Sunday, June 14, 2009

ለአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ

ለአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የጎሳ ፖሊሲን የነደፉ የወያኔ ጭንቅላቶች ለሁለት ሲከፈሉ የማን ደጋፊ ነበሩ?
ለሁለት ተከታታይ ሳምንት በነፃነት ራዲዮ አወያይነት ተማክሎ በዶክተር አሰፋ ነጋሽ እና በአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ መካካል ሲካሄድ የነበረዉ ዉይይት እንደተከታተላችሁ ተስፋ አለኝ፣፣ የወይይቱ አርዕስት ወያነ ትግራይ ያመጣብን አደጋ እና መፍትሄዉ ነበር፣፣ ላምልጥ እንኳ ቢባል የዉይይቱን ብልት/አንኳር ለማሳየት “ጉዳቱና የጉዳቱ ደጋፊዎች” ከማንሳት (Identify-መለየት) ማምለጥ አይቻልምና ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ፣ወያነ ትግራይ ያመጣዉ የጎሳ ፖለቲካ በአገሪቱ ዉስጥ ያስከተለዉ ሰበብ እና ለዚህ የጎሳ ፖለቲካ ፈጣሪዎች እንክብካቤ እና ድጋፍ የሚሰጡ ክፍሎች እነማን መሆናቸዉ ለይተን ካላስቀመጥን እና መለየት ብቻ ሳይሆን ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሲያራምድ “ነፃ አወጣሃለሁ፣ እጠቅምሃለሁ፣’ በማለት በእርሱ/በጎሳዉ ማለትም በትግራይ ሕዝብ ስም እየተጠራ እንደመንግሥትነቱ የያዘዉን ሥልጣን ተጠቅሞ ለጎሳዉ ልዩ እንክብካቤ እና አትኩሮት ከሌሎቹ አካባቢዎች በበለጠ በመቆርቆር “የአስተዳደር አድልዎ” በማድረጉ፣ ይህ አድልዎ በሰፊዉ /በአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አሳድሯል፣፣ በዚህ ሳያበቃ ስርዓቱ የጎሳ ፖሊሲ ማራመድ ዓይነተና መመሪያዉ እና የታገለለት ፕሮግራም ስለሆነ በዛ ስርዓት አወቃቀር የሕዝቡን አንድነት እያጨለመ ‘አካባቢያዊ/ጎሳዊ”ሕሊና እንዲያድርበት በማድረጉ ምክንያት የአገሪቱ የሕሊና አመለካካት (Psychology) ከአንድነት ይልቅ አካባቢያዊና ክልላዊ- ማለትም “ትግራዋይነት፣ ጉራጌነት፣ ኦሮሞነት፣ አደሬነት፣ ሶማሌነት ወዘተ…”በመከናነብ “ኢትዮጵያዊነትን እና የጋራ ሰብአዊ ቤተሰብነትን”አኮስምኖታል፣፣ ለዚህም በተጨባጭ የታዩት የጎሳ ግጭቶች፣ እልቂቶች ፣መፈናቀሎችና እና ምሬቶች ህያዉ ማሕደር ይዘዋል፣ እና ለዚህ ችግር “ኤሊቱ” በተለይም በስሙ የሚነገድበት “የትግራይ ኤሊት” ተቃዉሞዉ ጎልቶ አልታየም፣ ስለዚህ “ኤሊቱ”በግምባር ቀደም ሕዝቡን አስተባብሮ የጎሰኛ ስርዓት የሚያስተምረዉን ትምህርት ከማመንመን ይልቅ ወይም “ዝምተኛ”ሆኗል አልያም “ስርዓቱ ደጋፊ”በመሆን ለተማረረዉ ሕብረተሰብ መከራዉ እንዲራዘም “በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ” አስተዋጽኦ እያደረገ ስለሆነ “ መፍትሄዉ ለመሻት (ጎሰኛዉን ስርዓት ለማስወገድ”)1-አስከ ዛሬ ድረስ ስርዓቱ በቀጣይነት ለራሱ ጎሳ (ከድህነት ነፃ አወጣሃለሁብሎ ለታገለለት የትግራይ ኗሪ)እያደረገለት ያለዉ እጅግ ቁሳዊም ሆኑ ሞራላዊ ድጋፎች በአድሎአዊ ፖሊሲዉ እየታጀበ ጎሰኛ መንግሥታዊ አስተዳደር ማራመዱን ሳንሸሽግ (ፈራ ተባ ሳንል) ያለዉን ሃቅ መነጋገር መቻል አለብን፣፣ (2) ለዚህ ጎሰኛ-ፖሊሲ እንዲቀጥል የትግራይ ኤሊቶች እዉነት ወያኔን እንቃወማለን/የጎሳ ፌደራሊዝመ እንቃወማለን የሚሉ ከሆነ እና “በነሱ ስም መነገዱ ካልወደዱት ቅዋሜአቸዉ ጎልቶ መዉጣትና ያለዉን አድልዎ “ደፍረዉ” መዘርዘር “ማመን” አለባቸዉ፣፣ ይህ ያደረጉ የትግራይ ተወላጆች ካሉ በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፣፣ ስለሆነም በነሱም ላይ መወያየት “የችግሩ ግማሽ መፍትሄ” በመሆኑ “ሊሂቁ” ለምን “ሎሆሳሳ” ድምፁን ወደደዉ? ነበር የዶክተር አሰፋ ነጋሽ ክርክር (በራሴ ቃላቶች ሳጠቃልለዉ) የተደመጠዉ፣፣
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ደግሞ ያሉት እጠቅሳለሁ፣- “አሁን ዶክተር አሰፋ ነጋሽ እያለ ያለዉ ምንድነዉ? “…ሃሳቡን እየገለጸ ያለዉ የት ቆሞ ነዉ ብለህ ስትጠይቅ”ዶክትር አሰፋ ራሱ የሆነ ጎሳ ግቢ ዉስጥ ገብቶ ነዉ”፣፣ …እያለ ያለዉ In this case ይሄ የአድልዎ የጎሳ ፖለቲካ ትግሬዉን እየጠቀመ ነዉ! እንግዲህ ትግሬዉ እየተጠቀመ ነዉ ካልክ “እሚጎዳ ሌላ ወገን አለ ማለት ነዉ”፣-እሱ ደግሞ “አማራ” ነዉ ማለት ትችላለህ፣፣ አሁን ዶከትር አሰፋ እምገምተዉ “አማራ” ማለቱ ይመስለኛል፣፣ እና እንደዚህ አሉ አሃዞች (ደ/ር አሰፋ የዘረዘራቸዉ በትግራይ ዉስጥ ከሌሎቹ አካባቢዎች እያነጻጸረ ያቀረባቸዉ የግንባታ መሰረቶች/ተቋሞችን ነዉ አሃዝ እያለ አለዉ) complete ሊሆን አይችልም፣፣ በአሃዙ መከራረከር ኢቻላል፣፣አንተ የተቀበልከዉ አሃዝ እኔ ላልቀበለዉ እችላለሁ፣፣ እ..well የሚቀበለዉም ሊኖር ይችላል፣፣ እዚህ ላይ ብዙ “ዘመን” አዉርተንበታል፣፣ለና ሊጠቅመን የሚችለዉ ጠቅለል ባሉ ነገሮች መስማማት ስንችል ነዉ፣፣ ምን ማለት ነዉ “Ethnic federalism” የጎሳ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ እሚበጅ አይመስለኝም እሚለዉ አስማማለሁ ተቀብየዋለሁ፣፣ ለምን የሚለዉም ካሁን በፊት ተነጋግረንበታል፣ -አሁን መደረግ ያለበት የሚመስለኝ እኔ ከ35 ኣመት በፊት ሌላ ያ የምናወግዘዉ አሁን ማለት ነዉ- እሚያደርገዉን አሁን በሌላ መንገድ አቅርበን (35በፊት የሚለዉ ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ሲሰብኩት”አማራዉ ጎድቶሃል፣ የሸዋ ክፍል ሲበለጽግ አንተን/ትግራይን እንድትደኸይ አደርገዋል ሲሉ የነበሩትን ቅስቀሳ ማለቱ ነዉ)፣-አንድ ጎሳ በሌላ ጎሳ ሊያነሳሳ እሚችል (ቅስቀሳ በዚህ በ21ኛዉ ክፍል ዘመን ዛሬም እየደገምከዉ ነዉ)፣- ለምሳሌ ስማ ኢሳያስ (የራዲዮኑ አዘጋጅን ነዉ) ትግሬዉ እየተጠቀመ ነዉ ብለህ ስትናገር ምን እያልክ ነዉ?ሌላዉ ትገሬ ያልሆነ ምንድነዉ እሚሰማዉ? ይሄዉ ትግሬዉ እየተጠቀመ ስለሆነ አንተ ዝምብለህ ሞኝ ነህ!ምነድነዉ “በሞኝ ደጃፍ ምንድነዉ የሚባለዉ?{ዋትኤቨር?}(ሞፈር/ዛፍ ይቆረጣል፣ እንደሚባለዉ ማለት ነዉ፣፣ የኢትዮጵያ ንብረት ባይዘወይ አዲስ አይደሉም፣፣ ኢትዮያ እየተዘረፈች፣ ትግሬዎች ኢትዮጵያን እየዘረፉት ነዉ ብሎ የሚናገር ሰዉ ነዉ፣፣ እና እየዘረፉ ሊሆኑ ይችላሉ፣፣ እሱ አይደለም ችግሩ፣፣ግን ካንድነት “አንግል”እምታየዉ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ አንድነት-እሚቆረቁርህ ከሆነ ተዳክሟል የምትለዉ አንድነት እንዲጠናከር እምትፈልግ ከሆነ፣ ግን ሁሌ መርሳት የሌለብህ፣ እምትሰራዉ ነገር እና የምትናፈገረዉ ነገር አንድነትን ያጠነክራል ወይስ እያላላ ነዉ?እሚለዉ ላይ ትኩረት መደረግ ያለበት ይመስለናል፣፣ አሁን ዶ/ር አሰፋ ምን እያለ ነዉ “ጎበዝ!ትግሬ ያልሆንከዉ እየተዘረፍክ ነዉ በትግሬዎች! አድልዎ እየተፈጸመብህ ነዉ!” እያለ ነዉ፣፣ እና ይሄ ምን፡መጣል መሰለህ “እሱ ያለዉ ግሩፕ ሳይኮሎጂ “Group psychology” ያለዉ ተገልብጦ “ትግሬ ባልሆነዉ ላይ ሊሰራ ይችላል” ምን ማለት ነዉ? By the way Group Psychology” ያለዉ እቀበለዋለሁ፣፣ ግለሰዎች በደርጀት ማሰብ ወይም በቡድን ማሰብ በግል ማሰብ ሲችሉ ለደርጅት surrender እንደሚችሉ ይገባኛል፣፣አሁን ደ/ር አሰፋ እያደረገዉ ያለዉ ግን ያኛዉ ሪቨርስ ለማድረግ እየታገለ ነዉ፣፣ ለምሳሌ ምን እያለ ነዉ “ስማ አማራ እየተዘረፍክ ነዉ! ስለዚህ አንተም “ኢሞሽናል ታደርገዉ እና “አማራዉ ምንድነዉ እሚለዉ “እነዚህ ትግሬዎች አድቫንተጅ እየመቱብኝ ነዉ- ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለብህ እማን ላይ? “ትግሬዩ ላይ”፣፣ ስለዚህ አንድንት የሚያጠናክር አይደለህም እየሰራኸዉ አለኸዉ ዶ/ር፣፣ አንድ ጎሳ በሌላ ኮሳ የሚያጨቃችቅ ፣ እሚጨምር ነገር እየተናገርክ ነዉ፣፣” ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ፣- አቶ ሙሉጌታ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል፣-አንዴ ላቋርጠዎት እና እኔ እነደገባኝ እና እርስዎ እንደሚሉት ባጭሩ አርስዎ “አሁን ያለዉ ስርዓት አድሎዋዊ የሆነ ነገረ (አስተዳደር)አይፈጽምም,…“ይፈጽማል ብለዉ ለመናገር ያልደፈሩበት ምክንያት (ዳርዳሩን እየሄዱበት ያሉት ምክንያት) ምንድነዉ? አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣- ይሄዉልህ፣-“አድሎአዊ የሆነ ነገር አይፈጽምም አላልኩም፣-ግበቶሃል? አድሎአዊ ነገር ይፈጽማል ስትል ግን፣ “በጎሳ ማየት አልፈልግም!” ነፃነት ራዲዮ፣- አሁን እርስዎ በሚያዩት አተያይዎ…. አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣- አቶ ኢሳያስ አድልዎ ያልኩህ ለምሳሌ ዶ/ር አሰፋ የሚለዉ አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ መንገስት አድልዎ ሲፈጽም ትግሬዉን ለመጥቀም ነዉ,፣፣ የሚለዉ፣፣ እኔ እሱን Reject(አልቀበለዉም፣ ወያነ ትግራይ ቡድን “ትግሬዉን ለመጥቀም “አድልዎ” አያደርግም ማለቱ ነዉ፣፣ ሙሉጌታ -)አደርጋለሁ! ይሄ መንግሥት አድልዎ ሲፈጽም የራሱን ፖሊሲ ተቀብለዉ የሚያራምዱትን ነዉ የሚጠቅመዉ፣፣ ማአት አማራ ተጠቃሚ አለ!ማአት ኦሮሞ ተጠቃሚ አለ!ይኼ መንግሥት ፍልስፍናዉን ደግፈህ ከእርሱ ጋር እስከተሰለፍ ድረስ መጠቀም ትችላለህ፣፣ትገሬ ሆነህ ፍልስፍናዉን ካልተቀበልክና ከእርሱ ጋር ካልተጠጋህ-ትግሬም ብትሆን ትመታለህ፣፣ ስለዚህ ይኼ መንግሰት ትግሬዎችን ነዉ የሚጠቅመዉ ብሎ በደፈና ፣ይሄ መንግስት አማሮችን ነዉ የሚጎዳ የሚለዉ እኔ አልቀበልም፣፣ ነፃነት ራዲዮ፣- ዶ/ር አሰፋ በርስዎ ዙርያ ያጠነጠኑ አሳቦች ተሰንዝረዋልና ባጭሩ ያጠቃልሉልኝ እና ወደ አቶ ሙሉጌታ የሚጤቁ በርካታ ጥያቄዎች አሉ እመለስባቸዋለሁ? ደ/ር አሰፋ ነጋሽ፣ እሺ!አንደኛ ምንድነዉ፣-አንድነትን እኮ የሚያላላዉ እኔ እምለዉ ነገር ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተጨባጭ እየሆነ ያለዉ ነገር ነዉ፣፣እ…ይሄ ከ35 ዓመት (የወያኔ መሪዎች)በፊት ሸዋ ተጠቀመ ይሉ ነበር ምንትስ ይባል ነበር …የሚባለዉ (አሁንም አሰፋ ትግራይ ተጠቀመ አማራዉ ደኸየ ይላል) ለሚለዉ (ሙሉጌታ ለሚለዉ)-ነገር ፣ሸዋ የሁሉም መኖርያ ነዉ፣፣ ሸዋ የሚባለዉ አሁን በቲ ፒ ኤል ኤፍ አጠራር “ሸዋ ስትል “ሰሜን ሸዋ ማለትህ ነዉ?) ያ ከሆነ- በወቅቱ I can tell you- ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ከ2(ሁለት) ሃይስኩል በላይ አልነበረም፣፣ በትግራይ ደግሞ 5እሰከ 6ሃይስኩል እንደነበሩ (በሃይለስላሴ ጊዜ) መናገር እችላለሁ፣፣ እዛ መግባቱ አሁን አላስፈላጊ ቢሆንም (አሁንም ሆነ በዛ በድሮ ጊዜ ካወዳደርነዉ ሸዋ ተጠቀሞ ነበር የሚባለዉ የወያኔዎች ክርክር ከእዉነታዉ ጋር አያስኬድም- ቅንፎቹ ሁሉ የኔ ናቸዉ -ለማብራረት የተደረጉ ናቸዉ)፣፣ አቶ ሙሉጌታ እንዴት ሊገባዉ እንዳልቻለ አላቅም እንጂ “ይሄ ስርዓት እኮ ሳያፍር በጎሳ Identity/አማክሎ እኮ ነዉ የተመሰረተዉ፣ ፣ ይሄ እኮ ጥቂት ከተለያዩ ጥቂት ሰዎች በካድሬነት “ኦፒዲኦ” ዉስጥ አሉት ወይንም “ በ አማራ” የተደራጁ ብቻ ነዉ (አገልጋዮቹ ብቻ ናቸዉ) የሚጠቀሙት/ ወይንም አገኙት የሚባለዉ ጥቅም እሱ “በጣም ቁጥር ዉስጥ የማይገባ ነዉ”እኛ የምንለዉ ያለዉ ከዛ በላይ ያለፈ ነገር ነዉ ፣፣በክልል ደረጃ ነዉ ማየት ያለብን፣፣ እንዴ! ትግራይ ዉስጥ ይሄ ሁሉ ትምህረት ቤቶች የተሰሩት እና በስፋት ተዘርግተዉ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት እኮ ለመለስ ዜናዊ ጥቂት ቤተሰብ ለመጥቀም እኮ አይደለም! እንዴ! ይሄ ሁሉ መንገድ የተዘረጋዉ እኮ የመለስ ዜናዊን ጥቂት ቤተስቦች ለማጓጓዝ እኮ አይደለም፣፣ ይሄ ቀደም ብየ በዝርዝር ለማሳየት እንደሞከርኩት በንጽጽር ሌሎች ታዎች አናየዉም፣፣ አንድ ነገር ስናገር እኔ “አንድን ጎሳ” ወክየ አይደለም የምናገረዉ (ሙሉጌታ አረጋዊ “አማራዉን ወክለህ እየተናገርክ ነዉ ብሎ በፈጠራ ደ/ር አሰፋን ስለወነጀለዉ ነዉ)፣፣ እኔ በኢትዮጵያ ሲሰተም ነዉ የምናገረዉ (ከሬከርዱ እንደምታዳምጡት ደ/ር አሰፋ የአማራ ጎሳ እወክላለሁ ብሎም አያዉቅም አሁንም በዛዉ አላነሳም- ትዝበቱ ለናንተ ልተወዉ)፣፣ “ኢትጵያ በዚህ ዓየነት መንገድ ልትጠቀም አትችልም! የትግራይ ብሄረተኝነት ባለፉት 18 ዓመታት በፈጸማቸዉ ነገሮች የኢትዮጵያ አንድነት ከሚገባዉ በላይ አላልቷል፣፣በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ቤተሰቦች/ቤቶች በፈጠረዉ የጎሳ ግጭት ካካባቢያቸዉ ተፈናቅለዋል!በአስር ሺሕዎቹ የሚቆጠሩ ተገድለዋል!በባድሜ ጦርነት ተወስዶ በብዙ ሺሕ ሰዉ ሊያልቅ ምክንያት የሆነዉ እኮ “ሁለት የጎሳ ፖለቲከኞች”በፈጠሩት ሃላፊነት የጎደለዉ አለስፈላጊ ግጭት እኮ ነዉ! ያለቀዉ ሰዉ እኮ ከማሃል-አገር በዚህ ጎሰኛ ስርዓት ሲቀጠቀጥ የነበረዉ ሰለባ (ቪክቲም)የነበረዉ እኮ ነዉ ሄዶ ነዉ እዛ ጦርነት ዉስጥ ሊማገድ የቻለዉ! ይሄን የፈጠረዉ እኮ ይሄ ስርዓት ነዉ! እኔ ዲፕሎማቲክ ፖለቲካ አደለሁም እየተናገርኩ ያለሁት፣፣ ዲፕሎማቲክ ለመሆንም አልፈልግም፣ አይጠቅመንም!ያለዉ ነባራዊ ተጨባጩን ሁኔታ በሕዝቡ ላይ በአገሪቱ ላይ እየደረሰዉ ያለዉ ግፍ፣ አድልዎ እና አገሪቱ እየጎተታት ወዳለዉ አሰከፊ እና አስፈሪ ሁኔታ መናገር መግለጽ ካልቻልን “ቀስ በቀስ መጥፎ ስሜት እየፈጠረ ነዉ”!፣፣ ችግሩን በድፍረት መግለፅ እንደ “ጠላት”መቆጠር የለበትም፣ ፣… ስለዚህ “We have to face this reality”. ኢትዮጵያ ዉስጥ እየከፋፈለዉ ያለዉ ይህ ጎሰኛ ስርዓት ነዉ! አቶ ሙሉጌታ “For all I know” አንተ አሁን አቶ ሙሉጌታ አንተ አሁን የEthnic ፈederalism” እቃወማለሁ ትላለህ፣Ethnic-Federalismተቃወምኩ የምትል ከሆነ ይሄ የኤትኒክ ፌደራሊዝም ያመጣቸዉ “ዉጤቶች” (ሰበቦች/ጉዳቶች) መከፋፈል፣ ቅሬታ፣ ይሄን ሁሉ “አድሚት ማድረግ/መቀበል ያስፈልጋል”!ግን ወደ “Solution”ወደ መፍትሄዉ እንሂድ ትላለህ፣ ግን አንድ “መፍትሄ” ለማግኘት ችግሩ“ይሄ”ነዉ ሳንል እንዴት ብለን ነዉ “ወደ መፍትሄዉ ዘለን የምንሄደዉ?እንዴ አነጋገሩ ራሱ እኮ አለ-“ችግሩን መረዳት የችግሩን መፍትሄ 50%ግማሽ መፍትሄዉን ማግኘት እኮ ነዉ” ይባል የለ?!
አሁን አንተ የለም ያንን ነገር እንለፈዉ የሚል አመለካከት አለህ፣፣ ሌላዉ አቶ ሙሉጌአተ እዚህ ላይ ግልጽ ላደርግ የምፈልገዉ-ለምሳሌ አንተ እንደ ግለሰብ “የወያኔ አመራር ለሁለት ሲሰነጠቅ (የዛሬ 8 ዓመት አካባቢ) የገብሩን ቡድን ደጋፊ ሆነህ ነዉ ወጣኸዉ፣፣ይሄ-ግሩፕ(የነ ገብሩ አንጃ) የሚያራምደዉና የሚከተለዉ ፖሊሲ “Ethni Federalism” ነዉ….. ሙሉጌታ አራገዊ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽን ንግግር በማቋረጥ “እባክህ ደ/ር እማታዉቀዉን…. እንዴ!.... ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ፣- ጉዳዩን ወደ ሌላ ሙሉጌታ አረጋዊ “ምን ማለትህ ነዉ? እንትን አደረግከዉ እኮ! (ለ ዶክተር አሰፋ ነጋሽን ነዉ ምን ማለትህ ነዉ/ ያለዉ) ነፃነት ራዲዮ አዘጋጅ-፣- ይቅርታ! አንዴ! ዶክተር አሰፋ አስቀድመህ ጥሩ አድረገህ አስቀምጠኸዋል- ችግሩን መረዳት የመፍትሄዉ አንዱ ክፍል ነዉ፣፣ አሁን አቶ ሙሉጌታ እንደምትለዉ ወደ ችግሩ ከመነጋገር ይልቅ ወደ መፍተሄዉ እናተኩር ነዉ የሚሉት፣- (ችግሩ “ለዘመናት” ተነጋግረንበታል ነዉ የሚለዉ ሙሉጌታ፣- ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ለመጥቀም ሲል ከሌላዉ ሕዝብ ለይቶ በልዩ ዓይን አያየዉም ነዉ የሚለዉ አቋሙ)- አስኪ አቶ ሙሉጌታ አርስዎ መፍትሄ የሚሉዋቸዉ አንድ ሁለት ብለዉ እንዲለዩልን አንድ ሁለት ብየ ልጠይቀዎ፣፣ የጎሳ ፌደራሊዝም ‘ችግር እንደፈጠረ ገልጸዉልናል፣ ያ ችግር አለ፣- ይሄንን በኢትዮጵያ የተመሰረተዉ የጎሳ ስርዓት ለማስወገድ “ማስገድ” ከሚለዉ ዉጪ ምን ‘መፍትሄ አለ? በዚህ መፍተሄ ይስማማሉ ወይ አርስዎ? ሙሉጌታ አረጋዊ.- ማስወገድ እሚለዉ ቃል እፈራዋለሁ፣፣ ነጻነት ለኢትዮጵያ፣- ለምን?ያብራሯት፣ ሙሉጌታ አረጋዊ፣-ማስወገድ ማለት፣ እንዴት አድርገህ ነዉ የምታስወግደዉ? ነፃነት ራዲዮ.- እሱ ላይ እንነጋገራለን ፣ በግቡ ብቻ እንስማማ፣፣ ሙሉጌታ አረጋዊ፣-- የጎሳ ፌደራሊዝም ችግር ይፈጥራል፣፣ ነፃነት ራዲዮ- ፣ ፈጥሯል ብለን እናምናለን መጀመሪያ? ሙሉጌታ አረጋዊ፣- አዎ ፈጥሯል፣፣ ለወደፊቱም የባሰ ችግር ሊገጥም ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፣፣ ነፃነት ራዲዮ- እንደ ስርዓት መወገድ አለበት? ሙሉጌታ አረጋዊ፣- እንደስርዓት መቀየር አለበት፣፣ “ማስገድ” ስትል እኔ ፖሎሲዉን ነዉ እየተቸሁ ያለሁ፣፣ ማስገድ ስትል “እኔ ጦርነት እየጋበዝኩ አይደለሁም ያለሁት”፣፣ ፖሊሲዉ ትክክለኛ አይደለም፣፣ ይሄ ፖሊሲ መቀየር አለበት፣፣ ላገር በሚጠቅም መረጋጋት የሚያመጣ፣ አስተማማኝ የሆነ ፖሊሲ መነደፍ አለበት፣፣ አዲስ አፕሮች መኖር አለበት፣፣ ይሄ ፖለቲካ አያዋጣም ባይ ነኝ፣፣መወገድ አለበት ስትል፣ -ለምሳሌ አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ነዉ አንግዲይ ይሄ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም”-ስራ ላይ ያዋለዉ፣፣ ስለዚህ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም” “መወገድ” አለበት ስትል “ይሄ መንግሥት መጥፋት አለበት”የምትል ከሆነ “እኔ እዛ ዉስጥ መግባት አልፈልግም”፣፣ የመጠፋፋት ሳይኮሎጂ እንዲኖረኝ አልፈልግም፣፣ አሱ አይደለም ዲቤት ለማድገር የመጣሁት፣፣
ነፃነት ራዲዮ (አቶ ዓለም)፣-……ከ አንዳን አድማጮቻችን አንዳንድ አስተያየቶች ሰንዝረዋል,፣ ለምሳሌ እርስዎ ያለፈዉ ምንም አያስፈልግም ስለወደፊቱ እንነጋገር እሚባለዉ ላይ ስሕተት ያለዉ በአቶ ሙሉጌታ በኩል “ያለፈዉ ቢቆም ኖሮ እኮ ነዉ” የሚካሄደዉ ፖሊሲ ቢቆም ኖሮ አዎ ስለወደፊቱ እንነጋገር ግን ይሄን ፖሊሲ የሚያካሂደዉ ቡድን “የትግራዩ” ቡድን፣ ይሄንኑ እያካሄደ ነዉ (ቀደም ተብሎ በስፋት በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ተዘረዘሩት አድለዎአዊ እና አገርን እና አንድነትን የሚያላላ አስተዳደር) እንዴት አደርገን ነዉ የምናቆመዉ? ሙሉጌታ አረጋዊ፣-Thank you!እንዴት አድረገን አንደምናቆመዉ ለመግለጽ እችላለሁ፣-ማለትም ‘እሞክራለሁ’፣፣መጀመሪያ ዶ/ር አሰፋ እንዲያዉቅልኝ የምፈልገዉ “እኔ የገብሩ አስራት ደጋፊ ሆኜ አላዉቅም!-የማንም ድረጅት አባል ሆኜ አላዉቅም!-የማንም ቡድን አባል-ሆኜ አላቅም!ደጋፊም ተቃዋሚም ሆኜ አላቅም!”ሁሌ እኔ የምቃወመዉ ፖሊሲዩን ነዉ፣፣በጅምላ ይሄኛዉ ትክክል ነዉ ፣ይሄኛዉ ስህትት ነዉ ብየ አላቅም፣፣ እኔ ከተቃዋሚዉ የምቀበለዉ አለ፣ ከመንግሥትም,-የምቀበለዉ አለ፣፣ እኔ እሚመስለኝን የኔ የግል ኦፒንየን ነዉ እያቀረብኩ አለሁት፣፣ የማንም ሆኜ አላቅም ከማንም ተጠግቼ አላቅም፣፣…..” ማጠቃለያ አሁን -ወደ ኢትዮጵያ ሰማይ ወደ እኔዉ የግል አስተያዬን በተነጋገሩበት ጣልቃ ገብቼ ልሰንዝር፣፣አቶ ሙሉጌታ የሰነዘራቸዉ አስተያየቶች ሰፊ ጽሁፍ የሚጋብዝ እና በሁኔታዉ ካሁን በፊት ብዙ ያልኩበት ስለሆነ አሱን ለናንተዉ ግምገማ ልተዉና አቶ ሙሉጌታ ያቀረበዉ የመጨረሻዉ፣ “የማንም ደጋፊ ወይንም የነ ገብሩ ደጋፊ ሆኜ አላቅም የሚለዉ መልሱን፣-ካሁን በፊት “አገሪቷን በጎሳ ሸንሽነዉ” አንድነቷን በማዳከም ጣሊያን በወረራ ጊዜ የታየዉ ጸረ አማራ ዘመቻ፣ ብዙ የጎሳ ግጭቶችም በፖሊሲዉ ምክንያት እንዲጎዱ ያደረጉት እቃወመዋለሁ እያለን ያለዉ የፖሊሲዉን ፈጣሪ ችንቅላቶች/ማለትም እነ ግብሩ ከወያኔዉ ከመለስ ቡድን ለሁለት ሲለዩ (አሁንም ተለይተዉ ያዉ ፖሊሲ ለማራመድ በዓረና/ወያነ ፕሮግራም ያስተዋወቁ) አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የማንም ቡድን ይሁን የነ ገብሩ ቡድን ደጋፊ አልነበርኩም ሲለን -አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የወያኔ መሰነጣጠቅ እሰየዉ ሲል’-እነ ሙሉጌታ-አረጋዊ “ኤትኒክ ፌደራሊዝም ዕድሜዉ እንዲረዝም - “መሰነጣጠቃቸዉ ሕጋዊነት የለዉም ፣ወደ ቦታቸዉ ይመለሱ፣ ስለ ደህንነታቸዉ እጅግ እጅግ ሰግተናል.እነኚህ አገር ወዳዶች፣ ጀግኖች ናቸዉ….” ሲል በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ጊዜያዊ ሊቀመንበር በመሆን ‘-ከሰባት ዓመት በፊት” በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ትልቁ ዜና ሆኖ ሲተላለፍ የነበረዉ እስኪ እናዳምጥ እና ወንደሜ አቶ ሙሉጌታ እኔ የለሁበትም፣ አኔ አይደለሁም የሚል ከሆነ መልሱን እንጠብቅ፣፣ ሙሉጌታ አረጋዊ ማለት እኔ አይደለሁም ካለም ይቅርታ እነጠይቃለን፣፣ ልትቀስ ተከታተሉት እነሆ.-“
“ከሰባት ዓመት በፊት የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የሚቀጠለዉ ዘገባ አቅርባ ነበር_“ከዚህ ከዋሽንግተን ከቨርጂኒያ ከሜሪላንድ ከኒዉዮርክ ከቦስቶን ከፍላደልፊያና ከአትላንታ የተወከሉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ስለሁኔታዉ ከተወያዩ በሗላ አንድ “ኮሚቴ”መመስረታቸዉን፣የኮሚቴዉ አባል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ገልጿል ። ኮሚቴዉ የተመሰረተዉም የሕዝቡን ድንጋጤና ስሜት ለኢትዮያ መንግሥትና ለሕዝባዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆዩ ድርጅቶች ለትግራዩና ላጠቃላዩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተላለፍ ነዉ ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ አስተላልፈዋል።አስራ አንዶቹ አንጋፋ የህወሓት አባላት የተወገዱት በሕገወጥ መንገድ ነዉ ይላሉ። ይህንን መሰረት በማድረግም የሚከተሉትን ዉሳኔዎች በማብራራት አቶ ሙሉጌታ እንዲህ ይላሉ፦“በመጀመርያ እነዚህ አስራሁለት የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለይም በቅርቡ ማለትም ከሻዕብያ ጋር የተደረገዉ ጦርነት…ጀግንነታቸዉ ያስመሰከሩ፣ አገር ወዳድነታቸዉ…በግልጽ ያሳዩ ከመሆናቸዉም በላይ፣ አሁን ታግደዉ ,ከስራ ተባርረዋል። ስለዚህ ሕይወታቸዉ አደጋ ላይ የወደቀ ይመስላል። ችግር ብያጋጥማቸዉ አንድ ነገር ይፈጠራል ብለንም እናምናለን። ችግር ቢገጥማቸዉ ያባረራቸዉ መንግሥት ተጠያቂ እንደሚሆንከዚያ ቀጥሎ ያስተላለፍነዉ ዉሳኔ ምንድነዉ፦
እነዚህ የተባረሩ አስራሁለቱ ሰዎች ያለ ቅድመ ሁኔታዎች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ፦ ሦስተኛ-በድርጅቱ ሕግና በሌሎችም ተጓዳኝ ሕጎች መሰረት የህወሓት ቁጥጥር ኮሚቴ ባሳለፈዉ መሰረት አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ ጉዳያቸዉ በጉባኤ እንዲታይ፡- አራተኛ፦ጉባኤ አስኪጠራ ድረስ ነጻ ሚድያ እንዲፈቀድላቸዉ፡ አምስተኛ፦አሁን በስልጣን ላይ-ያለዉ ክፍል በነዚህ ሰዎች ላይ የሚያካሂደዉ ፕሮፖጋንዳ ስም-በማጥፋት፣ በራሳቸወና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ቀጣይ የማባረር እርምጃ ..ባስቸኳይ እንዲያቆም፡ ስድስተኛዉ ዉሳኔ-ደግሞ፦ ከኤርትራ ጋር የሚደረገዉ ድርድር በታገዱት በሰላማዊ የቲ-ፒ-ኤል-ኤፍ አባላች ተሳታፊነት መካሄድ ሲገባ አሁን ግን አስራ-ስምነት ብቻ ስለቀሩ ባስራ ስምንቱ ብቻ 2/3ኛ ድምፅ ሳይኖራቸዉ ማለት ነዉ፡ በነሱ ብቻ የሚደረግ ድርድር ተቀባይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ድርድሩ ባስቸኳይ እንዲያቆም ነዉ።””(አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ)ካሉ በሗላ ትላለች አዳነች ፈስሃየ “የትግራይ ክፍል ሀገር ተወላጆችን ወክለዉ የተናገሩተር አቶ ሙሉጌታ በመቀጠል “የህወሓት ካድሬዎችና በተለይም የመከላከያ ሠራዊቱ አገሪቱን ከዚህ ቀዉስ በሰላም እንድትወጣ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸዉ ሳያሳስቡ አላለፉም። ሌሎቹም የኢሕአዴግ አባሎች ያስታራቂነት ሚና እንዲጫወቱ የትግራይ ተወላጆች መጠየቃቸዉ ገልፀዋል።””
አሜሪካ የኢንዲያና ክፍለሃገር አቶ ሃይለማርያም አበበ ደግሞ ከ70 አባላት የሆኑ ኢትዮጵያዊያን አባላት ወክለዉ ተናግረዋል። አቶ ሃይለማርያም አበበ Ethiopian Commentator”የተባለ መጽሄት አዘጋጅ ሲሆኑ በሙያ “Micro Biologist” ናቸዉ። “በዚህ መጽሄት ዙርያ የተሰባሰቡት ሰዎች ባለሞያዎች ሲሆኑ ቡዱኑ የፖለቲካ ስብስብ አይደለም:ያለዉን ሁኔታ ኢንፎርመሺን ለሕዝቡ ለማሳወቅ ሲባል ብቻ የተደራጀ ነዉ”ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አበበ አስምረዉበታል። በዚህ ዙርያ በህወሓት የተፈጠረዉ ችግር የቡዱኑ ስሜት አንጸባርቀዋል።
“ባሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ የተፈጠረዉ ችግር የኛ ሜምበሮች ተሰባስበን አቋም ወስደናል። ይህም ምንድነዉ የነዚህ አስራሁለቱ በተመለከተ በእዉነቱ የእነ አቶ መለስ ዜናዊ ቡድን የህወሓትን ሕግ ጥሰዉ እንዳገድዋቸዉ ሙሉ በሙሉ እናምናለን። እንዲሁም እዚህ ያሉት የትግራይ ተወላጆች በሙሉ (በእነ አቶ መለስ የተወሰደዉ እርምጃ)መቶ በመቶ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እርምጃዉ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እኛም እናምናለን፡በዘህ ትልቅ፣ትልቅ ቁጣና ንዴት ተሰምቷቸዋል።ስለዚህ የተባረሩት ሰዎች ወደ ስራቸዉ ባስቸኳይ እንዲመለሱ በብዙ ከተሞች የሚኖሩ ትግራይ ተወላጆች ለአቶ መለስ ዜናዊ የቅሬታ ደብዳቤ አስተላልፈዋል፡ ለዚህ አስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም ። በጣም በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነዉ።””
አዳነች ፍስሃየ ትቀጥልና “አቶ ሃይለማርያም አበበ አያይዘዉም “በህወሓት ሕግ መሰረት የትግራይ ምክር ቤት መሰብሰብ የሚችለዉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገብሩ አስራት ናቸዉ::አሁን ግን የትግራይ ምክርቤት ባቶ መለስ ተጽዕኖ ራሱ ስበሰባ ጠርቶ ፕረዚዳንቱን ማዉረዱ ራሱ ተገቢ አይደለም። ካሉ በሗላ “ዲሞክረሲን በመርገጥ ዲሞክራሲን ማምጣት አይቻልም”ብለዋል።..በመጨረሻም አቶ ሃይለማርያም “ዉጭ ያለን ኢትዮጵያዊያን አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች የሚል እምነት ስላለን ሕዝቡ ያልተበረዘና ተገቢ የሆነ ኢንፎርመሺን ለማግኘት የራዲዮ ስርጭት ለመክፈት እየተዘጋጀን ነዉ ብለዋል:”:ስትል የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የህወሓትን-መሰንጠቅ አስመልክቶ ከመቀሌ እና ከዉጭ የሚኖሩ የትግራይ ክፍልሃገር ተወላጆች የተጠናቀረዉን ዘገባ እላይ የተዘገበዉ ዓይነት ለነገብሩ የድጋፍና የደህንነት መቆርቆር ስሜት ለዛሬዉ የዓረና የፍቅር እርሾ መነሻዉ ያኔ ያስተላለፏቸዉ-ዉሳኔዎች እንደነበሩ ልብ ልንለዉ ይገባል። ድብቅም ይሁን ደብቅ ያልሆኑ የጎሰኝነቶች እንዋጋ!
ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com