Wednesday, June 8, 2016

ለሻዕቢያ ባንዳዎቹ ለሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፤ለካሳ ከበደ እና ለንአምን ዘለቀ መልስ!ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

ለሻዕቢያ ባንዳዎቹ ለሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፤ለካሳ ከበደ እና ለንአምን ዘለቀ መልስ!

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ- Ethiopian Semay

ዜጎች ሆይ! የወያኔ ባንዳነት ያበቃል ስንል፤ ከእነሱ የማይሻሉ፤ በተቃዋሚ ጎራ ተስልፈው ፤ እንዲህ ይሆናሉ ብለን ያልጠበቅናቸው “ቀንድ ያበቀሉ” አዳዲስ ባንዳዎች ተፈልፍለዋል። ወያኔ ቢወገድም፤ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በመራራ ጎዳና የተጓዘቺውን የ25 ዓመት ዘግናኝ ጎዳና የሚያበቃ መስሎ አይታይኝም። ዛሬ ስለ ጥቂት ግምባር ቀደም አዳዲስ ባንዳዎች እተቻለሁ።

የውጭ ጠላቶቻችን ዛሬም አልተኙብንም።የውስጥ ባንዳዎችን በማሰማራት በተለመደው ግን በአዲስ መንገድ መጪው ዕድላችን ለድጋሚ ለመራራ ጽዋ እየጋበዙን ነው።ጠላቶቻችን ከቶውንም የሚተኙብን አይመስልም።አገራችን ከዘመነ አክሱም ጀምሮ እስከ ዘመነ ወያኔ ያለው ታሪክ ጦርነት ያላባራበት ምክንያት፤ የጠላቶቻችን የቀላ ዓይን በኢትዮጵያ ላይ ማንሳት ስላልቻሉ ብቻ ሳይሆን ደካማ ሕሊና ያለቻው፤በክህደት የሚጓዙ፤ የውስጥ ሰራተኞችና ሰላዮች ስለሚያሰማሩብን ነው። ዛሬም የሚያባራ አይመስልም። አዲሱ ትውልድ የሚያነቃው ካልተገኘ፤ በውስጥ  ሰራተኞች ምክንያት የውድቀት ውድቀት መከናነቡ የማይቀር ነው። ዛሬም፤ ባንዳዎችን መታገል ለይደር የማይባል ከባድ ፈተና ነው። ወያኔና ሻዕቢያ ኢትዮጵያን ሊቆጣጠሩ ያቸሉት በውስጥ  ሰራተኞችና ከዳተኞች ግዝገዛ ምክንያት ነው። መረጃውም ወደ ታች ለንባብ ስትደርሱ ትመለከቱታላችሁ። ዘመናዊ ባንዳዎች የተማሩ ስለሆኑ ፤ስልታቸውም ያንነ ያህል አሳሳችና ሞለጭላጫ ስለሆነ፤ ብርቱ ግንዛቤ ከሌለህ ማንነታቸው ለማወቅ ያስቸግራል። ትግላችን ሁለ ዘርፍ ነው። ስለሆነም እተቻለሁ። መልካም ንባብ።

ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ማን ነው? ዳዊት የተባለው ራሱን ለውርደት የሚዳርግ ፤ቀላል ሰው፤ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረ በባንዳነቱ የማያፍረው ግለሰብ ባለፈው ትችቴ፤ ዳዊት ለኮለኔል መንግሥቱ የጻፈውን አሳፋሪ የሆነ የእጅ ጽሑፉን ማቅረቤ ይታወሳል። ባለው ወር ከደቡበ አፍሪካ  ወደ ዋሺንግተን ገስግሶ አማራዎችን እየለየ ሲገድል የነበረው ነብሰገዳዩና በየዓለማቱ ከሩስያ እስከ ጀርምን ከጀርመን እስከ ሶማሊያ እስከ ኢትዮጵያ፤ኰንጎ እና አፍሪካ አገራት እንዲሁም በየዓረባቱ አገራት የመሳሪያ፤የሉል፤ የወርቅና የገንዘብ የመሳሰሉ ጥቁር ገበያ በማስፋፋትና ግድያ በመፈጸም የታወቀው ወንጀለኛው የሻዕቢያው መሪ ወደ  እሚሞገስበት “ኢሳት” ወደ ተባለው የግንቦት 7 ቴ/ቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ‘ኢሳያስ አዋቂ ሰው ነው” ፤“ዓሰብ የኤርትራ ነወ” ፤ ኤርትራ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና  በሕግ የተነጠለች አገር ነች”፤ “ ዓሰብ  በተዘዋዋሪ ለዓረቦች ተሰጥቷልና እንግዲህ ስለ ኤርትራና ወደቦቿ መናገር ኢትዮጵያውያን አፋቸውን መዝጋት አለባቸው”…. እያለ ባንዳዊ ጥብቅናው ለአዲሱ ትውልድ ሲያስተላለፍ አድምጣችሁታል።

ሳብቨርዢን በሚል በሰፊው የሰጠሁትን ቃለ መጠይቅ አስታውሱ። አገር ማፍረስ፤ባሕል፤አስተሳሰብ፤ሥርዓት፤ሉዓላዊነትን ለአደገኛ ሁኔታ መቀየር ማለት ነው። ንአምን ዳዊትና ካሳ ከበደ እንዲሁም መሰሎቻቸው፤  በሳብቨርዥን ፤አገርን በማፍረስ ብረዛ ሥራ ተሰማርተዋል። ዜጎች ይህነን በጠብቅ ማስተዋል አለባችሁ። አዲሱ ትውልድን ማበላሸት፤ አስተሳሰቡን መቀየር፤ማሳሳት፤መጠምዘዝ፤ የሳብቨርዢን ቡድኖች ዋነኛው ትኩረት ነው።ኮሎኒያሊስቶች/ቅኝ ገዢዎች፤ በፕሮክሲ/ልኡካኖቻቸው በኩል የሚያደርጉት የመጀመሪያነ ቀላሉ መንገድ እነ ዳዊትና ካሳ እንዲሁም ንአመን ዘለቀ እየሰሩት ያለውን መንገድ ማስፋት ነው። ልብ ብላችሁ አስተውሉ።

ከዳዊት ቀጥሎ አብሮ ከዚህ ባንዳ ጋር ጋርም ፈላሻዎች ኢትዮጵያዊያን አይደሉም ብሎ ገንዘብ ተቀብሎ (ለዚህም በውጭ አገር ጸሐፍት ታሪኩን በመጽሐፍ መልክ ተጽፎበታል። ፈታኝ በሆነ ቀውጢ ቀን አርበኞች ሲታኮሱ፤ ከኢትዮጵያ በመሸሸሽ ሲወጣ አይሁዶች በሬሳ ሳጥን እንደ ሞተ ሰው ከትተው እንዳስወጡት መጽሀፉ ላይ ተገልጿል።) ይህ ግለሰብ ሕዝባችን ለእስራሎች ያስተላለፈውን ደላላው ይሁዳው “’ካሳ ከበደ” ይባላል።

ካሳ ከበደ፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆር መሆኑን ሳያፍር “አፉን ከፍቶ” ስለ ኢሳያስ ጥብቅና ቆሞ ሲሟገትና ባንዳዊ አረፋውን ሲደፍቅብ ኢሳት የታበለው ጣቢያ አስደመጦናል። ኢሳያስ የተባለው ሰው በመግደል የቀወሰ ፤ሕሊናው የተዛባበት፤ማርሻ ቤዲ ባዶ እግሩ በመሄድ አብዶ የነበረውን አማረ የተባለ ወንድሙን መርፌ አስወግቶ እንዲገደል ያዘዘ (በመጽሐፍ ተጽፎለታል)፤በማንነት ቀውስ የሚሰቃይ፤ የራሱን ቀውስ ለመሸፈን ሲል፤ አማራና አማርኛ የተባለ ቋንቋ በመጥላት “ኤርትራዊ” እንዲባል ያልጫረው አሳፋሪ ባሕሪ አልነበርም።

ይህ ጸረ አማራ፤የሆነ አርኩስ  እና የወንድሙንም የእናቱንም ስም ወደ ጀብሃ ሲቀላቀል በመታወቂያው ላይ “አዳነች” የሚለው የእናቱ ስም “አድሓነት” ብሎ አንዳስመዘገበው እና “አማረ” የሚለው የወንድሙን ስም “አምሐረ” ብሎ ሲያስመዘግበውና ከትምሀርት ቤቱ ‘ኦሪጅናል’ መታወቂያ ጋር አነጻጽሬ ካሁን በፊት አዳነችወደአድሓነት” ……አስመራ ውስጥ ዘኢትነገር የት ነው? (ክፍል 2) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ) Tuesday, April 14, 2015http://ethiopiansemay.blogspot.com/2015/04/2-ethiopian-semay.html በሚል ከነ ማስረጃው ፎቶግራፍ እና የትምህርት ቤት የምስክር ወረቀት እንደትመለከቱት አቅረቤው እንደነበር ይታወሳል።

በቅርቡ ደግሞ በኢትዮጵያ የ25 አመት ታሪካችን ታይቶ ተሰምቶ በማያውቅ እርቃኑ ወጥቶ አደባባይ ላይ የአዋቂዎች መሳቂያና መሳለቂያ የሆነው “ባንዳው” በመባል የሚጠራው “ንአመን ዘለቀ” የተባለው የግንቦት 7 አመራር አባልም ሰሞኑን ኤርትራ ወጣቶችን አዛውንቶችን ዓይነ ሰውራን ሳይቀሩ፤ በኢሳያስ ምክንያት ለምን እንዲሰደዱ እንደፈለጉ ወደ ትግራይ ተሰድደው የተናገሩትን ቪዲዮው አንድ ቀን እለጥፍላችሗለሁ) ወደ ‘ሳዋ’ እየላከ፤ የወታደሮች የወሲብ ማርኪያ፤ ድንጋይ እና እንጨት ፈለጣ እንዲሁም የማዓድን ቁፋሮ በነጻ በማሽሸቀል፤ እምቢ ያሉትንም “እንዳ አቦይ ርጉም” (የእርግማን ቤት) ወደ ተባለ በዓለም ውስጥ ያልታወቀ፤ ውስጠ ምድር እስር ቤት በማስገባት ፤ እዛው ስትገባ በ5 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ “የሰው ጸጉር” ወደ ነጭ ዱቄት በመለወጥ ቡን፤ ቡን፤ቡን ብሎ፤ እስረኛው ራስ ከመቅጽበት ወደ መላጣነት የሚለውጥበት፤አስደንጋጭ፤ ጋሃነማዊ፤ ምድረበዳዊ፤ ውስተ መሬት፤ ማሰቃያ እስር ቤት፤ ባጭር ጊዜ ቆይታ እስረኛው አከላቱ በሙቀት ስለሚገሻለጥ በቅጽበት ቆዳው ቆስሎ ገምቶ፤ ትሎች በመፍጠር፤ እስረኞች በግማትና በመግል ሽታ በማስታወክ የሚሰቃዩበት እስር ቤት በመላክ ፍጡር የሰቃየውን ናዚው ኢሳያስ አፈወርቂን ለማዳን ፤ ኢትዮጵያዊያን ከሻዕቢያ ጎን ሆነው የተባበሩት ምንግሥታት በኢሳያስ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ (ለስሙ ቢሆንም) አንዲነሳለት ቱልቱላውን ሳያፍር ባንዳው ንአምን ዘለቀ በየድረገጹ ሃይለ ከተባለ ኤርትራዊ የኢሳያስ አሽከር ጋር ሆኖ የቪዲዮ ማስታወቂያ አሰራጭጧል።

የባንዳው ንአምን ዘለቀ መልዕክት ለማድመጥ እዚህ ያድምጡ።
 PFDJ's Desperate attempt to Undermine COI Report on the Dictator's Human Rights Violations

በነ ዳዊትና ካሳ ከበደ አዋቂ ሲባል የነበረው ኢሳያስ አፈወርቂ እርቃኑ ወጥቷል።፡ኢሳያስ በኤርትራኖች እጅግ ስለተጠላ፤ የሚፈርሙለት እጅግ ጥቂቶቹ አሽከሮቹ ብቻ ስለሆኑበት፤ ሰው ሲያጣ ባንዳዎቹን እነ ንአምን ዘለቀን ከግንቦት 7 ደጋፊዎች ፌርማ እንዲያሰባስቡለት ስላዘዛቸው፤ በትዕዛዙ መሰረት ባንዳዎቹ ሳያፍሩ ከላይ ያደመጣችሁትን አሳፋሪ ማስታወቂያ ለጥፈውለታል። አዋቂው ኢሳያስ አፈወርቂ እርቃኑ ወጥቷል። እርቃኑ የወጣ ዓለም ያወገዘው፤ የቀወሰ ፤ኮንትሮባንዲሰትና ነብሰ ገዳይ በነዳዊትና በነ ንአምን እንዲሁም በነ ካሳ ከበደ አዋቂ እየተባለ ሲሰበክለት ዛሬ የረዳት ያለህ እያለ ጨንቆት “ጩኸቱን እያስተጋባ ነው”።

ባንዳዎቹ አዋቂ  ሰው እያሉ ሲሰብኩለት የነበረው “በላኤ ሰብ’ እንግዲህ ንአምንም ሆነ በእነ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እና ካሳ ከበደ የሚነገርለት የኢሳያስ አፈወርቅ “አዋቂነት” ምን እንደሆነ ባይገባንም፤ እኛ የምናውቀው፤ኢሳያስ አዋቂ ሳይሆን ደንቆሮ፤የአእምሮ በሽተኛ፤ነብሰገዳይ ወንጀለኛና ጸረ አማራ የሆነ አሳፋሪ ፍጡር ነው። አዋቂነቱን ተውት እና፤ ሌላ ቀርቶ የወላጆቹና የቤተሰቦቹ “አማርኛ ያዘለ” ስም እንዲያይ ካለመፍቀዱ ሌላ፤ አማራ የተባለ ሁሉ ከምድረገጽ መጥፋት እንዳለበት ያደረገው ወንጀል በዓይን ምስክሮች ለእነኚህ ባንዳዎች እንዲያውቁት ኢሳያስ ጸረ የሰው ልጅ ፍጡር፤ ከይሲ፤ እና ሞንስተር/ባላኤ ነብስ፤ አልፎም አማራ ሙርኮኞችን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለይቶ በመግደል ጀነሳይድ የፈጸመ ወንጀለኛ እና በፍርድ የሚጠይቅ ሰው ነው።

ዛሬ ባንዳው የግንቦት 7 ንአመን ዘለቀ የተባለ አሳፋሪ ሰው ለዚህ ነብሰገዳይ ወንጀለኛ ሰው፤ኢትዮጵያውንን ያውም አማራዎች ጭምር፤ ለኢሳያስ ድጋፍ ፌርማ እንዲያሰባስቡ ለአማራ ሕብረተሰብ ያለው ንቀትና በኢሳያስ ደብዛቸው ለጠፉ  ለተገደሉ፤ ለተደበደቡ፤ንብረታቸው ለተዘረፉ፤ለተባረሩ’ምራቅ ለተተፋባቸው፤ አህያ ተብለው አህያዋን ወታደራዊ ልብስ አስለብሰው አህያዋን እየጎተቱ አስመራ ከተማ ውስጥ እንዲዞሩ ለተደረጉ አማሮች እና ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን  ዜጎቻችን ክብር ሳይሰጥ ንአምን የተባለው ባንዳ በዜጎቻችን ላይ ንቀቱን ያለ ምንም ገደብ እና ዩሉኝታ በግልጽ አሳይቷል።ኪዳነ አለማዮህ የተባለ አዲስ (የሚያውቁት ነባር ባንዳ ነው ይሉታል) ባንዳም አብሮ እየጨኸ እንደሆነ በኤርትራኖች ድረገጽ አንብቤአለሁ። (ስለ እሱ ሰውየ እራሱ የቻለ መረጃ ስላገኘሁ በሌላ ቀን እመለስበታለሁ)

የዓይን ምስክሮች የጦርነቱን ሁኔታ በመዘከር እምባ እየተናነቃቸው አማራዎች እየተለዩ፤ ጊዜ የጣላቸው የተማረኩ መኮንኖችና ጄኔራሎች ኢትዮጵያዊያን በኢሳያስ ትዕዛዝ ምን እንደደረሰባቸው፤ በተለይም አማሮች እየተለቀሙ በጅምላ እንዲረሸኑ ኢሳያስ ያደረገው ወንጀል እንድናውቀው እንዲህ ቀርቧል።

የሚከተለው የምስክርነት ቃል የተገኘው ድንቅና እውቁ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ  አውስትራሊያ አገር ሆኖ ከሚያስተላልፈው CBS ራዲዮ ጣቢያ ምፅዋ ላይ ከነብርጋዴር ጀኔራል ተሾመ ተሰማ፤ ሻምበል ሸዋን ታዬ ዓለሙ እና ከነ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ እና ሌሎች ጀግኖች ጋር በመገኘት ጦርነቱን ከተካፈሉት ከመቶአለቃ ታደሰ ቴሌ ያደረገው ቃለ መጠይቅ የተገኘውን እንፈትሽ። የእነ ዳዊት ከበደ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም የነ ንአምን ዘለቀ አዋቂና ተደናቂያቸው ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ወታደሮች ላይ ያለው ጥላቻ ወንጀል ሲፈጽም እዛው ተገኝተው ያዩት የዓይን ምስክር ላቅርብ።  Interview with Tadesse Tele Salvano -- Pt 2 https://youtu.be/qWbKrEV-VRQ

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

እነዚህ እና የመሳሰሉ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊቱ መጨረሻውን ከፍተኛ የሆነው መስዋዕትንት ከፍለው፤ምፅዋ ላይ ወድቀዋል። በዛው ወቅት ደግሞ፤ እንደዚሁ በተቃራኒው ብርጋዴር ጀኔራል ክፍሌ ጥላሁን እና ብ/ጄ/ዓሊ ሓጂ እጃቸውን ለሻዕቢያ ሰጥተው ከጠላት ጋር ሆነው መከለከያ ሠራዊቱ እጁን እንዲሰጥ ይቀሰቅሱ ነበር ተብለው ከተወነጀሉት መካካል ናቸው። በዛው ወቅት፤በሠራዊቱ ውስጥ የነበረው ስሜት ምን ነበር?  እርስዎስ ያንን የቅስቀሳ ጥሪ ሲሰሙ ምን ተሰማዎት?

መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

ጀኔራል ዓሊ እና ጥላሁን የውግያ ሰዎችም አልነበሩም። ምንም ወታደራዊ ስልት የተከተለ ወታደራዊ አመራር አልሰጡም።ለማሸነፍ ያደረጉት ጥረት የለም።ከተሾመ ውጪ የውግያ ብቃት አላየሁም። ሻዕቢያ ወታደሩ እጁን እንዲሰጥ ጥሪ እንዲያስተላልፉ በቴፕ ቀድቶ ንዲተላለፍ ያደረገው በሠራዊቱ ሞራል ላይ የመሸነፍ የሞራል ተጽእኖ አሳድሯል። ጀኔራሎቹ እጃቸውን እየሰጡቱ እንዲህ ካሉ እኛ ለምን እንሞኖታልን የሚል አንዳንድ ወታደሮች ላይ ተንጸባርቆ ነበር።፡ጀ/ተሾመ የማያዳግም ወታደራዊ ፍልሚያ መርተው በራሳቸውም ላይ መስዋዕት አርአያነት ካሳዩ በሗላ ወታደሩ ተረጋጋ እንጂ ተጽዕኖ ፈጥሯል።

ጀኔራል ተሾመ በሕይወተ ካሉት ከነዚህ ጀኔራሎች በላይ በክብር በታሪክ ማሕደር ተመዝግበው ተሞግሰው እየኖሩ ናቸው።እነሱ ተሰደበው፤ተደብቀው ነው የሚኖሩት። ከቤታቸው አይወጡም። የተቆጨ ሁሉ መንገድ ላይ ካገኛቸው በሄዱበት ቦታ ድንጋይ ውርወራ፤በሄዱበት ቦታ በላያቸው ላይ መትፋት ነው’፤በድንጋይ መወገር፤በጥፊ መመታት፤ ወዘተርፈ… እየተፈጸመባቸው ነው። ህይወት አይደለም።ከቤታቸው ወጥተው ወደ ቤታቸው ለመመለስ አስቸጋሪ ኑሮ ነው የሚኖሩት፤ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡ እቤታቸው ውስጥ ነው ታምቀው አብዛኛው የሚያሳልፉት። እነኚህ እንደነገርኩህ ነው። ተሾመ ማለት ግን ኢትዮጵያዊ ማለት ነው! እነሱ ግን በፍርሃት ምክንያት የጠላት መሳሪያ ሆነዋል፤ በራስ ወዳድነት ለሻዕቢያ ብዙ መረጃ አሳልፈው ሰጥተዋል። ብዙ ጥቅም ሰጥተዋል። በስብሰባ የተነገሩ፤ የተፈጸሙ እና ወታደራዊ ምስጢሮችና አሰላለፍና ንድፎች ለሻዕቢያ አሳልፈው ሰጥዋል።

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

ጦርነቱ ከተካፈሉት ውስጥ አንዱ ነዎት፤ከተማረኩት ውስጥ አንዱ ነዎት። አንዴት ለሙርኮ በቁ?

 መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

ለመማረክ ፈቃደኛ አልነበርኩም። አጋጣሚ ቆስዬ ነበር፤ ቀኝ እጄ ተመትቼ ነበር። ዉሃ ጠጣሁና እንቅልፍ ወሰደኝ። እንደሰመመን ነገር ነው። መሞቴን እንጂ መኖሬንም አላውቅም። ከዚያ ከሰመመኔ ስነቃ፤ ጠመንጃየም የለም፤ ዙርያየ ‘የሻዕቢያ ሠራዊት ከብቦኛል”። መሳርያ ጠምደው አነጣጥረውብኛል። ተሾመን የሚያውቅ እሱ ነው፤ አብሮ የነበረ ነው የሚል መረጃ አግኝተዋል። ወደ ዶጋሊ ወሰዱኝ። ዶጋሊ ከሙርከኛ የተሰጣቸው የጀኔራል ተሾመ መረጃ እሱ በደምብ ያውቃል ስለተባሉ፤ እንደገና ወደ ምፅዋ ወሰዱኝ። ጄኔራሉ ጥይታቸው ሲጠጡ የትኛዋ ቦታ እንደነበረች እንዳሳያቸው ምራ ተባልኩ። ሄድን። የሚቻላቸውን ውግያ ካደረጉ በሗላ እዚህ ቦታ ቆመው ለሠራዊቱ የመጨረሻ ንግግር አድርገው ነው እራሳቸውን የገደሉ፤ ….እያልኩ መግለጫ እየሰጠሁ ሳሳያቸው “እሳቸው የምትለው ፤ጌታህ ነው?! እየሱስ ክርስቶስ ነው?! “ እሱ እያልክ ጥራው!” “ተሰሾመ በለው” ብሎ በጥይት ሊገድለኝ አነጣጠረብኝ።  ”እሱ” እያልክ ጥራው አለበለዚያ ትረሸናለህ ብሎ ሊተኩስብኝ ሲል፤ ‘እሺ፤ አልኳቸው። ስለ ገለጻቸውና ሁኔታቸው እንዴት አንደነበር ስገልጽ ፤ ‘ምን ድራማ ትሠራለህ!!’ ፤ ፈጠራ እየሰራህ ነው? ብሎ እኔን ሊገድለኝ አሰበና።

እኔ የምነግራችሁ እውነቱን ነው።፡የሆነውን ነው ንገረን ያላችሁኝ፤ የሆነውን ነው እየነገርኳችሁ ያለሁት። ስትፈልጉ እነ እገሌ እነ እገሌ ሙርኮኞች አሉ እነሱን ጠይቁ አልኳቸው። እሺ እንግዲያውስ ብለው፤ ያቀባበሉብኝን አፈሙዝ መለሱት። ወደ ሃርጊጎ ወሰዱኝ። ሬሳ ጠምብቷል፤ መለየት አይቻልም፤ በሺሕ የሚቆጠር ሬሳ ተጋድሟል። ሽታው አያስጠጋም። ከዚያ መፈጠሬን ጠላሁና እነሱን ሳይ፤ ‘ትዝ አለኝ’ እና ‘ለምን በዛው ወቅት ከነዚህ አንዱ ያልሆንኩት!’ የሚል ቁጭት ተሰማኝ። ከዚያ ወደ ናቅፋ ወሰዱኝ።

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

ሙርኰ ህይወትዎ ምን ይመስል ነበር?

መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

የሙርኮ ህይወት፤….. ያው የጦርነቱ ታሪክ እና የመሳሰሉት ቃል እንድሰጥ ወደ ማዕከላዊ ምርመራ ክፍላቸው ወሰዱኝ። ሰፊ አዳራሽ  ነው፤ ከዚያ ከፍተኛ ምስጢር ያውቃሉ ከተባሉት ጄነራሎችና ኮለኔሎች ጋር ደበሉኝ። እዛው የታሰርንበት ቦታ “ምሽግ” ነው። ጥበቃው ሃይለኛ ነው።24 ሰዓት ያለ እረፍት ጥያቄ ላይ ነበርኩ። ከዚያ አስወጥተው ዓራሪ ወደተባለ ወደ ሙርከኞች ቀላቀሉኝ።ከነ ፓይለት ባዘብህ ጴጥሮስ (የበየነ ጴጥሮስ ወንድም) ከእነ ዓሊ ሓጂ ከነ ኮለኔል ግርማ የሚባሉ ከነሱ ጋር ነው የቀላቀሉኝ። የራሺያ ሙርኮኞችም ነበሩ። 1900 የምንሆን መኮንኞች ብቻ ባንድ ቦታ ታስረናል።

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

የርስዎም የመኮንኖችና የሌሎች ምሮኮኝ የለት-ተለት ኑሮ ምን ይመስል ነበር?

 

መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

ሙርከኞው በ4 ደረጃ የተከፋፋለ ነው። ባንደኛ ደረጃ ሞኮንኖች የሚታሰሩበት ነው፤ ሁለተኛ የበታች ሞኮንኖች፤ሦስተኛ የመረጃ ክፍሎች ፤አራተኛ-የደህንንት ሰዎችን ነው በ4 ቦታ መድበው ነበር ያሰሩን። 4 እስር ቤቶች አሉ። እነዚህ እሰር ቤቶች በምንም ታምር አይገናኙም። ቀይ መስቀል ከመጣ እየዞሩ ነው የሚያነጋግሩን። 10 አመት የታሰሩ ሰዎች ያለተገናኙ አሉ።

የሚሰጠው ምግብ፤ ቀይ መስቀል የሚሰጠው ብስኩት አለ፤ የነሱም “ወዲ ዓከር” (ሟሽላ እንጀራ) አለ፤ ቦቆሎ,..

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

ከባድ የጉልበት ሥራስ ያሰሸቅልዋችሁ ነበር?

መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

አዎ፤ ጀኔራል የለ፤ተራ ወታደር የለ፤ ሁሉንም ቀላቅለው ምሽግ ስራ፤እንጨት ለቀማ፤መንገድ ሥራ፤ ሁሉንም ይሰራል። ከዚያ ውስጥ ደግሞ መልምለው፤አደራጅተው አስታጥቀው ወደ “ወያኔ ትግራይ” ይልካሉ። ሙያተኛ፤ የመሳሰሉ እጅ ችሎታ ያላቸው ግን፤ ለነሱ አስቀርተው እንዲሰራላቸው ያደርጉታል። መኮንንም ሆነ፤ ታራ ወታደር’ የመረጃ እና ወታደራዊ የደህንነት የነበረ ግን አይለቁትም ፤ አጅግ ከባድ የሆነ የጉልብት ስራ ያሸቅሉታል፤መንገድ፤የምሽግ የቁፋሩ ስራ ያስሰሩታል። ዕረፍት የለም፤ በቀን እስከ ምሽቱ 10 ሰዓት ያሸቅሉታል። ደም ባፍንጫው እስኪፈስ ያሽሸቅሉታል።ደም ባፍንጫቸው እየፈሰሰባቸው፤ የሚሞቱ ነበሩ።

እዛው አልሰራም፤ ማለት፤አምቢ ማለት፤ መብት መጠየቅ፤ክርክር ማድረግ እዛው መግደል፤መረሸን ነው። እጁ ሥራ ሰርቶ የማያወቅ፤ ስስ አጅ፤ ደግሞ እጁ እየቆሰለ፤እየመገለ በዛው እንዲሰራ ይደረጋል።በጠላትነት ነው የምንታየው።በጣም ዘግናኝ ነው።

በተለይ ደግሞ የአማራ ብሔረሰብ ለብቻ ለይተው ድንጋይ ፍንቀላ እና መንገድ ሥራ ላይ ነው ያስሰማሩት። አማርኛ ተናጋሪ ለብቻ መልምለው፤ እናንተ ናችሁ ለኤርትራ ጦርነት ምክንያት የሆናችሁ ነው የሚሉት።

ለኦሮሞች ደግሞ፤ ሌንጮ ለታ ነበር። ሌንጮ ይመጣል፤ ኦሮሞዎችን አነጋግሮ መልልምሎ ወደ ኦነግ ይወስዳል። ወያኔም የደቡብ ሰዎች፤ማሃል አገር… እነማን አላችሁ ተብለው ተለይተው፤ምን ብለው አንቅቶ፤ ጠመንጃ አስታጥቆ ይወስዳቸዋል። ህወሓት ወስጥ እንደ ወፍ ዘራሽ ተቀላቅለው ይዋጋሉ። ኦነግም እንደዚሁ እያደረገ ይወስዳል። ተቀራመቱት።

እንግዲህ ከሁሉም ብሔረሰብ እስረኛ ግን አማራ ተወላጅ ላይ ጭካኔአቸው ይበረታል። ሲመዘገብ ድግሞ  (ምን አንደሚደርሰው ስላማያውቅ) ነገድህ ተብሎ ሲጠየቅ “አማራ ነኝ” ብሎ ስለሚያስመዘግብ፤ አማራ የተባለ ዘር “ፋይል/ማሕደር’ ለብቻው ተለይቶለታል። በዛ ማሕደር ነው ሲጠቀሙበት የነበረው። በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ እጅግ በጣም የከረረ ነው። አንድ ቃል ከተናገረ፤ መልሱ ጥይት ነበር የሚተኩሱበት።

ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፤

እርስዎ እንዴት አመለጡ?

መቶ አለቃ ታደሰ ቴሌ

እዛው አካባቢያችን ብቻ 30 ሺህ ሙርከኛ ታስረን ነበር። 300 ባንድ ቡድን፤ 300  በሌላ ቡድን እያደረጉ በቡድን ተደርጎ ነው እንጨት ቆረጣ እንድንሄድ የሚደረገው። ወደ ባርካ ወስደው እንጨት ለቀማ ሲያሰማሩን፤ባርካ በደምብ ስለማውቀው -የሱዳን ጠረፍም እስከ ግርማይካ በደምብ ስለማውቀው፤…… ባጋጣሚ እንኔ ሲጠብቅ የነበረ ክላሽን የታጠቀ ሻዕቢያ መኪና እስኪመጣ ጠብቁ ተብለን ስንጠብቅ ብቻችን ስለነበርን፤ ለእንጨት ለቀማ የተሰጠኝን መጥረቢያ ምሳር ስለነበረኝ፤ እርምጃ ወስጄ፤ ጠመንጃውን ነጥቄ ወደ ሱዳን ሸሽቼ አመለጥኩ።ከሰላ ገባሁ፤ ጀለቢያ ለበስኩ፤ዓረብኛ እችላለሁ። ትውልዴም ሱዳን ጠረፍ ጎጃም ክ/ሃገር ‘መተከል’ አውራጃ ወስጥ ተወላጅ ስለሆንኩኝ ዓለብኛ እችላለሁ። ሱዳን እንደገባሁ አምባሲው ኤርትራዊ ስለነበሩ፤ እንዳይዙህ ፎቶግራፍህንም በየቦታው ስለተዘረጋ፤ አደጋ አንዳይደርስብህ ብለው ስሜን “ዓብደላ መሐመድ” ብለው ፓስፖርት አወጡልኝ፦ከዚያ…… ኢትዮጵያ ገባሁ።

እያሉ ጀግናው ኢትዮጵያዊው ታሪክ ከቶውንም የማይረሳቸው የመቶአለቃ ታደሰ ቴሌ ታሪካቸውን እና የኢሳያስ ጭካኔ ነግረውናል።ከላይ እንዳስነበብኳችሁ፤ አውድየውንም ማድመጥ ትችላላችሁ፤ አማራ ላይ ኢሳያስ ምንኛ ጥላቻ እንደነነረውና እስካሁን ድረስ አማርኛ መናገር እየቻለ መናገር የማይፈልግ ‘የቀወሰ ጸረ አማራ ዘረኛ ሰው ነው። ኤርትራኖች አብዛኛዎቹ አማራ የተባለ እንደ ጠላት እየተመለከቱ ስለአደጉ፤ኤርትራኖች ዛሬም ስለ አማራ ማሕበረሰብ ያላቸው ግንዛቤ እጅግ የወረደ ስለሆነ፤ ከብዙ አመት ልምድም መመራመር ያልቻሉ፤ የደደበ ሕሊና ስላላቸው (ምሁራኖቹ በተልይ) አማራውን ለይተው በጥላቻ እንደሚያዩት የሚታወቅ ነው። የሚጽፉትን በዓዋተ.ካም፤መስከረም፤ አሰና፤ አስማሪኖ.ካም ወዲ ኣበት፤ አና በመሳሰሉ ኤርትራ ድረገፆችን፤ እና ፓልቶክ ክፍሎችን አድምጡ።

እንዲያ የሚያንገሸግሽ በአማራ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋት የፈጸመውን ወንጀለኛው ኢሳያስ አፈወርቅን እንደግፍ ብለው ባንዳዎቹ እነ ንአመን ዘለቀ፤ ኪዳነ አለማዮህ የተባለ አዲስ (ዳላስ ውስጥ ኪዳኔ አለማዮህን የሚያውቁ፤ “ነባር ባንዳ” ይሉታል) ባንዳ እና ግንቦት 7 የተባለ የታሪክ ዝቃጭ የሆነ የሻዕቢያ ውሻ፤ በአማራውና በኢትዮጵያዊ ደም በሚያሸፍ መልኩ፤ ኢትዮጵያዊያንን የገደለ፤ባሕር በራችንን ለዓረቦች አሳልፎ የሰጠ፤ ለኢሳያስ ድጋፍ ፌርማ እናሰባስብ ብለው በየድረገጻቸው አሰራጭተውታል። ይህ ደግሞ ማንም ኢትዮጵያዊም ሆነ አማራ የተባለ ነገድ በእነዚህ አሳፋሪ የሻዕቢያ መልዕክተኞች ላይ የሚሰሩት ስራ እየተከታተለ እንዲያከሽፈው ጥሪዬን አቀርባለሁ። ”አይ ምፅዋ ደራሲ ታደሰ ተሌ (ከሞላ ጐደል ታሪኩን ላምነበብ Tuesday, November 11, 2008 (Ethiopian Semay) የታተመወን ታሪክ ያንብቡ) https://ethiopiansemay.blogspot.com/2015_03_27_archive.html

አንድ ቀን ጊዜው ሲደርስ እነኚህ ባንዳዎችና ኢሳያስ አፈወርቅ ለፍርድ ይቀርባሉ።


‘ጠላት ምንጊዜም ጠላት ነው፤ አስቀድሞ መግደል አሾክሻኪውን ነው’። የመሚለውን የወላጆቻችን ትምህርት ትዝ ይላችሗል? ወላጆቻችን ያለምክንያት እንዲህ ያለ ግጥም አልገጠሙም። ባንዳ ከጠላት በላይ አደገኛነቱን ለማሳየት ነው። እነሆም ዛሬ አደገኛነቱን እያየን ነው። ጽሑፎቼን ለማንበብ ከድረገጼ ሌላ በ welkait.com በ Ethiopatriots.com ድረገጾች ተከታታሉ። እነዚህ ድረገፆች የትም የማይገኙና የማይለጠፉ ማሕደሮች የሚመዘገብባቸው ድረገጾች ናቸው።አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ Ethio Semay) getachre@aol.com