የበጎችን በር ሰብረው የገቡት የአብይ
አሕመድ ቶክላዎችና የ80 አመትዋ አዛውንት እምባ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
October 24/2020
ከዚህ በታች ተያይዞ የምታዩት ስዕለ ደምፅ “የ80 ዓመትዋ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነዕቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ” በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የእዮሃ ሚዲያ” ዘጋቢ “ተሻገር ጣሰው” ኢትዮጵያውያን እንድንመለከተው የዘገበው አሳዛኝ እና የአብይ አሕመድ አፓርታይዳዊ የናዚ ሥርዓት ኦሮሙማው ብልጽግና የማን አለኝህን “የግፍ” እርምጃዎችን የሚያሳይ የዛሬ የመነጋገሪያ አጀንዳ አድርጌ አቅርቤዋለሁ።
በዘገባው ውስጥ የምታደምጥዋቸው እኚህ የ80 አመት ሴት አዛውንት ኦሮሙማው አስተዳደር አዲስ አበባ ውስጥ የተወሰኑ ብሔረሰቦችን ከሚኖሩባቸው ቤቶቻቸው በሃይል በማስወጣት በመንግሥት ሥልጣን ያለ ሕግ የተኮፈሰው የ አፓርታይዱ የኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ “ፍንፍኔ” ብሎ በሚጠራት አዲስ አበባ ኦሮሞዎች ብቻ እንዲሰፍሩባት ባቀደው መሰረት በሁለት አመት ተኩል ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን በዘረኛነት ፖሊሲው እየተመራ ወደ በረንዳ በመጣል የዜጎቻችን የሲኦል ኑሮ እንዲኖሩ እያደረገ ነው። በአፓርታይዱ ኦሮሙማው የጥቃት ኢላማ ቅደም ተከተል ቀዳሚው አማራ ቀጥሎ የደቡብ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ ተብለው ግፍ ከሚፈጸምባቸው ቀዳሚ ናቸው።
የናዚ ጀርመን የመጀመሪያ የጀርመን ዘር ጠላት ተብሎ የተቀመጠው አይሀዱ ማሕበረሰብ ሲሆን የተቀሩት እነ ፖል ሮማኒያ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች እንዲሁም አካለ ስንኩላን ወዘተ መለያ ቁጥሮች እና ቀለሞች ነበራቸው። አሁንም አገራችን ውስጥ በተመሳሳይ ስልት የለየለት የወንጀለኞች ጥርቅም የሆነው የብልጽግና አፓርታይዱ የአብይ አሕመድ ድርጅት “አማራን፤የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፤ ምሁራንን እና አረጋውያንን” በቀየሰላቸው የማጎርያ ቦታዎች ቀስ በቀስ ያለማቛረጥ ሁለት አመት ሙሉ ወደ ምድር ሲኦል እንዲጣሉ እያደረገ ነው። ለምሳሌ በናዚ ጀርመን ወቅት “ኦሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ” (Auschwitz concentration camp) ተብሎ የሚታወቀው ስቃይ የሚካሄድበት እስር ቤት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የፖለቲከላ ተቃዋሚዎቹን ሰብስቦ ማአከላዊ እና ቅሊንጦ በማጎር በኮቪድ ቫይረስ በሽታ ከተበከሉ እስረኞችና ተራ ወንጀለኞች ጋር ቀላቅሎ ሞራላቸው እንዲነካና በበሽአውም ተበክለው እንዲሞቱ ያስራቸዋል። አደገኛ የሆነው የልብ ሕመም ያላቸው እንደ እነ ልደቱ አያሌው የመሳሰሉ ትንታግ ፖለቲከኞችን እንዳይፈቱ በማንገላታት ልክ እንደ ፕሮፌሰር አስራት በዘዴ እንዲሞቱ እንደተደረገው ልደቱ አያሌውም ያንን የሞት ጽዋ እንዲደርሰው እየተደረገ ነው። ይህንን በሚመለከት በማዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ ልደቱ እና አስራት የአያያዝ ስልት ተመሳሳይነት በሰፊው አቀርባለሁ።
ተቃዋሞዎችን በዚህ መልክ ሲያጉራቸው፤ አረጋውያን ደግሞ ከሚተኙበት አልጋ እየጎተተ በለበሱት አንሶላ እንደ ዕቃ ጠቅልሎ ደጅ ላይ እንዲጣሉ ተደርገው በረንዳ አዳሪ እንዲሆኑ እያደረገ ነው።
በሚገርም አጋጣሚ ይህን ጽሑፍ ስጽፍ ፤አሁን በካሊፎርኒያ ሰዓት አቆጧጠር 6:25 PM ላይ አንድ አረጋዊ ስለተሰወሩና ስለደህንነታቸው ስላሳሰበን ዜጎች ሁሉ እኚህ አዛውንት ካገኛችሗቸው ባስቸኳይ ለፖሊስ በመደወል አሳውቁ የሚል “ብሩራዊ የአደጋ ማስጠንቀቂያ” (ሲልቨር አለርት ኢመርጀንሲ”_የሚል የስልክ ደወል ተደውሎልኝ ባየሁ ወቅት ፤በተጸራሪ በዚህ ቪዲዮ የምትመለከትዋቸው የ80 ዕድሜ አዛውንት ሴት ታመው አልጋቸው ላይ ጋደም እንዳሉ እንዲህ ያሉ ጠበቃ እና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው አቅመ ደካማ የአዛውንት በር ሰብረው የገቡት የአብይ አሕመድ ቶክላዎችና የ80 አመትዋ አዛውንት እምባ እያወዳደርኩ ስጥል ሳወርድ ‘ኢትዮጵያውያን እንዲህ ያሉ የአፓርታይድ እንሰሳዎች እንዴት እንደምንገላገላቸው ሳስበው ኣእምሮየ ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል’።
“የ80 ዓመትዋ አዛውንት ከሚኖሩበት
ቤት ከነዕቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ” የሚል ዘገባ ስትመለከቱ ምን ተሰማችሁ? እስኪ ሼር አድርጉትና የግፉ ብዛት ምን
ድረስ እንደደረሰ ሰው ሁሉ ይመልከተው። ባንድ ወቅት የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ዲስሞን ቱቱ አፓርታይዱን ስርዐትና ፤ ልክ እንደ
አብይ አሕመድ “የጥገና ለውጥ” አራማጆቹ ለሚደግፉ ደጋፊዎች እንዲህ
ብለው ነበር "We don't want our chains made more comfortable, we want it to be
removed" ሰንሰለቶቻችን እየላሉ የበለጠ እንዲመቹን ሳይሆን ጭራሽኑ እንዲወገድ እንፈልጋለን” ብለው ነበር። እኛም በተራችን በሕዝባችን እግሮች ላይ የተቆለፉት የኦሮሙማ ብልጽግና ፓርታይድ የማሰቃያ የእግር በረቶች
እንዲላሉ ሳይሆን ተሰብረው እንዲጣሉ ነው።
ሼር ለምታደርጉት ሁሉ በአዛውንትዋ
ስም እና በዘጋቢው ተሻገር ጣሰው አመሰግናለሁ።የ80 ዓመቷ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነእቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ!!
| ተሻገር ጣሰው!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
October 24/2020