Friday, October 9, 2020

የአእምሮ ስውር ቦታና ክሕደት (ዲናያል) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) October 09, 2020

 

የአእምሮ ስውር ቦታና ክሕደት (ዲናያል)

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

October 09, 2020

የአእምሮ ስውር ቦታ ፈረንጆች ሜንታል “ብላይንድ እሥፓት” የሚሉት ጭፍን ሥፍራ ነው። የዘረኝነት ባህሪን የሚያካሂዱ ሰዎች እራሳቸውን እንደ ዘረኛ የማያዩበት ምክንያት በዚህ ክፍል የሚከናወን የክሕደት ውሳኔ ነው። ሰዎች እኛ ዘንድ እንዲህ ያለ ዘረኝነት የለም፤ ዘረኛነት እኛ ጋር ቦታ የለውም ፤ ዘረኛነት እነ እገሌ ናቸው የሚለው ጭፍን ክሕደት የሚከራከሩበት ምክንያቱም ነገርየው በራሳቸው መንደር ሲከሰትና ወደ እራሳቸው ባህሪ ሲመጣ በመሠረቱ “የአእምሮ ስውር ቦታ” አላቸውና ሮጠው የሚወሸቁበት “የአእምሮ ስውር ቦታ በሚባለው የሕሊና ክፍል” ጋር ነው።

ብዙውን ጊዜ መኪና ነጂዎች ለጉዳት የሚዳረጉት ከጎን ግራ በኩል (በግራ በኩል ለሚነዱ አገሮች) ያለውን ለዕይታቸው በጣም ስውር ቦታ በመሆኑ መኪናው አጠገባቸው እያለፈ መሆኑን እንኳ ማየት ስለማያስችላቸው “ለአደጋ ይጋለጣሉ”።አንዳንድ ማሕበረሰዎች በማሕበረሰባቸው ውስጥ ሰላማዊ እንጂ ዘራፊ፤ ነብሰገዳይ፤ ዘረኛ፤ አመጸኛ የለንም የሚል ድምዳሜ ስለሚደርሱ በማሕበረሰቡ ውስጥ ቀስ በቀስ እየተፈለፈለ የሚያድገው ይህ ክፍል በማሕበረሰቡ ምሁራን ክሕደት ምክንያት ወደ አደገኛ ቡድን እና ወንጀለኛ ሆኖ የማደግ ዕደል የመከሰቱ ዕውነታ እውን ይሆናል። አንድ ነገር መከሰቱን ያለማመን በማሕበረሰቡም ሆነ በሌላው አጎራባች ማሕበረሰብ ላይ የከፋ አደጋ ያስከትላል። ኦሮሞ አክራሪዎች እየተበራከቱ ነው ፕሪ-ፕሮፓጋንዳቸውን ባጭር መዋጋት አለብን ብለን ስንል ሰፊው ኦሮሞ ቦታ አይሰጣቸውም “የትም አይደርስም” እየተባለ ይኼው አሁን ላለው ሁኔታ ደርሰናል። እንዲህ ያለውን ክርክር የገጠሙን ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው። አክራሪዎችን በድጋፍ ቆመው እኛ ሲሞግቱን ሲዘልፉን የነበሩት ብዙዎቹ አማራዎች ነበሩ። አማራ ወጣት ላይ እየታየ ያለው አክራሪነትም ዉሎ አድሮ ከጫጩትነት ወደ ዘንዶነት ማደጉ አይቀሬ ነው። ይህ የሚሆነው እኔ እየሞገቱኝ ያሉት ሰዎች “ወያኔ እንጂ አማራ በዚህ ስራ በፍጹም አይታለምም አይሳተፍም” የሚሉ የክሕደት ቁልቁለት የሚጓዙት ክፍሎች ናቸው።

 

በቅርቡ ባሕረዳር ከተማ በአክራሪ አማራዎች ትግሬዎች ውጡ የሚለው የተበተነው ወረቀት ሰብስበው የለቀሙት የመንግሥት ወታደሮች ናቸው፡ ይህንን በሚመለከት በለጠፍኩት አስተያት ላይ ብዙ አማራዎች ጣታቸውን የቀሰሩት “አማራ አክራሪ ክፍል የለውም” ፤ ምናልባት ተከስቶ ከሆነ “በወያኔዎች የተደረገ ሴራ ነው” ፤ ብለው ሲከራከሩ አንብቤአለሁ። አንዳንዶቹም እኛ አማራዎች ዘረኝነት አይነካንም ይልና መደምደሚያው ላይ “ቅማላም ትግሬ” እያሉ የትግሬ ጥላቻቸው በኔ ላይ ሲያዘንብ አይቻለሁ። ያ ጽሑፍ ሕዝቡ እንዲመለከተው በሚል አላነሳሁትም፤ አሁንም አለ። ይህ ሰው በዘረኝነት ባሕሪ የሚዋኝ መሆኑን ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የዘረኝነት ባህሪ የሚያጠቃቸው ሰዎች እራሳቸውን ማየት የማይችሉበት “የአእምሮ ስውር ቦታ” ላይ ስለሚገኙ ነው።

 

“የአእምሮ ስውር ቦታ” ባለው አጥር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በደረሰባቸው ተመሳሳይ የጥቃት ባህሪ ምክንያት ያንን ጥቃታቸው፤ውርደታቸውና የበታችነት ስሜትና ቁጭታቸውን ለመወጣት ሲሉ በራሳቸው ላይ የተፈጸመ ዘረኝነት በሌሎች ላይ እራሳቸው ሲደግሙት እናያለን። እስራኤሎች በፍልስጥኤም ህጻናትና አዛውንቶች ላይ፤ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ባፍሪካ ጥቁር ስደተኞች ላይ የሚያሳዩት የዘረኝት ነጸብራቅና ግፍ ፤ መነሻው በዘረኝት ተጠቅተው ስለነበር ያንኑ የደረሰባቸው የጥላቻ ግፋና ባሕሪ በሌሎች ላይ ሲወጡት ማየት እኔም አምንበታለሁ የሕሊና ተመራማሪዎችም የሚያምኑት እውነታ ነው።

 

አማራዎች እስካሁን ድረስ በዘረኝት እየተቀጠቀጡ ዘልቀውታል፤ መቋጫም አልተገኘለትም። አማራዎች እራሳቸው ሊያቆሙት አልተቻላቸውም፤ እው ነታው ይህ ነው። አማራ ሪፑብሊክ አገር አንመሰርታለን የሚሉ ወጣቶች አላየንም አልሰማንም የምትሉ አማራ ምሁራን ካለችሁ ያው እናንተም በዚያ ክሕደት ውስጥ መሆናችሁ የሳየኛል። እንዲህ ያለ ሕሊና የሚያንጸባርቁ አማራ ወጣቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጋር ለመኖር አንፈልግም ከሚል ከጥላች ሌላ ትርጉሙ ምንድን ሊሆን ይችላል? አንዲህ ያሉ አማራዎች ያበቀለች የአማራ ክልል “ከክልላችን ውጡ” የሚል ቅስቀሳ አያደርጉም ማለት ክሕደት ነው።

የአማራ ወጣት ያደገው መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቂ የሰጥዋቸውን ኤርትራን ያልጨመረች ቆራጣዋን የኢትዮጵያን የቆዳ ስፋት (ካርታ) አክብረው በየከናቲራቸው፤በፌስቡክ ገጻቸው፤በየቤታቸውና ሕዝባዊና ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ያንን ቆራጣ ካርታ ሲያከብሩ ይታያሉ፤ ያደጉበት ትምሕርት ሥርዓት “ወያኔና ፋሺሰታዊ ትምሕርቱን” ተቀብለው “ብሔር፤ብሔረሰብ ሕዝቦች” ሲሉ ይደመጣሉ፡ የኤርትራ ባንዴራ ሲያውለበልቡ አይተናል፡ ፋሺዝም ሲደግፉ አይተናል፤ ፋሺስቱን አብይ አሕመድ መሪያችን እያሉ ከናቲራቸው ላይ አሸብርቀውት ለብሰው በየፌስቡኩ የሚታዩ አማራ ወጣቶች አይተናል። ይህ ሁሉ ስንመለከት የአማራ ወጣት በዘረኛነት አልተበረዘም/አልተበከለም ፤ ዘረኛ ሊሆን አይችልም ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ወጣቶቻውን በቅጡ መፈተሽ ያልፈለጉ “በአእምሮ ስውር ቦታ”ውስጥ የመወሸቃቸው ማሳያ ነው። ባህርዳር ጎንደር፤ወሎ፤አዲስ አባባ፤ ባሌ፤ ወለጋ ጂማ ወዘተ… ሰላም ነው ..ወዘተ ምንም ዘረኛነት የለም ወዘተ… የሚሉ ሰዎች አንብቤአለሁ፤ አጠገባቸው ላይ እያንዣበበ ያለው ጥቁሩ ዳመና ያንን ማየት አልተቻላቸውም። የሚገርመው ነገር ከራሳቸው ውጭ በሌላ ሰው ሲፈፀሙ ሲያዩ እነዚያን ባህሪዎች በሌሎች እንጂ እነሱ ተሰታፊ እንዳልሆኑ ያምናሉ።ለዚህ ነው አእምሮ የአደጋ ስውር ቦታ መወሸቂያ ነው የምለውም ለዚህ ነው።

 

ወጣት አማራዎች ውስጥ ዘረኞች ወይንም ጸረ ትግሬነት ባሕሪ የላቸውም ብለው ተከራክረውኛል። በየ ፌስቡኩና ዩቱብ አማራዎች ራሳቸው በትግሬዎች እና በሌሎች የሚያንጸባርቁት ባሕሪ አቅርብ ብትሉኝ አቀርባለሁ። አማራ እንኳን “ ለቅማላም ትግሬ ለጋላም መጠለያ ሆነናል” ብሎ የጻፉልኝ አማራ አለ። አለ፤ ስትል አማራ መሆኑን እንዴት አወቅክ የሚል የሽፋን መከራከሪያ ያቀርባሉ። የዘረኝነት ባህሪን የሚከላከሉ ሰዎች እራሳቸውን የቻሉ ድብቅ ዘረኞች የመሆናቸውን ምልክት ነው። አጠቃላይ ድምደማቸው “አይደረግም” የሚል ድምዳሜ ይደርሳሉ። ምክንያቱም ወደ እራሳቸው ባህሪ ሲመጣ ጥሩ “የአእምሮ ስውር ቦታ” አላቸውና አድራጊው ሌላ እንጂ ከራሳቸው ወገን እንደማይከሰት እርግጣኖች ሆነው ይከራከራሉ። እስኪ አንድ ቪዲዮ እንድታዩት ልስጣችሁ-

ትግሬ ውሽማ እንጂ ባል አይሆንም https://youtu.be/duahOhloZP8

 

"ይጠመቃል በጋን ይጠጣል በዋንጫ እንዴት ነሽ ወልዲያ የትግሬዎች መቅጫ" . “ይጠመቃል በጋን ይጠጣል በዋንጫ እንዴት ነሽ ወልዲያ የትግሬዎች መቅጫ” ከሚለው ወሎየ ገጣሚው* በዚህ ዘረኛ ቅስቀሳ የተደሰተ አማራ ወጣት እንዲህ ይላል፤ “"አቤት ልቤን ነው ቂቤ ያጠጣልኝ*! ሲል የዘረኛነት ደስታውን ገልጿል። ለ29 አመት ኢትዮጵያ ወጣትና አማራ ወጣት ጭምር ከዚህ በሽታ ነፃ ነው ማለት በግብዝ ክሕደት መጓዝ ነው።

 

እንዲህ ያለውን የጥላቻ የፕሮፓጋንዳ እየቀዱ በየቱዩቡ ላይ የሚለጥፉት አማራ ወጣቶች አማራ ወጣት አልተበከለም የምትሉን ንጹሃኖች ይህ መልእክት ስንቱን ወጣት መበከል እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም። እንዲህ ያለ ነጸብራቅ የምን ውጤት ይመስላችሗል? የምሬት፤ የግፍ የመበደል ውጤት ነው ወይስ ይህ ቪዲዮም እናንተ እንደምትሉት ‘የወያኔ ሴራ ነው?” በሞቴ እስኪ ንገሩኝ? በየ ዩቱቡ ላይ ቁልቃል እየቀለጠች ቁልቋሉን እያሳየች “ትግሬ ቁልቋል በሊታ፤አምበጣ በሊታ፤ ቅማላሙ ትግሬ” እያለች የለጠፈቺው በዕድሜዋ በጣም ወጣት ሎጋ የሆነች አማራ ለበርካታ ጊዜ መነጋገርያ የነበረቺው ይህች ወጣት በጀግንነት ሰይመዋት በየፓልቶኩና በየ ዩቱብ ሲጋብዟት የነበረቺው አማራ ወጣት ትዝ አይላችሁም? ጎጃሜ ነኝ የሚል ዮኒ ማኛ የተባለው “ቅማላም ትግሬ አምበጣ በሊታ” እያለ ሲሳደብ ሰምታችሁ አታውቁም? ይህ ሰው አማራ ወጣት አልበከለም ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዲህ ያለ ወጣት የ29 አመት የሳብቨርሲቭ አጠባ “ሰለባ ሆኖ” በዛው ርዕዮት ማደጉን ምልክት አይመስላቸሁም? አንዳንዶቹ መረን የለቀቁ ዘረኛ የአማራ ወጣቶች የሚጽፉትን የሚናገሩትን ሰምታችሁ አታውቁም፤ አማራ ወጣት በዘረኛነት ሊበከል አይችልም፤ አይበከልም ፤ አልተበከለም ማለት ምን ማለት ነው?

ከላይ የተመለከታችሁት ቪዲዮ በግልባጩ በትግሬዎች ቢነገር (ተደርጓልም) አማራዎች ድርጊቱ ከራሳቸው ውጭ በሌላ ሰው ሲሰሙት እነዚያን ባህሪዎች እንደ ዘረኛ ያዩዋቸው ይሆን ወይስ ምንም ማለት አይደለም ብለው ይደመድማሉ? መታወስ ያለበት ዋናው ነገር ለ29 አመት የተሰራጨው የፏሲሰቶች ትምህርት ምንም ቢዘገይም ብዙዎቹ ወጣቶች የነገድ ፍቅር ስለሚያጠምዳቸው ዘረኞች መሆቸውን በሚነገራቸው ጊዜ ዘመዶቻቸውም ይሁን እራሳቸው “ዓይነ ስውር ቦታቻውን” (ዳርክ-እስፓት) ማየት አይችሉም ። በዘረኛነት እየተቀጠቀጠ ያደገ ማሕበረሰብ ወጣት ለምን ዘረኛ እንደሚሆን በሚቀጥለው ጽሑፌ በማስረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ያተየው እና ለወደፊቱ የሚታየው በየክልሉ/አፓርታይድ/ ቦታዎች/ ቅሪቶቹ ለረዢም ጊዜ እኛ ጋር እንዴት እንደሚቆዩ አቀ ርባለሁ። ተከታተሉ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)