Sunday, November 20, 2022

መልስ ለዶ/ር ደረጀ ዘለቀ መኮንን - ተግባርና ትንተና አብሮ የማይሄድ የልሂቃን ዝቅጠት ጌታቸው ረዳ Ethiopain Semay 11/20/22

 

መልስ ለዶ/ር ደረጀ ዘለቀ መኮንን - ተግባርና ትንተና አብሮ የማይሄድ የልሂቃን ዝቅጠት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopain Semay 11/20/22

ዶ/ር ደረጀ በአዲስ አባባ ዮኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ነው። የሕግ ትምህርት ከተማሩት ጥቂት የትግራይ እና ኢትዮጵያ ምሁራን ጋር በየፌስቡኩ ስከራከራቸው የዶ/ሩ ቃል ልጠቀምና ፡ጭራሽ የደነቆሩ” ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ደ/ር ደረጀ ካሁን በፊት ስለ ባሕር ወደቦቻችን አንስቶ በሰጠው አስተያየት በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ በለጠፍኩት መልስ እንዳነበባችሁት ይታወሳል። እንደ የሕግ ባለሞያነቴ እያለ ሁሌም የሚሽከረከርበት ልግጫ “ዓሰብ ዓሰብ የሚሉ ጦርነት ውስጥ እራሳቸውን አያስገቡም” እያለ የወያኔ ን ፕሮፓጋንዳ እየደገመ የሚያሾፍ የሕግ ምሁር ነው።

ኤርትራን በሚመለከት ከሦሰት ጊዜ በላይ በተጣሱ የኮሎኒያል ሕጎች እንደተከናወነ ይታወቃል (ከፈራሚዎቹ ጀምሮ በጉልበትና በሻጥር የተከናወነውን እንዳለ ሆኖ በሕግ ከተነሳም እኛ እንዳልወከልናቸውና ዓለም ሕግም እንደሚደግፈን ሳላነሳ ማለት ነው)። ኢትዮጵያዊ መሪ ሲገኝ ያኔ ጉልበት ወይንም ሕግ የሚያነሳው ጉዳይ ሆኖ ያንን አሁን አልገባባትም፡ ሆኖም  ዶ/ር ደረጀን የተቸሁበትን June 6, 2019 ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)   https://ethiopiansemay.blogspot.com/2019/06/ethiopian-semay.html ማንበብ ትችላላችሁ።

ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ዶ/ር ደረጀ በሁለት ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ አድረጓል።በርዕዮት “ቴድሮስ ፀጋዬ” እና በቪ ኦ ኤው የድሮ ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ የሚዘጋጀው “አዲሱ ሚዲያ” በሚባለው አውታር- ከመስከረም አባራ ጋር ያደረገው”።

 ደረጀ አማራን አስመለክቶ በርካታ ሃሳቦቸን ሰንዝሯል።

 ወደ ሰጠው አስተያየት እንምልከት፤

ወደ አዲሱ ሚዲያ ከመግባቴ በፊት ከርዕዮት (ቴድሮስ ጸጋዬ) ጋር ያደረገው “በእራሱ መዳን ላይ የቆለፈው አገር? ለኳሽ ሀሳቦችና ተንኳሽ እውነቶች . . .| ቆይታ ከዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ጋር 11/19/22” በሚል ውይይት ስለ ደርግ ስርዓት ተነስቶ ሲተነትን “ደርግ ማንም ሰው ያለ ምንክንያት አይገድልም” ይላል። “ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ የተገደሉበት ምክንያት በምክንያት እንደሆነና እሳቸውም ኦሮሞ ስለሆኑ ኦነግ ጋር እየሄዱ ሲሞዳሞዱ እንደነበር ባንድ መጽሄት ስላነበብኩ ደርግ በዛው ምክንያት ገድሏቸዋል” እያለ የሌለ ታሪክ እየፈጠረ የደርግ ገዳይነት በምንክያት እንደነበር የሕግ ዕውቀቱ ጎርፍ እንደወሰደበት አመላካች ንግግር ተናገሯል።

በዛውም አላበቃም፡ ስለ አማራ ብሔረተኛነት አንስቶ ሲናገር ፡ ማንኛውንም ብሔረተኛነት ኩፍኛ ሲኮንን ይደመጣል። እኔም ያንን አይነት መስመር ሳካሂድ ነበር። ሆኖም ውሎ አድሮ የተማርኩት መሬት ላይ ያለው የአማራ መገፋት ወደ አማራዊ ብሔረተኛነት እንዲቆሙ ያደረጋቸው ምክንያት እና ደረጀ እየተናደደበትና እየዘለፋቸው ያለው አማራዊ ብሔረተኛነት ከሚለው ጋር አይገናኝም። ጥቂት የአማራ አክራሪዎች አሉ- ያ ግን ሙሉ አማራዊ ጤነኛ ብሔረተኛውን ሙሉ በሙሉ “ቁስሉን” መደፍጠጥና ምክንያቱን ማናናቅ  ሕግ እያለ የሚሽከረከርብት የመስደቢያ ቆብ ተጻራሪ ነው።

የብሔረተኛነት ትርጉም ኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን “ኦነጎች አማራዎችን  አንድ ሞት ሳይሆን ብዙ ጊዜ እንዲሞቱ አርደው እንደ ከብት ሰውነታቸውን በቢላዋ እየቆራራጡ ሲበልዋቸው እራሳቸው ባሰራጩት ቪዲዮ ተምልክታችሗል (እኔ እንኳ ገና ጫፉን ከፍቼ ሳይ ደንግጬ ማየቱን አቆምኩኝ)”። የአማራን ነብስ ለማዳን ግማሹ ጫካ ጠመንጃ ይዞ ለመዋጋት “ሃ ብሎ ለተነሳው አማራዊ ብሔረተኛውን”፤ብዙዎቹ ደግሞ በተደራጀ እና ባልተደራጀ መልኩ የአማርን ብሶት እያስተጋባ ሕዝቡ እራሱን መከላካል እንዳለበት አሁን ያለው መንግሥትና ወኪሎቹ ጋር ፍልሚያ እንዲያደርግ እና እየደረሰበት ያለው ግድያና መፈናቀል እንዲቆም እየታገለ ያለውን አማራዊው ክፍል ጭራሽ ምክንያት እንደሌለው “ጭፍን ብሔረተኛ” (ደረጀ የሚያከብረው በወያኔው አፍቃሬ “ሃገረ ትግራይ” በቴዎድሮስ ጸጋየ ገለጻ“ ያገጠጠ ብሔተኛ” የሚለውን አድርጎ  ደረጀ አማራዎቹን ይፈርጃቸዋል።

ደረጀ “ብሔረተኛነት” ሲገልጽ “ኣእምሮን ቁጭ አድርጎ በስሜት የሚነዳ ትምክሕተኛ የሚያደርግ ስሜታዊነት ነው” ሲል ይገልጸዋል። እኔ ደግሞ እነ ደረጀ የመሳሰሉትን ለማስረዳት የከበደኝ ነገር “አማራው ስለ አማራ ሲቆም ስሜት ነድቶት ሳይሆን ተግባር ነድቶት ነው”” አማራ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ “ስሜት” ሳይሆን “ጨካኝ ተግባር” ስለሆነ አማራው በስሜት አልተነሳሳም፤ በትምክሕት አልተነሳሳም፤የበላይነት ተሰምቶት አልተነሳም።  የገፋፉት ‘እስካሁን ድረስ በላዩ ላይ እየተደረጉ ያሉ የ30 አመት ጨካኝ ግፎች ናቸው”።  አማራው አጣብቂኝ እንደገባ ደረጀ እራሱ የውቃል። አማራው ኢትዮጵያ ብሎ ሲታገል “የድሮ ሥርዓት ናፋቂ” ይባላል፤ “አማራ ብሎ ሲነሳ ደግሞ “ያገጠጠ ብሔረተኛ” ይባላል፡ ምን ይሁን ነው የምትሉት? እዚህ ላይ “ስሜት” የት አለ? ደረጀ አማራውን ከመታረድና ከመፈናቀል ነፃ ለማውጣት ንድፍ ነድፈህ ሕዝብ የመራኸው የትግል ስልት የለም። አንተ በሌለህ ‘ባዶ ስልት’ አማራው ምን ይሁን ነው የምትለው? ዝም ብሎ እየታረደ የኦነጎች ምግብ ይሁን ነው የምትለው? ትግሉን መምራትና መንደፍ ካልቻልክ እንደ ጨዋ “አፍን መዝጋት” ምን ይከብዳል? ባንተው ቃል ኢትዮጵያ የሚባል ሕዝብ “ጨካኝ ማሕበረሰብ ነው” ስትል አማራው ጨካኝ በሆነው አርዶ ሰውን በሚበላ በጉምዝ ጫካና በኦሮሞ ከተሞችና ጫካዎች “ለእርድ ቅርጫት” ሲከበብ አማራው ብሔረተኛ ከመሆን ሌላ “ምን ይሁን” ነው የምትለው? ስሜት ጋር ምን አያያዘው? ሁሉንም ሞከረው አልተሳካም! የደሞዝ ጭማሪ አይደለም እየጠየቀ ያለው፤ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው የተጋረጠበት። ስሜት ገባ እንበልና አማራዎች እየታረዱ ሰው የሚበሉ የሰው አራዊቶች ምግብ ሲሆኑ አይቶ በስሜትና በቁጣ ቢነሳ ይፈረድበታል? ሰው ግፍ ሲፈጸምበት ስሜታዊ ከመሆን እንዴት ሊርቅ ይቻላል (የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ ሆኖም ምክንያታዊ ስሜት እና ትዕቢታዊ ስሜት ለየብቻ ናቸው፡ሁኔታውን መረዳት አለብን)።

የሚገርመው ደግሞ ደረጀ እንዲህ ይላል፡

<< የአማራ ብሔረተኛነት ድግሞ ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሰ ነው -Almost ወደ near madness የደረሰ ነው) ያ ደግሞ በኔ ላይ ሲፈጸም አይቼዋለሁ (ከመስከረም አበራ ጋር ባደረገው ውይይት ነው እየተናገረ ያለው)ባጠቃላይ “ናሺዘናሊዝም” ሲባል ከ ‘ሪዝን’ (ከምክንያት) የሚፋታበት ነው፤ ለራሱ ትርክት የሚሆኑት ፋክቶች በኪሱ ይዞ የሚሄድ የሚንቀሳቀስበት ሂደት ነው። ለምሳሌ ጀርመን የነ ሲግሞይድ የነ ካርል የነ ብዙ ሊቃውንት ሀገር ነው….ሰው እስከ መቀቀል ድረስ ያበደ ብሄረተኝነት ያደረሰው ብሔረተኛነት ነው……>>

እያለ ይተነትናል።

ደረጃ የሳተው ነገር አለ። አርደው ቀቅለው እየበሉት ያለው የኢትዮጵያ ናዚዎች አማራው ሁለት ጊዜ ተጠቂ ሆኗል። አንዱ በነ ደረጀ የመሳሰሉ መጽሐፍን ብቻ በሚያነበንቡ ምሁራን ዓኢን “ብሔረተኛ” ተብለው እንደ ናዚዎቹ ስም ሲለጠፉበት፤ ሌለው ደግሞ አራጆቹ አርደው የሚበሉት “የአብርሃም በግ”  ሆኗል።

 በሕግ አስተማሪዎች በእነ ዶ/ር ደረጀ ዘ መኮንን ፍርድ አማራው ብሔረተኛ “ከምክንያት የተፋታ፤ ለራሱ ትርክት የሚሆኑት ፋክቶች በኪሱ ይዞ የሚሄድ ተንቀሳቃሽ በስሜት የሚጓዝ” ሆኖ ሲሳል መስማት እንኳን ለአማራው ለሌላውም ያሳምማል።

አልፎም የኢትዮጵያ ብሔረተኞች ሁለት ናቸው ይላል ደረጀ

<< የመጀመሪያው ብሔረተኛው “የእየየ ናሺናልዝም” ነው፡ በድለውን ጡታችን አርደውን፤እንዲህ አድርገውን  …የሚሉት ‘የአልቃሾች ናሺናሊዝም’ ነው፤ ሁለተኛው ደግም የናዚ ጀርመን ናሺናሊዝም አይነት ነው። ይህ ደግሞ የሱፐርየር (የባላይነት) የሚደልቅ የዘር ልዕልና የሚያንጸባርቅ ነው፤ ሌለው ዘር መትቶ ደማችንን አቆሸሹት የሚለው ነው። >>

እያለ በሁለት መልክ ይተነትናቸዋል።እየየ ናሺናሊስቶቹ (አልቃሾች) የሚላቸው ኦነግና ኦሆዴዶች እንደሆኑ ይገልጻል። የበላይነት (ሱፕረማሲሰት) የሚላቸው ደግም

“ትግሬና አማራ” ናቸው።  << ለናዚው አይነት የበላይነት ለማንጸባረቅ “ፖተንሻሊቲ” ያላቸው ይላቸዋል።

በዚህ ትንታኔው ውስጥ የድሮ ታሪክ ከተነተነ በሗላ  

እያወገዘው የነበረውን ያገጠጠ የአማራ ብሔረተኛ የሚለውን “አማረራዊ ብሔረተኛ” ተመልሶ ምን ሲለው ይደመጣል? ይኼው አድምጡልኝ፤

<< አሁን የአማራ ናሺናሊዝም የሚባል የለም ነው የምለው >> << ከኖረ ግን እግዚአብሔር አይቅናው ቀንቶት ሥልጣን ከያዘ የአማራ ናሺናሊዝም የሂትለርን የሚመስለው ፋሺዝም ነው እዚች ሃገር የሚያሰፍነው! >> ሲል በሚያስቅ እና በሚያስደነግጥ ሁለት አስተያየቶች ይተነትናል።

 የሚያስቀው (አየሚያስቅ ከሆነ ) መጀመሪያ  የአማራ ብሔረተኛነት እንዳለ እራሱ እንዲህ ይገልጻል፤

<< << የአማራ ብሔረተኛነት ድግሞ ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሰ ነው -Almost ወደ near madness የደረሰ ነው) ያ ደግሞ በኔ ላይ ሲፈጸም አይቼዋለሁ >> ሲል ቆይቶ ተመልሶ እንደገና እራሱን በሚቃወም መንገድ

<< አሁን የአማራ ናሺናሊዝም የሚባል የለም ነው የምለው >> ይላል ዶ/ር ደረጀ ።

አንድ የሕግ ምሁር ያውም የየኒቨርሲቲ መምህር  እርሱ በሚያስተምርበት ክፍል ውስጥ እነዚህ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች አንስቶ ቢያስትምራቸው ተማሪው የትኛውን ይያዝ ቢባል “የትኛውን ይይዛል”?

ሌለው በጣም የሚገርመው ደግሞ የትግሬዎች ናሺናሊዝም ልክ እንደ ጀርመኖቹ የትግሬ ናዚዎች/ ወይንም “የትግሬዎች ፋሺዝም” ላለማለት << “የወያኔ እየየ ብሔረተኛነት” >> እያለ ይጠራዋል። አማራው ጋር ሲደርስ ግን

<< “የአመራ ናሺናሊዝም የለም እንጂ ከኖረ እና ቀንቶት ሥልጣን ከያዘ የሂትለር የሚመስለው ፋሺዝም ነው እዚች አገር የሚያሰፍው” >> ይላል።

27 አመት ያየነው የትግሬ ፋሺዝም “በእየየ አልቃሻ ናሺዘናሊዝም” ቃል ብቻ ሲፈርጀው የአማራው ብሔረተኛ ግን  “ወያኔ ያላደረገው የናዚ አይነት ፋሺዝም” እንደሚያመጣብን ሳያመነታ ይናገራል።  ይህ የፖለቲካ ድንቁርና ወይስ ፍርደገምድል?

የአማራው ናሺናሊዝም(ያውም እንደ ሌለ እና እንደ ናዚ ይሆናል የሚለንን እርግጣኛ ሳይሆን ግምታዊ መሆኑን ነው የነገረን)  ከትግሬው ናሺናሊዝም በተለየ መንገድ “የአማራው እንደ ጀርመን ናዚ” ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ምን ይሆን? ጠያቂውም አልጠየቀውም (ብዙም ባይጠበቅም)።

ደረጀ ለአንድ አመት “ዲፕረሺን” (ድብርት) ታምሞ በዛው ድብርት ሕመሙ ላይ ሲያስተምር እንደነበር ገልጾልናል።ከምላሱ የሚናገራቸው ካንድ የሕግ ምሁር የማይጠበቁ ቆሻሻ ቃላቶች ሲናገር “ምናልባት በጤና ቀውስ ሊሳበብበት ይችል ይሆናል” ሆኖም ደረጀ ከበሽታ የራቀ ጤናማ ሰው ነው። በሽታው ግን “ድንቁርና” ሊሆን  ይችል ይሆናል። በዚህ ድንቁርናው እንዲህ ይላል፡

<<  አይበልና አማራ ብሔረተኞች ሥልጣን ብይዙ በግልጽ ነው ዛሬ የምናገረው ‘ይኼ ወላሞ፤ ሻንቅላ ምናምን እያሉ ካገር የሚያባርርዋቸው ነው የሚመስለኝ። ወይንም ሂትለር እንዳደረገው በጋዝ ቸምበር አስገብቶ አይሆዱን አንደጨረሰው እነዚህም ሥልጣን ከወጡ የተጠቀሱትን ነገዶች ሰብሰው የሬሳ ማቃጠያ ውስጥ አስገብተው እንደሚያቃትልዋቸው ነው የማምነው።>> አብየት ቴድሮስ ጸጋዬና ወያኔዎች እንዲሁም ኦነጎች እንዴት ደስ ብሏቸው ይሆን ይህንን ሲሰሙ!?

እንዲያ ያለ ነውረኛ ትንቢት እጅግ የሚገርም ዘግናኝ የትንቢት ውንጀላ ይገልጻቸዋል ።ይህ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን ወላሞችና ሻንቅላ የሚላቸውን ነገዶች (ሌሎችም ጭምር) አማራው ይበልጥ እንዲጠቃ ለማናከስ የሚቀሰቅስ ንግግር ነው። ፕሮፌሰር ምስፍን ወልደማርያም በጻፉት አናካሽ ጽሑፍ (ስለዚያኛው በዚህ ድረገጼ ላይ ፈትሹት አሁንም አለ) አማራን አስምልክቶ ለሶማሊዎች የጻፉትን ታሪክ የዶ/ር ደረጀ ንግግር ተመሳሳይ ብቻ ሳይሆን አጅግ የከፋ የማናከስ ቅስቀሳ ቀስቅሷል። ለዚህ ወንጀላው ደግሞ አማራ ብሔረተኞች የሚላቸውን እነ ምምህርት መስከረም አበራን የመሳሰሉት ቅን ሰዎችን ነው ለወደፊቱ ሥልጣን ቢይዙ ይህ አሰቃቂ የናዚ ድርጊት ያደርጋሉ እያለ በቆሸሸ ምላሱ የሚተነብየው። ይህ አደገኛ ንግግር ከድንቁርና ብቻ ሳይሆን ያልተፈተሸ አንድ ነገር ከውስጡ የሚረብሸው ገፊ ነገር እንዳለ ምልክት ነው።

ያ አልበቃ ብሎት “ዛሬ ታጥቄ መጥቻለሁ” ባለው ድንቁርናው ስለ ኦሮሞና አማራ ሲናገር ‘የአማራ ናሺናሊሰቶች ጋላውን ግጥም እየገጠሙ ገና ወጣት ሆኜ ነው የሰማሁት” እያለ የተገጠመን ሁሉ ገጣሚው አማራ ነው እያለ ማስረጃ ሳያቀርብ ይወነጅላል ይህንን በተመለተ ነብስ ይማር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ የጻፉትን ቢያነብ እመክረዋለሁ)። ይሁን እንበልና አሮሞውስ ያኔም ሆነ ዛሬ ተመሳሳይ ስድብ ሲሳደብ እንደነበረ ደረጀ ለምን ማንሳት አልፈለገም?

ዶ/ር ደረጀ ሆይ!

 በአማራና ኦሮሞ መካከል ቀዳዳ ለመክፈት ከሆነ ሙከራህ በሌሎች አናካሾች በኩል “ከቀዳዳነት አልፎ በር የሌለው የተገነጠለ ክፍት ሆኖ አማራዎች በኦሮሞ ምድር በኦሮሞ ልጆች መፈናቀል ብቻ ሳይሆን አንደ ከብት ታስረው ታርደው ስጋቸው እየታረዱ ተቀቅለው እየተበሉ ነውና እንዳንተው ኣይነት ፀብ ለኳሾች በሰነጠቁት ስንጥቅ በሩ ተገንጥሎ አማራውና ኦሮሞው ወደ እማይተያዩበት መንገድ ሄዷል።

አንተም ነግረኸናል እኮ “ከ አዲስ አባባ ወጥተህ አዳማ ድረስ መሻገር አይቻልም” ብለኸናል አደለም እንዴ? ስለዚህ ያንተ የድሮ ግጥም አምጣህ አላማጣህ ብርሌ ከነቃ አይሆን ዕቃ ነውና አናካሾች ካንተ በፊት ብርሌውን ሰንጥቀውታል።  

ያውም እኮ በአማራና ኦሮሞ ጥላቻ የለም ይል እና እያደረ እንጭጭ እየሆነ በሄደበት ንግግሩ “የኦሮሞ ሕዝብ አማራ እርጉዞችን እየጨፈጨፈ እንደሆነ” ሳይታወቀውም ሆነ አውቆ ነግሮናል።

እንዲህ ይላል፡

 << የኦሮሞ ኤሊቶች ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ይነግሩታል፤ ሰፊው ሕዝብ ይህንን ይሰማል ዋጋው የሚከፍለው ማነው ? ዕርጉዝ አማራ ትታረዳለች በዚህ “ናሬሺን” ምክንያት፤ ህጻናት አማራዎች በግፍ ይጨፈጨፋሉ። ኦሮሞ ኤሊቶች ደግሞ ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ምን ብለው ይነግሩታል ‘ምኒለክ የሴተችን ጡት ቆርጦ፤እንዲህ አድርጎ…..እየሉ ሲነግሩት የኦሮሞ ሕዝብ ገጀራውን ይይዝና በአማራ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ያካሂዳል። >>

ሲል በግልጽ ኦሮሞ ሕዝብ አማራን እየጨፈጨፈ እንደሆነ በግልጽ ነግሮናል።

ስለዚህ አማራ ስለ ጋላ ግጥም ገጥሞ ነበር ብለህ ለማናከስ የሞከርከው ምንም ፍሬ የለውም፤ 27 አመት ኦሮሞዎች ልክ እንደ ትግሬዎቹ  በልሂቆቻቸው እየተመሩ እዚህ ባለንበት እርከን ስለደረሱ በማናከሱ ጉዳይ “ተቀድመሃል” ብትባል እውነት ነው። ድንቁርናው እየተለጠጠ ሲሄድ ደግሞ ይህ ከላይ የገለጸው “ኦሮሞዎች ገጀራ ይዘው በአማራ ዕርጉዞች እና ህጻናትን ያለ ምሕረት ይጨጭፋሉ” ሲል ቆይቶ “በሊህቃን መካካል እንጂ ሕዝብ ለሕዝብ ምንም ቁርሾ የለም” እያለ “ጨፍጫፊው ሕዝብ” እያለ የነገረንን “ከደሙ ንጹህ” አድርጎ ለማቅረብ ሲጥር “እውነትም በሽታ ወይስ ድንቁርና?” ያስብላል።

አንድ ሕዝብ ገጀራ አንስቶ ዕርጉዞችና ህጻናትን ጭፍጨፋና ግድያ ውስጥ ገብቶ የወንጀል ተዋናይ ከሆነ “አገር ካፈረሰ” በሁለቱ ሕዝቦች መካካል ቁርሾ/ፀብ/የለም ማለት እንዴት እንችላለን? ከጭፍጨፋው ያመለጡ ሰዎች እኮ ወደዚያው ተመልሳችሁ ሂዱ ሲባሉ “ወደ ጠላቶቻችን መሬት አንሄድም፤ የፈጁን ሕዝቡ ጎረቤቱ ሁሉ ነው” እያሉ ሰምተናል ፤ አደለም እንዴ? ታዲያ በሕብ መካካል ጸብ የለም ብሎ ድንቁርና ምን እሚሉት የሕግ ዕውቀት ነው? አማራዎች እየታረዱ እኮ ወደ ምግብነት ተለውጠው እየተበሉ ነው! እግዚኦ መሃረነ!!!

እሰኪ በዚች በመጨረሻ ውይይቱ ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘመኮንን ድንቁርና ልደምድም።

ልጥቀስ

<< እኔ እንደ የየኔታ መስፍን ወልደማርያም አማራ የሚባል ሕዝብ የለም የሚል እምነት አለኝ። አማራ የሚባል የለም! >>

 ይልና በየመድረኩ ሲናገር የምትሰሙት ግን “አማራና ኦሮሞ፤ የአማራ ኤሊት እንጂ ሰፊውን የአማራ ሕዝብ፡ እያለ ሲጠቀም ትሰሙታላችሁ። አማራ የሚባል ሕዝብ ከሌለ ለምንድነው እራስህ  አማራ፤አማራ፤አማራ እያልክ በየንግግርህ የምትጠቀመው? መስፍን ወልደማርያም በጃንሆይ ጊዜ በጻፉት በራሳቸው ጽሑፍ አማራ እንዳለ ባመኑበት ጽሑፋቸው እኛ ጥቂት ጸሐፍት እንዳጋለጥናቸው ሁሉ አንተም በራስህ አንደበት “አማራ” እንዳለ ተናግረሃል። እንዲህ ስትል፡

 <<<< የኦሮሞ ኤሊቶች ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ ይነግሩታል፤ ሰፊው ሕዝብ ይህንን ይሰማል ዋጋው የሚከፍለው ማነው ? ዕርጉዝ አማራ ትታረዳለች በዚህ “ናሬሺን” ምክንያት፤ ህጻናት አማራዎች በግፍ ይጨፈጨፋሉ።>>>> ትላለህ አማራ እርጉዝ አማራ ሕጻን መኖሩን አምነህ እንደገና አማራ የሚባል ሕዝብ የለም ብሎ ክርክር ዕብደት ወይስ ድንቁርና?

በክፍል ሁለት ከመስከረም አበራ ጋር ያደረገው ውይይት ጊዜ ካገኘሁ ስለ ትግሬዎች ጦርነት የተናገረውን እስክመለስ ድረስ ይህንን ጽሑፍ አሰራጩት። ይህንን ስርጭት ካየሁ በሗላ እመለሰላሁ፤ካልሆነ ከንቱ ድካም መድከሙ የኔን ጊዜና ጉልበት ማባከኑ አይታየኝም።

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay