Friday, March 13, 2015

መልስ ለምንሊክ ሳልሳዊ፤



መልስ ለምንሊክ ሳልሳዊ፤
ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ)
March 13, 2015

አማራዎች ብቻ ሳይሆኑ ሲጠቁ ዓይናችን ወደ ሌላ ያዞርነው፤ እነኚህ በፎቶው የሚታዩ የኢትዮጵያ መከታ ነብሮችና አንበሶችም በውስጥ አርበኞች እና ከሃዲዎች ሲጠቁ ፤ማዕረጋቸው፤ኒሻናቸውን እና መለዮአቸውን አፈር መሬት በረንዳ ላይ አንጥፈው ሲለምኑም “ከቁም ነገር አላየናቸውም” ነበር። በግልጽ አንነጋገር። የ24 አመት ድብብቆሽ ይቅር።የራሳችንን ደካማ ጎንም ሆነ ተንኰል አንዳይነሳ እየሸፋፋንን አንዲህ መቀጠል አይችልም።
ግልጽ ግለጹን!

 በእውነተኛ ስማቸው የማይጽፉ ወይንም ማንነታቸውን ለማሳወቅ ፎቶግራፋቸው የማያሳዩ ማን መሆናቸውን ለማሳወቅ ፈቃደኞች ያልሆኑ “ቦቁባቆች” “የድብቅ ስም” ተጠቅመው በድረገጽ ላይ ፖለቲካዊ/ማሕበራዊ ትችቶችን ሲለጥፉ በብዛት አይተናል። ከነዚህ አንደኛው “ሳልሳዊ ምንሊክ” እያለ በዘሐበሻ እና በመሳሰሉ ድረገጾች አንዳንድ ጽሑፎችን በማስነበብ የታወቀው ግለሰብ ነው። በቅረቡ በዘሐበሻ ድረገጽ ላይ ታጥቦ ጭቃ … !!!! ወያኔም የሚፈልገው ይህንን እኮ ነውበሚል  ርዕስ አማራን ከጥፋት ለመታደግ/ለመከላከል በአማራ ድርጅት መደራጀት “ወያኔነት/ናዚነት” ነው ሲል “አማራን ከጨርሶ ውድመት ለማዳን የተነሱ ኢትዮጵያዊያን አማራዎች እና ደጋፊዎቻቸውን “ያለ ምንም የመከራከያ ማስረጃ” ሳያቀርብ የውንጀላ ጽሑፍ አስነብቦናል።

ንዲህ ይላል፦

“ትላንትና የአንድነት ሃይል ነን ሁላችን ለኢትዮጵያችን ሲሉን የነበረ ስለኦሮሞ ሕዝብ መበደል አቤት ሲባል ኦሮሞ መሆኔን ወደ ኢትዮጵያዊ መሆኔ/ሰው መሆኔ ይቀየር ብለው የሰብዐዊነት ዘመቻዎችን በጥፊ ለማላጋት የተንደረደሩ ኦሮሞ አሊያም ሌላው ብሄር ሲጠራ ጀመሩ ዘረኝነት የሚሉ አተፍታፊዎች ኢትዮጵያ ብለው በስሟ የሚነግዱ ጥቂቶች ዛሬ ላይ አማራው ይደራጅ አሊያም ይገንጠል እያሉ ማራገባቸው የፖለቲካ ስትራቴጂ አይሉት የድል ግብ ምን ያህል ማንነታቸውን ገልጸው እንዳወጡ በይፋ አይተናል።” (ምንሊክ ሳልሳዊ፦ ከላይ በርዕስ የተጠቀሰ፤- በዘሐበሻ ድረገጽ የተለጠፈ)

ይህ ሰው ቧልተኛ ነው፤ወይንም በስሜት የሚጋልብ ጋላቢ ጽሑፍ ነው ተብሎ አንደዋዛ የሚታለፍ አይደለም። አማራ በሚሊዮን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ሲጠፋ፤ በበርካታ ሺዎቹ ከመንደራቸው ሲፈናቀሉ፤ የአማራ ህጻናት ታጉረው በር ተቆልፎባቸው በንዚን ተረጭቶባቸው አንዲቃጠሉ ሲደረግ፤ የአማራ ሕብረተሰብ ሆን ተብሎ በወባ እና በትራኮማ እንዲሰቃይ ሲደረግ፤ የአማራ የገጠር መሬቶች እና ከተማዎች ሰፋፊ የእርሻ ለም መሬቶችና ከጠላት ለመከላከያ የሚረዱ የተፈጥሮ ምሽጎችና ተራራዎች በዘመናዬቹ ብረት በታጠቁ ትግሬዎች ተነጥቆ ለትግሬ ሕዝብ ሲሰጥ፤ አማራ በየፖለቲካ መድረኩ፤በብሔራዊ ቴ/ቪዥን/በራዲዮን/በጋዜጣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቃላማም የአማራዎች እና “የሰንደቃላማውም ምስል ከክርስትያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ” (ዘረኛው የወያኔው አሽከር የነበረው ፤አንቀጽ 39ኝ በወያኔ ቻርተር ሲጸድቅ ከመቀመጫዬ ተነስቼ እወለሉ ላይ ከጓዶቼ ጋር እንደ ውርንጭላ ስፈርጥ ስጮህ ስዘልል፤ስደሰት በሕይወቴ የመጀመሪያ የደስታዬ ቀን ነበረች ሲል የተናገረውን የነጋሶ ጊዳዳ ጌቶቹ አሜሪካኖቹ በቅርቡ የተነጋጋረውን ንግግር አድምጡ) አብሮ “ነፍጠኛ”፤ “ወራሪ”….እየተባለ ሲዘለፍ የቆጫቸው፤ ይባስ ብሎ የእስራል ዘረኞች አይሁዶች ወደ እስራል የተሸጡ (ሲያቀብጣቸው አይሁድ ነን የሚሉ) ፈላሻ ተብለው የሚታወቁ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታይ “ኢትዮጵያዊያን”ን ሴቶች አንዳይልዱ እና በአይሁዶቹ አገር ጥቁር ሕ  እንዳይራባ ወሊድን የሚያመክን መርዝ እየወጉ ወንጀል እንደፈጸሙባቸው ሁሉ ወያኔም  ምስኪኖቹ የአማራ ሴቶችን “መርዝ እየወጋ” የማምከን ዘመቻ ሲያካሂድባቸ፤ ያ ሁሉ  ጥቃት ለእዛ ለተበደለ ቆሞ የሚከራከልለት ላጣው ለአማራው ገበሬ ሕብረተሰብ መከላከል የሰብዐዊነት ዘመቻዎችን በጥፊ ለማላጋት” ነው ብለህ የምትለን ሰው እራስህ “ቧልት” መጫወት የታየህ” ወይንም “የአማራው ሕዝብ ሰቆቃ በውል ያልገባህ” ጮርቃ የፖለቲካ ተዋናይ ነህ ማለት ነው።  

በመቀጥልም አንዲህ ትላለህ፦

ኦሮሞ አሊያም ሌላው ብሄር ሲጠራ ጀመሩ ዘረኝነት የሚሉ አተፍታፊዎች ኢትዮጵያ ብለው በስሟ የሚነግዱ ጥቂቶች ዛሬ ላይ አማራው ይደራጅ አሊያም ይገንጠል እያሉ ማራገባቸው የፖለቲካ ስትራቴጂ አይሉት የድል ግብ ምን ያህል ማንነታቸውን ገልጸው እንዳወጡ በይፋ አይተናል።” (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ኦሮሞ አሊያም ሌላው ብሔር ሲጠራ ጀመሩ ዘረኝነት (ዘረኝነት ጀመሩ መባል ነበረበት አማርኛው ሲስተካከል) የሚሉ “አተፍታፊዎች”፤ ብሏል። “ኢትዮጵያ ብለው በስሟ የሚነግዱ” ሲልም ይወቅሳቸዋል። ወንድም ምንሊክ ሳልሳዊ ፤ ፖለቲካውን እያጣመምክ ያልተባለን አትጥቀስ። ኦሮሞ ሲባል “ዘረኝነት ጀመሩ” ያለ አሁን ለአማራ ሕብረተሰብ ለመከላከል የቆመ አርበኛ “የኦሮሞም ሆነ የማንም ነገድ ስም” ሲጣራ “ዘረኝነት ነው” ሲል የተደመጠ የለም። የተባለው “ኦነግ”፤ህወሓት”፤ኦብነግ የመሳሰሉ ተገንጣይ ቡድኖችን ነው ‘ዘረኝነት ጀመራቸው” ሲሉ መገንጠልን በመኰነን እያወገዙ ሲደመጡ የነበረው እንጂ፤ አንተ ለማምታታት ስትል “ኦሮሞ” ወይንም “የሌላ ብሔር ስም ሲጠራ” ባስቀመጥከው  የውንጀላ መልኩ ሲሰነዝሩ አልተደመጡም። ወንጀላህን አስተካክል። 

ይግረም ብሎ ደግሞ “አተፍታፊዎች” ብለሃል። “አተፍታፊ” እና “በኢትዮጵያ ስም የሚነግድ” ማን ነው?”  የአማራውን ስቃይ እየተከታተሉ የሚያሳውቁ፤ ጸረ አማራዎችን ወደ ፍርድ ለማቅረብ መረጃዎችን የሚሰበስቡ፤ አማራውን በቃኝ በል! ንቃ፤ ተደራጅ ታጠቅ፤ እራስክን ተከላከል፤ ብለው አማራውን ከኦነግ፤ከወያኔ፤ከሻዕቢያ እና የመሳሰሉ ሃይላት እየሰነዘሩበት ካለው ጥቃት የሚከላከሉ ወገኖች ናቸው “በስሟ የሚነግዱ እና አተፍታፊዎች” በማለት የምትወነጅላቸው ወይስ ማንነትክን ሸሽገህ በምትለቀልቀው “ክቡር ሳልሳዊ ምንሊክ” አንተው? 

ወንድም ምንሊክ ሳልሳዊ (በምንሊክ ስም ባትነግድ ምንኛ ባማረ ነበር)! ላንተ አልታይ ያለህን የአማራው ጥቃት፤ ከአድማስ ባሻገር ወዲያ ተሻግሮ የአፍሪካ ጋዜጠኞችን ዓይን እና ቀልብን ስቦ “ኪፕ ኢት ሪል” በሚባለው የሰሓራ ቲቪ ክፍለ ጊዜ ሽፋን ተሰጥቶት ዋና አዘጋጅዋ ናይጄሪያዊት ወጣቷ ወ/ሮ አዲዮላ እንኳ ጉዳዩ ክፉኛ ስላሳሰባት “አማራን ከጥቃት ተከላከሉለት” ብላ ለዓለም ሕዝብ ተደረገው ወንጀል ለመግለጽ ያሳየቺው ሰብአዊነትንስ “ሰብአዊነት ዘመቻ በጥፊ ማላጋት ነው” ብለህ ኢትዮጵያዊ አማራ ድርጅቶችን አንደወነጀልካቸው ሁሉ እሷም “ሰብአዊነትን በጥፊ አላግታወለች” ልትለን ይሆን? ወይንሰ ፤ “በኢትዮጵያ ስም የምትነግድ”፤“አተፍታፊ” ትላት ይሆን?
 
አቶ ምንሊክ ሳልሳዊ፤ ከላይ የተመለከተው ርዕስ ይነበብሃል? ምንድ ነው ሚነበበው? “Ethnic cleansing of Amhara in Ethiopia” በአማራ ነገድ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ” ይላል። መጀመሪያ መቀመጫዬ ትላለች ዝንጀሮ፤ መቀመጫዋ ላይ የተሰካው እሾህ መቆም መቀመጥ ስላሳጣት። አማራው መጀመሪያ ህልውናውን ሳያረጋግጥ ስለ ሰለጠነው ፖለቲካዊ ዲሞክራሲያችሁ እና “የሚያውቀው እና ግንባር ቀደም አስታባባሪ ሆኖ ለዘመናት የኖረበትን አንድነት” መፈክራችሁ  ከምታወሩለት በአማራ  እግር ውስጥ የተሰካው እሾህ መጀመሪያ መንቀል መቻል አለባችሁ። እናንተ እሾሁን መንቀስ ካልቻላችሁ፤ ጥቂት አርበኞች እሾሁን ከተሰካበት እግሮቹ ሁሉ እያመላከቱ ወረጦአቸውን ይዘው ለመንቀል ሲጥሩ በኢትዮጵያ ስም የሚነግዱ” ብላችሁ ለወያኔ የተሰጠውን ስም “በአማራዎች ላይ” ማላከክ ጅልነት ወይንም የወንጀሉ ድርጊት ተባባሪ መሆን ነው።   
     
“እንደገና ማራገባቸው የፖለቲካ ስትራቴጂ አይሉት የድል ግብ ምን ያህል ማንነታቸውን ገልጸው እንዳወጡ በይፋ አይተናል።” 

ብለሃል። 

ስተራተጂያቸው አማራውን እራሱን ለመከላከል እንዲችል “ማንቃት፤ማደራጀት ብሎም ከተቻለ ማስታጠቅ ነው።” ግቡም በጣም ቀላል እና ግልጽ ነው። ግቡ፤- በግራም በቀኝም ከብበው መውጫ መግቢያ ከሚያስችግሩት ጠላቶቹ እና ፤ አንዲሁም እንዳንተው ያሉ ውዥምብራም  ልጆቹ (አማራ ከሆንክ) እመሃል ላይ ቆመው ከሚያደናግሩት እና እንዲሁም ከጠላት ጋር ሆነው የወገኑ አማራዎች ለሚያደርሱባቸው ጥቃትና ከበባ ላንዴ እና ለመጨረሻ ለማስቆም ነው “ግቡ”። ስተራተጂውንም ግቡንም ይኼው ነው። ተደራጅ፤ ንቃ፤ ታጠቅ እራስክን ከአጥቂዎች ጠብቅ ማለት “ማንነታቸው” ግልጽ ያደረጉን ወገኖች  አንደ “ወንጀለኞች” እና “ድብቅ አጀንዳ” እንዳላቸው ራስክን አታልለህ ሌላውን ለማደናቀፍ የምትከጅል “የቀን ብርሃን እንቅፋት” እራስክን ከመንገዱ ዞር በልላቸው። እንቅፋት ለእንቅፋቱ የሌሎቹ እንቅፋት መታገሉ ይበቃቸዋል።

ዐማራዉን ማደራጀት ለምን አስፈለገ?  ብለህ ለምትጠይቅ ኢትዮጵያዊ ሆይ!

የአማራውን ጥቃት ሕዝባችን እና ዓለም በግልጽ አንዳይነጋገርበት ከለየለት ወያኔ እና ኦነግ ይልቅ፤ ድብብቆሽ እየተጫወቱ ተጨማሪ ጥቃት የሚያደርሱ ተማጻዳቂ ከአማራ አብራክ የወጡ አማራዎች ናቸው። አብዛኛዎቹ ምሁራን አማረዎች አነሱ ናቸው የባሰውን የወላጆቻቸው እና የዘመዶቻቸውን አማራውን ሕዝብ ሶቆቃ አንዳይደመጥ አጉል ፖለቲካ እያሰራጩ እንቅፋት ሆነው ያሉት።  በግልጽ እንነጋገር!!! 

“የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት“ ብሎ በኦሮሞነቱ ተመክቶ፤ ወያኔን ጎን ለመወሸቅ እንዲመቸው ንግሊዝ አገር ሆኖ፤ ወያኔዎች እጅ መስጪያ የጻፈው ለትውልድ የሚተርፍ ዘረኛና መርዘኛ መጽሐፍ ጸሐፊ፤ የኢሳያስ አፈቀላጤ “አንዳርጋቸው ጽጌ” እስካሁን ድረስ ወያኔዎች ያልጨከኑለት፤ ከወዳጆቹ ከወያኔዎች እሰር ቤት ሆኖ ፡ለማንም እስረኛ ያልተደረገ (እጅግ አስገራሚ) ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን ስልክ ደውሎ ልጆቹ እና ሚሰቱን ለማነጋገር የተፈቀደለት “አንዲ ጽጌ” ውይ!!!! ይ!!!! ዋይ!!!ዋይ!!! ተብሎ ሲለቀስለት” በሚሊዮን ለጠፋ አማራ ግን አታልቅሱለት ይሉናል ሱልጡ ዲሞክራት ተቃዋሚዎቻችን።

የመላ አማራ ድርጅት መስራች” የነበሩት የቀዶ ጥገና ከፍተኛ ሓኪም አስራት ወልደየስንም አማራውን እንታደግ ብለው “የአማራ ድርጅት“ በመመስረታቸው ምክንያት “አተፍታፊ”፤ “በኢትዮጵያ ስም የሚነግዱ” ካላልካቸው በስተቀር፤ ሃኪም አስራት የተከተሉት ስታረቴጂ/ዘዴ እና ግብ ፤አሁን “በሞረሽ አማራ ድርጅት” ብለው የተደራጁ ወገኖች ጥያቄውን የሚመልሱት ሐኪም አስራት በቀየሱት ግብ እና ዘዴ ነው እየተጓዙት ያሉት።

አስራትን የምታሞግስ ከሆንክ፤ አሁን በሞረሽ የተደራጁትም ተልእኮአቸው ሓኪሙ የተነሱበት ዐለማ እና ግብ ነው፤ በመቀጠል ላይ ያለው። በወያኔ/በዘመኑ አማርኛ “አንድ እና አንድ ነው” ሳይሆን "አንድ እና አንድ ሲደመር “ሁለት” ነው። ግባቸው ሁለት ነው። አማራን ከጨርሶ ጥፋት ለመከላከል ማንቃት፤ማደራጀት ከተቻለም ማስታጠቅ እና ኢትዮጵያን በተደላደለ መደላድል በሰላም እንድትኖር ስታረተጂው እና ግባቸው ያ ነበር፤ አሁንም ያው ነው።

የሐኪም አስራት ፈለግ የተከተሉት ዛሬ አንተ “አተፍታፊዎች እና በስሟ የሚነግዱ” የምትላቸው ለመደራጀት ምክንያት የሆናቸው የሚከተሉት የፕሮፌሰር አስራት ፈለግ ነው ብዬ አሁንም ላንተ እና ግራ ለተጋቡ ሰዎች እደግምልሃለሁ። እኔ የሞረሽ አባል አይደለሁም፤ ነገር ግን ሞረሾች እያደረጉት ያሉትን አማራን ከጠላት የመከላከል ሙከራ ሐኪሙ አማራው መደራጀት አንዳለበት የቀየሱትን ግብ መከተላቸው እጅግ ደስ ብሎኛል። 

የጋዜጠኞች፤የወይዘሪት ብርትካን የአቡበከር የወዘተ….የወዘተርፈ… እስረኞች ስም እና ስቃይ ብቻ ነጋ ጠባ እያነሳችሁ፤ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! ስትሉ ለ24 ዓመት የዘለቃችሁ የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ ደብቃችሁ የተጓዛችሁ ወገኖች አንጀቴን እንዳሳረራችሁኝ ሁሉ፤ “ሞረሾች” ስጠብቀው የነበረውን መብራት እጨለማው ላይ “ቦግ”  አድርገው ማብራተቻው እጅግ ደስ ብሎኛል። ለእነ ሳልሳዊዎች ደግሞ የመብራቱ ደማቃነት እና ሃያልነት ካስበረገጋቸው “የበረገገው ዓይነ ሕሊናቸው” እንዲጠገን “ሓኪሞችን” ማማከር ነው።

ለመሆኑ የአማራ ጥቃት ዛሬስ ቢሆን ቆሟል ወይስ ብሷል? ካልቆመ እና ከባሰበት ለምን የሐኪም አስራት ወልደየስን ፈለግ መከተል አስፈለገ?  አንተ አንደምትለው ትላንት የአንድነት ሃይል ነን የሚሉ ግሳንግሶች ዛሬን ስለመገንጠል እና ስለ ጎሳዊ መደራጀት ሊሰብኩን ሲሞክሩ ምሞከራቸው ጤነኝነታቸውን እንድንጥራጠር አድርጎናል።” ስትል አማራውን ከጥፋት ለማዳን መደራጀት “ጤንነታቸውን እንድትጠራጠር” ያደረገህ ሁኔታቸው ምንድ ነው? “መገንጠልን ሰብከዋል” የምትለውስ አንዲት ብጣሽ መግለጫ ሰነድስ ማቅረብ ትችላልህ? አትችልም! አሁን እኔ የምከራከርህ ፤ገንኖ ስሙ የታወቀው “ሞረሽ” ተብሎ በአቶ ተክሌ የሻው እና ብዙ እኔ የማውቃቸው ከኔ እና ካንተ በላይ አርበኞች/አገር ወዳዶች ያሉበትን ድርጅትን ነው። አንተ ስለ ጤንነታቸው የምትጠራጠርበት ወይንም መገንጠልን የሰበኩበትን መረጃ አቅርብ። ይህ ስም የማጥፋት ዘመቻ ከጀመረ ጥቂት አመታት ቢያልፈውም፤ ከኣምና ጀምሮ በተከታታይ ተጧጥፋል። የሚጮኹት ደግሞ እራሳቸውን መፈተሽ ያቃታቸው የሕሊና እውሮች ናቸው። በሚሊዮን እና በሺዎች የተጃጃሉ ተከታዮች ማፍራት እና ጥቂት እና ጥራት የተሞላበት አባል ይዞ ግቡን ለማድረስ መነሳት የተለያየ ነው። ናዚም፤፤ሻዕቢያም (ያውም ኢትዮጵያዊያን ጀሌዎችም በድሮ ጊዜም ሆነ በዚህ አመት በቅርቡ ሳይቀር ጀሌዎችን ያፈራ ድረጅት ነው) ወያኔም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች አፍርተዋል። ቁም ነገሩ ግን፤ ውሎ አድሮ የሃቅ ምርኩዝ ስላልተመረኰዙ ፤ዘንጋቸው ሲሰበር እና ሲጐብጥ አይተናል። እያየንም ነው።  

ሐኪሙ ለምን አማራው መደራጀት አንዳለበት አጥብቀው ፈለጉ? ጥቃቱስ ዛሬ ቆሟል ወይስ ብሷል? ካልቆመ እና ከባሰበት ለምን የሐኪሙን ፈለግ መከተል አስፈላጊ ሆነ? አሁንም ጥያቄው አንዲገባህ እደግመዋለሁ። ሓኪሙ በ1984 ዓ.ም መላው አማራ ድርጅት ሊመሰርቱ ምን አሰገደዳቸው? አንተ አንደምታወራው አማራን ለማስገንጠል ነበር?  እንወያይ አንጂ!  

ወያኔ እንደገባ አማራን እንወክላለን ብለው በወያኔ የተቀጠሩ አሽከሮቹን መልምሎ በታምራት ላይኔ እና በመሳሰሉ ወራዳ ግለሰቦች መሪነት ወደ ኤርትራ በመጓዝ ለመላ የባሕር ነጋሽ ሕዝብ “እኛ የቅኝ ግዛት ገዢአችሁ የነበርነው አማራዎች፤ ብዙ መከራ አድርሰንባችሗል ። ያ ጥፋት አማራውን ውክለን እዚህ ድረስ ተጉዘን ይቅርታ አንድንጠይቅ የአማራ ሕዝብ ወክሎ ስለላከን፤ በማራ ሕዝብ ስም ይቅርታ እንድታደርጉል እንጠይቃለን” ብሎ በአማራ ሕዝብ ሲነገድ “ሐኪሙ” እኛ እነዚህ ሰዎች አልወከልንም፤ አማራም የባሕረ ነጋሽ ሕዝብ በቅኝ አልያዝንም ፤ የአማራ ሕዝብ በባሕር ነጋሽ ሕዝብ ላይ ያደረሰው በደል የለም፤ ሲሉ የአማራውን ሕዝብ ወክሎናል ያሉ ቀጣፊ አስመሳዮችን አጋልጠዋል። ይህ ደግሞ ሌላው ጎሳ ዝም በማለቱ፤ እሳቸው አማራ ሆነው በስማቸው ስለተነገደ ቆጭቷቸው አማራውን ማደራጀት እና በስሙ ከሚነግዱበት አጭበርባሪዎች እና ውሸታሞች፤ እራሱ መከላከል እንዲችል የመደራጀት፤ የመንቃት አስፈላጊነት አስምረውበት በ1984 ዓ.ም ወደ አማራ ድርጅት ምስረታ ገቡ። እነ ታምራት እና ወያኔዎች እንዲሁም “ኦነጎች” ወደ “መረብ ምላሽ” ሕዘብ ሄደው በአስጸያፊ ንግግር በማድረግ ብቻ አልተወሰኑም።

 የሚከተለውን እንመልከት:- ከዚያ በአማራ ላይ  የተከተለው ጥቃት ምን ነበር?
 
መለስ ዜናዊ እና በስሩ ተወሽቆ ለሥልጣን ቅልውጥ ልሃጩን ሲያዝረከርክ የነበረው “ኦነግ” አብረው አስመራ እና ከረን ከተሞች ሄደው ያስሰሙት የነበረው “አማራ ቀኝ ገዢ” የሚለው የጥላቻ መቀስቀሻ መፈክር ወደ ኦሮሞ እና ወደ መሳሰሉት ጎሳዎች እና መንደሮች በስፋት በመጓዝ ካድሬዎቻቸውን እና እራሳቸውም በየአዳራሹ ስብሰባ እየተገኙ ያንኑ “ነፍጠኛ፤ ቅኝ ገዢ” የሚለው የሐሰት መፈክር በማስተጋባታቸው፤በዛው አካባቢ ሲኖሩ በነበሩ አማራዎች ላይ “ተስፋፊ፤ ቅኝ ገዢ፤ነፍጠኛ…” በሚሉ የስድብ ቃላቶች አልፈው ፤ግድያ ዝርፍያና መፈናቀል በሓኪም አስራት ወልደየስ የተዘገበ በሐኪም አሰፋ ነጋሽ እና ጓደኞቹ ወደ እጭ አገር ለዓለም ሕዝብ ዓይን አንዲደርስ  የተሰራጨ  የአማራው እልቂት ዘገባ የሚገልጽ በበዴኖ፤ ግራዋ ኩርፋ ጨሌ፤ ላንገ፤ከርሳ፤ሶካ፤ደደር፤ሒርማ ፤ቁኑ፤መሰላ፤ ገላቲ፤ ዶባ፤ሓበሮ፤ ቦክ ፤በደሳ ገለምሳ  ሜንጫ አርሲ ነገሌ ወለጋ እና ሌሎች ቦታዎች… የደረሰው ግፍ ማንበብ ፤መዘከር የስፈልጋል።በነዚህ ቦታዎች ሴቶች ጡታቸው ፤ወንዶች ብልታቸው ተቆርጧል። ህጻናት፤ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥለው ተለያይተው እስከመቸውም እንዳይገናኙ ተደርጐ እንዲበተኑ ተደርጓል፤ ሽማግሌ፤ወጣቶት ሴቶች እና ወንዶች መኖሪያ ቤቶቻቸው ተቃጥሎ፤ ንብረታቸው ተዘርፈው በገፍ ከአካባበዊው እየተገፈተሩ ተባርረው በአማራዎች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል። ዛሬም በጉራ ፈርዳ በቤንሿንጉል፤በወልቃየት (ጞንደር)፤በወሎ…በአራቱ የአገሪቱ መዓዝን ሁሉ ጥቃቱ ቀጥሏል፡ ዜናው ትኩስ ነው፤ ቀይ መብራት በርቷል፤ ግን ማን ይቁም? ሁሉም እያየው እየጣሰው ያልፋል፤ ዳኛ የለም፤ ምሁር ተብየው እና ተቀዋሚው አማራ እና ሌላው ዜጋ አማራ እየተደፈጠጠተ ቀዩን መብራት እየተጣሰበት ኑሮው ቀጥላል። ለአማራው የበራው ቀይ መብራት ለሌቻችሁ አረንጓዴ ሆኖላችሗል። በግልጽ አንወያይ አንጂ! የምን ድብቅብቆሽ ፖለቲካ ነው የምታወሩት!  

ንተ መሳይ ግራ አጋቢ ውዥምብራሞች፤ በቅርቡ ከዚህ ዓለም የተለየው አውቁ ገጣሚ ገሞራው (ሃይሉ ገ/ዮሐንስ) የገጠመውን ግሩም ጥቅስ ወዳጄ ሐኪም አሰፋ ነጋሽ አንዲህ ሲል ይጠቅሳል፦

 "አንደበት ላጣ ሕዝብ ካልተናገሩለት፤
 ወንጀል አይሆንም ወይ ወገኑ ነኝ ማለት”

ይላል። ታዲያ አንደበት ላጣ አማራው ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍ የተፈጸመበት ይህ ሕብረተሰብ አንደበቱ ሆኖ መናገር (ያውም ከአማራ ልጆች የተወለዱ አማራዎች) አንዴት “ስብእናን በጥፊ መለጋት ነው” ተብሎ በአቶ ሳልሳዊ ምንሊክ ሊወሰድ ቻለ? ወይስ ሳልሳዊ ምነሊክ በኢትዮጵያ እየማሉ ሌላ ድብቅ አጀንዳ ካላቸው “ሳብቨሪሲቭ” በድን የተላከ? ካልሆነ እማ የሐኪም አስራት ወልደየስን አርማ እና ፈለግ አንስቶ በመከተል “ስለ አማራዎች መናገር፤መከላከል” ስብእናን በጥፊ መለጋት ነው’ ብሎ የሚል ጅል ወይንም የቀወሰ ዕብድ ብቻ መሆን አለበት። በወያኔ ፓርላማ ወያኔዎች ከገቡ ጀምሮ ለ24 አት ሲነገር ስሙ በመጥፎ ሲነሳ ፤ሲወቀስ ሲወገዝ፤ስለ አማራ ሕብረተሰብ በሚሊዮን ከምደረ ገጽ መፋት ሲነገር የነበረው “ሰንደቃማው እና አማራው ሕብረተሰብ ነው”። በግልጽ አንነጋገር!   
    
የሳልሰዊ ምንሊክ “ታጭቦ ጭቃ” ጽሑፍ በዛው እብደቱ አልተወሰነም። እንዲህ ይላል፡-

“በእምነቶች ዙሪያ የሚደረጉ ትግሎችን ውስጥ ውስጡን ለማክሰም ሲራወጡ ያየናቸው አዛኝ ቂቤ አንጓቾች ድፍርስ የፖለቲካ ባህሪያቸውን አደባባይ ላይ እያስነበቡን መሆኑ ለሽሙጥ ዳርጓቸዋል።”

ስለ አማራ መንገላታት ስለተናገርን ለሽሙጥ መዳረጋችን ፤ደንቆሮዎቹ እና የወንጀል ተባባሪዎቹ እኛ ወይስ “አሽሟጦቹ? አሽሟጭ ከማሽሟጠጥ ሌላ ለ24 አመት ለአማራው ምን ፈየደለት እና ነው ስለ አማራ ተነገረ ብሎ የሚያሽሟጥጠውእየተበደለ ባለው ሕዘብ ሕይወት ሟሽሟጠጡ ይብቃ ፤የምንለው እኰ “አሽሟጣጮች ስለበረከታችሁ ነው”።  በየገጠሩ እየተገፈተረ ከመኖሪያው እየተባረረ፤ አዳዲስ እመጫቶች ህጻን ይዘው ደም በማህጸናቸው እየተንጠባጠበ፤ በላብ ተጠምቀው በትኩሳት እየተሰቃዩ ባለበት የአራሥ እናትነት ወተታቸው እየፈሰሰ፤ ህጻን ልጆች ታቅፈው አንዳሉ ከአልጋቸው እየተጐተቱ ወደ ደጅ ሲጣሉ፤ አባወራዎች በሚስቶቻቸው ፊት ሲደበደቡ፤ሲገፈተሩ ማዘን ፤ ለነሱ መጮህ አንዴት “ድፍረስ ፖለቲካ፤ እንዴት አዛኝ ቅቤ አንጓች” ተብሎ ይፈረጃል/ሽሙጥ ውስጥ ይገባል? ስለ አማራ መጮህ ስብእና ሳይሆን ፖለቲካ ነው የሚሉ በጣም አደገኛ ዕብዶች የሰብአዊነት ምሰሶአቸው ዓይነቱ ምን ይሆን? አንደ ሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጅል ለተነጣጠረበት ማሕበረሰብ ተደራጅቶ መመከት በምን ታምር  “ትግሉን ውስጥ ውስጡን ለማክሰም” ተብሎ በሳልሳዊ ምንሊክ አንዴት ሊተረጐም ቻለ? ይህ የአገራችን ፖለቲካ ተቃወሚ ነኝ የሚል ተመጻዳቂ  ምን ቅጥ ያጣ ተቃዋሚ ሆነላችሁ እባካችሁ?

እገሌ ነው ብለን ማወቅ ያስቸገረን በፎቶም ሆነ በእውነተኛ ስሙ የማይታወቅ ሳልስአዊ ምኒልክ የሚባለው የዘሐበሻ ቋሚ ጸሐፊ በዚህ አላበቃም። 24 ዓመት ሙሉ በዘራቸው እየተጠቁ ላሉ አማራዎች ለስብእናቸው ዘብ መቆም “ከኢትዮጵያዊነት ያፈነገጠ” ትግል ነው ይለናል። እባካችሁ አትሳቁ! “እኔ ምንምን ምንም የጎሳ ዘር የለብኝም ፤እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፤ስለዚህም “ወደ አማራ ድርጅት ዝግጅት አልገባም ፤ችግሩን አላዳምጥም፤ ከሚሊዮበን የአማራ ስቃይ ያንዳርጋቸው መታሰር ያሰቃየኛል፤ አማራን ከጥቃት አንታደግልት ብለው የሚደራጁ ደግም ‘ኢትዮጵያዊነቴን መጻረር ማለት ነው” ብሎ አንዱ ታዋቂ ሰው አማራነት መደራጀት እንዴት አንዳየው ሃሳቡን በኢመይል አንደላከልኝ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ ልጅ ሳልሳዊ ምንሊክ እየደገመልን ያለው፤  
ያንን የተጃጃለው ቅኝት ነው።

ንዲህ ይላል፦

“መስመራችን ለአንዲት ኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ጥርጊያ እያበጀን እሾህ እና አሜኬላ እየነቀልን ወያኔን ከነግሳንግሱ በጋራ ተባብረል በአንድነት ሃይላችን እናስወግድ የጎሳ ፖለቲካ ከቅኝ ገዢዎች የተወረሰ የመከፋፈያ እና ሕዝቦችን የመርገጫ መሳሪያ ነው እያልን ባለንበት ሰአት እየተወያየን ለትግላችን በምንተባበርበት እና የዳበረ የሰለጠነ ሃሳብ በምናፈልቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ የወያኔን የጎሳ ፖለቲካ ልዩ መርዛዊነት ታከን ለመደራጀት ሲከፋም ለመገንተል ማሰባችን የምንሄድበት መንገድ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ከጭቃ ወደ እሾሃማ ሽቃ እያዘነበልል መሆኑን ልንረዳው ግድ ይላል::
 
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሚባሉ እነማን ናቸው? ኢትዮጵያ ማለት አገር ነው። ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በውስጧ የሚኖሩ ዜጐቿ ናቸው። ጥርጊያው የሚበጀው፤ አማራው ከምድረ ኢትዮጵያ እየተነቀለ ነው ጥርጊያው የሚበጀው? እሾህ እና አመኬላ 24 አመት በፊት በአማራ ሕብረተሰብ ጭንቅላት እና በተሰበረው የሕሊናው ሜዳ ላይ፤ እሾሁ እና አመኬላው መብቀል ሲጀምር ነበር ነቅሎ የሚጓዝበትን “ጥርጊያ” መበጀት የነበረበት? ወይስ የበቀለው አመኬላ እና እሾሕ ለ24 አመት ስድ ሆኖ ተለቅቆ፤ ፍሬ አፍርቶ፤ጫካ ሆኖ፤ ተንሰራፍቶ በእጅ ለመንቀል በሚያስቸግር ዕድገት ተንሰራፍቶ ባለበት ወቅት ነው? ለ24 አመት ምን ዓይነት ጥርጊያ ነበር ስትጠርጉ የባዘናችሁ? ምን እሚሉት “ርብርብ” ነው አንተ ተረባረብን የምትለው? ብትረባረብ ኖሮ አማራው በዚህ ሁኔታ በኖረ ነበር? ከ4 ሚሊዮን ሕዝብ አማራ ለልዩ ልዩ ጥፋት ተዳርጎ አንደተሰወረ ይነገራል! የት ሄደ ? በየትኛው የጠረጋችሁት የማዳኛ መሿለኪያ ጥርጊያ ነበር ሾልኮ እራሱን ከጥፋት ልታድኑት የስቻላችሁት? ምንድ ነው የዳበረ እና የሰለጠነ ሃሳብ የምትለው? የሰለጠነ ሃሳባችሁ 24 አመት ስልጠናውን አላጠናቀቀም? ፈትሽነው፤ጥርጊያችሁ እና መሿለኪያችሁ ለ24 አመት አየነው፤ዳሰስነው፤ፈተሽነው፤ “ሆኖም” አማራውን ከመጠቃት አላዳነውም።

አማራን ማዳን ያልቻለ አማራውን ማደራጀት ያልቻለ ፤መሰልጠን ያልቻለ ሃሳባችሁ በምን ሊዳብር ይቻለዋል? የአማራ እናቶች ልጆቻቸው ታቅፈው ለጅብ እራት ሲዳረጉ ነው የሰለጠነው ሃሳባችሁ መዳበር የሚችለው? አዛውንት በቪ ኦ ኤ፤ በጀርምን ራዲዮ አምባቸው እየተናነቀባቸው ደራሽ እና ነጋሪ ሲያጡ፤ የሰለጠነው ሃሳባችሁ ምን እያደረገ ነበር? አሁንስ የማን ቡሃቃ እያማሰለ ነው? ከዚህ ወዲያ እሾሃማ ጥርጊያ የት ሊኖር ይችላል? 24 አመት ሙሉ የአማራው ገበሬ እግር  አንዲጓዝበት ሆን ተብሎ የተነጠፈው እሾህና አሜኬላ እንዲጓዝ መደረጉም እያያችሁ “አማራ አይደለሁም ፤ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ምን ማለት ነው? አማራው ከተነጣጠረበት ጥቃት ተደራጅቶ ኢትዮጵያዊነቱን ማስከበር አይቻለውም የሚል ሕግ ጽፎ የሰጣችሁ የት እና ማን ነው?  ሴት በሴትነትዋ እና በዜግነቷ ሁለት ድርብ ትግል ማካሄድ አይቻላትም እያላችሁን እኮ ነው። አማራው እራሱን ከጥቃት እየተከላከለ አገሩን በተጓዳኝ ማዳን አንዴት አይቻለውም? ሁለት ጥቃት ደርሶበታል። ከገዛ አገሩ ወጣ እየተባለ ተባርሯል፤ አገሩን አጥቷታል።በራሱ እና በቤተሰቡ የዘር ማጥፋት ጥቃት ተፈጽሞበታል። ሁለቱንም በደሎች በመንታ ትግል መታገል አለበት። አማረውን ለመከላከል እራሱን ማንቃት፤ማደራጀት እና መታጠቅ ስልጡን አይደለም የምትሉት የናንተ ስልጡን ሃሳብ 24 አመት አማራውን ለማዳን ምን ሰራ? ናቲንግ/ናዳ/ “0”/ዚሮ/ዚፕ !!!

ንደገና ልጠይቃችሁ! “ለአንዲት ኢትዮጵያ መስመር መቀየስ ማለት የአማራን ጥቃት ለመከላከል አትደራጁ የሚል ሕግ ቀይሶ የፈቀደላችሁ ሕግ ከየት ነው ያመጣችሁት?” የሰለጠነው ጥርጊያችሁ ማን እንዲጓዝበት ነው 24 አመት እየጠበቀ ያለው? ጥርጊያችሁንስ ጠርጋችሁ የምታስመርቁትስ መቸ ነው?    
አንደውም እንዲህ ትላለህ እኮ:-

“ትላንት የአንድነት ሃይል ነን የሚሉ ግሳንግሶች ዛሬን ስለመገንጠል እና ስለ ጎሳዊ መደራጀት ሊሰብኩን ሲሞክሩ ምሞከራቸው ጤነኝነታቸውን እንድንጥራጠር አድርጎናል፡” ስትል አስነብበኸናል፦

ወይትጉዱ! አለ ትግሬ። አንባቢዎች ሆይ! አማራን ከጥቃት ለመከላከል የተነሱ ዜጎችን ደግሞ “ግሳንግሶች” እኮ ነው የሚላቸው። እሲኪ በሕዝብ ፊት ነው ይህ ሰው እየጠየቅኩት ያለሁት፤ “ ትናንት የአንድነት ሃይል ነን ሲሉ የነበሩ፤ ዛሬ ስለመገንጠል እና ስለጐሳ የሚሰብኩ የአንድነት ሃይል ነን ሲሉ የነበሩ፤ ዛሬ “አንድንትን” “ያወገዙ” የአማራ ነገድ ሰዎች “አቶ ምንሊክ ሳልሳዊ” ለማስረጃ እንዲጠቅስልን እጠይቀዋለሁ።

“ወያኔ የሚፈልገው እኮ የታገለለትም አላማ እኮ ይህ ነው።” ይላል።

“እዛ ዳዋ እተምጻኦ አለዋ”። ይላል ትግሬ። ይቺ ዳዋ (መርዛማ ቅጠል) የምታመጣው ነገር አለ እንደ ማለት ነው? ሰውዬው በጫካ ውስጥ ለውስጥ ሲጓዝ መርዘማዋ ቅጠል ድንገት እታፋ እግሩ ላይ ገረፍ አድርጋ ነካ ስታደርገው “ቆዳው” ከፉኛ ስላሳከከው፤ሳልነካት አንዴት ነክታ ቆዳየን አቃጠለቺው? አንደማለቱ ነው። ወያኔ እንዴት እና ከመቼው ወዲህ ነው “አማራን ለመከላከል” አላማው ያደረገው? ይህ የዳበረ እና ሥልጡኑው “ምንሊክ ሳልሳዊ” የሚናገረው ያውቃል? ወያኔ “የሚፈልገው” እንደ እነ ሳልሳዊ ምንሊክ የመሳሰሉ ግሳንግሶች (የራሱን ቃል ልጠቀም) አማራውን አትከላከሉለት፤ ብሎ እንደ ሥልጡን ሃሳብ ቀይሶ በሰለጠነውና በዳበረው ጥርጊያ የሚጓዝ እንጂ ወያኔ የሚፈልገው “ተደራጅታችሁ አማራውን ከጥቃት ተከላከሉለት” የሚል ዓላማ ከቶ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም። የወያኔ ዓላማ አማራውን ማጥፋት ነው። በሕገ ደምቡ በመነሻው ላይ ጽፎ ግልፅ አድረጎታል። በራዲዮን ቃለመጠይቅ በፓል ቶክ ሩም የተደመጠው “ኦርቶዶክስ እና አማራው አከርካሪው ሰብረናዋል” ብሎ ወያኔ ነግሮናል። ወያኔ የታገለለት አላማ ግልጽ ነው። “አማራ እንዳይደራጅ እና እራሱን መከላከል አንዳይችል ተንኮል መሸረብ ነው”!!!!!! ኢትዮጵያ እንጂ አማራ የሚባል የአማራን ጥቃት የሚከላከል ድርጅት አላውቅም የሚሉ እንደ ሳልሳዊ ምንሊክ በዘይት የተወለወለ በአንጸባራቂው በሰለጠነው ጥርጊያ የሚጓዙ ‘ተጓዞች” ሞልተዋል!!!! አማራው የሰለጠ ጥርጊያስ ይቅርበት ወደ ሞቃታዋ ደሳሳ ጐጆው የምትወስደውን ጉራንጉሯ መንገድ መተላለፊያው እንዳይተላለፍባት ተዘግታበተታለች: ። ትግሬ “አንዲህ ያለ ጉድ ሲያገኝ “መርዓስ ይቕረያዋ ዓዳ ትኽረም” ይላል፤ (ሰርግስ በቀረባት እቤቷ በከረመች) ይላሉ።  እኔ የምመመኘው ለእነ ሳልሳዊ ምንሊክ “ምሕረት የውርድ!” እላለሁ። “ምህረቱን ያውረድ!” ማለት ነው።  
  
ሳልሳዊ ምንሊክ በመጨረሻ እንዲህ ሲል ጽሑፉ ይደመድማል፡-

 የታገለለት ኣላማ ሆነ  ኢትዮጵያውያን በጋራ በአንድነት ተያይዘን የወያኔን አምባገነን ዘረኛ መንግስት እናስወግድ ብለን ከዳር እስከዳር እያስተባበርን እየቀሰቀስን ባለንበት ወቅት ላይ አደፍራሽ ሃሳቦችን በማራገብ የወያኔን የቤት ስራ ለመስራት መራወጥ ወንጀለኝነት እና የትግል አደፍራሽነት ቢሆንም የዚህ ሃሳብ ባለቤቶች ሩጫ ወንዝ እንዳማያሻግራቸው እና እንደማይሳካላቸው አስረግጠን ልንነግራቸው ይገባል::” ይላል።

ተያይዘን? ምን እሚሉት መያያዝ ነው? ተያይዞ የሚሄድ አማራ ከምደረገጽ ጠፍቷል እኰ ነው እያልናችሁ ያለነው።ልጅ ከወላጁ ሚሰት ከባለቤቷ ተለያይተው አንዲኖሩ በትነዋቸዋል እኮ ነው እያልን ያለነው። የተቀረው ደግሞ ለማጥፋት "ኦኖሌ ሃውል"ት ተገንብቶ የቀረውን አማራ ለማጥፋት ተንኰል እየተሸረበበት ነው እ ነው እያልን ያለነው። ስለዚህ ከማን ጋር ነው እጅ ለጅ ተያይዘህ ምትሄደው? እየጠፋ ካለው? እየተበተነ ካለው እረኛ ካጣው በግ እና ለጅብ እራት ሆኖ ተበትኖ የትም የተዘራውን ነው? ከየት ትለቅመዋለህ? መችስ ጊዜ ትለቅመዋለህ? አሁን ካልለቀምከው፤ካልሰበሰብከው፤ ከተቀሩት፤ ከጠፋ በሗላ፤ ከሌሎች ነገዶች ጋር አጅ ለጅ ተያይዘህ በሰለጠነው በዳበረው ጥርጊያህ ብትሽሞነሞን ለአማራው ምን ይረባዋል። ልቅሶወን በራዲዮ ታደምጣለህ? ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ ቀዳሚ ጠላቶች ኦነጐች እና ወያኔዎች እንደዚሁም አሽከሮቻቸው ተጠያቂ ሲሆኑ በሁለተኛ ተባባሪነት ደግሞ አማራው እንዳይደራጅ እራሱን ቆሞ ጠላቶቹን መክቶ ከሞት አንዳያመልጥ ለምትሸርቡ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች በሁለተኛ ደረጃ ተጠየቃዎች መሆናችሁ ልግልጽላችሁ እፈልጋለሁ። ከዛ ከተጠያቂነት ለማምለጥ፤ የጠፉት በጎች ለመፈለግ፤ የተቀሩትም ከተኩላዎች ለማከላከል ዋል እደር ሳይባል “አማራውን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!”
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com