Tuesday, May 19, 2015

1-ተቃዋሚ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆሙ ናቸው? 2-እሳቶቹ ፋሲል የኔአለም እና የደረጀ ሃብተወልድ ምስጢር ከጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)


1-ተቃዋሚ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆሙ ናቸው?
2-እሳቶቹ ፋሲል የኔአለም እና የደረጀ ሃብተወልድ ምስጢር
ከጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com
ሞት ይሻላል! አለች ጦጢ።እነ ንአምን ዘለቀ እና ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ውስጥ በምቾት እየኖራችሁ የዋሁን ከማታለል ከዚህ የታሪክ ውርደት ለመሸሽ፤ ኤርትራ መሬት ሄዳችሁ ካታለላችሁት ወጣት ጋር ጎን ተሰልፋችሁ ተወግታችሁ ብትሞቱ ይሻላችሗል ብሎ የሚመክራችሁ መካሪ ሰው ታጣ? የኢትዮጵያ የኤሊት/ሊሂቃን ውድቀት ሲደጋገም ማየት እጅግ አንጀት ያቃጥላል።

ከፋሺስቱ ከኢሳያስ አፈወርቂ ወኪሎች እና የፋሺሰት ሰንደቃላማ ፊት ለፊት ደቅኖ መቀመጥ  ምንኛ “በክትነት መሆኑን ማን በነገረልኝ” ወገኖቼ! ንአምን ዘለቀ እና ብርሃኑ ነጋ ጓደኛቸው አንዳርጋቸው ጽጌን አስይዘው፤ የአዞ አምባ አፍስሰው፤ ኤርትራ በረሃ ሄደው እንዳይዋጉ “ፈርተው፤ ሃሞታቸው ፈስሶ” መትረየስ መሸከም የሚችል ‘የትልቅ በሬ ትክሻና አንገት የሚያክል ይዘው”፤ በየአዳራሹ ሞኙን እየሰበሰቡ፤ አሜሪካ ውስጥ በምቹ አልጋ ተንጋልለው እያደሩ፤ ኤርትራ ውስጥ “የድሃ ልጅ በጥይት እየተቆላ” እንዲሞትላቸው እየሰበኩ፤ የሽምቅ ተዋጊ መሪ ነኝ ከማለት የሚያሳፍር በዚህ ምድር ውስጥ ምን ይኖር ይሆን?

ኢትዮጵያዊያን ይህ ዓይን ያወጣ ውሸትና ማጭበርብር ለስንት ጊዜ ተሸክማችሁት ልትኖሩ ነው? አዋጊዎቹ አመሪካ ውስጥ ስራ ተቀጥረው ልጆቻቸው ትምሕርት እያስተማሩና ሚስቶቻቸውን አቅፈው እየኖሩ፤ የሽምቅ ተዋጊ መሪዎች ነን ሲሏችሁ ይህ በታሪክ  የሚያስከስስ የማጭበርበር ቅጥፈት፤ ከእውነታው ጋር መለየት እንዴት ያቅታችሗል? ዲያስፖራ ሞኙ! መታለሉ ዛሬም አልበቃህም ወይ?! ዛሬ በሌላ ርዐስ ነው የምንወያይ፤ በዚህ ላይ በሚቀጥለው ሰሞን እመለስበታለሁ።

እስኪ ወደ ዋናው ርዕሴ ልግባ።ግለሰቦች ተቃዋሚው ወያኔ እስከተቃወመ ድረስ ለምን ትወቅሳቸዋለህ እያሉ ብዙ ሰዎች ይጠይቁኛል። ደርግ ይውደቅ እንጂ ከደርግ የባሰ የሚመጣ የለም፤ ብለው የወያኔን መግባት ሲናፍቁ የነበሩ ነበሩ። ዛሬም ወያኔ ይውደቅ እንጂ ከወያኔ የባሰ አይመጣም የሚሉ ሞኞችም አሉ። በዚህ ረገድ ግንቦት 7 እና አሽቃባጮቹ ብዙሃኑ ተቃዋሚ ሚዲያዎቻቸውም በዚህ ሞኙን እያጃጃሉት እያየናቸው ነው።
 ተቃዋሚው ጸረ ኢትዮጵያ ንግግር፤ ጸረ አንድነት ዱሎታ ሲያካሂድ፤ እውነት እየሸሸ ውሸት ሲሰብክ ዝም ብለህ እለፋቸው፤የሚል ወይንም፤ ከነቀፌታ ነፃ ይውጡ የሚል አዋጅ/ሕግ እስካላሳዩኝ ድረስ፤ሃሰት የሚሰብኩ ሁሉ ማጋለጤን አላቆምም። ውሸታምና ቅጥረኛ ስርዓት ይወገድ እያልን፤ሌላ ውሸታምና ቅጥረኛ ባንዳ መተካት ያስነውራል። በሕዝብ ፊት ውሸት መትፋት ያስነውራል። ‘መትፋት ያስነውራል’ ያሉት ማን ነበሩ? አዎ አቶ አሰፋ ጫቦ።
አገርና አንድነት የሚገነባ በሃሳዊ መሲሆች ሳይሆን ፤ እውነትን ነክሰው ብግራም በቀኝም የሚዥጎደጎድባቸው የስደብ ውርጅብኝ ችለው ሃሰተኞችን ሲጋፈጡ ብቻ ነው።ዓለም በሃሰተኞች እና በእውነተኞች ጎራ የተከፈለች ነች። ለዚህም የእውነትና የውሸት ቡድኖች ተፋጥጠናል።ትግሉ ከወያኔም ከሃሳዊ መሲሕ ተቃዋሚዎችም በመንትያ ትግሉ ይቀጥላል። የዋሆች ከቅጥረኞች ጋር ሊዘሉ፤ ሊፈርጡና እስክስታ ሊረግጡ ሊያንጨበጭቡላቸው መብታቸው ነው። ውጤቱ ግን ያው ታጥቦ ጭቃ ሲሆኑባቸው የምንለውን ሁሉ እውነት ሆኖ ሲያዩት የሗላ፤ሗላ የምንኮራበት ነው።

ወያኔዎች በ1983 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ የውሸት መርዛቸው ብዙ ተቃወሚዎችን በክሏል። ባጭሩ በዛው በወያኔ ሕዝብን የማታለል በሽታ የተለከፉ ተቃዋሚ ጋዜጠኞች በብዛት ተራብተዋል። አሁንም ተቃዋሚ ነን የሚሉ ጋዜጠኞች ያንን ከአገር ይዘውት የመጡ የውሸት ባሕሪያቸው የፖለቲካ መሪዎቻቸው ሲዋሹን እነሱም አብረው ሲያራቡት እያየን ነው።ሚዲያዎቹ ነፃ እንዳልሆኑ እየታወቀ፤ የሕዝብ ልሳን፤ጀሮ እና አይን አይደለንም፤ ነፃ ሚዲያም አይደለንም፤ ብለው እቅጩን ከመናገር ይልቅ ፤በነፃ ሚዲያ ስም የመሪዎቻቸውን  ውሸትና ማጭበርብር ለሕዝብ ሲያናፍሱ ዝም በሉ የሚሉን ሰዎች “የአገሪቱን መከራ እያራዘሙት እንደሆነ አልተረዱትም”።    
ውድ አንባቢዎቼ ለዛሬ የምንመለከታቸው ሁለት ርዕሶች ይዤላችሁ መጥቻለሁ። የተቃዋሚ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆሙ ናቸው? የሚለው በቅድሚያ እንመለከት፤ ከዚያ ወደ ፋሲል እና ደረጀ ሐብተወልድ እንመለከታለን፤፡

ሚዲያዎቹን በሚመለከት ካሁን በፊት በተለያዩ ርዕሶች ግለሰቦቹም እያነሳሁ አደገኛነታቸው እና ውሸታምነታቸውን ጠማማነታቸው እና የማጭበርበር ማሕደራቸውንና አልፎም ዘረኞች መሆናቸውንም ጭምር በማስረጃ አቅርቤአለሁ።ለማን ወግነው፤ ማንን እያፈኑ አንደነበረ፤ አሁንም የነማን ልሳን እየፈቀዱ፤የነማን ጽሑፍ እና ክርክር አፍነው፤ በድረገፆቻቸው እንዳይታተሙ ከሕዝብ እይታ እንዲደበቁ ያደረጉ ብዙ አሉ። ሌላ ቀርቶ የኢትዮጵያዊው ኤርትራ ተወላጅ ዶክተር መስፍን አርአያ የመርዶ ዜና እንዲለጥፉ ልከንላቸው፤ አላወጡትም። የወያኔ ደጋፊ የነበሩና ሰዎች ሲሞቱ ግን  የዕረፍታቸው ዜና የሚለጥፉ ማፈሪያዎች አሉ።

በሊቢያ እና በየመን ላሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ለመርዳት የፌርማ ድጋፍ ለማፈላለግ የድረገጽ ባለቤቶች እንዲተባበሩን፤ ሞዴሊስት እና ሰብአዊ መብት ተማጓች እንዲሁም ቴክሳስ ውስጥ የምትኖር የመጀመሪያዊቷ ሴት ኢትዮጵያዊት ለፕረዚዳንትነት ተወዳዳሪ ሆና የቀረበች ወ/ሮ የሃረር ወርቅ ጋሻው የመሰረተቺው Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group በኩል፤ በሊቢያ የኢትዮጵያ ስዴተኞችን አስመልክቶ ጥበቃ እንዲደረገላቸው ከሊቢያ መንግስት ጋር መነጋገር በመጀመርዋ (ከሊቢያው መሪ ከሞአመር ጋዳፊ ዘመን ጀምሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስለነበራትና አሁንም ሥልጣን ላይ ካሉ የሊቢያ ባለስልጣኖች በኩል ንግግር በማድረጓ)፤ አስፈላጊው የፌርማ ድጋፍም ከማሕበረሰባችን ማሰባሰቡ አስፈላጊና ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘቺው፤የተሰበሰበው ፌርማ ለባለስልጣኖቹ ለነ Mr. Wafa Bugaighis  እና አምባሳደር ኢብራሂም ደባሺ እና አስፈላጊው ድጋፍ እናደርጋን ብለው ለተባበሯት የሊቢያ መሪዎች እና የጸጥታ ክፍሎች እንዲሁም ለተባበሩት መንግሥታት መሪው የተሰባሰበው የማሕበረሰባችን ፌርማ ለማስረከብ ባደረገቺው ጥረት ድረገፆች የፌርማ ድጋፍ በመለጠፍ እንዲተባበሯት በኔ በኩል በተላከላቸው ደብዳሜ/ኢመይል ተልኮላቸው፤ ሁለት ድረገፀች “አሲምባ.ኦርግ እና ኢትዮፓትርዮሪክ.ካም ብቻ ሲተባበሩ፤

የተቀሩት ኢትዮ፤ሚዲያ፤ ዘሃበሻ፤ኢኤምኤፍ፤ቋጠሮ፤ የመሳሰሉ ወገንተኞች እና ከዚህ በታች የተላከላቸው ድረገፆች ትብብራቸው ነፍገውናል። ትብብራቸው ለኛ ሳይሆን፤ ቢላዋ ባንገታቸው ተደቅኖባቸው ለነበሩት እና አሁንም በሞት አፋፋ ላይ ላሉት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድያውቀው፤ ይህ ታሪክ አስተላልፋለሁ።

ትብብር የነፈጉ ድረገጾች የኢመይል አድራሻ የሚከተሉት ናቸው፡
 Original Message-----
From: getachre <getachre@aol.com>

To: editor <editor@ethiomedia.com>; <editor@addisvoice.com>; addisdimt
 ecadf <ecadf@ecadforum.com>; webmaster <webmaster@nazret.com>; media.emf <media.emf@gmail.com>; zehabesha <zehabesha@yahoo.com>; henocka2001 <henocka2001@yahoo.com>; ethrev <ethrev@gmail.com>; shengo.pr <shengo.pr@ethioshengo.org>
Sent: -Sat, Apr 25, 2015 2:32 am
Subject: -    Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group
የኢትዮጵያ ስዴተኞችን አስመልክቶ ጥበቃ እንዲደረገላቸው ከሊቢያ መንግስት ጋር መነጋገር ጀምርዋል።

Help!!!!!!! Help!!!!!! Help!!!!!!!! "
Voice of the Ethiopians in Libya
Please post the attached petition on your websites for Ethiopians to participate on the petition to save Ethiopians in Libya from the barbaric slaughter going on.
                              Thanks
Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group.

ይላል ለትብብራቸው በተጠየቀው ኢመይል የተላከ መልዕክት። እስኪ አስቡት፤ ይህ ፖለቲካ ነው? ይህ ድምፅ እንዴት ሊታፈን ተፈለገ?  ወገኖቼ እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ድረገፆቻቸው በቀን 3ሺህ ጎብኚ አለን የሚሉ ናቸው። በዚህ መሰረት ትብብሩ የተጠየቁበት ምክንያት ጐብኚ ብዛት አለን ስለሚሉ፤ ፈራሚን በብዛት ለማግኘት እንዲመች ነው ማስታወቂያው አንዲለጥፉት የተላከላቸው ዋና ዓላማ፤ ሆኖም እነዚህ ሰዎች የግል ጥላቻቸው በሕዝብ ሕይወት ሲመነዝሩ አይተናቸዋል። ለምን?

እኔን ላይወዱኝ ይችላሉ፡ እንዲወዱኝም አይደለም ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት፡ ጉዳይም አልለው፤ (ውሸታቸውን በማስረጃ ስለማጋልጣቸው)፤ የሐረርን ላይወዷት ይችላሉ (አንዳንዶቹ እርሷ ያቋቋመቺው ተራድኦ እና ስም በመስረቅ ግልባጭ እያደረጉ በሷ ስም መጠቀማቸው እንድያቆሙ ባደባባይ ስላጋለጠቻቸው)፤ እና ብዙዎቹ ከሃዲዎች፤አደገኞች፤ በሕዝብ ስም፤ ባገር ስም የሚሸቅጡ ደላላዎች፤ የውጭ ቅጥረኞች ሆነው በመታዘቧ፤እንደሆነ ነግራኛለች።

ይህ ደግሞ ያየነው እና አሁንም እያየነው ያለው ትኩስ ጉድ ነው)፤  ሆኖም የፖለቲካ ጥላቻ ከሕዝብ ሕይወት የማዳን ዘመቻ እያጣመሩ በጥላቻ ተነሳስተው እኛን ያገኙ እየመሰላቸው፤ባንገታቸው ቢላዋ ተጋድሞ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ወገኖች ‘ፌርማ’ እንዳይደረግላቸው፤ ማስታወቂያው ከሕዝብ እይታ በመሰወር ትብበራቸውን ሲነፍጉ ማየት፤ ለወደፊቱ እነዚህ ሰዎች “የስልጣን ለውጥ ተደርጎ፤ስልጣን ላይ ወጥተው፤ በሚዲያ ላይ ቢሰለፉ፤ ወይንም ሥልጣን ላይ ቢወጡ፤ ቂም በቀልተኛ ባሕሪያቸው ላልወደዱት ሰው/ድርጅት ምን ዓይነት አፈና አንደሚያደርጉበት ሳስበው ፤ከወያኔ ፕሬስ አፈና የማይሻሉ፤ “በጣም አስፈሪ “እንሰሳዎች/ሞንሰተሮች/ እንደሚሆኑ እጅግ ያስፈራኛል። አማርኛ እና አንግሊዝኛው አሳምረው መጻፍ ስለቻሉ ሕዝቡን ማጃጃላቸው እንጂ፤ ፕሬስ ምን እንደሆነ ትርጉሙና ተግባራቸው ሲገናዘብ ለፕሬስ የማይገቡ፤ እጅግ “ማይሞች” የድሮ ጉልተኛ ባሕሪ የተላበሱ ‘ቂመኞች’ ፤ ናቸው።

በእርግጠኛነት ልነግራችሁ የምፈልገው ግን፤ ወያኔ ሲወቅሱ ከወያኔ እንደማይሻሉ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፤(በዚህ ካሁን በፊት ብዙ ማስረጃ አቅርቤአለሁ)። በየጎራችሁ ድረሱልን ለሚለው የየመን እና የሊቢያ ጩኸት ለፌርማ ማሰባሰብ ማፈናቸው እጅግ ያሳዝናል። እንኳን እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ነን፤ለሕዝብ ቆመናል የሚሉ ተቃወሚ ሚዲያዎች ቀርቶ “ግብፆችም” እስከ ሊቢያ ድረስ ሄደው ወገኖቻችንን ከሞት አድነዋል ተብሎ በዜና ተሰራጭቷል። እነዚህ የድረገጽ ባለቤቶች በዚህ አሳፋሪ እና ቂም ልቦናቸው ተሸርሽሮ ለወገኖቻችን ፌርማ አንዳይሰበሰብላቸው የተላከላቸውን የትብብር ጥያቄ በድረገጻቸው እንዳይለጠፍ “ከሕዝብ እይታ ሲያፍኑት” እንዴት ተብሎ በፖለቲካው እና በሚዲያ ሃቀኛነታቸው ለወደፊቱ በሕዝባችን ፊት ሊታመኑ ይችላሉ?

ይህ አሳዛኝ ጉድ ካየሁኝ በሗላ፤ ይህ ሰይጣናዊ እና ሃሳዊ መሲሕ ባሕሪያቸው ካለፈው ተግባራቸው ተደምሮ ሳገናዝብ ይህንን ‘ቂም በቀልተኛ” ባሕሪያቸው ለመግለጽ ቃላት አጥሮብኛል።
 
በጣም የሚገርመው ደግሞ፤ በእስላማዊ ጽንፈኞች ሊቢያ ውስጥ ለታረዱት ወገኖቻችን በየአሕጉራቱ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሻማ መብራት ተሳትፈዋል። ይህ ጥሩ ቢሆንም፤ በሞት አፋፍ ላይ ላሉ በፌርማው ማሰባሰብ ረገድ የተባበሩት ግን በሁለት የፌርማ አሰባሳቢ ድርጅቶች የተመለከትኩት ጥናት ላይ ከመቶዎቹ ውስጥ ብቻ ናቸው በፌርማው ውስጥ የተካፈሉት። በዚህ ወያኔዎች ያዘጋጁት የፊርማ ማሰባሰብ ተቃዋሚውን በፈራሚ ቁጥር በልጦታል። ወደ ኤርትራኖቹ የፌርማ አሰባሳቢ ቡድን ሄጄ ስመለከት (በታወቁት የኤርትራ ተቃዋሚ ድረገጾችም አለፍ አለፍ ብሎ ጽሁፌ ስለሚስተናገድ እዛው ሄጄ ድረገጾችን እና ባለቤቶችን በስልክ ሳነጋግር፤ የተደረገው የፌርማ እና የትብብር አንድነት እጅግ ከኢትዮጵያዊያን ፌርማ አሰባሳቢ እና አንድነት ሲነጻጸር፤ የኛው አሳሳዛኝ ሆኖ ነው ተመለከትኩት።

ይህ ሕዝብ  ወደ አንድ አቅጣጫ በተለይ እንደዚህ ያለ ጥቃት ሲፈጸም ወደ አንድ ድምፅ እንዳይገባ “እየነጠለው” ያለው ቡድን፤ የፖለቲካ እና የሚዲያ ሰዎች እነማን ናቸው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ቁልጭ ብሎ ማየት ትችላላችሁ። ያው ከላይ የምታይዋቸው ሚዲያዎች ላለመተባበር ትልቅ እንቅፋት እና ሚና ከቅንጅት መፍረስ ጅምሮ አፍራሽ ተራ የነበራቸው ቡድኖችና ግለሰቦች የነበሩት ናቸው።

ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከሁለት አመት በፊት (2013) በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን በደረሰው ጥቃት ላይ ተቆጭተን እንደምንተባበራቸው በታማኝ በየነ፤ በአበበ ገላው፤ በነአምን ዘለቀ ፤በሜሮን አጐናፍር፤ ሉሊት መስፍን፤አክሎግ ቢራራ፤ሂሩት ልሳነወርቅ፤….. በመሳሰሉ ሰዎች በወቅቱ የተመሰረተው በኢሳት ቲ/ቪ  ጡሩምባ የሚነፋለት “Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia” የሚለው የሰብኣዊ ድርጅት መሕበር፤ እኔም ሆንኩ “የእስክመቸ” ድረገጽ አዘጋጅ የፖለቲካ ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን ሳውዲ ላሉ ወገኖች ለመርዳት በምንችለው ያህል ለመተባበር ዝግጁ ነን ፤በዚህ ኢመይል ታገኙናላችሁ ብለን ለየቅላችን ብንልክላቸውም ፤ጀሮ ዳባ ብለው መልስ ሳይሰጡን ቀሩ። እስከመቸም በጠም ተገርሞ እኔም ሆንኩኝ እሱ ለየግላችን በዚህ የተነሳ ትችት ጽፈናል። ማሕደሩም በድረገጽ ማግኘት ትችላላችሁ።

በተሰበሰበው ገንዘብ የፎከሩበት ጠበቃ ምናምን አቆሙበት፤ ሰንትስ ገንዘብ ለተራድኦ ወኪሎች አስረከቡ? ምናምን በሚል እኔ በማላውቀው ገብቼ ልተች አልችልም። እኔ እስከማውቀው ድረስ የተሰበሰበው 30፣ ሺሕ ዶላረ ብቻ ነበር፤ ይፋ ያወጡት። ብንተባባር ከብዛታችን አንጻር በሚሊዮን ዶላር ነበር ሚዋጣው። ግን አልታደልንም። የግንቦት 7 የፖለቲካ መጠቀሚያ እና ዝና ለማትረፍ የሚፍጨረጨሩ የፖለቲካ ሰዎች አንዳሉበት ግን ብዙ ሰዎች ያሟቸዋል። በርግጠኝነት ለመስቀመጥ የታዘብኩት እና በማስረጃ ማቅረብ የምችለው ግን፤ ድርጅቱ ከሰብአዊ ድርጅትነት አልፎ ወደ ፖለቲካው እና ወደ ምርጫ ዜና፤ አንዲሁም በመሳሰሉ ከፍተኛ የፖለቲካ ጽሑፎችን ሲያትም በኢሳት ፌስ ቡክ በኩል ሲያስተላልፍ ተመልክቻለሁ። እንግዲህ እንዲህ ያለ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ወደ ለፖለቲካ መሸፈኛ እና ዝና ማንጸባረቂያ ማድረግ ከምን የመነጨ ስነ ምግባር ነው? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል።

በወቅቱ ያስገረመኝ፤ የኛን ትብብር ነፍገው፤ የወያኔ ቀንደኛ መሳሪያ/ፑፔት የሆነውን ብርሃኑ ዳምጤን (አባ መላን) አምነው ከወያኔ ጋር ነበር ጥምረት ያደረጉት። እንግዲህ ከወያኔ ጋር ህይወት ለማዳን ብለው ከወያኔ ካድሬዎች ጋር አንድነት ሲፈጥሩ እኛ ጋር አንድነት ላለመፍጠር ያዳገታቸው አቀበት ምስጢሩ ምን ይሆን? እስካሁን መልስ አልተገኘለትም።

ይህንን ጉድ እስኪ አንብቡልኝ፡
   
   Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia November 16, 2013
FOR IMMEDIATE RELEASE
A Global Coalition, Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia, has been formed to coordinate efforts to stop violence against Ethiopians in Saudi Arabia On Tuesday, November 12, 2013, concerned Ethiopians and Ethiopian Americans held a conference to deliberate on effective strategies to respond to the recent Saudi government’s deadly crackdown on and inhuman treatment of immigrants from Ethiopia and formed a Global Alliance to coordinate efforts.

The following prominent activists were elected to lead the Global Alliance:
1. Activist Abebe Gellaw
2. Activist Berhanu Damte (Abamela)
ይህ አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን በሳውዲ አረቢያ የተሰኘው ሰብአዊ ድርጅት ለምን በግንቦት 7 በሚመራው በኢሳት በኩል ገንዘቡ እንዲላክ ተደረገ የሚሉ ጠያቂዎች አሉ፡፤ ይህ ጥያቄአቸውም ይህንን መረጃ በመመርኮዝ ነው፤ “those who want to send a check, please make the check payable to:
Global Alliance for the Rights of Ethiopians and mail to:
c/o ESAT USA
P.O. Box 11261
Alexandria, VA 22312
Contact information:

ዛሬ ደግሞ በየሐረር ወርቅ ጋሻው በኩል የተመሰረተው በሊቢያና በየመን ለሚጠቁ ወገኖች ተሎ እንድንደርስላቸው ፌርማ በብዛት እንዲሰባሰብ ይረዳን ዘንድ እባካችሁ ተባበሩን ተብለው ለተጠየቁ ከላይ የተመለከቱት ድረገጽ አዘጋጆች፤ ትብብራቸው መንፈጋቸው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ጭንቀት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸውና ለታሪክ ፍርድ ትተነዋል። በወ/ሮ የሐረር ወርቅ ጋሻው የተሰረተውና የሚመራው ተቋም ለመመልከት እንዲሁም የሷን ትችት ለማንበብ ይህንን የድረገጽ አድራሻ ይጠቀሙ። http://dfwethiopiancommunity.blogspot.com/2015/04/blog-post_23.html 

ይህ በእንዲህ ላብቃ፡ እና ወደ ሁለተኛው ርዕስ ልግባ።

2-እሳቶቹ ፋሲል የኔአለም እና ደረጀ ሃብተወልድ
እውነትም የእሳትም እሳቶች ናቸው። በትግርኛ “ሓዊ ዝላሓሰ” ይላላል። ‘እሳት የላሰ’ ማለት ነው። አንደተርጓሚው የሚለያይ ብዙ ትርጉም አለው። ይህ ሰው እሳት ነው ሲባል ግን “ሞላጫ” ሰውን የሚያሞኝ ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች በፖለቲካው ረገድ እጅግ “ሞላጮች” ናቸው። ኢሳት ቲቪ እና ራዲዮንን/ግንቦት7ን ወክለው ወደ ኤርትራ ምድር ተጉዘው (መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔአለም) በነበሩበት ወቅት ደረጀ ሃብተወልድም ከአውሮጳ የኢሳት ማሰራጫ ጣቢያ ሆኖ የነሱን ዘገባ እና ክርክር ሲያደምቅላቸው አድምጠናል። ይህ ደግሞ የተመለከትኩት በቅርቡ አንድ ወዳጄ ይህ ጉድ አደምጠሃል ሲለኝ ነበር፤ ደረጀ ሃብተውልድ የተቸበትን ዘገባ ልኮልኝ ያደመጥኩት። ብዙም ስለማልከታተላቸው አምልጦኛል። የምመለከተው “የብጻይ “ቢሆንስ!” ሾው” ነው የሚያሚያምረኝ።
ፋሲል የኔ አለም እና ደረጀ ሃብተወልድ አስመራ ላሉት ተዋጊ ሃይሎች ስብከት ሲያሰራጩ፤ ሌላው ወጣት ወደ ኤርትራ ተጉዞ ግንቦት 7 ተዋጊ ሃይችሎችን እንዲቀላቀሉ ሲሰብኩ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ኬኒያ ውስጥ ሲኖሩ ወደ አውሮጳ እንዲመጡ እንጂ  ግንቦት 7ን ለመቀላቀል ብለው ወደ ኤርትራ ምድር እንዳይሄዱ ያገዷቸው ምስጢር በሚቀጥለው ሰሞን እንመለከታለን። ወንድሞቻቸው ወደ ኤርትራ ከመጓዝ አግደው፤ ሌላው ምስኪን ወጣት ሲንከራተት፤ በእነሱ ‘ላብና ደም’ ዜና ሲሰሩባቸው፤ ፎቶግራፍ ሲነሱባቸው፤ ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩላቸው ማየት እጅግ ያሳዝናል። ውሸታሞች የጊዜ ጉዳይ እንጂ ይጋለጣሉ።

አንዳርጋቸው ጽጌ ኤርትራ በነበረበት ወቅት 4 ወር ሙሉ ጊዜውን ያጠፋው የተስፋ ገብረአብ መጽሐፍ ሲያሳትም እንደነበረና፤ሻዕቢያ አልጋ እና ቤት ሰጥቶት “ሳምራዊት” ከምትባል ኤርትራዊት ወጣት ፍቅር ይዞት አስመራ ውስጥ እንዴት ሲቀብጥ እንደነበረ አያይዘን አንመለከታለን። ወይ ጉደኛ ዘመን! ይቀጥላል……ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com