Tuesday, May 19, 2009

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል (ከወያኔ የገበና ማሕደር) ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
የህዝባዊ ሓርነት ወያነ ትግራይ መንግስት በማለት ራሱን የሚጠራ ለባዕድ አገሮች ያደረ ትግራይ ዉስጥ የተመሰረተ ጸረ ኢትዮጵያ ወራዳ ቡድን “ፕሮፌሰር-አስራት-ወልደየስን”የሐሰት-ክስ-በመመስረት-ባልሰሩትና-ባልተሳተፉበት ወንጀል ተሳትፈዋል በማለት “ከአራት ዓመት”በላይ አስሮአቸዉ በወቅቱ ሲታመሙ መታከም የሚገባዉን የሕክምና ደረጃ ምርመራ-ተነፍገዉ በመቆየታቸዉ ሕመማቸዉ ጠንቶባቸዉ መዳን እንደማይችሉ “ወያኔ” ሲያዉቅ፣ ሆን ብሎ ለፕሮፖጋንዳ ዉጭ አገር ሄደዉ እንዲታከሙ ከፈቀደ በሗላ ለሞት መዳረጋቸዉ ይታወቃል፣፣ በሃሰት የተወነጀሉበት ምስጢር በወያኔ ሲቀነባበር ድርጊቱ በዓይኑ የተመለከተዉ የቀድሞዉ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ታጋይ እና የወያኔ/ኢሕአዴግ የህዝብ ደህንነት ሰራተኛ “ፍስሃ ሃይለማርያም”-ምስጢሩን ለህዝብ ይፋ አዉጥቶ ወያኔንን ያጋለጠበትን የቃለ መጠይቅ “አዉዲዮ-ቪዲዮ” ለማየትና ለማዳመጥ ከበስተቀኝ በኩል የተለጠፈዉ ቪድዮ ይመልከቱ፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ትዉልዱ ትግራይ ዉስጥ ተምቤን አዉራጃ ዓብይ ዓዲ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማይ ሎሚን ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ነዉ የተወለደዉ፣፣ ወያኔ በመጨረሻዉ ሰዓትደርግን ለማሸነፍ ሲቃረብ በስለላ ስራ መድቦት ይህንኑ ስራዉ ሲያከናዉን ከቆየ በሗላ የደርግ ስልጣን ሲወገድ፣ ፍስሃ እና 20 የሚሆኑ የህወሓት አባላት ለስለላ ስልጠና ሱዳን አገር ተልከዉ ወደ 10 ወር ገደማ ሰልጥነዉ ሲመለሱ ፣ ፍስሃም በቀጥታ አዲስ አበባ ዉስጥ ተመድቦ ከ1984 እስከ 1992 ዓ.ም. በአገር ደህንነት መከላከያ በልዩ ጽ/ቤት ዋና መምርያ ሓላፈ ሆኖ ቆይቷል፣፣ ከስለላ ስራ ጎን ለጎንም የህወሓት መሰረታዊ ማሕበራት ዋና ጸሃፊም ነበር፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ወያኔን ከድቶ ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት “የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ”(TPDM) ተብሎ በሚጠራ በኤርትራ ይደገፋል የሚባለዉ ጸረ ህወሓት ድርጅት መሪ ሆኖ ከቆየ በሗላ ምስጢሩ እስካሁን ለኛ ግልጽ ባልሆነ መንገድ “የላይኛዉ ጋሽ ባርካ” ተብሎ በሚጠራዉ የኤርትራ ድምበር አካባቢ “በወያኔ ክትትል እንደተገደለ ይነገራል፣፣ የአገዳደሉ ቅንብርና ምስጢር ለወደፊቱ ብዙ ምስጢር እንደሚወጣ ይጠበቃል፣፣” ለማንኛቸዉም በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተጠነጠነዉ የሓሰት ወንጀል እንዴት እንደተጎነጎነ እና ማንስ በዛዉ የፈጠራ ወንጀል ልዩ መሪ ሆኖ እንደተሳተፈ ምስጢሩ ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ ሚዲያዎች በኩል የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እነሆ፣፣ ቃሉ የተጨመረ ወይንም የተቀነሰ የለም፤ እንደወረደ ነዉ። “እኔ በዓይኔ ያየሁት አንድ ነገር ነበር! ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አንድ ጊዜ በዚህ ደብረብርሃን እስረኞችን ለማስፈታት በተደረገዉ ኦፔረሽን ተሳትፈዋል ብሎ አስወንጅሎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድባቸዉ በማሰብ፣ ባገር ዉስጥ ሚኒሰትር ምክትል ሚኒስተር የነበረ ደብረጽየን ገብረሚካኤል የሚባል የሰረዉን ስራ እኔ በዓኔ ያየሁት ነበር፣፣ ፕሪፌሰር በዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ስራ ተሰማርተዋል ብሎ በታይፕ አርጎ ጽፎ፣ ፌርማቸዉን የፕሮፌሰር በሌላ ወረቀት የፈረሙት ፌርማ ኮፒ አደርጎ አስመስሎ በመፈረም እሳቸዉ ወደ እስርቤት ከገቡ በሗላ፣ ጽ/ቤታቸዉ የማአድ ጽ/ት እንዳለ ዘግቶ ማሕተም አምጥቶ አትሞ በቀጥታ እንደመስረጃ ብሎ ለፍርድ ቤት አቀረበዉ፣፣ ያ ወረቀት እንደ ዶክዩመንት ተቆጥሮ፣ ፍርድ ቤት ይሄ ጽሑፍ፣ የሄ ፌርማ፣ ይሄ ማሕተም የርስዎ ነዉ ብሎ….ምንም ባልፈጸሙት ወንጀል በእስር ቤት ተሰቃይተዉ ለሞት ተዳረጉ፣፣ እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ግፍ እየተፈጸመ ይህ የታገልክበት ዓላማ በግልባጩ ሲተገበር እያህ…እኔ በግሌ ለሕሊናየ በጣም ቁስል ነዉ የፈጠረብኝ፣፣ በታሪክም ተጠያቂ የሚያደርግ ስለሆነ የነበረኝም ሁኔታ ከግምት ሳላስገባ የታገልኩለትን ዓላማ የትግራይ ህዝብ በመሆኔ ሌላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የታገለበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የተሰዉ ታጋዮች ወንድሞቻችንና ጓዶቻችን አደራ ያሉንን ዓላማ ከግብ እንዲደርስ ዳግም መታገሉን መረጥኩ፣፣”(ፍስሃ ሃይለማርያም -የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የስለላ ሰራተኛ፤ በሓላም “የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ሽምጥ ተዋጊ ሊቀመንበር)
በዚህ ሁኔታ ነበር ፕሮፌሰር አስራት በሃሰት ተወንጅለዉ ለሞት ተዳረጉት። ወያኔም ሆን ብሎ ፍስሃን ተከታትሎ እንዲገደል ያስደረገበት ዋናዉ ምክንያት ይህ በጣም አስገራሚ ጉድ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም ፍስሃ በምስክርነት እንዳይቀርብ ባጭሩ ህይወቱ እንዲቀጭ አደርጎታል። ፍስሃ ሃይለማርአም ስጋዉ ቢሞትም ቃሉ ህያዉ በመሆኑ የወኔ ጥይት የማይሞት የምስክርነት ቃሉን መግደል አይቻለዉም።/-/www.Ethiopiansemay.blogspot.com

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል

የሓሰት ሰነድ አቀናባሪዉ ደብረጽየን ገብረሚካኢል (ከወያኔ የገበና ማሕደር) ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com
የህዝባዊ ሓርነት ወያነ ትግራይ መንግስት በማለት ራሱን የሚጠራ ለባዕድ አገሮች ያደረ ትግራይ ዉስጥ የተመሰረተ ጸረ ኢትዮጵያ ወራዳ ቡድን “ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን” የሐሰት ክስ በመመስረት ባልሰሩትና ባልተሳተፉበት ወንጀል ተሳትፈዋል በማለት “ከአራት ዓመት” በላይ አስሮአቸዉ በወቅቱ ሲታመሙ መታከም የሚገባዉን የሕክምና ደረጃ ምርመራ ተነፍገዉ በመቆየታቸዉ ሕመማቸዉ ጠንቶባቸዉ መዳን እንደማይችሉ “ወያኔ” ሲያዉቅ፣ ሆን ብሎ ለፕሮፖጋንዳ ዉጭ አገር ሄደዉ እንዲታከሙ ከፈቀደ በሗላ ለሞት መዳረጋቸዉ ይታወቃል፣፣ በሃሰት የተወነጀሉበት ምስጢር በወያኔ ሲቀነባበር ድርጊቱ በዓይኑ የተመለከተዉ የቀድሞዉ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ታጋይ እና የወያኔ/ኢሕአዴግ የህዝብ ደህንነት ሰራተኛ “ፍስሃ ሃይለማርያም” ምስጢሩን ለህዝብ ይፋ አዉጥቶ ወያኔንን ያጋለጠበትን የቃለ መጠይቅ “አዉዲዮ-ቪዲዮ” ለማየትና ለማዳመጥ ከበስተቀኝ በኩል የተለጠፈዉ ቪድዮ ይመልከቱ፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ትዉልዱ ትግራይ ዉስጥ ተምቤን አዉራጃ ዓብይ ዓዲ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማይ ሎሚን ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ነዉ የተወለደዉ፣፣ ወያኔ በመጨረሻዉ ሰዓትደርግን ለማሸነፍ ሲቃረብ በስለላ ስራ መድቦት ይህንኑ ስራዉ ሲያከናዉን ከቆየ በሗላ የደርግ ስልጣን ሲወገድ፣ ፍስሃ እና 20 የሚሆኑ የህወሓት አባላት ለስለላ ስልጠና ሱዳን አገር ተልከዉ ወደ 10 ወር ገደማ ሰልጥነዉ ሲመለሱ ፣ ፍስሃም በቀጥታ አዲስ አበባ ዉስጥ ተመድቦ ከ1984 እስከ 1992 ዓ.ም. በአገር ደህንነት መከላከያ በልዩ ጽ/ቤት ዋና መምርያ ሓላፈ ሆኖ ቆይቷል፣፣ ከስለላ ስራ ጎን ለጎንም የህወሓት መሰረታዊ ማሕበራት ዋና ጸሃፊም ነበር፣፣ ፍስሃ ሃይለማርያም ወያኔን ከድቶ ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት “የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ”(TPDM) ተብሎ በሚጠራ በኤርትራ ይደገፋል የሚባለዉ ጸረ ህወሓት ድርጅት መሪ ሆኖ ከቆየ በሗላ ምስጢሩ እስካሁን ለኛ ግልጽ ባልሆነ መንገድ “የላይኛዉ ጋሽ ባርካ” ተብሎ በሚጠራዉ የኤርትራ ድምበር አካባቢ “በወያኔ ክትትል እንደተገደለ ይነገራል፣፣ የአገዳደሉ ቅንብርና ምስጢር ለወደፊቱ ብዙ ምስጢር እንደሚወጣ ይጠበቃል፣፣” ለማንኛቸዉም በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተጠነጠነዉ የሓሰት ወንጀል እንዴት እንደተጎነጎነ እና ማንስ በዛዉ የፈጠራ ወንጀል ልዩ መሪ ሆኖ እንደተሳተፈ ምስጢሩ ከመሞቱ በፊት ከኤርትራ ሚዲያዎች በኩል የሰጠዉ የምስክርነት ቃል እነሆ፣፣ ቃሉ የተጨመረ ወይንም የተቀነሰ የለም፤ እንደወረደ ነዉ። “እኔ በዓይኔ ያየሁት አንድ ነገር ነበር! ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አንድ ጊዜ በዚህ ደብረብርሃን እስረኞችን ለማስፈታት በተደረገዉ ኦፔረሽን ተሳትፈዋል ብሎ አስወንጅሎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድባቸዉ በማሰብ፣ ባገር ዉስጥ ሚኒሰትር ምክትል ሚኒስተር የነበረ ደብረጽየን ገብረሚካኤል የሚባል የሰረዉን ስራ እኔ በዓኔ ያየሁት ነበር፣፣ ፕሪፌሰር በዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ስራ ተሰማርተዋል ብሎ በታይፕ አርጎ ጽፎ፣ ፌርማቸዉን የፕሮፌሰር በሌላ ወረቀት የፈረሙት ፌርማ ኮፒ አደርጎ አስመስሎ በመፈረም እሳቸዉ ወደ እስርቤት ከገቡ በሗላ፣ ጽ/ቤታቸዉ የማአድ ጽ/ት እንዳለ ዘግቶ ማሕተም አምጥቶ አትሞ በቀጥታ እንደመስረጃ ብሎ ለፍርድ ቤት አቀረበዉ፣፣ ያ ወረቀት እንደ ዶክዩመንት ተቆጥሮ፣ ፍርድ ቤት ይሄ ጽሑፍ፣ የሄ ፌርማ፣ ይሄ ማሕተም የርስዎ ነዉ ብሎ….ምንም ባልፈጸሙት ወንጀል በእስር ቤት ተሰቃይተዉ ለሞት ተዳረጉ፣፣ እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ግፍ እየተፈጸመ ይህ የታገልክበት ዓላማ በግልባጩ ሲተገበር እያህ…እኔ በግሌ ለሕሊናየ በጣም ቁስል ነዉ የፈጠረብኝ፣፣ በታሪክም ተጠያቂ የሚያደርግ ስለሆነ የነበረኝም ሁኔታ ከግምት ሳላስገባ የታገልኩለትን ዓላማ የትግራይ ህዝብ በመሆኔ ሌላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የታገለበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የተሰዉ ታጋዮች ወንድሞቻችንና ጓዶቻችን አደራ ያሉንን ዓላማ ከግብ እንዲደርስ ዳግም መታገሉን መረጥኩ፣፣ ” (ፍስሃ ሃይለማርያም -የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የስለላ ሰራተኛ፤ በሓላም “የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ሽምጥ ተዋጊ ሊቀመንበር)
በዚህ ሁኔታ ነበር ፕሮፌሰር አስራት በሃሰት ተወንጅለዉ ለሞት ተዳረጉት። ወያኔም ሆን ብሎ ፍስሃን ተከታትሎ እንዲገደል ያስደረገበት ዋናዉ ምክንያት ይህ በጣም አስገራሚ ጉድ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም ፍስሃ በምስክርነት እንዳይቀርብ ባጭሩ ህይወቱ እንዲቀጭ አደርጎታል። ፍስሃ ሃይለማርአም ስጋዉ ቢሞትም ቃሉ ህያዉ በመሆኑ የወኔ ጥይት የማይሞት የምስክርነት ቃሉን መግደል አይቻለዉም።/-/www.Ethiopiansemay.blogspot.com