Sunday, March 31, 2019

የለማ መገርሳ አትጠራጠሩኝ ዥዋዡዌ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


የለማ መገርሳ አትጠራጠሩኝ ዥዋዡዌ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
Lema-Megersa-Pendulum (Cartoon source Welkait.com)
ውይ!! ያች አገር ምን ብትደርግ ይሻላት ይሆን? ‘ትናንትም ፤ ዛሬም ነገም “ውሸትን”  በውብ ቃላት እያስዋቡ የተናገሩትን ውሸት ሲነቃባቸው ቆርጦ ቀጥል ነው እያሉ “አሉ” ይላሉ:፡የኦሮሞ አፓርታይድ (የኦሮሞ ክልል) አስተዳዳሪው ለማ የአላልኩኝም የትናንቱ “የአሉ/ታ” ንግግር አድምጨዋለሁ። ይሄ የክህደት፤የማስተባበል አመል በኢትዮጵያውያን ልሂቃን እጅግ የበታ ፈውስ ያልተገኘለት ‘በሽታ’ ነው። ይህ ‘ይቅርታ’ አለመጠየቅ፤ ‘ስህተትን ያለማረም’ አመል፤ ድርቅ የማለታቸው መጥፎ ልምድ አገሪቱ ወደ ማጥ ከሚያስገባት ዋነኛው ምክንያት ይህ አመል ነው። የአለምነው መኮንን “ቆርጦ ቀጥል ነው” መከራከሪያ ዛሬ በለማ መገርሳ ተደገመ!
እንደዚያም ሆኖ- በለማ የተዋቡ ቃላቶች ሰክረው “ተጠራጥረንህም አናውቅም” እያሉ የሚጽፉ ጸሃፍት የድረገጹ ሲንጋጉ አስተውያለሁ። የሕዝባችን የለመጠራጠርና በየ አዳራሹ በእጅ እና በፉጨት የማንጨብጨብ በሽታም ይሄም መድሃኒት ያልተገኘለት ሌላው ችግር ነው።
በቅርቡ የታዘብነው ‘የአላልኩም እና ይቅርታን መጠየቅ” ያልለመዱ ‘ከስህተታቸው መታረም ያልፈለጉት’ ምሁራን እና ፖለቲከኞች መካከል አብይ እና ለማ የቅርቡ ዋነኛ ምሳሌዎች ናቸው። ስለ አብይ “ወደ ለየለት ጦርነት እንገባለን፤ እና እኔ እውነት ከደሜ ውስጥ ነው፤ ኢንሳ ውስጥ ስሰራ ኢትዮጵያን ወይንም ዜጋን የሚጎዳ ስራ አልሰራሁም….”  ንግግሩ በሰፊው ስለተነጋገርንብት ወደዚያው ሳልገባ ዛሬ ደግሞ፤ይግረም ብሎ ‘ለማ መገርሳ’ አብዛኛዎቹ ከሶማሌ፤(አንባቢዎች ብዙዎቹ ኦሮሞዎች መሆናቸውን አትዘንጉ) “ወደ አዲስ አበባ እንዲሰፍሩ ያደረግኩዋቸው ‘ተፈናቃዮች” “ፖለቲካዊ ይዘት የለውም፤ ምንም ፖለቲካ ፋይዳ አይደለም” የአዲስ አበባውን ናሪ የዲሞግራፊ (የሕዝብ ስብጥር ‘ተዋጽኦ’) ለመለወጥ አይደለም…” ሲል በጣም ቁጣ አዘል የተሞላበት ንግግር ሲናገር አድመጫለሁ። ሰፋሪዎቹ ለምን ወደ አዲስ አበባ እና ዙርያዋ ለማስፈር እንደፈለገ ከራሱ አንደበት ያለፈው ወር ንግግሩ የምንረዳው ነገር፡ የትናንቱን የአሉታ እና አውንታን “የመሸፋፈን ንግግሩ” እውነታውን ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን /ር አብርሃም ዓለሙ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ ‘የለማ መገርሳ ንግግር” (ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ  ፋይዳ እንዳለው የተናገረውን) ረስታችሁት ከሆነ ለምን ለማን መጠራጠር እንደሚገባን ይህንን ይፋዊ ንግግሩን ላስነብባችሁ።
 በነገራችን ላይ ተርጓሚው (ካልተሳሳትኩ) ለማ መገርሳ “የአመቱ ሰው ሽልማት መሸለም አለበት” ብሎ ስለ ለማ መገርሳ መሸለም ሃሳብ ሲሰጥ የነበረ ምሁር ነው። ስለዚህ በለማ ላይ ምንም ጥላቻ የሌለው ሰው መሆኑን እንድታውቁት ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ማወቅ ያለባችሁ ተርጓሚው ዶ/ር አብርሃም የቋንቋ ምሁር ነው። ለማ መገርሳ አላልኩም የሚል ከሆነም ፊት ለፊት እኔ ከተረጎምኩት ትርጉም ሁለታችን ቀርበን ሚዲያ ላይ እውነታውን ልንከራከርበት እንችላልን ብሏል ደ/ር አብርሃም።ለማ ግብዣው ተልኮለታል፤ ግን እስካሁን ሊጋፈጠው አልፈለግም።
በነገራችን ላይ ተፈናቃዮቹ ወደው ሳይሆኑ በገዳ ሽማግሌዎች እባካችሁ ተብለው እንደምንም ተብሎ “በግፊት ነው እንዲሰፍሩ የተደረገው” (ይህንን የእባካችሁ እዚህ ስፈሩ ወደ ሰፈራችሁ አስፍሩን አትበሉን የሽማግሌዎች እነ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ግፊት “ለፖለቲካዊ ሴራ” እንደሆነ አስቡት) ሴራው ደግሞ ለማ እንዳለው፦
“የከተማ ፖለቲካን (አርበን ፖለቲክስ) ማጤን አለባችሁ፤ ችላ ልትሉት አይገባም፤’ ያላችሁት፣ ትክክል ነው፡” የከተማ ፖለቲካ (አርበን ፖለቲክስ) ሊጤን ይገባዋል፣ ምክንያቱም የዚህ ሀገር ፖለቲካ ማእከል (ሴንተር ኦፍ ፖለቲክስ) ከተሞች ስለሆኑ ነው፡፡ የዚህን ሀገር ፖለቲካ የሚወስነውም ከተማ ነው፤ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተማ ውስጥ ፖለቲካ ማለት አንድ ቁጥር ዲሞግራፊ (የህዝብ ስርጭት) ነው።ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት። ይሄ በፖለቲካ ላይ ያለው ፋይዳ፣ ሄዶ ሄዶም በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ” ይላል ለማ መገርሳ (ምንጭ ኢትዮ ሰማይ) አሁን ወደ እራሱ አንደበት እናምራ። ይህንን የለማ መገርሳ የቀድሞ ንግግሩን ለማወቅ በቴድሮስ ጸጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) የተለቀቀው የትርጉም ጽሁፍ እነሆ።
የአዲስ አበባንና ዙርያዋን የህዝብ ተዋጽኦ demography ለመለወጥ ከግማሽ ሚልዮን የሚበልጡ ኦሮሞዎች አዲስ አበባ ማስገባታቸውን አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ!!! (Reyot – ርዕዮት)
ጥያቄዎች፣
1. “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ብሎ ያለ ርዕሰ መስተዳድር፤ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን” የሚል ጠቅላይ ሚኒስትር በጋራ በቋንቋ ተከልለው ከስር ከስር “ኢትዮጵያ” በማለታቸው ያከበራቸውንና እምነት የጣለባቸውን ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚገፋና ከአገር ባለቤትነት የሚፍቅ ሸፍጥ መስራት ምን ያህል ያስጉዛቸው ይሆን?
2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም ጉዳይ “በቦታው የነበርኩ ቢሆንም ሲነገር አልሰማሁም፣ አላውቅም” ሊሉን ይደፍሩ ይሆን? የለማ ቡድን አባላት የሚከተለው መልእክታችን ይድረሳቸው፡፡
ይሄ ጨዋታ ለአሳዳጊያችሁ ለህወሀትም አልበጀ፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ሊጥሏት ያሰቡትን ሁሉ ጥላ የምትነሳ ሀገር ናት፡፡ “እፍ ይሏታል እንጂ አያጠፏትም” እንዲል ገጣሚው፡፡
Reyot – ርዕዮት
የ3 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ Video ትርጉም በጽሁፍም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተደረገ የጨፌ ኦሮሚያ የእርቅ ህዝባዊ ሸንጎ (አቶ ለማ መገርሳ ከጉባኤው ተሳታፊዎች አዲስአበባንና ኦሮሚያን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጧቸው መልሶች)፦
አብርሃም አለሙ (ዶክተር) እንደተረጎመው
( ” ‘የከተማ ፖለቲካን (አርበን ፖለቲክስ) ማጤን አለባችሁ፤ ችላ ልትሉት አይገባም፤’ ያላችሁት፣ ትክክል ነው፡፡ የከተማ ፖለቲካ (አርበን ፖለቲክስ) ሊጤን ይገባዋል፣ ምክንያቱም የዚህ ሀገር ፖለቲካ ማእከል (ሴንተር ኦፍ ፖለቲክስ) ከተሞች ስለሆኑ ነው፡፡ የዚህን ሀገር ፖለቲካ የሚወስነውም ከተማ ነው፤ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተማ ውስጥ ፖለቲካ ማለት አንድ ቁጥር ዲሞግራፊ (የህዝብ ስርጭት) ነው፡፡ እዚያ ላይ አንዱን ወደዚያ መግፋት፣ አንዱን ወደዚህ መጎተት፣ አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ሳይሆን፣ እንደ ኦሮሚያ ብዙ ነገሮች እየሰራን እንዳለን መገንዘብም ያስፈልጋል፤ በቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ የጀመርነው በጣም አበረታች ነው፡፡ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን ከ 500፣000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡
ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ ከ 500፣ 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤ እሱ ቢቸገርም ለልጆቹ የሚሆን ስለሆነ፣ ብለን ህዝባችንንም አስቸግረን ካለን ነገር ላይ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው ያሰፈርናቸው፡፡ አብዛኛው የሀረርጌ ሰዎች ናቸው፣ እወቁ፡፡ ቦርደዴ ማስፈር ይቻል ነበር፤ ምስራቅ ሀረርጌ ልናሰፍራቸው እንችል ነበር፡፡ ማስፈር ትክክል ከሆነ እንዲያውም እዚያው አካባቢ ነበር ማስፈር የሚገባው፤ ያን ባህል ነው የሚያውቀው፣ ያን አየር ነው የሚያውቀው፡፡ ወደማያውቀው ባህል እዚህ አምጥተን አዲስ አበባ ውስጥ አሰፈርነው፡፡ ቢቸገር ቢቸገር ሁለት ዓመት ነው ሊቸገር የሚችለው፤ ከዚያ በኋላ ሰው ሆኖ ይወጣዋል፡፡ ይሄ በፖለቲካ ላይ ያለው ፋይዳ፣ ሄዶ ሄዶም በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በብዙ መንገድ ስለሚፈይድ፡፡
ወጣቱንም ስራ እናስይዛለን ብለን በንግድ ስም፣ በሌላም ነገር ስም ብዙ ነገር ስናደርግ ነበር፤ እናም አብዛኛውን ከተማ ውስጥ አስገባነው፡፡ ወደ ከተማ ስናስገባው የሚኖርበት ቦታ ኖሮት ነው፡፡ ከ500፣ 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያን ክልል ሰራተኞች ዘንድሮ መሬት የሰጠናቸው ገጠር ውስጥ አይደለም፤ ይብዛም ይነስም ከተማ ውስጥ ነው የሰጠናቸው፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ለሚሆኑ ነው የሰጠናቸው፡፡ ብዙ ልንቆጥር እንችላለን፡፡ ይሄ በቂ ነው ብዬ አይደለም፤ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ሆኖም ችላ ያልነው ነገር አይደለም፤ እየተሰራበት ያለ ነገር ነው፡፡ ስንሰራም በከፍተኛ ጥንቃቄ መስራት የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ ይህም በዚሁ ረገድ ቢታይ መልካም ይሆናል ብዬ ነው የማየው፡፡”)
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)