Wednesday, December 23, 2020

አብይ አሕመድ ዓሊ የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ እንጂ መሪ አይደለም! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay Wedensday, December 23, 2020

 

 

አብይ አሕመድ ዓሊ የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ እንጂ መሪ አይደለም!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Wedensday, December 23, 2020

ከመገረሜ ብዛት ከመጻፍ ልቆጠብ እልና አላስችል ይለኛል።  የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ያስናቀው ለ30 አመት በመላዋ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በኦሮሞዎቹ ክልል እና በጉሙዞች መተከል ውስጥ እየተካሄደ ያለው በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየባሰ የመሄዱ ጉዳይ ስመለከት አንጀቴ “እሬት” እስኪተፋ ድረስ ያቅረኛል። ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲካሄድ መንግሥት ማስቆም ያቃተው እንዳይመስላችሁ። አብይ እየመራው ያለው የ3 አመት አገር በቀል የቅኝ ግዛት አስተዳደር ነው ብየ እስኪደክመኝ ድረስ ጽፌኣለሁ። አብይ ስለ አማራ በተመለከተ ሲናገራቸው የነበሩት ንግግሮቹ ወደ ሗላ መርምሩዋቸው። ሃቁን ከምላሱ ታገኙታላችሁ።

 

 ክስተቱ 27 አመት በትግሬዎች 3 አመት በኦሮመዎች እጅ የወደቀች አገር ምስጢሩ “የተረኛ ቅብብሎሽ ምስጢር” መሆኑን ማየት ምትችሉት ዘር ጥቃት እና ግድያዎች እየተባባሱ እንጂ መቆማቸው እንዳልሆነ በቂ ማሳያ ነው። ለዚህ ከስተት ደግሞ “ተቃዋሚ ተደማሪ” እየተባሉ የሚጠሩት ወደ ነዳሃቸው የሚነዱ በጎች ለውጭ አገር ለተረኛው ንጉሥ ለአብይ አሕመድ ከፈተኛ ድጋፍ እና ድምጽ በመስጠት አማራ እንዲያልቅ ተጨማሪ እሾሆች መሆናቸውን አትዘንጉ። ተርኞቹ ዛሬም አጨብጫቢ አላጡም። በትንሽ ነገር ይረካሉ በትንሽ ነገር ያፍራሉ።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ፋሺሰት አገር ገንጣይ መሪዎች እና በኦሮሙማው ፋሺሰቱ መሪ ኮ/ል አብይ አሕመድ “ቸልተኝነት ምክንያት” የተከሰተው ጦርነት ያስከተለው የሰው እና የንብረት ጥፋት አስቀድሞ መቆጣጠር ወይንም መቀነስ ይቻል እንደነበር ብዙ ምክር ቢሰጠውም ያንን ካለመቀበል አሁን ላለው ዕልቂትና የውጭ አገር ከበባ ዳርጎናል። በሚገርም ሁኔታ ዛሬም እንደ ባድሜው “ካድሬዎቹ” ያለምንም ሓፍረት በባድሜ ጦርነት ከሚገባው በላይ ለመለስ ዜናዊና መሰሎቹ የተቸረው “ኢትዮጵያ ጀግኖች ” እያሉ በውሸት ሰንደቃላማችንን ስያውለበልቡ በነበረበት ወቅት ሲቸራቸው የነበረው “ኢትኦጵያዊነት” የመሆን ጋጋታና ሙገሳ ልክ እንደዛው ሁሉ ዛሬ ያንኑ ስዕል ለአብይ አሕመድ ተችሮታል።

 

 እነ እስክንድርን እና እነ ልደቱን እንዲሁም ብዙዎች ብርቱ እህቶቻችንን እስር አስገብቶ በሽብር በመወንጀል ማሰቃየቱን እንድንረሳው ለማድረግ ያንን ወንጀለኛ እና ቅጥረኛ ውሳኔውን ወደ ጓዳ ገሸሽ ተደርጎ “አብይየየየ ኢትዖጵያዊየየ! መሪየየየ” እያሉ የሕሊና ቀውስ ያሰቃያቸው የፌስቡክና ዩቱብ “ዕብዶች” ሲያቆላምጡት ሰምተናል። ይህ የሚያሳፍር “የማሽቃበጥና የማንቛለጥ”ታሪክ እንደገና ያፈርንበትን እንደገና ተደጋግሞ የመደገሙ ክስተት ምን ማድረግ እንደሚሻል ግራ ገብቶኛል።   

 

ፒየር በርጌሮን የተባሉ ቄስ ይሁኑ ዳኛ ብቻ እንዲህ ያሉትን “ቅጠረኛ እና እረኛ” ልይነቱ  ምንድነው? በሚል የጻፉት አንብቤ ልቤን የነካው አባባላቸው ላጋራችሁ። እረኛ የሚሉት “እየሱስን ነው”፡ ቅጥረኛ ደግሞ በገንዘብ ወይንም በሥልጣን የተደለለ የውጭ ተላላኪ፤መሰሪ፤የጥፋት ሃይል፤አታለይ ማለት ነው።፡እንዲህ ይላሉ፡እረኛው ለመንጋው  በፍቅር እና በፍላጎት ሲያገለግል በሌላ በኩልአገልግሎቱን ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞችና ስምምነቶች የሚሸጥቅጥረኛእንጂ የሕዝብ እረኛ ሊሆን አይችልም ፡፡” ይላሉ፤ እውነት ነው።

 

 አንድ ቅጥረኛ አገልግሎቱን ከሸጠላቸው ሰዎች ጋር የተለየ ስሜትና ዝምድና አለው እረኛው ደግሞ ለመንጋው ሙሉውን ልብ በመስጠት እለት ከለት ደቂቃ በደቂቃ በጎቹ በአራዊት እንዳይበሉ በጋለ በፍቅር ይከታተላል፤ይከላከልላቸዋል። ዘርዘር አድርጌ እንዲህ ላስቀምጠው። በአንድ አገር አደጋ ወይም ችግር በሚመጣበት ጊዜ የቅጥረኛው ተሳትፎ ውስንነቶች አሉት፡ አንዴ ወዲያ አንዴ ወዲህ የማለት ሸንጋይነትና፤ ወላዋይነት ባሕሪ በመያዝ ውሳኔዎችን በማቅማማት ጎርፉ “በርትቶ እንግዳ ደራሽ” እስኪሆን ድረስ ይጠብቃል። ምክንያቱም ህይወቱን እና ምቾቱን ከቀጠሩት ሰዎችና ከሚፈልጋት አልጋ (ዙፋን) ጋር የተያያዘ ነው ፡፡

 

በተቃራኒው እረኛው ሙሉ በሙሉ መንጋውን ከአደጋ ለመዋጋት ቁርጠኛ ነውና በጎቹን ለመጠበቅ የበጎቹ እንቅስቃሴዎችና የአራዊት ኮሽታዎችን ለመመዘን ሁሌም ዝግጁ ነው ፡፡ እንደ አብይ አሕመድ ያለው ኩሌ/ቅጥረኛው (ባጭሩ) በሰዎች ላይ (የአማራ ማሕበረሰብን ህይወትና ሰቆቃ) ምንም ልዩ ፍላጎትና ትኩረት ሳያድርበትዙፋኑና የከተማ ውበቶችን ብቻ “በእዩልኝ እዩልኝ” ያተኮረ ነው።

 እረኛው መንጋውን ስለሚመራ በየደቂቃው  ምግብን መመሪያን እና ጥበቃን” ይሰጣል ፡፡ እጅግ የሚያሳዝነኝ ግን ወታደሩ ለናት አገሩ ሲል በተጠራበት ወቅትና ደቂቃ በፅናት እና በክብር መስዋዕት ለመሆን ዋጋ ለመክፈል የማይፈሩ  ታማኝ ወንዶች እና ሴቶች ወታደሮቻችን ሁሌም አንጀቴን ይበሉታል።  ኢትዮጵያ አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ምንሊክ ቤተመንግሥት ውስጥ አብይ አሕመድን የሚተካ አውነተኛ ዕረኛ ትፈልጋለች ፡፡ ከሕግ ይልቅ ክብር ያለው ነገርራስን ከማገልገል ይልቅ የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ ምን ማለት ነው  እንደሆነ የሚያሳየን እረኛ እንሻለን፡፡ አመሰግናለሁ ፡ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethiopian Semay