Thursday, July 11, 2019

ስርዓተ አልባው “ታላቁ የመደመር ሴራ” እና ከአመታት በፊት በተቃወሚው ላይ የተነበይኳቸው ጥቅሶቼ እውን የሆኑትን ለማረጋጋጥ የጥቅሶቼ ክምችቶችን አንብቡ ጌታቸው ረዳ ((Editor Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)ስርዓተ አልባው “ታላቁ የመደመር ሴራ” እና ከአመታት በፊት በተቃወሚው ላይ የተነበይኳቸው ጥቅሶቼ  ውን የሆኑትን ለማረጋጋጥ የጥቅሶቼ ክምችቶችን አንብቡ
ጌታቸው ረዳ ((Editor Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)

ክፍል 2 ካለፈው የቀጠለ (ጌታቸው ረዳ ፌስ ቡክ ላይ የተለጠፈ)

ለጥያቄዎቻችሁ  ስ እና ከጥቂት አመታት በፊት የተነበይኳቸው ትንቢቶች፡

ባለፈው ትችቴ በለጠፍኩት ጽሑፍ ስለ ታማኝ የጠቀስኩት አንዳንድ የቆዩ ሂሶች አንብባችሁ ሰፋ አድርጌ እንድጠቅስላችሁ ስለጠየቃችሁኝጥቂቶቹ እነሆ።

ከዚህ ተያይዞ አብይ ከመምጣቱ በፊት ስለ ተቃዋሚ ተብየዎቹ (እንደ እነ ብርሃኑ ነጋም ሆነ እንደ እነ ኦነግ፤ጃዋር የመሳሰሉ የተቸሁትን እና አገር ውስጥ ተቃዋሚ የሚባለው ደደብ ተቃዋሚም የተቸሁዋቸው ትንቢቶች) አብሬ እጠቅሳለሁ።

ከጥቂት ቀናት በፊት በከፈትኩት የመጀመሪያየ “ፌስ-ቡክ” ከላይ ስለጠቀስኳቸው አያይዤ ስለ ግንቦት 7 ጀሌዎች እና ኢሳያስ አፈወርቂ’ አስመልክቶ የተቸሁትን ዝርዝር የጠየቃችሁ አሳያለሁ። ያንን ለመመለከት የደም መርገም ተካፋዮች” የሚለው ጉገል ብታደርጉ የተቸሁበትን ዝርዝሩን ታገኙታላችሁ።

ተያይዘው የሚታዩ ፎቶግራፎች፡
1)የወላጆቻቸው ሰቆቃ ተሰምቶአቸው ሰቆቃውን ለማስቆም የታጠቁ የአማራ ወጣቶች ፎቶግራፍ፡

(2) በጉሙዝ ውስጥ አማራዎች ተገድለው ስጋቸው ተበልቶ በተባለበት ዜና የተገኘው ፎቶግራፍ፤

(3) የግንቦት 7 ጀሌዎች ከኢሳያስ ጀሌዎች ጋር አንድነት በመፍጠርኢሳያስ ለፍረድ መቅረብ የለበትምበማለት የኤርትራ ሕዝብ የጭቆና ዘመን እንዲራዘም የድጋፍ ሰልፍ ሲያደርጉ ነው። ታቀውሞ ሲያስሰሙም የሻዕቢያ ሰንደቃላማ እያውለበለቡ የአገራችንን ሰንደቃላማ እንደ አልባሌ ጨርቅ አንጠልጥለው ድጋፍ ሰወጡ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ነው።

(በ4ኛው) ፎቶግራፍ የሚታዩት “ሻዕቢያ በአንድ ውድቅት /ቀን/ 2000 ኢትዮጵያዊያን ወታደራዊ ሙርኮኞች ከረሸናቸው አንዳንዶቹ  በዚህ ፎቶግራፍ ውስጥ  እንዳሉ የሚነገር።

ስለ ኢሕአፓ

ስለ ኢሕአፓ ደጋፊዎች (የአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች) ጉዳይ በፕራይቬት ስለጠየቃችሁኝ አንባቢዎች ባጭሩ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ‘አማራዎች” የደረሰባቸው የጻፍከውን አልሰማንም ለላችሁኝ አንባቢዎቼ መልሴ ባጭሩ ከ3 አመት በፊት የሆነው ጉዳይ  እንዲህ ነው። እነሆ፦

«በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል» በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ .የሰጠውን በሃቅና በተጨባጭ መረጃ የተደገፈውን ዘገባ፤ ኢሕአፓ ደጋፊዎችና ነባር ታጋዮች የሆኑ የአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ዘጋጀውን መግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ .በሬዲዮ ስያስተላልፍ፡ በጽሑፍ ደግሞ «አሲምባ» እና «ደብተራው» በተባሉ ድረገጾች በማሰራጨት እንዲህ ሲሉ ዘለፉን፡

እጠቅሳለሁ፤

«በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።» በማለት የተሰጠው መረጃው የቱን ያህል አስተማማኝ ነውሌላስ ሁለተኛ እና ሦስተኛ አካል መረጃውን እንዴት ማግኘት ይችላል?» ብሎ ሣይጠይቅ ነው በጉምዝ ሕዝብ ላይ ጸያፍ ዘመቻ አድርገዋል ሲሉ ሞረሽንም እኔንም ከአደጋው ሸሽተው ያመለጡትንም አማራዎች ጭምር የኰነኑን።

የጉምዝ ሕዝብ/ ቤንሻጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ፣ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው አደለም” ሲሉ ተመጻደቁብን። ምንጭ የአክብሮት ምስጋናየ ለኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትን ምርምር ዘርፍ ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) ከሚል የጻፍኩት” (1/7/2018)


(በ3ኛው) ፎቶግራፍ ልጀምር (ግንቦት 7)።

እነኚህ ከተያያዘው ፎቶግራፍ ሻዕቢያ አማራ ወታደሮችን እየለየ በከፋ መልኩ ስቃይ ያደረሰባቸውን ኢሳያስን ደግፈው የግንቦት 7 መርገምትሰንደቃላማችን ለጠላትዋ ባንዴራ አጋር እንድትቆም ራሳቸውን ለታሪክ ውረደት ከማጋለጥ አልፈው፤ ሰንደቃላምችንን እንደ አልባሌ ጨርቅ አዘቅዝው እያንጠለጠሉ፤ ኢሳያስ መታሰር የለበትም፤ ኢሳያስ ወንጀለኛ አይደለም፤ ኤርትራ ነፃ አገር ነች ኢሳያስ በኤርትራ ሕዝብ የተወደደ ነው፤  ሕዝቡ በኢሳያስ ደስተኛ ነው፤ ሕዝብ አልተገደለም፤ በየእስር ቤቱ እየታጎረ ድብደባ አልደረሰበትም፤ በወጣት ዘማች ሴቶች ላይ አመጾች አይፈጸሙም፤ ብዙዎቹ ኤርትራ ነን ብለው የተመዘገቡ ሰደተኞች ኢትዮጵያዊያን እንጂ ኤርትራኖች አይደሉም፤ የኩናማ፤ የዓፋር፤የሳሆ፤የከበሳ ሰዎች በኢሳያስ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ግድያ አልተፈጸመባቸውም፣ ኢሳያስ አሸባሪ አይደለም፤ ኢሳያስ ለአልሸባብ ደጋፍና ስልጠና አልሰጠም፤ ኢሳያስና ጓዶቹ ከንቅዘት ነፃ ናቸው!”  ብለው ባደባባይ ከሻዕቢያ ሎሌዎች ጋር መቆማቸው እንዲህ ያለ እጅግ አስገራሚ የሆነብን ዓይኑ ያፈጠጠ ባንዳነት ታይቶ ተስምቶ አይታወቅም  “ ብየ ነበር።

************************************************************************************************************************************

 በወቅቱ ግንቦት 7 ጀሌዎች እና መሪዎቻቸው “ስለ ኢሳያስ ጥብቅና መቆማቸው” ዳጋግሜ የተቃወምኩበት ምክንያት ፤ኢሳያስ ጸረ አማራ ማሕደሩ ስለማውቅ ነው። ማስረጃየን ላቅርብ። እንዲህ ብየ ነበር፦

   <<የድርጅቷ መሪዎች (ግንቦት 7) ጸረ አማራ ለመሆን የቻሉት ከጎኑ ከቆሙት ከኢሳያስ ሻዕቢያ ፖሊሲ የቀዱት ዘረኛነት ባሕሪ እንደሆነ መጠርጠር ይቻላል።   ምፅዋመጽሐፍ ደራሲመቶአለቃ ታደሰ ቴሌ” እንባ እየተናነቃቸው ከካሳሁን ሰቦቃ (አውስትርአሊያ ራዲዮ) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ኢሳያስ ጸረ አማራነት ተማርከው ያዩትን እንዲህ ይላሉ-

እንዲህ ይላሉ፤-

በተለይ ደግሞ የአማራ ብሔረሰብ የሆኑትን ለብቻ ለይተው ድንጋይ ፍንቀላና መንገድ ስራ ያሰሯቸዋል።አማረኛ ተናጋሪ ከሆንክ ለብቻ ያደርጉና እናንተ ናችሁ ለኤርትራ ጦርነት ምክንያት የሆናችሁ ይልዋቸዋል።ሁሉም ሰው አማራ ላይ ይበረታል ።አማራ ብሔረሰብ ሲመዘገብ “አማራ ነኝ” ብሎ ስለሚመዘገብ  አማራ የሚባለው ዘር ፋይል ለብቻ አለው። ፋይሉን ለብቻ አውጥተው ነበር የሚጠቀሙበት። በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ እጅግ በጣም የከረረ ፣አንድ ቃል በመናገሩ አንድ ጥይት የሚሰጡበት ሁኔታ ነው የነበረው።  ይላሉ “ዋ ምፅዋ!” መጽሐፍ ደራሲ ተማርከው ናቅፋ ላይ የታዘቡት ሁኔታ።ግንቦት 7 ግን ጸረ አማራ የሆነውን ኢሳያስን ደግፈው በተባበሩት መንግሥታት ጥብቅና ቆመው ነበር። ይህ ሃገራዊ ክሕደት ነው። ብየ ነበር። ምንጭ የደም መርገም ተካፋዮች” ጌታቸው ረዳ ( Ethio Semay አዘጋጅ የተገኘ- 7/3/2016)

“አዎ! ዛሬም ስለ የግንቦት7 የደም መርገምቶች/ባንዳዎች/ ደግምን ደጋግምን እንነጋገራለን። አሳዛኙ የሁለተኛው ዙር ገድል ጀምረነዋል (አንደኛው በወያኔ ዘመን ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር ድግሞ በግንቦት7/ ኦነግና በመሳሰሉ የውጭ ቅጥረኞችና ተገንጣዮች በአማራው እና በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለሚያቅዱት መጪው አፍራሽ ሚና ለመታገል የተያያዝነው ፊታችን ላይ ቆሞ ያለው መጪው ፈታኝ ገድል።) ሁለቱም ዙሮች እጅግ አሳዛኝ ክህደት የተሞሉበትና በውጭ ጠላቶች የሚታገዙና የሚተውኑበት/የተካፈሉበት ስለሆነ ትግላችን ረዢምና መራራ እንደሚሆን እርግጣነ ነኝ።” ምንጭ የደም መርገም ተካፋዮች ጌታቸው ረዳ ( Ethio Semay አዘጋጅ- 7/3/2016)

************************************************************************************************************************************

 


ስለ ታማኝ እንዳብራራለችሁ የጠየቃችሁኝ መልስ ይኼው።

እንዲህ ብየ ነበር፦

“አንደበት ላጣ አማራው ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍ የተፈጸመበት ይህ ሕብረተሰብልሳኑሆኖ መናገር (ያውም ከአማራ ልጆች የተወለዱ አማራዎች) ባስገራሚ ዘለፋ ተጠምደው ሞረሽን ሲዘልፉ ማየት ፈረንጆች "ስትረንጅ" የሚሉት "አዲስ ክስተት" ነው፤ ይህ ባሕሪ ካልቆመ ወደ ቀጣይ የቁርቁስ አዙሪት ውስጥ የሚጠመደን ይመስለኛል። ያውም ለአማራው መጮህ የተጀመረው እኮ ለጋምቤላ ለኦጋዴኖች ለኦሮሞች ከተጮኸ በኋላ ነው ዘግይቶ ከስንት አመት በኋላ ተቃዋሚው ስለ አማራው መጮህ (ዳበስ ዳበስ ማድረግ) የጀመረው! ማስረጃ ላቅርብ። (ትችቴ ለታማኝ በየነ - ከሚል ጽሑፍ ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay የተገኘ)

************************************************************************************************************************************

 


የአመቱ ከፍተኛ ሐዘናችን በሚል ርዕስ በጋምቤላ/ጉምዝ ውስጥ ስጋቸው በተበሉ  እነዚህ  አማራዎች ምክንያት የጻፍኩትን ለአንባቢ ላስታውስ፦

መስከረም 1/ 2008.ም።  የተወለድንባት ምድር ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ታይቶ ተስምቶ በማይታወቅ ብሔራዊ ሐዘን ውስጥ ተወጥራ በምትገኝበት በዚህ “አዲስ አመት” የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ  እንደወትሮው እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እንዳይል የአማራው ሕብረተሰብ በወያኔ ትግራይ መሪነትና ሥልጣኑን ለማቆየት በየቦታው
ባሰማራቸው ተባባሪ “የሰው ጅቦች” በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት/በጀነሳይድ ጥቃት ከመቸውም በተጠናከረ በስፋት በከፍተኛ ሂደት እየተስፋፋና እየተፈጸመ ነው። ስለሆነም አዲሱ አመት ብሔራዊ ሐዘን እንዲሆን “ይህ ጥቃት በቁጭት የሚሰማው” ዜጋ ሁሉ፤ በጥቃቱ የተጠቁትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ወጣት ገበሬዎች፤ እናቶች፤ህጻናትና አረጋዊያን አባቶች ነብስ ለመዘከር በየድግስ ቤቱ/ኮንሰርት የሚገኝ ወጣት ብሔራዊ ሰንደቃላማውን ዝቅ አድርጎ ሐዘኑን ለመግለጽ የደቂቃ ጸሎት በማድረግ እንዲያስባቸው ጥሪ አቀርባለሁ። ከፍተኛ ውርደትና ሐዘን የደረሰባቸው በሚሊዮኖች የሚጠቆጠሩ የአማራ ገበሬዎች በዚችው የመጀመሪያዋ ቀን በሐዘን ተኮማትረው ይገኛሉ።   ልጆቻቸው ተበታትነዋል፤ተገድለዋል፤ ምስቶቻቸው ተነጥቀዋል፤ 

ገሚሶቹም ታስረው እየተደበደቡ ሽንታም አማራ  ምን ታመጣለህ ተብለዋል። በቆጨራ ፤በጥይት፤ በቢላዋ ሰውነታቸው ተዘልዝሎ በየጫካው የተጣሉ አማራዎች ሬሳቸው የትም ወድቆ የቀባሪ ያለህ ይጮሃል። አማራው “ሽንታም አማራ” ተብሎ ተሰድቦ ተዋርዷልይህ ውርደት ያልተሰማው ምሁር ክፍል 
በተለይም የአማራው ምሁር፤ ውርደት ለምን እንዳልተሰማው ደግሜ ደጋግሜ ብጠይቅም፤ እስካሁን ድረስ መልስ ያልተገኘለት “ዝምታ” ሆኖ አግኝቼዋለሁ።(ምንጭ፡- መስከረም 1/2008 /የአመቱ ከፍተኛ ሐዘናችን ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)


***********************************************************************************************************************************


ባለፈው ሰሞን ዋሺንግተን ከተማ ውስጥ Tamagne Beyene’s speech at Gondar solidarity protest in Washington DC” https://youtu.be/ZLPCTKV5nHI በሚል ርዕስ በድረገፆች የተለጠፈውን ስዕለ ድምፅ/ አውድዮ ቪዲዮ/ ስመለከት አንድ ያስገረመኝ የታማኝ በየነ ንግግር አደመጥኩ።

እንዲህ ይላል፦

በአማራ ስም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በኦሮሞ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች፤ በሌ፤በሌላም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች በእውነት ይኼን ሕዝብ የምትውዱት እና የምትደክሙለት ከሆነ ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” ይላል አቶ ታማኝ። ተሰብሳቢውም በተለመደው ስሜት ጭብጨባውና ፏጨቱ አስተጋባው።

ታማኝ በየነ ለአገሩ ያለው ሁነኛ ፍቅር እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፖለቲካ ብስለቱና በንግግሩ ውስጥ የሚዘባርቃቸው ነገሮች የሰዎችን አመለካከት የሚያዛቡ ሆነው የታዘብኳቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። በዚህም ተደጋጋሚ በማስረጃ መተቸቴ ታስታውሳላችሁ። ከተቸኋቸው ትችቴ አንዱ በእስላሞች ስብሰባ ላይ ሄዶ የሰነዘረው ንግግሩ ነበር። በዚህምበሃይማኖትና በፖለቲካ የማሻኾር ባሕሪበሚል ተችቼዋለሁ። ዛሬ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው ስብሰባ ተገኝቶ፤

በአማራ ስም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በኦሮሞ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች፤ በሌ፤በሌላም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች በእውነት ይኼን ሕዝብ የምትውዱት እና የምትደክሙለት ከሆነ ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” ይላል። ምን ማለት ነው? ሁለት ነገሮችን ላስቀምጥ።

ወንድም አቶ ታማኝ አማራና ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎቹ የተደራጁበት ዓላማ አንድ አይደለም። (ምንጭ -መስከረም 1/2008 / ትችቴ ለታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay ከሚል ትችት የተገኘ)

************************************************************************************************************************************

 


 ታማኝ በየነ እንዲህ ይላል፦

"ትናንት የጋምቤላ ወንድሞቻችን በግፍ ሲረሸኑ፤ ትናንት ኦጋዴን ባውሮፕላን ሲደበደብ፤ ትናንት አዋሳ..ሁላችንም ጮኸናል። ዛሬ ሁላችን ለነዚህ ድሃ ኢትዮጵያዊያን መጮህ አለብን።" (ምንጭ-መስከረም 1/2008 /ታማኝ በየነ ከኢሳት መሳይ ጋር ያደረገው የስልክ ቃለ መጠይቅ ያገኘሁት)

************************************************************************************************************************************

 


ድሃ ኢትዮጵያዊያን" እያላቸው ያለው "አማራ" ለማት ነው። ታማኝአማራለማለት አልፈለገም ማለቴ ሳይሆን (ኋላ ደጋግሞ ብሎታል) ‘አማራየማለት ልምድ ስላልተለመደ "ድሃ አትዮጵያዊያን" ወደ ሚለው በብዙ ተቃዋሚ አንደበት የተለመደ የሽፋን ስም ነው።

************************************************************************************************************************************


የአማራው ሰቆቃ እየበረታ እኛ ጥቂቶቹ ስለ አማራ መጮህ እምባ መቆጣት ስንጀምር፦

ታማኝም ከኔው ጋር እንዲህ ሲል ይስማማል፡

"ዛሬ ማንኛውም ሰው ሲታሰር ወይንም ሲገደል የምንጨኸውን ያህል አማራ ሲሆን ግን፤ ሌሎቻቻን አማራ እንዳንባል እንሸሸዋለን ያንን ሃሳብ፤ ምክንያቱም ሁሉም የዘመተበት ስለሆነ አማራነትን እንደ ወንጀል አድርጎ የማት….ሕዝቡ ግን እንዲያውቀው የምፈልገው፤ ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ውስጥ ቢያንስ 20 እስከ 22 ሚሊዮን ያላነሰ ቁጥር ያለው ሕዝብ ነው። ይህንን ሕዝብ እንደጠላት ፈርጆ ወይንም እንደማይመለከተው አድርጎ ማየት "ኢትዮጵያ" ስለምትባለዋ አገር እያሰብን ነው ወይ? የሚለው የሚያጠያይቅ ይመስለኛል። ስለዚህ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቀውሶች ሲከሰቱ ድምጻቸው የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች እዚህ ነጥብ ላይ ዝም ማለታቸው፤ ለኔ አልገባኝም።" ታማኝ በየነ በሚከተለው ቪዲዮ ያድምጡ The Silent Genocide on the Amhara
https://youtu.be/z1qyhUOOW3s 

እዛው ቪዲዮ የተካተቱ የተፈናቀሉ አማራዎች ድምጽ ሰምታችሁ ልባችሁ እንዳይሰበር በተቻለ ዝግ ብላችሁ እየቻላችሁ አድምጡት። ይህ የአማራዎች አሳዛኝ ብሶት ስታደምጡ፤ ግራ የገባው ተቃዋሚው ስለሚሰብካችሁ "ዲሞክራሲ" ነው ወይስ ስለ እነዚህ ሰዎች ህይወትና አቤቱታ ቅድሚያ መስጠት ያለባችሁ?

(ምንጭመስከረም 1/2008 / ትችቴ ለታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)
************************************************************************************************************************************

 


“አማራዎች ለምን ተደራጁ? “በኢጎ/በደንቃራ ባሕሪያቸው” መነሻ  ነው? ምንድነው ጉዳያቸው?

መሬታችን ተነጥቆ ለትግሬዎች በመስጠት እህቶቻችን፤ ሚስቶቻችን፤ልጆቻችን፤በሚያመክን መርፌ እየተወጉ አማራ እንዳይራባ ወንጀል ተፈጽሞብናል። ማንም ሊደርስለን አልቻለም። ነው እያሉን ያሉት። ዓለምም ሆነ ምሁራን እንዲሁም ፖለቲከኞች “ጀሮ ዳባ” ያሉበትን የዘር ማጥፋት በኦሮሞ ድረጀቶች በወያኔ/ሻዕቢያ/ኦነግ/ኦፕዲኦ/ ወንጀል ተፈጽሞብናል ብለው ስለጮኹና ያንን ብሶታቸው የሚያስጋባላቸው ምሁር ስለታጣ ((አማራው በራሱ ልጆች ሳይቀር ኦሮሞዎችን ይቀርታ ይጠይቅ፤ የሚሉ አማራዎች እንደ “ዘላለም እሸቱ” የተባለው በዘሐበሻና ኢትዮ ሚዲያ የለጠፈውን አስታውሱ)  ዘመዶቻቸውና እና እራሳቸውንም መጠቃታቸውና በብዙ ጠላት መከበባቸው ያንገበገባቸው አማራዎች፤ ተሰባስበው ብሶታቸውን ለማስተጋባት ፤ትግላቸውን ፈር ላመስያዝ የተደራጁትን አመራዎች “በኢጎቲስቲክ/ሰልፍ ሰንተርድ”  መክሰስ “ጠባቦች” ብሎ መዝለፍ ሳያገናዝቡት ጸረ አማራ መሆን ነው፤ ወይንም ወንጀል ነው። (ምንጭ - ትችቴ ለታማኝ በየነ  -ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semayመስከረም 1/2008 /)

************************************************************************************************************************************


ስለዚህ “ታማኝ ምን አደረገህ? ብላችሁ በግል ስለጠየቃችሁኝ አንባቢዎች ማብራሪያ እንድሰጣችሁ ለጠየቃችሁኝ ጥቂቱ ይህንን ይመስላል። ስለ ታቃሚዎች የነበረኝ ስጋትም  አብይ የሚባል የኦሮሞዎች መንግሥት ጠ/ሚኒስትር ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት የነበረኝ ስጋት ለማሳየት የተነበይኩትን አስነብቤአቸዋለሁ። አሁን እየታየ ያለው ሌሎቹ ትንቢቶቼ አሁን እየታዩ ያሉት አስከፊ ክስተቶች የተነበይኩባቸው ትችቶች በስፋት እስክመለስበት ያልኩት ይህ ነበር:።

ከጻፍኳቸው ትንቢቶቼ እውን የሆኑት ልጥቀስ፡

ወያኔ ከወደቀ በላ ምን ዓይነት አሳዛኝ ክስተት ይታያል ካልኳቸው ጥቂት አመታት የተነበይኳቸው ትንቢቶቼ ጥቂቶቹን ላስታውሳችሁ።

በቡራዩና በለገጣፎ እና በመሳሰሉ ላይ ስለደረሰባቸው የዘር ማትፋት እና የቤት ማፍረስ ግፍ አንጀቴ ስለተቆጨ “አብይ አሕመድ” እኛን ዲያስፖራዎችን “እግዚሓር ይይላችሁ” እንዳለው ሁሉ እኔም “በማርች ወር” ማለትም ከ4 ወር በፊት “ትላልቅ የወያኔ ባለስልጣኖች ሃዘን እንደሚቀመጡ የኢትዮጵያ አምላክ ሓዘኑን ያወርድባቸዋል ብየ ነበር።

************************************************************************************************************************************

 


(ትንቢቶቼ) (1)
"ኢትዮጵያ አጆችዋን ወደ ፈጣሪዋ ዘርግታ የፋሺስቶቹ መሪመለስ ዜናዊንከፊታችን እንዳስወገደው አሁንም ኢትዮጵያ እጆችዋን በገለጣፎ የእናቶች እና የህጻናት እምባ በኩል እጆቿን ዘርግታለች እና እናንተም በተራችሁ እንምባችሁ ሲፈስ በቅርቡ እናያለን!! ባጭሩ መጥሪያችሁ ተዘጋጅቷል እና ወደ ሃያሉ ፈጣሪ ትጠራላችሁ ማለት ነው!! ይህ ትንበያ ከሃቅ የራቀ እንዳይመስላችሁ። ካሁን በፊት በመለስ ዜናዊ አድርገናል (አልጄሪስ ስምምነት በተመለከተ ካናዳ ሓዋሪያ ጋዜጣ የጻፍኩትን ትንበያ ተመለክቱ)  ትንበያ ዛሬም በናንተ ይደገማል! ምንጭ "የኦሮሞ ንጉሠ ነገሥቶቹ የአብይ አሕመድ እና የለማ መገርሳ አሽከሮች!  TUESDAY, MARCH 12, 2019 Getachew Reda ኢትዮ ሰማይ)

************************************************************************************************************************************

 


(2ኘው) ትንቢቴ፦

ለምሳሌ፤ ባለፈው የታየው ኦሮሞ ወጣቶች እንቅስቃሴ፤ ክልላዊ የነገድ ጥቅም አስከባሪ ከመሆን አልፎ፤ የመገንጠል ጥያቄን እና ባይተዋርነትን የሚያጎለብት “ኢትዮጵያዊ ግንዛቤ የሌለው” ሥር ነቀል የስርዓት ለውጥ የማያመጣ፤የአገሪቱን አስኳል አናግቶ “መሪ የሌለው ወደ አናርኮ ፋሺዝም” የሚያመራ፤ “ራእየ ቢስ” የተገንጣዬች አብዮት የበከለው እንደነበር ከሌሎቹ ሃያሲያን ተለይቼ መተቸቴ ይታወሳል። ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ብየ ነበር (ይህ ከስንት አመታት በፊት የጻፍኩት ነው)።

ከየወያኔ በሗላም አገር ሲገቡ ይታያል ብየ መስመራቸው ካልተለወጠ በእርግጠኛነት የምግመተው ችግር ያመጣሉ ብየ ነበር።

************************************************************************************************************************************

 


(3ኛ)
 ፓኪስታን/ ኤርትራ/ ሶማሊ/….የመሳሰሉ በጭቆና፤በወረበሎች፤ በነገድና በሃይማኖት ግጭት እየታመሱ በመዋለል፤ ለቀውስ የዳረጋቸው ምክንያት የዛው አካባቢ ምሁራኖች (ሃይማኖታዊ እና ዓለማዊ ምሁራኖች) “የነቀዘ ሕሊናቸውን” በሕዝቡ ላይ በማራባት ስራ ላይ በመዋሉ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም ጤነኞቹን ብቻ በማስጠጋት እነኚህን ከወንጀለኞቹ በመለየት የራሳቸው ባንዴራ ያውለበለቡ ‘ተገንጣዮች’ “በወንጀል የተጨማለቁና የተሳተፉ ነብሰገዳዮችና ጊዜው ያለፈበት ባንዴራን ሰርተው ሚያውለበልቡ የነቀዙ፤ እና የፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ድርጅቶች እንደ ኦነግ እና ኦብነግ የመሳሰሉትን” ወደ ጤነኛ ፖለቲካ ከመቀላቀላቸው በፊት፤ ጊዜአዊ የሆነ ‘ፖለቲካዊ እገዳ’ አካልተደረገላቸው፤ እጣ ፈንታው የነ ፓኪስታንና የነ ደቡብ ሱዳን “ግርግር” ትክክልኛ ቅጂ በአገራችንም ውስጥ ይደገማል።” ብየ ነበር። (ምንጭ (1)ኤፍሬም ማዴቦ ዛሬም ከአማራዎች ራስ መውረድ አልቻለም (2) ኦብነግ እና ግንቦት7 (ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ   5/19/17)

************************************************************************************************************************************ታገዱም አልታገዱም ወንጀል ስለሰሩ፤ ሓጢያታቸው ሲነገር “አሻፈረኝ’ ብለው ወደ ግርግር እንደሚሄዱ ርግጥ ስለሆነ፤ ቅድሚያ ዘው ብሎ ግምባር ፈጥሮ የፕሮፓጋንዳቸው መሰላል መሆን ከወዲሁ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው የፖለቲካ ብስለት ነው። (ምንጭ (1)ኤፍሬም ማዴቦ ዛሬም ከአማራዎች ራስ መውረድ አልቻለም (2) ኦብነግ እና ግንቦት7 (ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ )  5/19/17)

************************************************************************************************************************************

 

 አብዛኛዎቹ በወንጀል የተሳተፉ ናቸው። ነብስ ጠፍቶ ደግሞ ግርግር ፈርቶ፤ የተገዳዮችን ጩኸት መልሶ መቅበር፤ ተበዳዮቹ ነፍጥ እንደሚያነሱም ከወዲሁ ማወቅ ብልሕነት ነው። አማሮች ወደ መደራጀቱ እያመሩ ያሉትም ምክንያት ለወደፊቱ አቤቱታቸው በነ በርሃኑ ነጋ ዓይነቶቹ ‘አድርባዮች’ በሰላምና መረጋጋት ስም ለሥልጣን ሽሚያ በድፈን ድፍን እንዳይሸፈን ስለሰጉ ነው። ሁኔታው ሁሉ ወደ እዚያውም  እያመራ እንደሆነ ተከታዮቻቸው በጥንቃቄ ሊያዩት ይገባል። ቴምፐራሪ የ “ፊክስ/ጥገና/ “ጊዜያዊ ምርቃና እንጂ” ዘላቂ “ኢፎርያ”/ “እፎይታን” አያመጣም።” ብየ ነበር።  ከሁለት አመት በፊት የተነበይኩት ኢትንቢት ዛሬ በአብይ ዘመን እውን ሆኗል። (ምንጭ ጌታቸው ረዳ (Editor (1)ኤፍሬም ማዴቦ ዛሬም ከአማራዎች ራስ መውረድ አልቻለም(2) ኦብነግ እና ግንቦት7 (ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ )  5/19/17

ለጠየቃችሁኝ አንዳንዶቹን መልሻለሁ ።(አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ  ኢትዮጵያን ሰማይ  አዘጋጅ Ethiopian Semay )
_________________________________________________________________________________________________________________________________

";እንዲህ ያለ አገራዊ መሰረት ለማናጋት የተሰለፉ የውስጥም የውጭም ጠላቶች በጥንቃቄ ካልተከታተልካቸው፤ በቸለተኝነትና “ወያኔ” ብቻ ይውደቅ እንጂ የሚል “ጊዜያዊ ጥገና” temporary fixation የሁለት ክፍሎች ጥምረት ማለትም “የሰነፎች ወይንም ተንኮለኛ” ፖለቲከኞች የሚከተሉት ስልት ነው። አጃቢዎቻቸውም በዛው ግንዛቤ በጎደለው አስተሳሰብ እየተከተሉ መርህ አልባ ሆነው፤ ዳግም ለሌላ ዙር “ግርግር” ይጋለጣሉ። አሁን እየተጓዝን ያለበት ሁኔታ ያንን ያመላክታል። "ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"አስኳሉ ሲፈስስ፤ በተለይም የታጠቁ ክፍሎች ከሆኑ! የሚያመጡት ትርምስ ብዙ ነው። “ግድየለም” እየተባለ በቸልተኝነት በወዳጅነት እያየህ ቆይተህ፤ “ማአከሉ ሲናጋ”፤ የሚቆጣጠሩትም ሆነ ግርግር የሚፈጥሩት እነዚህ ክፍሎች ናቸው የምለውም ለዚህ ነው። የእገሌ ድርጅት መሪ ከታጠቁ ተግንጣዮች ጋር አብሮ እየሰራ ነው! እያመጣቸው ነው፤ ወደ መሃል እየጎተታቸው ነው፤ ጎበዝ ድረጅት ነው የሚል የሰነፎች ሙገሳ እየተቸረው፤ ተገንጣይንና በተለይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉትን ‘በወዳጅነት መመልከቱ” ባሕሪያቸውን አለማወቁ ከፍተኛ ጠንቅ እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በተለይ አማራው ሕብረተሰብተቃዋሚና ሚዲያዎቹ ከድተውሃል እናመከታአለኝ ብለህ ከውጭም ከውስጥም አትጠብቅ (ውጭ ጥቂት ልጆችህ አሉህ እነሱም እየታገሉዋቸው ነው) እራስህ ከአምላክህ ጋር ቆመህ  እራስክን ለመከላከል ሞክር፤ እግዚአብሔር መወጣጫው ይስጥህ! (Editor Ethiopian Semay) የተቃዋሚ ሚዲያዎችና ድርጅቶች ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ የተነሱትን የኦሮሞ ፋሺስቶችን እያገዙ ናቸው!ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay 1/29/16)"
-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
"በሚሊዮኖች አማራዎች ከምድረ ገጽ ተሰውረዋል፤ በአማራ ነገድነታችን በጥቃት ኢላማ ገብተናል! ይህ ተሎ ይቁም! ብለው ባሕር ዳር ውስጥ መጥቶ ሲጎበኛቸውአቤትላሉ አማራ ማሕበረሰብ ምሁራን እና ቀሳውስት የተጨቆናችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም አማራ ብቻ ተለይቶ አልተጨቆነም! ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ስትሉ ቆይታችሁ እንደገና ተመልሳችሁ አማራ አማራ” ወደ እሚለው ትሄዱ እና ታበላሹታላችሁ…” በማለት የአማራዎች አቤቱታ ሲያናንቅ አድምጠን እኔም ሆንኩ ሌሎች  ባጭር ጊዜ ውስጥ የሰውየው “ የአማራ ጥቃት የሚያይበት መነጽሩ የተበላሸ መሆኑንበመንቃታችን (የመጀመሪ ተቺው እኔ ነበርኩ)(ምንጭ  -የታጠቁ  እና ያልታጠቁ ቆሻሻ ፖለቲከኞች የፋሺስቶችን ሥርዓት በመንከባከብ ላይ ናቸው!  ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay 11/9/2018)"
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
;አሳዛኙ ኢትዮጵያ ትግል በነዚህ ተምበርካኪዎችና ባንዳዎች መኮላሸቱ በግልጽ እንድታውቁት ይሁን። 24 አመት የተጓዙት ጉዞ ትምህርት ካልሆናችሁ፤ እናንተም የአገራችሁ ቀብር አብራችሁ ቅበሩ፤ እኔና ጥቂት አርበኛ ጓዶቼ የነ ብርጋዴር ጄኔራል ተሾመ ተሰማ እና እልፍ ኣእላፍ አርበኞች በምፅዋ ወደብ እና በኤርትራ ተራራ ስር የወደቁ የአርበኞቻችን ኢትዮጵያዊያን አደራ ይዘን እስከ ህልፈተ ሞታችን ጠላቶቻቸውን በማጋለጥ ለታሪክ እየነገርን እናልፋለን። ሕሊናችን በቆመው ተራራ ላይ ቆመን ሰንደቃላማችንን እያውለበለብን በጽናት ቆመናል።አዲሱ ትውልድም ያንኑን አርማ ያነሳል። (Editor Ethiopian Semay)የተቃዋሚ ሚዲያዎችና ድርጅቶች ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ የተነሱትን የኦሮሞ ፋሺስቶችን እያገዙ ናቸው!ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay 1/29/16 "
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የሚሊዮኖች የሰው ሕይወት ግብር የተከፈለበት  ክቡር መሬት ህያው ይሆናል። ፋሺስታዊ ብሔረተኞች፤ ኢትዮጵያ ከመግደላችሁ በፊት እንደ መለስ ዜናዊበሳጥን ወስጥ ታሽጋችሁ ትሰናበታላችሁ የኢትዮጵያን ክፋትዋን ለማየት የወጠነ፤ ዕድሜው አጭር ነው። ይህ ደግሞ በመለስ ዜናዊ የታየ ታምራዊ የእናት ኢትዮጵያ ስራ ነው። በዚህ ታአምር የማታምኑ በማርክስና በሙሶሎኒ የማሾፍ መብታችሁ ተከብሯልና ማሾፍ ትችላላችሁ። ጌታቸው ረዳ (ምንጭ Editor Ethiopian Semay) የተቃዋሚ ሚዲያዎችና ድርጅቶች ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ የተነሱትን የኦሮሞ ፋሺስቶችን እያገዙ ናቸው!ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay -1/29/16"

------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"ከሳሽና ተከሳሽ በምትሰበስቧቸው አዳራሽ ውስጥ አብረው ዓይን ለዓይን እየተያዩ እያወቃችሁ፦ተጠያቂዎቹ በሞት እስኪለዩ ድረስ፦ዝምበሉ፡ በሞት ሲለዩ በሗላእሪታችሁን አስሰሙ ወይንምአሁን ስላለው ስርዓት ብቻ ጩዅወይንም እኛ የሰራነውን ወንጀልከጻፋችሁ/ከተናገራችሁሕብረት አይኖርም። የሚለው ንግግር እጅግ ያስገርመኛል። መቸ ነው የሕዝብ ዕምባ በሰፊው ለሕዝብ የመናገር መብት የሚከበር? ስልጣን ስትይዙ ደግሞ ዕርቀ ሰላም/ሪኮንስሊየሽን ላማምጣት ነው እና  ሕብረተሰቡ ሳናረጋጋአክራሪዎችእባካችሁ አትንጫጩዝምበሉ፤ እንደምንባል የታወቀ ነው። መፍትሄ ስጡን አንጂ! (ምንጭ ቅር ሳይላቸው የሚናደፉ መርዝ ፖለቲከኞች (ክፍል 1 ጌታቸው ረዳ(Ethiopian semay ድረገጽ አዘጋጅ  - Friday, January 22, 2016)"
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የሴቶች፤የነብሰጡሮች፤የሽማግሌዎች የህጻናት እሪታና ልቅሶ ድምጽማን ፈጠረው? በምን ዓይነት ስርዓት? እንዴት ተነሳ? ካሁን በፊት ማን ተካፈለበት? ተካፋዮችስ እንዲህ ያለ አሰቃቃ ድርጊት እንዳይደገምስ ምን እርምጃ ወሰዱ? ለምንስ ዝምታ ተመረጠ?  በወያኔ ብቻ ሳይሆን በኦነግ የተፈጸመ በደል የለም እያሉ ጋዜጠኞች የኦነግ መከታ እና ጠለላ እየሆኑ ነው። ይህ እኛም እናውቃለን። አስከመቸ ሳንነጋገርበት ይቀጥላል?”
(ምንጭ-  ሳይላቸው የሚናደፉ መርዝ ፖለቲከኞች (ክፍል 1) ጌታቸው ረዳ(Ethiopian semay ድረገጽ አዘጋጅ- Friday, January 22, 2016"

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"እንደ ሰደድ እሳት በሁሉምክፍሎችማለት ይቻላል የሚሰነዘሩት ንግግሮችባሁኑ ሰዓት ዋናው ጠላቴ ወያኔ ነውና ወያኔ መጀመሪያ እናውርድ፤የሌሎቹ ፖለቲካ ወያኔ ሲወርድ የምንመለከተው ይሆናልየሚል ነው። ይህ ግብዝ መስምር እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ያደረገውግንቦት 7” የተባለው ዱርዬና አታላይ ቡድን ነው። ግንቦት 7 ትምህርቱን የቀሰመው ለበርካታ አመታት ይህንን ማጃጃያ መስመር አጥብቆ ሲሰብከን ከነበረው ኦነጎች/OLF” ነው። ኦነግ ደግሞ ይህንንስልት/ታክቲክየቀሰመው ወያኔዎችነው። ሦስቱም ይህንን ስልት ሊጠቀሙት የቻሉት፤ወያኔ ስልጣን ለመንጠቅ መጀመሪያደርግንእንጣል ሲል ነበር፤ደርግ ጣለና ዋና ጠላት አድርጎ የፈረጃቸውድህነት፤ኦነግ፤ኦብነግ፤ግንቦት7፤ሻዕቢያ…” ናቸው። በሁለተኛ አስቀምጦአቸው የነበረው ክፍሎች ወደ አንደኛ ደረጃ ጠላት አድርጎ መድቦ እስካሁን ድረስ ስልጣኑ በሰላም መምራት አልቻለም። በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጦአቸው የነበሩት ክፍሎችየህልውናውተፈታታኝ ሆነው አግኝቶአቸዋል።አስገራሚ የሚያደረገው ደግሞወያኔ እነኚህ ክፍሎች (ኦነግ፤ ሻዕቢያና ኦብነግን) ፖለቲካቸውን በማስፋፋት ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግና፤ አልፎም ፕሮግራማቸው እንዲተገበር ቡዱኖቹ ከጠበቁት በላይ ረድቶአቸዋል።ዞሮው ህልውናውን ተፈታተኑት!!ግንቦት 7 የተባለው የተገንጣዮች አቀንቃኝ የሚመራው ኢሳት ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ ማጃጃያ መስመር በስፋት የሚያስተጋባ ነው። ድርጅቱ ጸረ አገር መሆኑንናአማራ ሆነውጸረ አማራ ግለሰቦች የሆኑ ያሉበት የተገንጣይ አደግዳጊ ሚዲያ መሆኑ ከጅምሩ የምናውቀው ነው።
(ምንጭ - (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"ታማኝ በየነ የተባለው የኢሳትና የግንቦት 7 “አራጋቢስለ ኦሮሞ ተማሪዎች የተናገረውን ስናስታውስ ከላይ የጠቀስኩት የግንዛቤ ቢስነቱን ያንጸባርቃል። ምንም ይሁን ምንም የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ የመገንጠል ነው ተብሎ  አንዳንዶቹ የመገንጠል እንቅስቃሴ ፍላጎት ነው ቢሉም፤የመገንጠል ጥያቄ ባልደግፈውም መብታቸው ነውና አከብርላቸዋለሁ ዲሞክራሲ ማለት የመብት ጥያቄ ነው":: ብሎናል;ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"ዲሞክራሲ፤ ከአገር አንድነትና ደህንነት ጋር ተያያዥነትና ወሳን ሚና እንዳለው የሚገልጹ ተቃዋሚዎች የተበራከቱበት አገር ቢኖርኢትዮጵያ ምድርውስጥ ብቻ ነው። ትምህርቱ ከየት አንዳገኙት አለውቅም። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16" --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
"ዲሞክራሲ ሞንስተሮች የሚከተሉት በእራሱ ሂደት በየጊዜው እያበጃጀ እንደገና እራሱን የሚያቃጥልና የሚጻረር፤ ብዙሃን በአናሳ ወይንም በግለሰቦች መብት ላይ አመጽ የሚያስነሳሞብ-ሩልየሚያሰፍን ስርዓት የመሆኑንም ጭምር አይነግሩንም። ያንን ይሸፍኑታል። አሜሪካን አይነትየባንክ ባለሃብቶችየሚቆጣጠሩትየኦሊጋርኪስርዓት በዲሞክራሲ የሚጎናጸፉበትን ስልጣን እና ቁማር ተመልከቱት። ዲሞክራሲ ነው። ዲሞክራሲ፤ እንኳን አገርን ለማቆየት፤ እራሱንም በተመሰረተበት ሕግ ለመቆየት ዋስትና የለውም። ማንም የታጠቀ ዱርዬ የሚጠልፈው፤ የሚፈርስ፤የሚተካ ነው።ለዚህም ክስተት ስንት ህይወት ተገብሮበታል።መጨረሻው ገዢና የበላይ አስተዳዳሪ የሚሆነውራስ በራስ ማስተዳዳር ሳይሆን”  “ጥቂቶችወደ ምቾት ዓለም አንደላቅቆ፤ ሌላ አዙሪት ውስጥ የሚያስገባ፤ በንትርክ የተከበበ ስርዓት ነው። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"እየታየ ያለው የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ክልላዊ የነገድ ጥቅም አስከባሪ ከመሆን አልፎ፤ የመገንጠል ጥያቄን እና ባይተዋርነትን የሚያጎለብት “ኢትዮጵያዊ ግንዛቤ የሌለው” ሥር ነቀል የስርዓት ለውጥ የማያመጣ፤የአገሪቱን አስኳል አናግቶ “መሪ የሌለው ወደ አናርኮ ፋሺዝም” የሚመራ፤ “ራእዬ ቢስ” የተገንጣዬች አብዮት ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


"ኪስታን/ኤርትራ/ሶማሊ/….የመሳሰሉ በጭቆና፤በወረበሎች፤ በነገድና በሃይማኖት ግጭት እየታመሱ በመዋለል፤ ለቀውስ የዳረጋቸው ምክንያት የዛው አካባቢ ምሁራኖች “የነቀዘ ሕሊና” ስራ ላይ በመዋሉ ነው።  ኢትዮጵያ ውስጥም “በወንጀል የተጨማለቁና የተሳተፉ ነብሰገዳዮችና ፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ድርጅቶች ስለሆኑ” እገዳ አካልተደረገላቸው፤ እጣ ፈንታው የነ ፓኪስታንና የነ ደቡብ ሱዳን “ግርግር” ትክክልኛ ቅጂ በአገራችንም ውስጥ ይደገማል። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16" -------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

"አስኳሉ ሲፈስስ፤ በተለይም የታጠቁ ክፍሎች ከሆኑ! የሚያመጡት ትርምስ ብዙ ነው። “ግድየለም” እየተባለ በቸልተኝነት በወዳጅነት እያየህ ቆይተህ፤ “ማአከሉ ሲናጋ”፤ የሚቆጣጠሩትም ሆነ ግርግር የሚፈጥሩት እነዚህ ክፍሎች ናቸው የምለውም ለዚህ ነው። የእገሌ ድርጅት መሪ ከታጠቁ ተግንጣዮች ጋር አብሮ እየሰራ ነው! እያመጣቸው ነው፤ ወደ መሃል እየጎተታቸው ነው፤ ጎበዝ ድረጅት ነው የሚል የሰነፎች ሙገሳ እየተቸረው፤ ተገንጣይንና በተለይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉትን ‘በወዳጅነት መመልከቱ” ባሕሪያቸውን አለማወቁ ከፍተኛ ጠንቅ እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል። ምንጭ (ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/7/16"

Thanks
Posted  today at Ethiopian Semay (August 2019)