻችሁ ንብረታችሁ ቤተክርስቴአናቶቻችሁ የወደሙባችሁ ምዕመናን እና በጽንፈኛ ኦሮሞዎች የታረዱ ካህናቶቻችንና ምእመናን እንዲሁም በዚህ ፋሺት ግለሰብ ያለቁባችሁና የተፈናቀሉባችሁ ዜጎቻችን እንዲሁም “በእንቅርተ ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ማራዎች ያሳለፉት የ28 አመት ጭፍጨፋ እንዳይበቃ ዛሬም በአናርኮ ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ ትዕዛዝ በሚያዛቸው ወታደሮቹና ፍርድ ቤቶቹ ወደ እስር ቤት ተገፍትረው ጭለማ ውስጥ የተጣሉ አማራዎችና የሌሎች ነገድ ቤተሰቦች መጽናናትን ብርታቱን እንዲሰጣችሁ እመኛለሁ። ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Ethio Semay