Monday, May 10, 2010

የራሱን የቤት ሥራ ሳይሰራ በወያኔ የሚያመካኘዉ ምክንያት አብዢዉ ተቃወሚ

ጌታቸዉ ረዳ (ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ) www.Ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com ዛሬ የምተቸዉ ሁለት ርእሶች በጣምራ ነዉ። አንደኛዉ ትችቴ- በጋዜጠኝነት ስራ የተሰማሩ የጋዜጠኛነት ትርጉም ሳያዉቁ ጋዜጠኞች የሆኑ እና እየሰሩት ያለዉን ኩነኔ። ሌላዉ በወያኔ ተቃዋሚነት የቆሙ የራሳቸዉን የቤት ሥራ ሳይሰሩ በወያኔ የሚያመካኙ ምክንያት አብዢ ተቃዋሚዎችን በሚመለከት ነዉ። ትችቴን ከመቀጠሌ በፊት በወያኔ ምክንያት የሚወዳትን አገሩን ጥሎ የአስራ 13ዓመት ታዳጊ ጽፃን ልጁን ይዞ በሕንድ አገር በስደት እየኖረ ዛሬም ወሮበላዉ የደደቢቱ ነብሰበላዉ ቡድን እየተከታተለ ረፍት እየነሳዉ ላለዉ የጋዜጠኝነት ሙያዉ በረግባር እያስመሰከረ ያለዉ የኢትኦጵ ጋዜጠኛ የነበረዉ ኢየሩሳሌም አርአያን (አርአያ ተስፋማርያም)ለመርዳት በገንዘብ እና በሞራል እንዲሁም ወደ ዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋማት በማመልከት እየረዱት ያሉትን የቁርጥ ቀን ኢትዬጵያዊያን ዜጎች ባለፈዉ አምድ ስም ዝርዝራቸዉ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል። እርዳታችሁን እስከቀጠላችሁ ድረስ ስም ዝርዝራችሁን ለታሪክ እየዘገብን ለማስቀመጥ ስማችሁ በተከታታይ እንዘግባለን። ባለፈዉ ሰሞን ባገኘሁት መረጃ አቶ አለሙ ብያድጌ-የተባሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ወደ አርአያ የላኩትን ገንዘብ ደርሷል። ተቀብሎታል፡ በራሱ እና እናት በሌላት ታማሚ ህጽፃን ልጁ ኢየሩሳሌም አርአያ አመሰግንልኝ ስላለኝ፡ ምስጋናዉ በዚህ የህዋ መገናኛ መልዕክት ይድረሰዎት፡ እናመሰግናለን። ቀጥሎ ወደ ዓለም አቀፍ ተቋማት በመጻፍም ሆነ በዌብሳይታቸዉ መልክቱ ለሕዝብ እንዲደርስ የተባበሩትን ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ። ከነዚህ ዉስጥ ባለፈዉ ሳላመሰግን ያለፍኳቸዉ በጎ አድራጊ ተባባሪዎች አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አቶ ተድላ አስፋዉ እና የደብተራዉ የህዋ መገናኛ ሰሌዳ ዝግጅት ክፍል አመሰግናለሁ። የኢትዬጵያ አምላክ “ከመጎደኛ ፤ከሆድ አደር -ህግ አልባ ወሮበላ ጥቃት” “ከመከራ”፤”ከሥራ እጦት”፤ “ስራ ከማያሰራ በሽታ” እና “ከኑሮ መፈናቀል” ይሰዉራችሁ ለማት እፈልጋለሁ። የጋዜጠኛነት ትርጉም ሳያዉቁት ጋዜጠኞች የሆኑ ጋዜጠኞች እየሰሩት ያለዉ ኩነኔ ኩነኔ ማለት “በስሙ መዋሸት፤አለ ኣግባብ መጠቀም፤አታድርግ ተብሎ በሃይማኖት የተደነገገ”በሕግም በሞራልም የተወገዘ ማለት” ነዉ። “ሜይ 3 የዓለም ጋዜጠኞች ቀን” ተብሎ በዓለም ሕዝቦች የተደነገገ በዓል እንደሆነ ኣብዛኛዎቻችሁ በዕለቱ የተላለፉት ዜናዎች የተከታተላችሁ የምታዉቁት ጉዳይ ነዉ። እራሱን “የኢትዬጵያ ነፃ ፕሬስ/የጋዜጠኞች ማሕበር” እያለ የሚጠራ በክፍሌ ሙላት የሚመራ (ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ) ፤ አብርሃ በላይ፤ (ኢትዬ- ሚዲያ)፤ ክንፉ አሰፋ( አቲዬ-ፎረም)፤ ዳዊት ከበደ (የድምፅ አዘጋጅ) (የዛሬ አያድርገዉ እና ኤልያስ (ኢትዬፕያን ሬቪዉ) (ዛሬ ከነዚህ ሰዎች ጋር በኣባልነት ይኑር ኣይኑር የሚታወቅ የለም)፤ እና ስም ዝርዝራቸዉ ለኛ የማይታወቁ ሌሎች አባሎችን ያካተተ ነዉ። ይህ ድርጅት በጋዜጠኛነት ማሕበር ምን እንደሰራ እና ምንስ እየሰራ እንዳለ በዘገባ መልክ እወክላለሁ ለሚለዉ ሕዝብ መግለጫ ያወጣበት ጊዜ አይታወሰኝም። ካለም በሙያዉ አንፃር ማዉጣት የነበረበትን መግለጫ እና የስራ ዘርዝር ዉጤት ዘገባ በጣም ጥቂት ነዉ ማለት ነዉ። እነኚህ በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰልፈን ወያኔ “አላናግር አላሰራ”አለን በማለት ከወያኔ ማነቆ ወጥተዉ ወደ ዉጭ አገር በመምጣት በዚህ የይስሙላ ማሕበር ከተሰባሰቡ በሗላ ያሳዩት የጋዜጠኝነት ሙያ ጥረት እጅግ ደካማ ብቻ ሳይሆን፤ የሕብረተሰቡን አንድነት ከበጠበጡት ጥቂት የፖለቲካ ጎረምሶች (ማለትም ቅንጅት ሲበጠበጥ ከኤልያስ ክፍሌ ከእነ አንዳርጋቸዉና ብርሃኑ ነጋ፤ ከብርቱካን መዲቅሳ ወገን ጋር በመወገን……) የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩት ኢንጂኔር ሃይሉ ሻዉልን በሚሊዬኖች ብር ዘርፈዋል እያሉ ስም ከምያጠፉት ጋር ቦድነዉ ለሕብረቱ መደፍረስ ከጎረምሶቹ በላይ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ጋዜጠኛ ማለት ማንም ይሁን ማንም፤ የትም ቦታ ይሁን-አንድ ዜጋ ከሕግ ዉጭ በደል ሲደርስበት፤ ያንን በደል ሕዝብ እንዲያዉቀዉ በማድረግ ሙያ ላይ የተሰማራ ማለት ነዉ። ቀዳሚ ተግባሩ የሕብረተሰቡን ሰባዊ መብት በስልጣን እና በገንዘብ የተደላደሉ ክፍሎች እንዳይበድሉት መከላከል ማስተማር መሟገት ማጋለጥ ማለት ነዉ። እነኚህ ሰዎች ግን ወደ ዉጭ አገር ከመጡ በሗላ የሰርዋቸዉ ስራዎች ሲመዘኑ ፤ ለድሃዉ እና መናገር “ላልቻለ ልሳን”-የቆሙ ሳይሆኑ ፡ ለስልጣን የቋመጡ ግለሰቦችን ወደ ሚዲያዉ አዉድማ በማዉጣት አጉልተዉ እያሳዩ እንደበሬ ወደ ሳቡት የሚሳበዉ ህብረተሰብ ዓይን ዉስጥ በመለኮትነት እንዲታዩ ምቹ ጉዝጓዝ በመሆን ቡድናዊ የጋዜጠኛነት ስራ እየሰሩ ነዉ። ከብረቱካን እስከ ብረሃኑ እስከ ግዛቸዉ እስከ ገብሩ እና ስየ እስከ መረራ ባልቻ አስከ በየነ አሁን ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍንን “ወያኔ”-እስከ ማለት የደረሱ ፖለቲከኞቻቸዉን በድጋፍ ቆመዉ የተጨማለቀ ማፈርያ ሚዲያቸዉን ባልነቃዉ ሕብረተሰብ እየረጩ ሲያወናብዱ ይታያሉ። አብርሃ በላይ የተባለዉ “የኢትዮ ሚዲያ”-ባለቤት የመለስ ዜናዊ ወያኔ ድርጅት በመቃወም “የዉዥምብራሙ እና አድር ባዩ” የገብሩ አስራትን ሌላዉ የወያኔ ግልባጭ በመደገፍ ወላጆቻችን እና ቤተሰቦቻችንን የገደሉት እና በእሳት ሲጠብሷቸዉ የነበሩ እነ ገብሩ ፤እነ አዉዓሎም እነ አበበ ተክለሃይማኖት (የአብርሃ በላይ “አርበኞች”) በመልሶ ማቋቋም ፕሮፖጋንዳዉ ስራ ተጠምዶ የኢትዬጵያ ሕዝብ ጠላቶችን በግብዝ ህሊናዉ እየካበ ያለዉ“ስራ”እንዳይበቃዉ ዛሬ ደግሞ የኢትዬጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማሕበር የተባለዉ የይስሙላ ማሕበር የሚወክለዉ ሰዉ በማጣት “አዉስትራልያ” ዉስጥ ከሚገኝ አንድ የአበሻ የራዲዬን ዝግጅት አዘጋጅ “አብርሃ በላይን” በመጋበዝ ስለ “ፕሬስ” ምንነት እና ሃካፊነት “የሜይ ደይ 3” በዓልን አስመልክቶ እንዲያብራረለት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ላዳመጠዉ ሰዉ እና አብራሃ በላይ ከሚናገራቸዉ እና በግብር እንዲፈጽማቸዉ ተጠይቆ በተደጋጋሚ ደካማነቱ እና ወገንተኝነቱ ያሳየበት እና ከሙያዉ ጋር የሚጻረር የሰራቸዉ “ጣራ ብላሽ” ከሚናገርለት የሙያ ዘርፍ በሚመለከት ትዝብቱን ለናንተዉ ልተዉ። አብረሃ በላይ “የሜይ 3 በዓል” ሲያብራራ ፕሬስ ያለበትን ሃላፊነት ሲያብራራ ፣ ጨቋኞች ዜናዎችም ሆኑ የዜጎችን እሮሮ እንዳይገለጡ እያፈኑት እንደሆኑ ገልጿል። ዜጎች ሲበደሉ ያለወገንተኛነት ማስተጋባት የፕሬስ ሃላፊነት መሆኑና በጨቋኞች ሰበብ ጋዜጠኞች እየደረሰባቸዉ ያለዉን በደል ለማስታወስ እንደሆነ (አጠቃላይ አባባል)የበዓሉ ትርጉም ገልጿል፤፡ በዚህ ትርጉምም አብርሃ ለጋዜጠኞች መብት ለተግባርነቱ የቆመ ሆኖ እንዳለ ተናግሯል። አብርሃ በላይ ከጋዜጠኝነት ተግባር ፍጹም የማይገናኝ ስራ እየሰራ እንደሆነ ሁላችሁ የታዘባችሁት ጉዳይ ነዉ። አብርሃ የጋዜጠኛነት ትረጉም ሁሉንም በእኩልነት ማስተናገድ መድረክ መፍጠሩስ ይቅር መተርጎምስ ይቅር ራሱን በፖለቲካ ድርጅት ዉስጥ አባል በመሆን “ለዓረና ቡድን/ለብርቱካን ቡድን/(መድረክ)” እንደ ሚከራከር እና ሌሎችን የመለስ ተቃዋሚ ድርጅቶችን (የአብርሃ ድርጅትም ጨምረዉ የሚነቅፉ፤የሚቃወሙ)-የሚዘልፉ፤ስም የሚያጠፉ፤ የሚወነጅሉ ጽሁፎች በዌብ ሳይቱ ዉስጥ እንዲለጠፍ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከታዘብነዉ ሰዎች የሚሰወር አይደልም። ይህ ሰዉ የፖለቲካ ድርጅት አባል እንጂ “ጋዜጠኛ” ሆኖ ሁሉንም እንደየ ዕድገቱ፤እርመጃዉ፤ እንደየ ብርታቱ እና ደካማነቱ ለድርጅቱ ሳያዳላ ያቋቋመዉ ሚዲያ በእኩል እያገለገለ አይደለም። ይህ ግለሰብ ባንድ ድርጅት ብቻ ሳሆን በሲቪክ በጋዜጠኛነት እና በፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ በብዙ ዘርፍ ከጋዜጠኛነት ባሕሩ ዉጭ በመሰማራት ለሕብረታችን ጠንቅ ከሆኑት ጥቂቶቹ አንዱ መሆኑን በተደጋጋሚ የተተቸ ጉዳይ ነዉ። አስገራሚዉ ነገር ግን በጋዜጠኛነት ሙያ አበሳቸዉ ያዩ ጋዜጠኞች፤ (በየአረብ አገሮች በየእስር ቤቱ የተሰቃዩ ስቃይ ዉስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጆች እና ሌሎቹ ወንድሞቻችን/እህቶቻችን ለመርዳት ያስተላለፉኩለትን “የእንተባበር ጥሪ”-ጀሮ ዳባ ያለዉን ሳናነሳ፤ እንዲሁምአምናከ5’000-በላይ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዬጵያዊያን (እረጉዞች/እመጫቶች/አዛዉንቶች/ህፃናት አካለ ስንኩላን..) በዘረኞች ከደቡብ ምስራቅ እና አከባቢዉ እርሻ እና መኖርያቸዉን ለቅቀዉ እንዲወጡ ተደርጎ በየሜዳዉ በየትምህርት ቤቶች አዲስ አበባ ተጠልለዉ እንደሚገኙ የጀርምን ራዲዬ ጣቢያ ያስተላለፈዉን ዘገባ (በራሴዉ “በኢትዬፕያን ሰማይ” ብሎግ አሁንም ቪድዬዉ ተለጥፏል- እሱን ያድምጡ) አዳምጦ የራሱን የማጣራት ሂደት በማድረግ ለህዝብ ይፋ እንድያደርግ እና የዜናዉ ቅጅ በራሱ ድረገጽ እንዲለጥፈዉ ብጠይቀዉ - እሱን ትቶ ስለ ዶ/ር ያቆብ ሃይለማርያም ጥብቅና ቆሞ “ለምን ተነካብኝ” ኩፍኛ በመጮህ ለጠየቅኩት ጥያቄ መልስ ጀሮ ዳባ ከመስጠቱ ሌላ አንድ ኬኒያዊ ጋዜጠኛ ያዘጋጀዉን የኦነግ ሽምጥ ተዋጊዎችዉ ብርታት እና የዱር ቤቴ ፕሮፓጋንዳ ነበር የተጠመደዉ። በተለይም የዘር ማጥፋት የተለከፉት አንዳንድ ጠባብ ብሄረተኞች እና ጸረ አማራ ሕብተረሰብ የተጠመዱ “ነብሰ ገዳይ፤ ብላሾች”-እየሰሩት ያለዉን ወንጀል እንዲያጋልጥ እና እርዳታ እንዲደርስላቸዉ ለዓለም ህብረተሰብ እናስታዉቅ (/ጻፍላቸዉ/ተሟገትላቸዉ/ለሕዝብ አስታዉቅ/) ሲባል ከሚያመልካቸዉ ቡድኖች እና ግለሰቦች ዉጭ “ቅንጣት ታክል ከበሬታ እና አዘኔታ” የሌለዉ ወገንተኛ ጋዜጠኛነቱን ዛሬም እየቀጠለበት ነዉ። አብርሃ በላይ በቀርቡ የኢትኦጵ ጋዜጠኛ የነበረዉ አርአያ ተስፋማርአም (ኢየሩሳሌም አርአያ)ን ችግር ለመቅረፍ በምን መንገድ ብንረዳዉ እን ብንተባበር የተሻለ ነዉዩ ብየ ላቀረብኩለት የአክብሮት እና የኢትዬጵያዊነት እንተባበር ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቤለት ቅንጣት የሃሳብ መለስ አልመለሰልኝም። በእኔ እና በሱ መካከል ያለዉ የፖለቲካ አመለካከት የማይገናኝ እንኳ ቢሆንም- ልዩነታችን አንዳለ አምቀን ለጊዜዉ 13 ዓመት በሽተኛ ታዳጊ ህፃን ያለ እናት ብቻዉን እየተንከባከበ በስደት አገር በሕንድ አገር መከራዉን እያየ ላለዉ ባልደረባዉ እንነጋገር ብየ ስለዉ እንዳመሉ “ጀሮ ዳባ”-ማለቱን እና የሰዉየዉ የሕሊና ብስለት እና ጋዜጠኛ ነበርኩ ብሎ ለሚለዉ ሙያ ያሳየዉ ከበሬታ ሳነፃፅረዉ “ኢትዬጵያ” የምንላት አገር መቸ “ከደንቆሮ ዋሻ”-ነፃ እንደምትወጣ በጣም ጭንቅ ይለኛል። በቅርቡ ታዝባችሁት ከሆነ ኢትዬ-ሚዲያ ድረ ገጹ ላይ የኦሮሞለ ብሄረተኛነት “ቀዳሚ” የፖለቲካዉ መርህ ባደረገዉ የስታንፈርዱ ምሩቅ ወጣት ጃዋር መሃመድ እና ብርሃኑ በተባለ ግለሰብ በቪኦኤ አማርኛ በተደረገዉ ክርክር ሌላዩን የክርክሩ ክፍል ሳያወጣ የመጨረሻዋን “የ ዓረና ትግራይ አባል የነበረዉ በወያኔ መሰሪ ተገደለ የተባለ አረጋዊ ገ/ብረዬሃንስ” ስም ጃዋር በመጥቀሱ “ የወያኔ መንግስት ትግራይ ዉስጥ በእነ ገብሩ የዓረና እንቅስቃሴ ምክንየት ተደናግጧል”-ብሎ በማለቱ እሷን “ለማድመቅ”-ብቻ የመጨረሻዋን ክርክር ብቻ መርጦ ለጥፏታል። እንግዲህ የአብርሃ በላይ ሕሊና “ሳይክ”በቅ-ርብ ያጠናችሁ ሰዎች ምን ማለት እያልኩ እንደሆነ ይገባችሗል። በሱ ቤት ሌሎቹ ሁለት ክፍሎች ላድማጭ ጠቃሚ አይደሉም። ልናደምጥለት የፈለገን ግን “ትግራይ፤ ዓረና…”የሚሉ ሃረጎች እስካሉ ድረስ እንሱን ብቻ እትኩሮታችን ለማድግ መማጸኑ ነዉ። (ከፈለጋችሁ ሌላ ልጨምር -የተቀሩት ለሌላ ቀን እናቆያቸዉ!!) ልቀጥል!ኢየሩሳሌም አርአያን በሚመለከት መቸ እሱን ብቻ ነበር በትብብር እና በሃሳብ እንዲረዱ የጠየቁት!በእስክስታ ሙያ የታወቀ እስክስታ መቺ ነዉ የሚባልለት አዲስ ድመፅ ተብሎ ሚጠራዉ ሌላዉ ‘የዉዥምብራሞች ቡድን መሪዎች አድማቂ እና አድናቂ”-አቶ አበበ በለዉ የተባለዉ የራዲዮን አዘጋጅም ለአብራሃ በላይ ስልክ ለሱም አብሬ ልኬ በጣም አስገራሚ መልስ ነበር የመለሰልኝ። ሦስት ጊዜ በኢመይል ልኬ ጀሮ ዳባ ሲለኝ ፤ አልደረሰዉ ይሆን?ብየ ጨነቀኝ እና ስለክ ደወልኩለት። ስለ ኢየሩሳሌም እና የ13-ዓመት ህፃንዋ በበሽታ እና በመጠለያ እጦት አልባሌ ቦታ ወድቀዉ እየተንከራተቱ እናዳሉ እና ለዚህ መነሻ ምክንያትም በዝርዝር አስቀምጬለት ሳበቃ ፤ “አሁን ምን እነድናደርግለት ነዉ የምትጠይቀን?’ሲለኝ መልሼ ያንኑን ዝርዝር ደግሜ ስለማንነቱ በይበልጥ ለማቀውም ከፈለገም ተጨማሪ ማህደሮች እንዲያነብብ ጠቁሜዉ ሳበቃ፤ ብያንስ “ቃለ መጠይቅ አድርግለት እና አድማጮችህ እንዲያዉቀት በዚህ አስፈላጊ ትብብር ቢያደርጉለት…” ብየ ለጠየቅኩት “ከሌሎቹ ዝባዝንኬዉ” መልሱ ማመን ያቃተኝ ግን “ስልክ ስደዉል እኮ “ከኪሴ እያወጣሁ” ነዉ” ሲለኝ “ክዉ”ብየ ነበር የቀረሁት። ያኔዉኑ አንደበቴ ሁሉ ተዘጋ፡ ካግራሞቴ የተነሳ የምለዉ ሁሉ ስለጨነቀኝ “ኢየሩሳሌምን ካሁን በፉት በጆሮየ ሰምቼዉ አላዉቀዉም”-ሲለኝ፤ ‘የቆዩ እና የቅርብ ጹሁፎቹን እንዲያነብብ’-ከጠ ቆምኩት በሗላ “አረ የማቃቸዉ የኢትኦጵ ጋዜጠኞች ጓደኞች አሉኝ ፡ እጠይቃለሁ” ላለኝ አመስግኜ ተሰናበትኩት። ላለመተባበር ምክንያት ሊሆነዉ የሚችል ጠይቆ ያገኘዉ መልስ ምንም እንደሌላ በርግጠኝነት መናገር ብችልም፡ ጋዜጠኛዉ ካጋጠመዉ የህይወት ፈተና ምንም ይሁን ማን ኢትዬጵያዊዉን ጋዜጠኛ ላለመርዳት ቅንጣት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ካግራሞቴ ካጋገምኩ በሗላ ንግግሩ ስለቆጨኝ በኢንተርኔት መልክት “ቃለ መጠይቅ እድርግለት እንጂ “የሁለት እና የ አምስት ብር የስልክ መደወያ ካርድ/ፈቃድ” ካጣህ ገዝቼ ልላክልህ አልኩት። ያንንም ጀሮ ዳባ አለዉ። እኔ የገረመኝ ያማርኛዉም የትግርኛዉም የ ኦሮምኛዉንም አጠቃላይ ስራስኪያጅ የሆነዉ የቪኦኤዉ አቶ ንጉሴ ስለ አቶ አበበ ሲናገር (አዲስ ድምፅ ራዲዮ ለመርዳት በተዘጋጀዉ ግብዣ) የካበዉን የጋዜጠኝነት የምስጋና ክምር፤- ቁልሉ “ደሳለኝ” የተባለዉ የወያኔ አህያ ተሸክሞ አይችለዉም (አዉዲዬዉ ደግማችሁ ብታዳምጡት አሁንም ሆነ ካሁን በፊት አበበ የፈጸማቸዉን በታኝ ቡድናዊ ተግባሮች ሳመዛዝን ም ሆነ አብርሃ ክንፉ አሰፋም ሆኑ ሌሎቹ በዚህ ጉዳይ ያሳዩት ትብብር (በተለይም የክንፉ አሰፋን (ኢትዬ ፎረም ዳት ኦርግ አዘጋጅ) ለሌላ ቀን እናኑሮዉ- ያንን መንካት ጊዜ ይፈጃል!) ሰዉየዉ ቀን በርቶለት እራሱ ይተችበት። ታገሱኝ ጉዴ ገና አላለቀም፤ ልቀጥል ነዉ። ጥሪየን መቸ በነዚህ ብቻ ተወሰነ!በኢየሩሳሌም የተነሳ ማኣዛ ድምጽ (ፈረንጆች ሴክሲ ቮይስ የሚሉት “አሸብራኪ ድምጽ” ልበዉ?) ያላት ስታነጋግራት የጨዋ ሰላምታ እና ርህሩህ አንደበት የማይለያት የቮኦኤዋን “ወ/ሮ ትዝታ በላቸዉን”በስልክ አነጋግሬያት ነበር። አንዴ ብቻ ሳይሆን አንዴ በስልክ የመልክት መቀበያ ሳጥን ሁለቴ ደግሞ በአካል በስልክ ስለ አርአያ እና ስለ 13ዓመት ጽፃኒትዋ ልጁ ሁኔታ የምትረዳበት መንገድ ካለ አነጋገርኳት/ጠየቅኳት። ለ አንደኛዉ መልከቴ መለክቴን ላለመመለስዋ የሰጠቺኝ ምክንያትዋ “ዕረፍት/ቬኬሽን”-በመኖርዋ፡ ሁለተኛዉ የተቻለኝን ያህል እሞክራለሁ፡ ሦስተኛዉ ጊዜ እንደገና ስትዘገየኝ ለማስታወስ ስደዉል “አቶ ጌታቸዉ ደህና ነህ? አሁን ስትደዉል በስራ ስለተጠመድኩ፤ መልሼ ልደዉል?” እኔ ደግሞ “እሺ” ነበር ተባብለን ለመጨረሻ ጊዜ “ያለ ዉጤት” “ያለ መልሶ መደወል ” “ትብብር ባላሳየ” ጥያቄየ በደፈናዉ ጀሮ ዳባ መለሰቺዉ። ቮኦኤን በዚህ ጉዳይ በግልም ሆነ በስልክ መቀበያ መልከት ትተዉ የአንደኛቸዉም መልክት በራዲዮናቸዉ አልተላለፈም። ለምን?መልሱ ከኛዉ ከግብር ከፋዬች ለነዚህ ጋዜጠኞች በጋዜጠኝነት ሞያ እንዲያገለግሉን እና የራሳቸዉ ባልደረባም (ጋዜጠኛም)በጸረ ፕሬስ እርምጃ በሚያራምዱ አምባገነን ቡድኖች እና መንግስቶች ምክንያት ችግር ላይ ሲወድቁ ለዓለም እንዲነግሩ ደሞዝ ለሚቆረጥላቸዉ ለነዚህ “ጋዜጠኛ ተቀጣሪዎች”-እንዲመልሱልን እንተወዋለን። በዚህ አጋጣሚ ላማርኛዉ ክፍል ብቻ አይደለም፤ ለትግርኛዉ "አቶ በትረ ስልጣንም”በሌላ ጉዳይ (ማህበራዊ/ፖለቲካዊ) በሚመለከት እኔን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ደዉሎልኝ ስራዉ ከፈጸመ በሗላ፤ በእግረመንገዴ የኢየሩሳሌም አርአያ ጉዳይ እስኪበቃዉ አስረድቼዉ ሳበቃ ፤-እሱም ትብብር እንደ መሰሎቹ “የዉሃ ሽታ” ሆኖ ቀረ። በጉዳዩ አዝኛለሁ፤ነገር ግን እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር ስለገጠመኝ በሁኔታዉ ለመተባበር ድርጅቱ ወይም አለቃየ አልተስማም እና አዝናለሁ። ነገር ግን በግሌ እረዳለሁ፤ በግሌ እተባበራለሁ፤ ከቻልኩ በገንዘብ ካልቻልኩ በሃሳብ እተባበራለሁ። ማለት የሚያግደን ባህል፤ሞራልና ሕግ የትኛዉ ነዉ? እንዴት ራሳችንን ከነበርንበት አስከፊ ኑሮ ተሎ ራሳነዉ? እኔ የሚገርመኝ ከላይ ከአብርሃ በላይ ጀምሮ አስከ አበበ በለዉ፤ትዝታ በላቸዉ ክንፉ አሰፋ ዳዊት ከበደ……. በጋዜጠንነት ሙያ የተሰማሩ ከላይ የጠቀስኳቸዉ እና ያልጠቀስኳቸዉ ሰዎች ይወቁኝም አይወቁኝም ከኔ ጋርም የፖለቲካ አለመግባባት ይኑረንም በዚህ ሰብአዊ ጉዳይ ማሳየት የነበረባቸዉ “ስልጡን ኢትዬጵያዊነት” ሕሊና ምን ገጠመዉ? አዋቂነት፤ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነዉ? ለቡድን ፤በትዉዉቅ፤ ወይስ ለሰብአዊነት ስራ በሃላፊነት መወጣት?ሰዎች በትምህርትም፤ በስራም፤ መጽሃፍ በማንበብምና በማዳመጥ እና በመታዝብ የምንገበያቸዉ ዕወቀቶች ለዚህ ሰብአዊ ስራ ካላዋልናቸዉ ገበየናቸዉ ዕዉቀቶች መቸ እንድንገለገልባቸዉ ነዉ የምንቆጥባቸዉ? ዓለምን ያለምን መሪ እንድተቀር የምንመኘዉ ለምንድነዉ?አርአያንና ያስራ ሦስት ዓመት ዕድሜ ያላት ታማሚዋ ወጣት ኢየሩሳሌም ያለ መጠለያ በባዕድ አገር እንዲንከራተት ምክንየት የሆነዉ “ቅጥረኛ ጋዜጠኝነትን” ስራ እየሰራሁ “ሸራተን ሆቴል በዊስኪ እና በቡፌ” ስጋየን ከማለምለም ስጋየ በመከራ ተጠብሳ የህሊና ፍስሃ ይሻለኛል ብሎ ነዉ “ወደ ልመና” ዓለም ገብቶ እኛን በልመና እየተማጸነን ያለዉ። ለመሆኑ እኛ እያንዳንዳችን ማን ነን? በዛዉ በልመና ዓለም ተምበርክከን “ጀ ቪ ኤ” ም ሆነ “ዩ ኤን ኤች ሲ አር”ን ተማጽነን እምባ አዉጥተን አልነበረም ወይ ከሱዳን ከጁቡቲ፤ከሶማሊያ፤ከየመን፤ከኡጋንዳ፤…..አሁን ወደያለንበት ሃብታም ዓለም ገብተን ቤት እና ንብረት የሆንነዉ? (እኔ እንኳ ድሃ ነኝ ለነገሩ እንጂ!)፡ ታዲያ ያንን ሃሩር፤ያንን ኑሮ ከመቼዉ ረሳነዉና ነዉ “አንድ ገጽ” በምንቆጣጠርባቸዉ ሚዲያዎች የነኚህን የተወጠረ የወንድሞቻችን ህይወት ማስተናገድ “እምቢ” ብለን ፈቃደኛነታችንን ላለመሳት በትዕቢት የተወጠርነዉ?አሁን ከዚህ ካለንበት ምድር “አያድርገዉና” “ዉጡ!!!!!!” የሚል ሁኔታ ቢፈጠር “ምን ይዉጠን ይሆን?! በነዚህ ጭለ፤ማ በሆኑ መንገዶች ዉስጥ መብራት ሆነን የተቸገሩትን የተቻለንን መርዳት ካልቻልን “ሆደ ቡቡነታችን”መለገስ ምንድ ነዉ ያስቸገረን? ኢትዬጵያዊ ርህሩህ ነዉ፤አዛኝ ነዉ እየተባለ ይነገርለታል። ሰዉ ሲሞት ሬሳ ላይ ዕንባችንን እያፈሰስን የኖህ ዝናብ ከዓይናችን ከረጢት ሲፈስ ይታያል፤ አንድ የታወቀ ሰዉ ሞቶ ለ ዓመቱ ዝግጅት ሲደረግ ስለ ሰዉየዉ ድንቅነት እተነገረ የዕምባችን ብረታቱ ማሃረማችንን ሲያስርሰዉ ይታያል። በመዘክሩ የተናገርናቸዉ ድምጾቻችን በየራዲዮኑ መድመቂያ ሆነዉ እናዳምጣቸዋለን። እዉነት በሙት ላይ እንደምናዝነዉ “ርህሩሆች” ነን? “ተገሐስ፡ እም እኩይ፡ ወግበር፡ ሠናየ፡ ወትነብር፡ ለዓለመ፡ ዓለም” (ከክፉ ሽሽ፤ መልካምንም አድርግ፤ ለዘላም ትኖራለህ” (መዝሙረ ዳዊት):: ልቤ ሲቃጠል እያነበቡኝ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጠንንትህ እንዳትጎዳ እያሉ ለመከሩን ዉድ ወገኖቼ እያመሰገንኩ ፡ ለምን እየነደድኩ እንደሆነ እንደሆነ እና ከዉስጤም እየተጎዳሁ መሆኔን ይገባኛል፡ ለምክራችሁም በታም አመሰግናለሁ። ማለት የምችለዉ፦”ሲፈጥረኝ እንደዚሁ እንድነድ የተፈጠርኩበት ባሕሪ ነዉና ምን ላድርግ?”። አንዳንዶቻችን ታመንም፤ሞተንም፤ቆስለንም፤ተሰድደንም፤ታረዘንም፤ተሰድበንም ተዋርደንም፤ተቃቅረንም ”ኢትዬጵያ ሰላም”ትሁን ብቻ። ምኞቴ ያ ነዉ። ክፉ ዘመን ከወገን ከራስ ያቃቅራር። ክፉ ዘመን የለም፤ ክፉ ዘመን የምንፈጥረዉ ”ሳንተባበር ፤ሳንረዳዳ ስንቀር፤ሆድ እና ምቾት ሲያሸንፈን ብቻ ነዉ”። ክፉዉን ቀን አብረን እንዝለቀዉ፡ እዛዉ እንደርሳለን። በተቃወሚ ድረገጾች “ስለ ፖለቲካ ነጻነት፤ስለ መናገር፤ስለ መተቸት፤ ስለ ጋዜጠኞች መታፈን መሰደድ፤መከራ ማየት መታመም መታረዝ ተጽፈዉ የምናነባቸዉ እዉን አትኩሮት እንዲደረግባቸዉ ከልብ የሚለጠፉ ጽሁፎች ናቸዉ? ወይስ “መለስ ዜናዊን” ብቻ ለማጋለጫ መሳርያ እንዲሆን ሆን ተብሎ የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ? የፖለቲካ ጸሃፍት እና ተቺዎችስ የሚያቀርቧቸዉ ክርክሮች ባብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ብለዉ በየድረገጾቻቸዉ የሚያስተናግዱ እነ ኢትዬ-ሚዲያ እነ ኢትዬፎረም፤አዲስ ድምጽ፤አዲስ ቮይስ፤አቡጊዳ አባይ ሚዲያ እና ( የኔን ጽሁፎች የሚያስናግዱትንም አንዳንዶቹን ይጨምራል) ለሁለም በእኩል ያገለግላሉ? መልሱ ‘አያስተናግዱም ነዉ”! (ስንመዝናቸዉ ባንዳንድ ስራዎቻቸዉ ከወያኔዉ ከልበ ቢሱ “ከ ዓይጋ ፎረም” “የዉሸት ከረጢት ድረገጽ” አይሻሉም። የነሱን የፖለቲካ መሪ የማያወድስ ትችት ከሆነ ተሽቀንጥሮ ይጣላል (በተለይም የሚቃወማቸዉ ከሆነ እና ጸሃፊዉ “ስታዉንች” የሚሉት የቡዳናቸዉ ተቺ ከሆነ!!!)። ዕደለኛ ከሆንክ ለምን ለሕዝብ እንዲነበብ የላክካቸዉን ትችቶች እንዳይነበብ ስትጠይቅ መልስ ታገኛለህ፡ እጅግ የሚጠሉህ ከሆነ 10ጊዜ ብትጠይቅም የምታገኘዉ መለስ “ጅሮ ዳባ” ነዉ። በቅርቡ እኔ የማከብራቸዉ በልጂግ አሊ የተባሉ ጸሃፊ ሰሞኑን ያቀረቡት የኔን ኡሮሮ የሚመሳሰል ኡሮሮአቸዉን በግሩም ብዕራቸዉ በሰፊዉ ያተቱትን ልጥቀስ ““….ወያኔ በሃገር ውስጥ ያሉትን ነፃ ሜዲያዎች እየዘጋ ፣ ጋዜጠኞቹን እያሰረ ፣ ደራሲዎችን እየገረፈ ፣ እየገደለ፣ እያሳደደ የሕዝብን የማወቅ መብት ገፎ የራሱን ደጋፊዎች ብቻ ነፃ አድርጎ በባዶ ፕሮፖጋንዳቸው ሕዝቡን ያሰለቹታል ። በዚህም ምከንያት ደግሞ በውጭ አገር ሕዝቡ ስለሀገሩ ሁኔታ እንዲያውቅ ፣ እንዲወያይ በሚፈልጉ ወገኖች የተለያዩ ድረ ገጾች ፣ ራዲዮኖች፣ ጋዜጣዎች ተከፍተው አገልግሎታቸዉን በመስጠት ላይ ይገኛሉ ። የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን በስደት ከተቋቋሙት ሜዲያዎችም መሀከል ጥቂቶቹ ራሳቸዉ በራሳቸዉ ላይ የሳንሱር ማዕቀብ የሚያደርጉ መሆኑ ነዉ ።ድረ ገጾቹ ባለቤቶቻቸው የማይደግፉትን አቋም የያዘ ጽሁፍ በፍፁም እንዳይወጣ ይከለክላሉ ። ባለፈው ወር "የተደበቀው ድርቅ "_በሚል የጻፍኩትን መጣጥፍ አንድ የድረ ገጽ ባለቤት ያለፈ ታሪክ ነውና አላወጣም ብሎ ፃፈልኝ ። ከድርቁ ጋር ተያይዞ የመጣው ችግር አልፏል --አላለፈም የሚለውን የመከራከሪያ ምክንያት በማቅረብ የድረ ገጹ ገዥ የራሱን ውሳኔ በመወሰን የሌሎችን የማንበብና የመተቸት መብት አግቶ አቁሞታል ። ምንም እንኳ ጽሁፉ በዚህኛው ድረ ገጽ ባለቤት ቢታገድም ሌሎች በዚህ ዓይነት ያልተመለከቱት ለንባብ አብቅተውታል ። በወቅቱ ስለ ድርቁ እንድጽፍ ያስገደደኝ ጉዳይ ቢኖር በቅርብ ጊዜ ሰለ ወያኔና ድርቁ በውስጥ አዋቂዎቹ ቢቢሲ ላይ የተጋለጠው ዜና ነው ። ወያኔ በእርዳታው ገንዘብ መሣሪያ ይገዛበት እንደነበር በሰማሁ ጊዜ ፣በዛ ወቅት እኔ የማውቀውን በደርግ በኩል ሲደረግ የነበረውን አጣቅሼ ነበር ለሕዝብ ለማሳወቅ የጣርኩት። የዚህ ድረ ገጽ ገዢ እሱ የሚፈልገውን ብቻ እንድጽፍለት ነው የጠየቀኝ ። ካልሆነ ግን እንደምንለያይ አሳስቦኛል። እንግዲህ ግለሰቡ ድረ ገጹን ለመጠቀም ከፈለግሁ እሱ የሚፈልገውን መጻፍ ሊኖርብኝ ነዉ ማለት ነዉ።እንግዲህ የድረ ገጾችን ባለቤቶች ለማስደሰትና ጽሁፋችን ለሕዝብ እንዲቀርብ ከፈለግን ሳንወድ ቅጥረኛ ጸሐፊ ልንሆን ነው ማለት ነው ። ይህ በጣም ያሳዝናል ።” (ከፍለን እንታገል ፤ ከቀለሉ አይቀር እንደገለባ (በልጅግ አሊ) ኢየሩሳሌም ያደገችበት እንጀራ አምሯት በህንድ ደረቅ ቂጣ ስትሰቃይ (አም ተገኝቶ ቢሆን) እኛ ከተወለዱ ወር ላደረጉ ህፃናት ልጆቻችን ወይንም “ቤ ቢ ሻወር”-ለሚሉት ማለትም “ለምትወልደዉ እናት የደስታ የምኞት መግለጫ” (ገለብ የምንለዉ በትግርኛ) አስር ሺህ ዶላር የሚፈጅ የምግብ እና የሙዚቃ ድግስ በተንጣለለ አዳራሽ አስክስታ የምናቀልጠዉ፤ አበባ ተጎንጉኖ፤ማራኪ ምኡዝ ሽቶ ተቀብተን አምሮብን በመቶዎች ተሰባስበን የምንታየዉ ወይንም በየሙዚቃ ድግሱ በየምሽቱ በየምግብ ቤቱ የምንነሰንሰዉ ትርፍ ገንዘብ እዉነት ሕንድ አገር መጠሌአ እና በቂ ምግብ አጥታ በሰዉ አገር የምትንከራተት የጋዜጠኛዋ ልጅ ለወጣት እየሩሳሌም አርአያ ትንሽ ብር መለገስ ለምን አቃተን? ዛሬ እዉነቱን ልናዘዝ፦ - የ ዕለት እንጀራም ሆነ የሰዉ ሃይል ትብብር የሚፈልግ የሰዉ ፊት የሚያስፈታ ጉዳይ ከሰዉ እጅ መጠበቅ ኩፉ መሆኑን የታዘብኩት ዛሬ እኔ በተግባር የማዉቃቸዉን ጓደኞቼ ስለ አርአያ እንዲተባበሩ ያላቸዉን እንዲጥሉ እየተሳቀቅኩ በሰቀቀን ስገልጽላቸዉ እና አንዴ ሳይሆን ደጋግሜ ሳሳስባቸዉ/ስጠይቃቸዉ የሚያሳዩኝ “ዳተኛነት/ልግምት”የሚሰማኝ ዉስጣዊ ስሜት ልገልጽላችሁ በጣም ይከብደኛል፤፡ ብቻ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ዓለም እረስተን ምቾት አዘናግቶን እንዳለ ለናንተ ለተማራችሁ ወገኖቼ ስገልጽላችሁ እየተሳቀቅኩ ነዉ። ያለንበት ዓለም አስተማማኝ እንዳይደለ እኔ ለናንተ አልነግራችሁም። ብቻ ባጠቃላይ ወደ እዛዉ ዓለም እንዳትገቡ ከስራ መፈናቀል፤አካልን ከሚያደክም ከበሽታ እግዜር ይጠብቃችሁ። የሰዉ ዓይን እንዳያሳያችሁ ለኔም ለናንተም እጸልያለሁ። ሕብረተሰባችን በጣም አሳዛኝ የመበታተን እና የቡድን ስብስብ አጥቅቶታል። አንዱ ላንዱ የሚያዝን ልብ አጥተናል።በተቻለ መጠን አሁንም የጋዜጠኛዉ አርአያ እና የልጁ ኢየሩሳሌም ሁኔታዉ እንዲሻሻልለት እየጣርን ስለሆነ-እስከዛዉ ድረስ ግን ዛሬም ትብብራቺሁ ስለሚፈልግ (ባለበት ኒዉ ደልሂ ቢያነስ አንዲት ጠባብ መኖርያ አነስተኛዉ 400ዶላር በወር ይጠይቃል-ልጅ ይዞ ያለ ስራ ለኢትዬጵያዊ ስደተኛ ክብደቱ ምን አህል መሆኑን አስሉት) እርዳታችሁን ያልለገሳችሁ አሁንም እርዱት እንላለን። የረዳችሁ እና አሁንም እርዳታችሁ በቀጣይነት አትንፈጉት፡ የረዳችሁም ርህሩህ ለሚባልለት ኢትዬጵያዊነት ምሳሌ ናችሁ እና ምስጋና ይድረሳችሁ። ቆጭቷቸዉ ለመርዳት ያሰቡ እና ከልባቸዉ እና ከትከሻቸዉ ላይ ካበጠዉ “ባለ ጊዜነት”ፈንቅለዉ ወጥተዉ የጋዜጠኛነት ሙያቸዉን ለጋዜጠኛዉ ባልደረባቸዉ ለማገልገል ፈቃደኛነት ለማሳየት ካሉ አሁንም ጊዜዉ አልመሸም እነሆ። የ13ዓመቷ የጋዜጠኛዉ ልጅ ኢየሩሳሌም አርአያ ህይወት እና ዕድል በያንዳንዳችን ተጭኖብናል እና የተቻለንን ለመርዳት እንተባበር። እያልኩ ወደ ሁለተኛዉ የምርጫዉ ጉዳይ አጭር ትችቴን ልግባና ልሰናበታችሁ። ዉጭ አገር ያሉት ተቃዋሚዎች በግል የማከብራቸዉ የትግል አጋሮቼም ሆኑ ሌሎች በአካል የማላዉቃቸዉ አንዳንድ ተቃዋሚ ክፍሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ ወር ሊሚካሄደዉ ምርጫ “ልምን መሳተፍ አስፈለገ?”“ወያኔ እንደሚያሸንፍ እየታወቀ ለምን መሳተፍ አስፈለገ?”“ወዘተ ወዘተ….. በማለት የተቹትን ጽሁፍ እያነበብን ነዉ። ይሄኛዉ አዲስ አይደለም። ጋብ ያለዉ እና በጣም የሚያስደስት እርምጃ ያየሁት ግን በየሚዲያዉ በተለይም ዘረኞች የሚነዙት “ሃይሉ ሻዉልን ያለ መረጃ በመስደብ፤በመዝለፍ ወይንም በአሉባልታ በመወንጀል ፤ “ድረገጾቹ የሚለጡፏቸዉ የአሉባልታ ካርቱኖችንም ጨምሮ”-ድረገጾቻቸዉ ለዚህ ዓይነት ቡዱናዊ ፕሮፖጋንዳ ጠቀሜታ ለማዋል ሲታክቱ የነበሩት እንደ ኢትዬፎረም ዳት ኦርግ፤ ኢትዬሚዲያ .ዳት ካም እና አቡጊዳ የተባለዉ ጉደኛ ድረገጽም (የሕዝብ ወይስ የመድረክ ፖለቲካ ድርጅት ድረገጽ እንበለዉ?) ጭምር መረጃ የሌለዉ ስድብ እየቀነሱ እና ከዘረኞ ጸሃፊዎች ሰሞኑን ጋብ ያሉ ሆነዉ አግኝቼዋቸዋለሁ። ይሄ የተሻሻለ ይመስለኛል። ባንዳንድ ተቃወሚ በኩል የሚሰነዘረዉ ያልተሻሻለዉ አመለካከት ግን “ወያኔ ማሸነፉ እየታወቀ ለምን ምርጫ ዉስጥ ይገባሉ?” የሚሉት ነዉ።ነገሩ አዲስ ትችት አይደለም። እኔ እንደ አዲስ እነኚህን ክፍሎች የምጠይቀዉ ደግሞ “-አስራ ስምነት ዓመቱን ወደ ጎን ትተን “ምርጫ” ከተባለ ወዲህ ምን ስራ ሰራችሁ?” ብየ ለመጠየቅ ነዉ። ቦይኮት አድርጉ ነዉ? ጭራሽኑ ምርጫ የሚባል ትርጉም አይሰጥም ነዉ? ምንድ ነዉ? ይሄ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳ የለዉም የሚሉት ክፍሎች ባለፈዉም እንደዚያ ብለዉ ነበር። ነገር ግን ምርጫዉ የሰጠዉ ጠቀሜታ እነሱም የሚያጣጥሉት አይመስለኝም። (አሁን ዝርዝር ዉስጥ አልገባም)። መዉቀስ ያለብን ምርጫ ዉስጥ ተገብቶ ከሚታየዉ ዉጤት አንጻር የተገኘዉ ዉጤት ከንቱ ከሚያደርግ እርምጃ እና ዉሳኔ ዉስጥ እንዳይገቡ ከወዲሁ መምከር እንጂ ገና ለገና “ወያኔ ያሸንፋል” ተብሎ የሚደረስበት ድምዳሜ በጣም ይገርማል። ወያኔ አሸናፊ የሚሆንበት ሁኔታ ካለ ከምርጫዉ በሗላ እንዳለፈዉ ተቃዋሚዎች የተራመዱበትን ጎዳና እንዳይሄዱ ነዉ። ዛሬም ተቃዋሚዎች በተናጠል መወዳደራቸዉ ለወያኔ አመቺ ቢሆንም፤ ለብቻም ቢሆን ወያኔን መጣል ይቻላል። የቺኑን የተገኘቺዉን አሸናፊ ዉጤት በቀላሉ እጅ ሰጥተዉ ወያኔ ወደ ሚኒሊክ አዳራሽ ግማሾቹም ወደ ፓርላማ ግማሾቹም ወደ ቤታቸዉ ተመልሰዉ ወያኔ የሚቀጥልበት ዕድል የሚሰጡበት ሁኔታ ከፈጠሩ ግን ወቀሳዉ መሰንዘሩ አግባብነት አለዉ። ነገር ግን ማንኛችንም ቢሆን ግምታዊ እንጂ በርግጠኝነት የሚሀኖዉን መተንበይ አንችልም እና! ይልቁንስ ‘ወያኔ እንደሚያሸንፍ እየታወቀ ፋይዳዉ ምንድ ነዉ?” ከማለት ከምርጫዉ በሗላ ለሚደረጉ ወያኔ ሊሰራቸዉ የሚዘጋጅባቸዉን ስርቆት እና አጭበርባሪ ዘዴዎቹን እያፈላለጉ እየፈተሹ በተጨባጭ ለዓለም ማጋለጥ ይበልጥ ትግሉን ዉጤታማ ያደርገዋል የሚል አቋም ስላለኝ በዚህ እንበርታ። ምርጫዉ አይረባም ካልን እነሱ ማድረግ የሚችሉትን ያ ነዉ ብለዉናል። እኛስ? አመሰግናለሁ! www.Ethiopiansemay.blogspot.com Getachre@AOL.com 5/9/2010