Saturday, May 16, 2009

ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም

ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም ለፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመት ዓመት መዘክር የተዘጋጀ ዓምድ ጌታቸዉ-ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ፕሮፌሰር ዶ/ር አስራት ወልደየስ ከተናገሯቸዉ ጠቃሚ ንግግሮች ለጻፍትና ለታሪክ ተመራማሪዎች እንዲሁም ለአንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በየሳምንቱ በጥቅስ አቀርብላችሗለሁ። በጣም አስገራሚና ጠቃሚ ንግግሮቻቸዉ እንድታነብቧቸዉ እጋብዛለሁ። ወደ ዋናዉ ርዕስ ከማምራታችን በፊት ከኢትዮጵያን ረጅስተር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ካደረጉት ቃለ ምልልስ ያነበብኩትነ በጥቅስ ጠቅሼ ልለፍ። “…It is not only many other opposition parties, but also the TPLF/EPRDF that supports a federal state structure. Western government, too, support and advance such a form of government. Federalism is a burden that is being imposed on the people by those who claim to know what is best for us, and this is being done without assessing the advantage and disadvantage of federalism or without the Ethiopian people expressing their wish. If the west had advocated a monarch form of government and Mr. Paul Henze had written an article on this, the agenda would be different today. The foundation of federal structure is a nation divided along linguistic, ethnic, and religious lines in the name of democracy. We believe that a federal structure of regional administrations that are based on national unity, sovereignty, equality, economic and social benefits, and popular consent will be useful for advancement. But installing a federal government without foundation and especially at a time Ethiopia is being wrecked is like constructing a house in the midst of a violent earthquake. Even the much-lauded American federal system of government had to engage in civil war to ensure national unity…” ፕሮፌሰር አስራት በወያኔ የዉሸት ዉንጀላ ተወንጅለዉ ለጨካኝ እስር ተዳርገዉ ለሕይወታቸዉ ሕልፈት ምክንያት ሆኖ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰዉ እንድታጣ ሆኗል። “ለእኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም” በማለት የተናገሩት የወያኔ እስርኛ ሆነዉ እስር ዉስጥ እያሉ ታመዉ ሕክምና ተነፍገዉ ለረዢም ጊዜ ከቆዩ በሗላ ሕመማቸዉ እየበረታ ሲሄድ በጠና በመታመማቸዉ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስደዉ ሆስፒታሉ ዉስጥ ተኝተዉ በሕክምና ላይ እንዳሉ አሜሪካን አገር ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘዉ አንድ ኢትዮጵያ የተባለዉ “አፍቃሬ ወያኔ/ኢሕአዴግ”ራዲዮ በተኙበት ሆስፒታል ክፍል ዉስጥ በመግባት ካደረገላቸዉ ቃለ ምልልስ የሰነዘርዋቸዉ አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦች ዋና ዋናዎቹን አቀርብላችሗለሁ። አገር ወዳዱ አረጋዊዉ ፕሮፌሰር ቃለ መጠይቁ ሲያደርጉ ኢሕአዴግ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ልክ ሰባት ዓመት ሆኖት ነበር። ያኔ ከሰባት ዓመት በፊት ሰኔ ዉስጥ ኢሕአዴግ ባዘጋጀዉ ኮንፈረንስ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲን ወክለዉ በመገኘት በኢትዮጵያ ላይ የታለመዉን የመገንጠል አደጋ ብቻቸዉን በቆራጥነት በመቃወም ተጋፍጠዋል። በወቅቱ ጦቢያ ጋዜጣ ቀጠሮ በሚል ዓምዱ ላይ ቃለ መጠይቁን በሚመለከት እንዲህ ሲል ዘግቦት ነበር “ …በኮንፈረንሱ ላይ በቆራጥነት ሲቃወሙት የነበረዉን የፈሩት የጎሳ ፖለቲካም አገሪቱ በማመሱ በአማራዉ ሕዝብ ለይ ደረሰዉን አደጋ በሰላማዊ ትግል ለመከላከል ወደ ፖለቲካዉ ዓለም ገቡ። ከአራት ዓመት በፊት “ለጦርነት የሚያስነሳ ንግግር አድርገሃል”-በመባል ወህኒ ተጥለዉ ይገኛሉ።የጤና እና የዕድሜ ጫና ሳይበግራቸዉ አሁን፣ም ለሚወዷት አገራቸዉ እየተጨነቁ ናቸዉ።በርካታ ኢትዮጵያዉያን፣የዓለም ሕብረተሰብና የሰብኣዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች እኒህን አገር ወዳድ አረጋዊ ከእስር እንዲፈቱ ቢጪኹም ሰርዓቱ ርህራሄ አላሳየም። ከሰባት ዓመት በፊት የተቃወሙትና የፈሩት የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕጋዊነት የሌለዉ ፍቺ አገሪቱን ባስጨነቀበት ሰዓት ሰባኛ ዓመታቸዉን በርካታ ዓመታት ባገለገሉበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝተዉ ሲተክዙ አሜሪካ ዉስጥ ዋስንገተን የሚገኘዉ “የአንድ ኢትዮጵያ”-ድርጅት ሪፖርተር አልጋቸዉ ድረስ ገብቶ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። እኛም የፕሮፌሰር አሥራት ወልዴስን ቃለ ምልልስ በአሜሪካን አገር ከተሰራጨዉ ራዲዮ በማግኘት የመጀመሪያዉን ክፍል ለ አንባቢዎቻችን ስናቀርብ ለፕሮፌሰሩ ጤናን፣ ለአሠራቸዉ አካልም ልቦና እንዲሰጣቸዉ እየተመኘን ነዉ። አንድ ኢትዮጵያ፣- ኢትዮጵያ ከሦስት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ናት። የዓለም ታሪክ የመዘገበዉ ሀቅ ይህ ሆኖ ሳለ እድገቷ ሗላ-ቀር ሊሆን የቻለዉ በምን ምክንያት ይመስለዎታል? ፕሮፌሰር አስራት፣- የኢትዮጵያ ዕድገት ሗላ ቀር ነዉ የምንለዉ ያሁኑኑ ዘመናችንን ወይም ያለፉትን ጥቂት ዓመታት በመገንዘብ ነዉ። ሆኖም አዋቂዎች ጭምር በዓለም ደረጃ ሗላ ቀርነቷ ቢመሰክሩም በበኩሌ ኢትዮጵአን ሗላ ቀር ብየ የምመዘግባት አይደለችም። ለምሳሌ ቶይንቢ የሚባለዉ የዓልመ ታሪክ ሊቅ ስለ አፍሪካ ታሪክ በጻፈበት ጊዜ “ኢትዮጵያ ዓለምን በመርሳትና በዓለም በመረሳት አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ ኖራለች።”ብሏል-"ለኔ ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ዓመት አንቀላፍታ የኖረች አገር አይደለችም። ኢትዮጵያ አጋጣሚ ሆኖ ብዙ መሰናክሎች በታሪኳ እያጋጠሟት ብዙ የዉጭ ጠላቶች እያደከሟት፣ እየተነሳች እየቆመች በመምጣቷ እርግጥ በአሁኑ ጊዜ ሗላ ቀር ከተባሉ አገሮች ተራ ተሠልፋለች። እስከ አስራስድሰተኛ ክፍለ ዘመን በማያጠራጥር ሁናቴ የኢትዮ ጵያ እንቅስቃሴና ዕሰድገቷ ከአብዛኛዉ ከአዉሮፓ አገሮች እንኳ የማይተናነስ ነበር።ነገር ግን በገራኝ ወረራ …..። (ይቅርታ ቅጁ ከጋዜጣዉ ህትምት ስህተት ሳይታተም ተቋርጣል፣) አንድ ኢትዮጵያ፣- ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት አስተዳደር የሚበጃት ይመስለዎታል? ፕሮፌሰር አስራት፣- ዛሬ አስተዳደር ስንል አስተሳሰብ ማስገባት ያለብን ይመስለኛል። በዚህ መሠረት አንድ ቁንጽል የሆነ የዚህ ዓይነት አስተዳደር ብል ትርፉ አለመግባባት ብቻ ይሆናል። መሠረት መሆን ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ ማነዉ? ባለዉ ሁኔታ ዉስጥ ፍላጎቱና ችግሩ ምንድነዉ? ብሎ ለራሱ ተስፋ ለራስ በራሱ ልክ የሚሆንና ደግፎ ሚያስኬደዉ ዓይነት አስተዳደር መመሥረት አለበት። እንጂ እንዲያዉ ዝም ብለን ከአንዱ ጎራ ብቻ አምጥተን በፈረንጅ ቋንቋ እንናገራለን፣እናነባለን ብለን ያንን ወስደን ፈረንጅ አገር በተሠራ መሣሪያ እሱን አስገድደን እላዩ ላይ ስንችንበት የሚገኘዉ ዉጤት ታይቷል። ባለፈዉ ሰላሰ ዓመታት ይህንን ነዉ ስናይ የኖርነዉ። ይሄ አይመስለኝም ትልቁ ነገር።አፍሪካዉያን እንኳ በያሉበት በልባቸዉና በጉጉት ሲጠብቁን የኖሩት ሁሉንም ሞክረዉ ስላቃታቸዉና ስላልሆነላቸዉና ስላልበጃቸዉ እንደ ኢትዮጵያ ያለች ጥንታዊት አፍሪካዊት አገር መሀላችን እያለች እርሷ እኮ ምስጢሩን ይዛ ይሆናል የሚል ጉጉት ነበራቸዉ። ብዙዎቹን ሳገኛቸዉና ሳነጋግር ይሄ ምኞት በዉስጣቸዉ ይገኛል። ግን እኛ በበኩላችን የበለጠ ዝም ብሎ የፈረንጅ ስም በመከተል የምናመጣዉና በኢትዮጵያ ህዝብ የምንጭነዉ ነገር ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎሉበት አልሆነም።በተሠራበት አገር እንኳ ሊሠራ ያልቻለ ለስሙ ብቻ “እዛ ዲሞክራሲ ሲወራ ነበር፣ እዚህኛዉ የሶሻሊስት ይሠራ ነበር፣- እያልን የማይሠራዉን አምጥተን ህዝቡ ላይ በግድ በመጫናችን ሥርዓት ያጣንና ምንም ለአገራችን ማመንጨት የማንችል ሆነን ተገኝተናል። አሁን ሁሉንም ሞክረነዋልና እኔ በበኩሌ ከኢትዮጵያ ሰዉነት ጋር የሚሄድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር፣ከሁሉም ሕዝብ ጋር የሚሆንና የሚያራምደዉን ዓይነት ሥርዓት ዓላማ ነዉ ማስማማት ያለብን። አንድ ኢትዮጵያ፣- ኢትዮጵያን በዘር መከፋፈሉ አንድነቷን ያጠናክራል ወይንስ ይበታትናል ይላሉ? ፕሮፌሰር አስራት፣- በእኔ እምነት ብቻ ሳይሆን የትም ሥፍራ የታየ ነዉ። ለኢትዮያ ምንም አይበጃትም። የሚበታትናት እንጂ አንድነቷን የሚጠብቅ ነዉ ብየ አላምንም።ሩቅ እንኳ መሄድ ሳያስፈልገን እዚቺዉ ቅርባችን ወደ ደቡብ ብንሄድና ሱማሌዎችን ብንወስድ ይህን ያህል የሚለያዩበት ምንም ነገር የላቸዉም። አንድ ቋንቋ አንድ ባሕልና አንድ ሃይማኖት ቢኖራቸዉም እዚያች ዉስጥ በቁንጽል በጎሳ እንለያያለን ብለዉ ፍርክስክሳቸዉ ወጥተዋል። ወደ ሰሜን የሄድን እንደሆነ. ኤርትራን አንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል። እዚያ በምንም ዓይነት በጎሳ አይለያዩም።ጎሳ ማለት ይለያየናል ፣ያፈርሰናል ብለዉ እነሱ ጎሳን የማይቀበሉ ናቸዉ።ከላይም ከታችም ያሉት ጥሩ ምሳሌዎቻችን ሆነዉን እያለ ነዉ ጎሳ ይበጀናል የምንለዉ።እርግጥ በበኩሌ ጊዜያዊ አድርጌ ነዉ የምወስደዉ። ይህን ያሉት ወገኖች ለኢትዮጵያ ይበጃል ብለዉ ሳይሆን በአንድ በኩል የዉጪ ግፊትም አለበት። ሌላዉ ደግሞ በዚህ አመካኝቶ የተረሳን አካባቢ ለመጥቀም እንዲያመች የተደረገ ነዉ። አንድ ኢትዮጵያ፣- ፓርቲዎች ተለያይተዉ የየበኩላቸዉን ፕሮግራም ማካሄድ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጎዳና ይጠቅማል ወይስ ሁሉም ለአንዲት ኢትዮጵያ የሚያስቡ ከሆነ ባንድነት ተወሃደዉና ተጠናከረዉ ቢሰሩ ይመረጣል?ከዚሁ ጋር በቅርቡ ፓሪስ ላይ ለሚሰበሰበዉ የተቃዋሚዎች ጉባኤ አባታዊ ምክር አለ? ፕሮፌሰር አስራት፣- እኔ እዚያ ለተሰበሰቡት ለማስተማር አልችልም። እንዳልሁህ ላለፉት ዓመታት ከሁሉ ነገር የተገለልሁና ተጨባጭ መረጃዎች የሌሉኝ ስለሆነ የእኔ ሃሳብ ለእነሱ አስተላልፋለሁ ብየ እንኳ አልሞክርም።ግን አንዳንድ ሃሳብ ልሰነዝር እችላለሁ። በየጊዜዉ አነብባለሁ፣እሰማለሁም። ኢትዮጵያዉያን ባንድ ድርጀት ወይም ባንድ ስብሰባ ባለመሰብሰባቸዉ ምክንያት ወቀሳ ከያለበት ይሰነዘራል::ይህንን እኔ በበኩሌ የምደግፈዉ አይደለም።ምን ተይዞ ጉዞ! አባቶቻችን “ድር ብያድር አንበሳ ያስር”ብለዋል። ድር ቢያብር አንበሳ የሚያስር እኮ እያንዳንዷ ድር ደንበኛ ድር ስትሆን ነዉ። እንዳዉ ዝም ብለዉ አጥመልምለዉ ቢሰበስቡት አበረ ማለት አይደለም። በተፈጠረዉ አዲስ የኢትዮጵያ ሁኔታ ዉስጥ ድርጅቶች መቋቋም አንዳንድ ጂምናስቲክ መስራት፣መፍጨርጨር ራሱ ለኢትዮጵያ አዲስ ነዉ።አንዳንዱ ድርጅት ለምሳሌ ፣ሁለት ሦስት ሰዉ ብቻ ያለበት ነዉ በድርጅት ስም የተቀመጠዉ።አሁን ያ ተጨፍልቆ እንድ ድርጅትስ ቢሆን ጠነከረ ማለት ነዉ? እያንዳንዷ ድር ሲጠነክር ነዉ ሕብረቱ የሚጠነክረዉ። ስለዚህ ያ ሲጨፈለቅ ምንድ ነዉ የሚሆነዉ?ልክ ከአንድ ድርጅት የማይሻል ጥርቅም ይሆናል። ምክንያቱም የሙከራ ባሕል የለዉም።ስለዚህ የግለሰቦች ጥርቅም ይሆንና ተመልሶ እዚያዉ ነዉ ። እኔ በበኩሌ በበጎን አላየዉም።ሲበስል ችግሩ ሲደርስ የኛ መተባበር የግድ ይመጣል።ከተቻለማ የኛ ትብብር ነገ ጥዋት ቢፈጠር ጥሩ ነበር።በተጨባጭ ስናየዉ ግን ባዶ ነዉ። ስለዚህ አሁን ያለዉ ሁኔታ ለዚህ አመችቶ አላየዉም። አሁን የኤርትራ ሁኔታ የተፈጠረዉን እንመልከት፣-ህዝቡ ማንም ሳይጠራዉ ከያለበት በገራ ተነስቷል፣ ችግሩን ለመቋቋም ጠንካራ ገመድ መሆን የሚችለዉ እያንዳንዱ የራሱን ጥንካሬ ሲጠብቅ ነዉ። ስለዚህ በያለበት ጥረት በዉነቱ ጥሩ ነዉ። ስለዚህ እየተገናኙ መወያየት፣ በሃሳብ መፋጨት እንደዚህ ያለዉ ባህል እንዲጠነክር ማድረግ አለበት። አንድ ኢትዮጵያ፣- መገንጠልን ከመሠረቱ በጥብቅ እንደሚቃወሙ እናዉቃለን ይቀጥላል ዛሬ በኢትዮጵያ የሚታየዉ ሁኔታ ወደ የት እንደሚያመራ ቢገልጡልን? ፕሮፌሰር አስራት፣- አዎ እኔ በበኩሌ መቼም ይህንን የመገንጠል ነገር ለማንሳት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ኢሕአዴግ ባዘጋጀዉ የመጀመሪያዉ የሰኔ ኮንፈረንስ ላይ ተካፍየ ነበር።የተካፈልሁበትን ጉዳይ ይህን ያህል አዉቃለሁ ብየ አይደለም። ግን በወቅቱ ያጋጠሙኝ ልቋቋመዉ ያልቻልሁት ሆኖ ስላገኘሁት በዚያዉ ላይ የመገንጠል ነገር ተነሳ። የኤርትራ መገንጠል እንዲሁም ደግሞ አዝማሚያዉ የሌሎችንም መከተል ፍራቻ ስለነበር በተቻለ መጠን የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠበቅበትና በኤርትራ የነበረ ችግር እንዳለ እንዲታረም እንጂ ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያን ወደ ማፈራረስ እንዳይኬድ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠበቅበት ሁናቴ እንዲፈጠር አሳስቤ ነበር። ነገር ግን አዝማሚያዉ ስላላማረኝ “ኤርትራ ትገንጠል ከተባለ አገነጣጠሏ በደምብ በሕግ ስርዓትና በ አስተዳደር በሚገባ አንዲሰራ የመለያየቱ ፍቺ በደንብ እንዲፈጸም አለበለዚያ መዘዝ ነዉ የሚመጣዉ። በማለት በዚያን ጊዜ ተናግሬ ነበር። ይህም አነጋገሬ ነበር ሰዉ ጥርስ ዉስጥ አስገብቶኝ አስከዛሬ ድረስ ለማየዉ ፍዳ አስተዋጽኦ ያደረገዉ። አሁን የተከሰተዉ ነገር ታይቶኛል ብየ እንኳን ባልል ነገር ግን ፍጹም ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጠር አምኜበት ነበር። ምክንያቱም አገር ይቅርና ሁለት ባልና ሚስቶች ተፋትተዋል ከተባለና ተድበስብሶ ከታለፈ ነገ ጠዋት መነታረካቸዉ አይቀርም። ያ ንትርክ ደግሞ መዘዙ እየተባዛ እንጂ እየበረደ አይሄድም።የፈራሁት በሁለቱ መካከል ከፍተኛ ቅራኔ የተፈጠረ እንደሆነ የዚያ ቅራኔ ዉጤት ዘላቂ የሆነ ጥላቻ ነዉ በማለት ነዉ። ባልና ሚስት እንኳ ደህና ሕጋዊ ፍቺ ከፈፀሙ እንኚህ ሰዎች አልተጣሉም። እንደገና ሊታረቁ ይችላሉ። የዚያን ጊዜ ፍቺዉ ካልቀረ በደንብ ይሠራ ያልሁበት ዋናዉ ምክንያት ኤርትራዉያን ተገንጥለዉ ሲያዩት የሚለያዩበት ምክንያት አያስፈልግም በሚሉበት ጊዜ ተመልሶ ለመዋሃድ የሚያሳፍራቸዉ ነገር አይኖርም ። ኢትዮጵያዉያኖችም እንደዚሁ። ይህን በማሰብ ነዉ። www.Ethiopiansemay.blogspot.com