የእስክንድር ነጋ አጣብቂኝ የመጀመሪያ ግርዶሽ የሕዝቡ አደርባይነት ነው
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
8/12/22
የእምዬ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ
እስክንድር ነጋ በትግሬ የፋሺሰቶc ሥርዓት (27) አመት፤ በኦሮሞ
ፋሺሰታዊ ሥርዓት (3) አመት ጠቅላላ በ30 አመት በፋሺሰቶች ዘመን ውስጥ ሲታገላቸው፤ ሲያስሩት፤ ሲደበድቡት፤ ሲያንገላቱት፤ ሲሰድቡት፤
ስሙን ሲያጠፉትና ዕድሜ ይፍታ ሲበይኑበት የኖረ እርሱን መሳይ ለማግኘት የሚቸግር፤ ብቅ ብላ እንደምትሰወር ብርቅ የመስከረም ወፍ አይነቷ ፍጡር ነው።
ይታያችሁ' እስክንደር በይሁዳዎቹ
የብረት ብትር እየተቀጠቀጠ ይህንን መስዋእት ሲከፍል ባለቤቱና ልጁን ለፈጣሪ አስረክቦ ስለ ሕዝብ እና አገራዊ ልዕልና ነበር። ታዲያ
ምን ያደርጋል ሕዝቡ ከዳው!!
አንዳንድ ጭቃ ሕሊናዎች “ከጋዜጠኛነት
ወደ አክቲቪሰትነት” መዞሩ ለውድቀቱ ምክንያት ተከታይ አጥቷል እያሉ ጭቃ ሲያቦኩ አደመጥኩ። ይገርማል። ጋዜጠኛም ሆነ አክቲቪስትና
ፖለቲከኛም ሆንክ ፀሐፊ በቁሙ የሞተን አሕያ መጎተት አስቸጋሪ መሆኑን አላወቁም ። ማፊሪያው የኢትዮጵያ ወጣት “በቁሙ የሞተ አጋሰስ ነው” ከዳውና ብቸኛነት
አጠቃው! በመጨረሻ አበቃ! እሰይ አንኳን በቃኝ አልክ! ለዚህ ከዳተኛ እና አድርባይ ሕዝብ መስዋእት መሆን በፍጹም የማይገባውና
ባርያ የሆነ ማሕበረሰብ ቤዛ መሆን አያስፈልግም!
በጣም አዘንኩ! ዕምባ፤ዕምባም አለኝ!
እንዲህ ያለ ቆራጥ ፍጡር ለሕዝብ ብሎ ሲሞትለት ፤በማዶ ቆሞ የሚመለከት ማሕበረሰብ ለባርያ ገዢዎች ሰጥቶ መቀመጥ “አማራጭ የለውም”።
ይቀጥቀጥ ፤ይሙት ፤ በመኪና ይጎትሩት የራሱ ጉዳይ!
ይህ ልፍስፍስ የ30 አመት ትውልድ
ስንት ታጋይ ቆሞ አስበልቷል። ከዚህ ወዲያ ቆራጥ አታጋይ ከየት አባትህ
ሊፈጠርልህ ትሻለህ? አዲስ አበባ መግባት መከልከል ቀርቶ ሚሰትህን
ነጥቆ ቢያማግጡልህም በቁጭት የማትነሳ እንሰሳ ሕዝበ ነህና ‘መቸውም ጊዜ ከባርነትህ አትላቀቅም፤ የባርነት ምቾትህን እንደተመቸህ
ተመችቶህ ይኑር! ለዛውም ጥናቱን ይስጥህ!
እስክንድር በቃኝ ማለቱ ግን እንዳውም
ዘግይቷል። ለዚህ በቁሙ የሚጎተት “ላም” እንዲያ ያለ አርበኛ አይገባውም!
እስክንድር በፅናትህ መስክረናል! ዓለም አውቆሃል! ሽልሞሃል! ባንተም ኮርተናል! ባለህበት ሁሉ ሰላም እና
ምቾትና ጤና እመኝልሃለሁ፤
እኔም እንዳንተው ብዙ ጊዜ አሰኝቶኝ
ነበር ፤ አላስችል እያለኝ እምላለሳለሁ፡ ይኸየው አለሁ፡ አንድ ቀን አንተኑን እከተል ይሆናል። እኔም አንድ ቀን በቃ ማለቴ አይቀርም።
ጥቂቶች እየተቃጠሉ ቆሞ የሚያይ ባርያ ሕዝብ የሕሊና ቁስል ነው።
ይህ የባሮችና የባርያ ገዢዎች ዘመን
አልፎ እኔም አንተም አንድ ቀን በአካል ለሁለተኛ ጊዜ እንገናኝ ይሆናል!
ይህችን ለእስክንድር ባለበት አድርሱልኝ!
ጌታቸው ረዳ ነኝ
የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ
8/12/22
Ethiopian Semay