Monday, June 9, 2014

በዕውነት ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም? (ተክሌ የሻው፣የግል አስተያዬት)

 Ato Tekle Yeshaw Moresh Amara Chairman


ከአዘጋጁ ማስታወሻ፤

ጌታቸው ረዳ
በዚህ የአዘጋጁ ማስታወሻ አብርሃ ደስታን እና ፕሮፌሰር መስፍን እንዳስሳለን። ከኔው ካዘጋጁ የሚቀርበው ከላይ የጠቀስኳቸውን ፖለቲከኞች የተንሻፈፈ አቋማቸው ባጭሩ ሳቀርብ ዋው ትችት ግን”

  በዕውነት  ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ  በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም?

                                                      (ተክሌ የሻው፣የግል አስተያዬት)
በሚል ርዕስ የሞረሽ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም«  መልስ የሰጡበት ሰነድ ለዛሬ እንድታነቡ አቅርቤአለሁ። ስከዚያ በፊት ግን “የትግራይ ሕዝብ በብዙ መንገድ በህወሓት ሥልጣን መያዝ ተጠቀሚ ነው” ብለን የምንከራከር ሰዎችን የሚከራከሩን እና የሚሰድቡን (ለምሳሌ አብዛኛዎቹ የዓረና መሪዎች፤ አቶ በርሃኑ በርሐ እና አብርሃ ደስታ የተባለው፡ ”የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች/ ወይንም ደርጎች/ጽንፈኞች ናቸው እንዲህ የሚል መከራከሪያ ያላቸው” በማለት ሲዘልፈን መኖሩን ካሁን በፊት በራሴ ጽሑፍ ጠቅሼአለሁ። የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ “የፖለቲካ ጥናት አስተማሪ” የሚባልለት አብርሃ ደስታ “የትግራይ ሕዝብ ከደርግ ጊዜ ከነበረበት ብዙ የሚለይ አይደለም” (ሰብአዊ ነክ በሚመለከት) በልማቱም ጭምር “ህወሓት ለትግራይ “ምንም” የሰራለት ነገር የለም በማለት ሕዝቡ ይነግረናል” በማለት የኢሳያስ አፈወርቂ የግል አሽከር የሆነው የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ከአስመራ የተናገረው ትከክለኛ ቅጅ አብርሃ ደስታም ያንኑ “ዓይን ባወጣ” ድርቅና በመድገም ይከራከራል።

ብዙ አክብሮት ጥየባቸው የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ደግሞ ከባዶ ጋኖቹ ተቧድነው፤በባሰ መልኩ ( በግላቸው በአርአያነት የሚጠቅሷቸው ከ5 ሚሊዮን ትግሬ ውስጥ ፕሮፌሰሩ ሦስት አርአያዎች ብለው የሚጠቅሷቸው ‘አብርሃ ደስታ፤ ገብረመድህን አርአያ እና ደ/ር አረጋዊ በርሔ) በጐረነነ ጽሑፋቸው “አዲስ አበባ ውስጥ የሚለምኑ ትግሬዎች ስላሉ፤ትግሬዎች በህወሓት ዘመን አልተጠቀሙም” እያሉ መጐርነን ጀምረዋል። 

በደርግ ጊዜ የህወሓት ሊቀመንበር የነበረው ስብሓት ነጋም እኮ 

ከበረሃ በድብቅ ወጥቶ ወደ አዲስ አበባ በድብቅ በመግባት ለአንድ ኮለነሌ/ጀኔራል 

በዘበኝነት ተቀጥሮ የስለላውን ሥራ እየሰራ ለሦስት ወር ኖሯል። 

ከኔ መረጃ ሌላ የአቶ ተክሌ የው ወደ ታች ሌላ የልመና ድብቅ ሰነድ ያቀረቡትን 

ታሪክ ታያላችሁ። 

 ሲ ኤስ ቢ በተባለው አውስትራሊያ የሚገኘው በአቶ ካሳሁን ቸኰል የሚዘጋጅ የአማርኛ ራዲዮ ቀርቦ ሰሞኑን  አቶ አብርሃ  ደስታ “የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ዓረና አባል እና ደጋፊ ነው“ ብሎ ሲነግረን ባንድ በኩል ደግሞ ወዲያውኑ የተናገረውን በመቃረን “መገናኛ ሚዲያ ስለሌለን ከሕዝቡ ጋር ብዙ መገናኘት አልቻልንም” ይላል። የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ይቃወማል ይለናል፤ “አብዛኛው” የትግራይ ሕዝብ የዓረና አባል እና ደጋፊ እየሆነ ነው’ ይለናል፤ ታዲያ ሕዝቡን መገናኘት ችግር ካላቸው ‘ እንዴት ሆኖ ነው “አብዛኛው ሕዝብ  የዓረና አባል እና ደጋፊ ነው” የሚለን?   የዓረና ማኒፌስቶ ቅስቀሳ ወረቀት የገጠሩ ሕዝብ አግኝቶ የማንበብ እና የማወቅ ዕድል በፖሊሶች እየተከለከለ ነው፤ ወደ ገጠር ዝልቀን መግባት አንችልም፤ እያለ እየነገረን ‘ እንዴት “አብዛኛው ትግራይ ሕዝብ የዓረና አባል እና ደጋፊ ሊሆን እንደቻለ ለኔ “አንቆቅልሽ፤እውን፤ ፕሮፓጋንዳ”? የትኛው ነው?
የሆኖ ሆኖ የሰለቸኝ ትችት እዚህ ላቁም እና “በዕውነት  ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ  በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም?” ወደ ሚለው ክርክር ልውሰዳችሁ፤ እነሆ እንዲህ ይነበባል።  በዕውነት  ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ  በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም?
                     (ተክሌ የሻው፣የግል አስተያዬት)
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም«የወያኔ ጥላቻ ፍሬ» በሚል ርዕስ የጻፉትና በተለያዩ ድረ-ገጾች የወጣው ነው። ፕሮፌሰሩ በዚህ ፍሑፋቸው፣ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም፤ ተጠቃሚዎቹ «ጥቂቶች ናቸው» ብለው የደመደሙት ሀሳብ ዕውነት አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ክህደት በመሆኑ፣  ትግሬዎች በዘመነ የወያኔ አገዛዝ  እንዴት ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ተጨባች ነቃሾችን በማቅረብ የፕሮፌሰር መሥፍንን ሀሳብ መሞገት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ነው።

ሰዎች በሙያቸውና በሚያውቁት ቢናገሩና ቢጽፉ አድማጭ ያገኛሉ። ሥራቸውም ለትውልድ የሚቆይ ይሆናል።  እነርሱም አክብሮትና ሞገስን ያተርፋሉ። በዚህ ረገድ፣ ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም፣ የእኔ አስተማሪዎች አስተማሪ፣ የኢትዮጵያ ጂኦግራፊ ለአንደኛ ዓመት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መማሪያ (Introduction to Ethiopian Geography) የኢትዮጵያ አትላስ መጽሐፍት ጽፈው ተምሬባቸዋልሁ። ከዚያም በማከታተል ስለሶማሊያ የአፍሪካ ችግር መሆን፣ ስለድርቅ፣ የጻፏቸውን አንብቤአለሁ። «የክህደት ቁልቁለት»ን፣ «መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ»ን፣ «ሥልጣን ባህል አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ»፣ «አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ»----- » ወዘተ የመሳሰሉትን ሥራዎቻቸውን አንብቤ ይጠቅማሉ ያልኳቸውንም ሀሳቦች ቃርሜባቸዋለሁ። በነዚህ ሥራዎቻቸውም የሚከበሩ ናቸው። እኔም የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ አክባሪያቸውና አድናቂያቸው ከሆኑት አንዱ ነኝ።
  
ለነገሩ እኔ በሙያው ለትውልድ የሚበጅ፣ በሕይዎቱ ያለፈባቸውን ገጠመኞችና ከሙያው ጋር የተያያዙ መጻሕፍትን የሚጽፉ ሰዎችን አከብራለሁ፣ አደንቃለሁ። በዚህ ረገድ ትውልድ ያስተማሩትን  አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌን፣ አለቃ ደስታ ተክለወልድን፣ ከበደ ሚካኤልን፣ ተክለፃድቅ መኩሪያን፣ ሀዲስ ዓለማዬሁን፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን፣ ፕሮፌሰር ሰርግው ሀብለሥላሴን፣ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴን፣  ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን፣ ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያትን፣ ደጃዝማች ግርማቸው ተክለ-ሐዋርያትን፣ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸውን፣ ብላቴን ጌታ መርስዔ-ሀዘን ወልደቂርቆስን፣ ነጋድራስ ገብረሕይዎት ባከዳኝን፣ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረየሱስን (በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ልብ ወለድ መጽሐፍ «ጦቢያን» የጻፉ)፣ ለማ ፈይሳ?(የለማ በገበያ፣ለማ በትምህርት ቤትና ለማና ዘመዶቹ ጸሐፊ)፣  አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራን፣  አሰፋ ገብረማርያን (እንደወጣች ቀረች)፣  ወዘተ ወዘተ ሌሎች ምን እንደሚሏቸው ባላውቅም፣ እኔ ግን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ፣ በራሳቸው ቁጥጥር ሥር ባሉ ጉዳዮች ላይ ቁርጠኛ ውሣኔ ወስነው ለትውልድ ይጠቅማል ያሉትን የጻፉ ስለሆነ አከብራቸዋለሁ። አደንቃቸዋለሁም። የአድናቆቴ መሠረትም ሥራዎቻቸው መሆኑ ይያዝልኝ።
  
ሮፌሰር መስፍን የማደንቃቸው መምህር ቢሆኑም ከእውነታ ውጭ የሆኑ ሐሳቦችን ከቅርብ ጊዜ  ወዲህ ማስተላለፋቸው እየገረመኝ መጥቷል።  የሌላውን ችግር ሳይረዱ ስደተኛውን «ሆዳም፣ ይዞት የተሰደደው የሆዱን ብቻ ነው» ብለው የዘለፉበትን ጽሑፍ አንብቤ እጅግ አሳዘኑኝ። «የወጥን ጣዕም የሚያውቅ፣ ዞሮ የቀመሰ ነው» እንዲሉ፣ ስደተኛው ይዞት የተጓዘው የአመጋገብ ባህሉን ብቻ እንደሆነና ሆዱንም እንደሚወድ አድርገው መጻፋቸው በዕውነት፣እርሳቸው የገለጹትን ዓይነት የምግብ ዓይነቶች በልተው የሚያድሩ ስደተኞች የእርሳቸውን ቃል ልዋስና «በጣም ጥቂት »ናቸው። እንኳን ሊበሉት ስሙንም ከእርሳቸው የሰሙ ብዙዎች እንደሆኑ እገምታለሁ። ሁሉንም ዓለም ዞረው ያዩና የምግብ ዓይነቱን የቀመሱ እርሳቸው ስለሆኑ፣ ጉዳዩ «በፋሲካ የተሸጠች ባሪያ ሁልዜ ፋሲካ ይመስላታል»« ዓይነት ነው። በባህላችን ለእንግዳ ከዘወትሩ የተለዬ የምግብ ዝግጅት ይደረጋል። ተጋባዡም ቤተሰቡ አዘውትሮ ያን ዓይነት ምግብ ይመገባል ብሎ አያስብም። ካሰበ ያ ሞኝ ነው። የምግብ ዓይነቶቹን በሆቴሎች ያዩት ከሆነ ያ ሌላ ጉዳይ ነው። ሆቴል አዘውትሮ የሚመገብ ስደተኛ አለመኖሩን ይስቱታል አይባልም። በመሆኑም ስደተኛውን በሞጭ «ሆዳምና የሆዱን ብቻ ነው ይዞ የተሰደደ» ከሚያሰኝ መደምደሚያ ላይ አያስደርስም።

በአገሩ መኖር የሚችልበት ሁኔታ አጥቶ (በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ችግሮች) የተሰደደውንና እንደርሳቸው ረጅም የረፍት ጊዜ አጥቶ ሲዋትት የሚኖረውን ስደተኛ ደጋግመው ሲሰድቡት በማንበቤ ኅሊናዬን አቁስለውታል። አንዱ ስደተኛ በመሆኔም ዘለፋው በቀጥታ  ይመለከተኛል። በመሆኑም በአባባላቸው አዝኘባቸዋለሁ። ልብ ባይሉት ነው እንጂ፣ ስደተኛው ይዞት የተሰደደው የአመጋገብ ባህሉን ብቻ አይደለም። ሃይማኖቱን፣ የመከራና የደስታ መግለጫ ወጉን፣ አገሩን በልቡ፣ ባንዲራውን በእጁ፣ ባንገቱ፣ በኩታው በቀሚሱ ባልጋው፣ ወዘተ ይዞ የሚዞር፣ የአገሩ ጉዳይ የሚያብከነክነው፣ ለውጥ ለማምጣትም እርሳቸውን የመሰሉ ፖለቲከኞች አምጣ የሚሉትን ከልጆቹ አፍ እየነጠቀ የሚሰጥ ነው። የአገር ቤት ዘመዶቹ የዓመት ልብስ የዕለት ጉርስ ነው። እርሳቸው ይህን ዋቶ አዳሪ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እንደውሻ ቁጢጥ ብሎ የተቀመጠን ሰው፣ አንድ ቢሉ «ሆዳም» ይሉታል። ሁለት ቢሉ «በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎች ትግሬዎች ተጠቃሚዎች ናቸው እያሉ ይጮሃሉ» ሲሉ የዕውነት ጠበቃ የሆኑ ሰዎችን በድፍን ዘልፈዋል። በገሐዱ ዓለም የሚታዬውን፣ የኤቨረስት ተራራን ያህል የገዘፈውን፣ ባለቤቶቹ ያላስተባበሉትን፣ ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓይኑ አይቶ በእጁ የሚዳስሰውን እጅግ ጉልህ ነገር፥ «ሁሉም ትግሬዎች ተጠቃሚዎች አይደሉም፤ ተጠቃሚዎቹ ጥቂቶች ናቸው፣ እንዳውም የትግራይ ሕዝብ መደኸየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም ተሳቆ ነው፤» በማለት ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ አገዛዝ እንዳልተጠቀሙ የሰጡትን የክህደት ምስክርነት «የወያኔ ጥላቻ ፍሬ» በተሰኘ ርዕስ የጻፉትን አንብቤ ታዝቦ ማለፍን አእምሮዬ አልፈቀደም። በመሆኑም መነሻና መድረሻ ሀሳባቸው የተዛባ ብቻ ሳይሆን፣ ክህደት ስለሆነ ሳልወድ በግድ እንደ አብዱራህማን አህመዲን ጎልዳፋ ብዕሬን አነሳሁ። በዚህ አባባላቸው ትግሬዎች ይታዘቧቸዋል እንጂ፣ ፕሮፌሰር መሥፍን ዕውነት ተናገሩ እንደማይሏቸው እርግጠኛ ነኝ። ድርጊቱ ከአድርባይነት አልፎ ፍጹም ክህደት መሆኑን ያውቁታልና!

ለዚህ አባባሌ አንድ ተጨባጭ ምሳሌ ልስጥና ልለፍ። አንድ ትግሬ በዘመነ ደርግ ካገሩ ወጥቶ በአሜሪካ ይኖር ነበር። ወያኔ ሥልጣን ሲጨብጥ ጓዙን ጠቅሎ አዲስ አበባ ይገባል። መንግሥቱ የትግሬዎች ነውና ያላንዳች ውጣ ውረድ በፈለገው የንግድ መሥክ ተሠማርቶ አሁን አንቱ ከሚባሉት ሀብታሞች (በእኔ እምነት ሠርተው ያላገኙት ሀብት በመሆኑ ዘራፊዎች እላቸዋለሁ) አንዱ ነው። ይህ ሰው ለእረፍትና ለመዝናናት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ብቅ ይላል። ኢትዮጵያውያን እንደዛሬው ሳይፈራሩና ሳይጠራጠሩ ካሻቸውና ከመሠላቸው ሰዎች ጋር ጓደኝነት ይመሠርቱ ስለነበር፣ የድሮ አብሮ አደግ ጓደኛ የሆነችውን ከዐማራ ነገድ የምትወለድ ያገኛታል። እርሷም በተለመደ የአብሮ አደግነት ትውውቋና ኢትዮጵያዊነት ስሜቷ፣ በአእምሮዋ የሚብሰለሰለውን የኢትዮጵያን መጥፋት፣ በዐማራው ላይ የተከፈተውን የጥፋት ዘመቻ አንስታ፣ «ለምንድነው እነዚህን ሰዎች የማትመክሯቸው?» ብላ ትጠይቀዋለች። እርሱም ጥፋት መሠራቱን ሳይደብቃት፣ እንዲህ እንዳላት አጫውታኛለች። « ትግሬ እኮ እንደ ዐማራ አያስብም።» ይላታል። ምን ማለትህ ነው? ብላ ተከታይ ጥያቄ ስታቀርብለት የሰጣት መልስ ያልጠበቀችው ከመሆኑም በላይ ያስገረማት መሆኑን ነው የነገረችኝ። መልሱ እንዲህ የሚል ነበር። «ዐማራው እኮ የራሱን ሥርዓትና አባቶች ያጠፋና የገደለ ነው። የወያኔ መሪዎች እንደሚሳሳቱ ብናውቅም እንዲሞቱና የዘረጉት ሥርዓት እንዲፈርስ አንፈልግም። አባቶቻችን ናቸው። ለትግራይ ሕዝብ መብት፣ ጥቅምና ደህንነት መሥዋዕትነት የከፈሉ ናቸው።» ይላታል። ይህ የአንድ ሰው አስተሳሰብና አመለካከት ሊመስል ቢችልም፣ በተግባር የሚታየው ግን በዓለም አቀፍ መድረኮች ወያኔን ለመቃወም ኢትዮጵያውያን በየኢምባሲው በራፍ ሲጮሁ፣ ትግሬዎች በተቃራኒው የሚቆሙ መሆን ታዝበናል። በአገር ቤትም ተመሳሳይ እንደሆነ እንሰማለን። ይህም የብዙኃኑ ትግሬዎች እምነትና አመለካከት እንደሆነ ድርጊቱ አፍ አውጥቶ ይናገራል።

በሌላ በኩል ይህን የእርሳቸውን ጽሑፍ ያነበቡ፣ ሻዕቢያ በ1983-84ዓም ኢትዮጵያውያንን ወርቅ ጥርሳቸውን እያወለቀ ከኤርትራ ሲያባርራቸው፣ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ «ውሸት ነው»፣ ሲሉ ከሰጡት ምስክርነት ጋር አያይዘው፣ «ፕሮፌሰር ማለት በክህደት መካን ነው» እስከ ማለት የደረሱ ሰዎች አጋጥመውኛል። ምክንያቱም ትግሬዎች መጠቀማቸው ገሐድ ነው። አልሰሙ እንደሆን እንጂ፣ ከሁለት ዓመት በፊት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆነ፣ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ቀርቦ «ሕወሓትንና የትግራይን ሕዝብ መለያየት አይቻልም፤» በማለት ሕዝቡ  የወያኔ አባል እንደሆነ በይፋ ነግሮናል። ይህ ደግሞ ያለጥቅም የሚታሰብ አይደለም።

ፕሮፌሰር መሥፍን ለጽሑፋቸው መነሻ ያደረጉት አንድ ትግሬ ቄስ ሲለምን ማግኘታቸውንና ማንነቱን መደበቁ ነው። ከዚህ ግለሰብ ተነስተው የትግራይ ሕዝብ ችግረኛ እንደሆነ ደምድመዋል። በመጀመሪያ አንድ ለማኝ ሁሉንም ትግሬ አይወክልም። የውክልናን ቀመር ከእኔ የተሻለ ያውቃሉ ብዬ ስለማስብ ወደ ውስጥ አልገባም። አንድ መንግሥት ደግሞ የፈለገውን ያህል ዘረኛም (አምባገነን) ይሁን፣ ዲሞክራት፣ መቶ በመቶ በሆነ ስሌት የቆመለትን መደብ ወይም ነገድ፣ ወይም ዘር ይጠቅማል፣ ተቃራኒውን ፈጽሞ ይጎዳል አይባልም። መቶ በመቶ ይጠቅማል ወይም ይጎዳል ከሚል ድምዳሜ የሚደርሱ ሰዎች፣ የኅብረተሰብን ምንነት ያልተረዱ ወይም በምናብ ዓለም የሚኖሩ ብቻ መሆን አለባቸው። ሁሉም ትግሬ በዘመነ ወያኔ ተጠቃሚ ነው፤ ስንል በጣት የማይቆጠሩ ሰዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት አይደለም። በወቅቱ አብዛኛው ትግሬ ተጠቃሚ ነው። ለወደፊቱ ደግሞ ሁሉምን ትግሬ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ሌሎችን ማደኽየት ብቻ ሳይሆን፣ የሚያጠፋ ሥራ ወያኔ እየሠራ ነው፤ እየተባለ ያለው። ዕውነቱም ይህ ነው። ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ ተጠቃሚዎች የሆኑባቸውን መሠረታዊ ጉዳዮች ከመዘርዘሬ በፊት፣ ትግሬዎች በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ለምን ወደ ልመና አደባባይ ይወጣሉ? ለሚለው ጥያቄ ተዳሳሽ መልስ ሰጥቸ ልለፍ።
በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ትግሬዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች ወደልመና አደባባይ ይወጣሉ፤

አንድ፣ 
ሥርዓቱን ለማገልገል በልመና ስም የሥለላ ሥራ ለመሥራት፤ ማንም በግልጽ እንደሚያውቀው፣ ወያኔ በትጥቅ ትግል በነበረበት ወቅት በየከተማው የነበረው ትግሬ ከሚሠራቸው ሥራዎች አንዱና ዋናው «ልዋጭ! ልዋጭ!» እያሉ በየሥርቻው በመግባት የሕዝቡን አሠፋፈር፣ ማን የት እንደሚኖር ማጥናት፣ ቦታዎችን መለዬትና ማጥናት፣ የባለሥልጣኖችን ቤት እና መውጫ መግቢያቸውን ሰዓት ማወቅ፣ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ቦታዎችን ለይቶ ማወቅ፣ ከሁሉም በላይ፣ በልዋጩ የወታደር ልብሶችንና ጫማዎችን ማሰባሰብ እንደነበረ ይታወሳል። እነዚህ በልዋጭ ሥራ ላይ የነበሩ የምናውቃቸው ጎረቤቶቻችን፣ ወያኔ ከተሞችን ሲወርና ሲይዝ ቀድመው ቦታ መሪዎች፣ ጠቋሚዎችና አሳሳሪዎች እንደነበሩ በግልጽ የታዬና የሚታወቅ ነው። በዛሬው ጊዜም በልመና የተሠማሩት ሰዎች አብዛኛዎቹ ለሥለላ ሥራ እንደሆነ  አያጠራጥርም። በተመሣሣይ ሁኔታ በልመና ላይ የነበሩ በርካታ ትግሬዎች ፣ወያኔ  አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ከልመና ቦታቸው ለቀው መሣሪያ በማንገብ ሰዎችን ያስሩና ያሳስሩ እንደነበር በግልጽ አይተናል። ላበረከቱት ተግባርም ወያኔ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንደሰጣቸው ይታወቃል። ለምሳሌ የታምራት ላይኔ ቢሮ ውስጥ እንደ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ ባለጉዳዮችን ይቀበልና ያነጋግር የነበረ ሰው በአዲስ አበባ በልመና ሥራ የተሰማራ ነበር።

ሁለተኛ፣ 
 ፈዳያን (የከተማ ነፍሰ ገዳይ) ፦ ወያኔ በከተሞች የዓላማዬ ከፍተኛ እንቅፋት ናቸው ያላቸውን ሰዎች በፈዳያን አማካኝነ  ይገድል እንደነበር ይታወቃል። እነዚህ ነፍሰ ገዳዮች አብዛኛውን ጊዜ የሚገድሉትን ሰው መውጫና መግቢያ ሰዓትና መንገዶች፣የሚውልበትንና የሚያመሽበትን ቦታዎች የሚጠኑት ለማኝ መስለውና ሆው ነበር። ግንድያውንም ራሳቸው ወይም ሌሎች  ተመሣሣይ ሰዎች ይፈጽሙ እንደነበር የወያኔ ታሪክ ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል።

ሦስተኛ፣ 
ለተሻለ ጥቅም ፍለጋ፣ ትግሬዎቹ ከማረስ ይልቅ በልመና የተሻለ ጥቅም እንደሚገኝ ያውቃሉ። በነርሱ አባባል የመሃል አገሩ ሰው፣ ለሰው አዛኝ፣ ለተቸገረ ረጅ፣ ርኅሩህና ለጋስ ነው። በመሆኑም አፍ አውጥቶ፣ እጁን ለዘረጋ ለማኝ የመሃል አገሩ ሰው መጽዋች እንደሆነ ያውቃሉ። በዚህም የተነሳ የትግራይ ገበሬ መኸሩን ከከተተ በኋላ፣ አዳፋ ልብሱን ለብሶ፣ ባራባሶ ጫማውን ተጫምቶ፣ ራሱን ወዝ በጠገበ ጨርቅ አስሮ የየዕለቶቹን የጻድቃንና የሰማዕታት ስም እየጠራ  ሁለትና ሦስት ሕፃናት ልጆቹን አስከትሎ/አስከትላ እርዱኝ ማለቱ የተለመደ ነው።  በዚህም ጠርቀም ያለ ገንዘብ ይዞ፣ ሰኔ ግም ሲል ቀንጃ በሬ የነበረው ጥንድ፣ ፍየልና በግ ያልነበረው በግና ፍየል ይገዛል፤ አምና ያስገባውን ምርት ሳያባክነው ወይም ሳይመገበው የቆየ በመሆኑ፣ እርሱና ቤተሰቡ የቀጠናዎቹን ወሮች ማለትም ሐምሌ፣ ነሐሴና መስከረምን ወፍጮው እያጎራ፣ ሞሰቡ እንጀራ ሳይራብ፣ ድስቱ ወጥ ሳያጣ ይከርማል። የቤቱ ክዳን ሣር የነበረው በቆርቆሮ ይቀይራል። አንድ ቤት የነበረው እልፍኝ ካዳራሽ ይሠራል።

ይህም ሌሎች ልመናን የማያውቁትን ወደልመና እንዲሰማሩ ግፊት ሰጭ ዋና ምክንያት በመሆኑ፣ በያመቱ አዳዲስ ለማኞች አካባቢያቸውን እየለቀቁ ያለምናሉ ወደ ሚባልባቸው ከተሞች ይጎርፋሉ። ይህን የተረዳው የትግራይ ክልል መንግሥት በ1992-93 ላይ በማኅበራዊ ዘርፉ ኃላፊ በዶ/ር ሰሎሞን እንቋይን አማካኝነት ነገሩ አስጠንቶ፣ ከላይ የተጠቀሱት ዕውነት መሆናቸውን በማረጋገጡ፣ በይፋ የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ሳይቸገር ወደልመና የመሄድን ፍላጎት ለመግታት በልመና ላይ የሚገኙ ገበሬዎች መሬታቸው ይነጠቅ የሚል ውሣኔና መመሪያ ማስተላለፉ ይታወቃል። ይህን የክልሉን መንግሥት አቋምና ውሣኔ፣ ዶ/ር ሰሎሞን እቋይ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ባደረገው ቃለ-ምልልስ ይፋ ማድረጉን በጆሮዬ አዳምጫለሁ። ይህን ሬዲዮ የሚከታተል ሁሉ እንደሰማ አምናለሁ። ይህንም ፕሮፌሰር መሥፍን ሰምተውታል ብየ አስባለሁ፤ አልሰማሁም ካሉም ጠይቀው መረዳት ይቻላቸዋል ።

አራተኛ

 በዕውነት ተቸግረው ለመኖር ሲሉ የሚለምኑ፦ ዓለም በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉዕ አይደለችም፤ ካንድ እናት አባት የተወለዱ ልጆች በሀብት ይለያያሉ። አንዱ ሀብታም ሌላው ደሀ ይሆናሉ። በሌላም በኩል እናት ካሏት ልጆች መካከል የበለጠ የምትከባከው አልቃሻውን  እንደሆነ ይታወቃል። ዝምተኛው ልጅ የእናቱን ትኩረት ባለማግኘቱ ካልቃሻው ዕኩል እንክብካቤ አለማግኘቱ በአንፃራዊ መልኩ ተጎጂ ነው ማለት ይቻላል። ዕውነታውም ሁሉም ልጆች በዕኩል ደረጃ የእናታቸውን እንክብካቤ አለማግኘታቸው ነው። እናት ግን አዳላች ተብላ ስትፈረጅ እምብዛም ሲነገር አይሰማም። ከዚህ በመነሳት፣ አንድና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የትግራይ ለማኞች መኖር በዘመነ ወያኔ ትግሬዎች ተጠቃሚ አይደሉም ወደሚለው መደምደሚያ ሊያደርሰን አይችልም።

ዛሬ የዓለም የኢኮኖሚ ቁንጮ ነው በሚባለው አሜሪካ መኖሪያ ቤት የሌላቸው(በረናዳ አዳሪዎች) አያሌ ሰዎች አሉ። የዕለት ምግብ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እየተቸራቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በመንግሥት ድጎማ የሚኖረውማ የትእየለሌ ነው። ይህም ሆኖ ግን አሜሪካ የበለጸገች ናት የሚለውን የሚቃረን አይደለም። አሜሪካ በሁለተናዊ መልኩ ሀብታም በመሆኗም የዓለም ፖሊስ ለመሆን በቅታለች። ይህ ከምንም አልመጣም፤ በኢኮኖሚ የበላይነቷ በገነባችው ወታደራዊ ኃይል ከየትኛውም አቅጣጫ ሊነሳ የሚችልን ተቀናቃኝ የማንበርከክ ብቃቷ የጎለበተ መሆን ነው። በዚህ እሳቤ፣ ትግሬው ሁሉ በዘመነ-ወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚነው ሲባል፣ አንድም ትግሬ አይራብም፣ አይለምንም ማለት አለመሆኑ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት። አንድ ትግሬ ቀርቶ አሥር ሺ ትግሬዎች በዕውነት ሲለምኑ ቢታዩ፣ በወያኔ አገዛዝ ትግሬዎች ተጎጅዎች ናቸው፣ ወደሚል መደምደሚያ የሚያሸጋግር አይሆንም።  በትግራይ ውስጥ እየተገነባ ያለው የትምህርት፣ የጤና፣ የመገናኛ (የመንገድ፣ ድልድይ፣ ስልክ፣ የፖስታ)፣ የኃይል ማመንጫ፣ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ የተማረ የሰው ኃይል ልማት፣ የባቡር ኃዲድ ግንባታ፣ ከወሎና ከጎንደር በነጠቁት መሬት ላይ የዘመናዊ እርሻ ልማት ሕዝቡን በወታደራዊ አደረጃጀት አሰልፎ በአንድ እዝና ቁጥጥር ሥራ አሰልፎ ለትግራይ ሁለንተናዊ የበላይነት እየሠራ መሆኑን፣ ወዘተ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር የበላይነቱን መያዙን ፕሮፌሰር መሥፍን ውሽት ነው ሊሉን የሚችሉበት አንዳችም ተጨባጭ ማስረጃ ሊያቀርቡልን አይችሉም።

እርሳቸው ከዚህ ዕውነታ ራሳቸውን አርቀው፣ ዕውነታውን የተረዱትን ብቻ ሳይሆን፣ የሚያውቁትን፣ የሚያዩትን ካዱ፤ የምትሉት ውሸት ነው አሉን። በእርሳቸው አባባል ተጠቃሚዎች «ጥቂት» ናቸው ብለዋል። ጥቂት ሲባል በአሃዝ ሲገለጽ ስንት ነው? በራሳቸው አገላለጽ የመንደር ስሞችን በመጥቀስ ምሳሌ ሰጥተዋል። መቀሌ የተገነባውን የሕወሓት ባለሥልጣኖች ሠፈር «አፓርይድ»፣ አዲስ አበባ የተገነባውን የትግሬዎች ሠፈር «መቀሌ» ብሎ ሕዝቡ እንደሚጠራቸው፣ ይህም ትግሬዎች፣ እርሳቸው «ጥቂት ተጠቃሚዎች» የሚሏቸውን ትግሬዎች ተቃውሞ መግለጫ እንደሆነ አድርገው ገልጸዋል። በእነዚህ መንደሮች ስንት ሰዎች እንደሚኖሩ፤ ስንት የአገሪቱ ንብረት ባለቤቶች እንደሆኑ፣ ስንቶቹ በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ እንደሚወስኑ፣ ስንት ንብረት እንዳላቸው አልገለጡም።  የመንደሮቹን ስሞች ትግሬ፤ ጉራጌ፣ ዐማራ፣ ኦሮሞ፣ ጋሞ፣ ወላይታ ወዘተ እንዳወጣ ሳይገልጡ፣ ስሙን ትግሬ እንዳወጣውና በዚህም ትግሬ ተጠቃሚ እንዳልሆነ፣ እንዳውም ተቃዋሚ እንደሆነ የሚያስመስል እንደምታ ባለው አገላለጽ ገልጸውታል። አንድ የዘነጉት ወይም ሆን ብለው ሊገልጹት ያልፈለጉት ሐቅ አለ። በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ መሬት በመንግሥት የተያዘ ነው። መንግሥቱ ደግሞ ትግሬ ነው። ስለዚህ «ሥልጣናችንን ዐማራ ነጥቆ ለችግር ዳረገን፣ ከችግር የምንላቀቀው ዐማራን ከሥልጣን አውርደን ሥልጣኑን በእጃችን ስናስገባ ነው» ብሎ ሕዝቡን ቀስቅሶና አዋግቶ ሥልጣን የጨበጠ ቡድን፣ ለሥልጣን መደላድሉ ብቻ ሳይሆን፣ ማኅበራዊ መሠረቱ ለሆነው ኅብረተሰብ አይጠቅምም ማለት ጋት የሚያራምድ ሀሳብ አይሆንም። ሊሆን የሚችለው ክህደት አለያም አድርባይነት ነው።

አፓርታይድ የሚለውን ስም ትግሬዎች ራሳቸው እንደሰየሙት  እስማማለሁ። ምክንያቱም መቀሌ የሌላ ነገድ ተወላጅ ስለማይኖርባት።  ስያሜው ግን ትግሬዎች በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚዎች አይደሉም የሚለውን ሀሳብ የሚያከሽፍ አይሆንም። እንኳን ባንድ ሠፊ ማኅበረሰብ ቀርቶ፣ ባንድ እናትና አባት ልጆች መካከል የሀብት ልዩነት መኖሩ የታወቀ በመሆኑ፣ ድሀውና ሀብታሙ ባንድ ሠፈር አይኖሩም። በዚህ የተነሳ ድሆቹ፣ ለሀብታሞቹ ሠፈሮች ያን የሚገልጽ ስም መስጠት የተለመደ ነው። ሀብታሞቹም እንደዚያው። የናይሮቢውን ኪሪዮባንጊን ሰፈር ልብ ይሏል።

የአዲስ አበባው ስያሜ ግን ትግሬዎች አወጡለት ለማለት አያስደፍርም። አዲስ አበባ የልዩ ልዩ ነገዶች መኖሪያ በመሆኗ፣ ከነዋሪዎቹ ሁኔታውን የታዘበ ሊያወጣው ይችላል። የመንደሩ ነዋሪዎች ማንነት ራሱ ስሙን ይገልጣል። ስም ከተግባር ይወጣልና። «ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት» እንዲሉ። ስያሜዎቹን ማንም ያውጣቸው ማን፣ ስሞቹ በዘመነ ወያኔ ትግሬዎች ተጠቃሚዎች አለመሆናቸውን የሚያስረዱ አይደሉም። እንዳውም በተቃራኒው ትግሬዎች ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የሚመሰክሩ ናቸው። አንድ ለማኝ አይተው ትግሬዎች ሁሉም አልተጠቀሙም ከሚል መደምደሚያ ከደረሱ፣ የአንድ ሠፈር ነዋሪ የሆኑ ትግሬዎች (እርሰዎ ጥቂት የሚሏቸው) ከሆኑና እነርሱም የአገሪቱን ፖሊሲ የሚቀይሱ ከሆነ፣ በራሰዎ አመክንዮ አብዛኛው ትግሬ ተጠቃሚ ነው ከሚለው መደምደሚያ  ላይ ያደርሳል። ምክንያቱም በነዚህ በተጠቀሱት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ትግሬዎች በሚያወጡት የተዛባ ፖሊሲ ነገዱ ተጠቃሚ እየሆነ መሆኑን ያሳያል። የአብዛኛው ነገድ አባል ተጠቃሚም ባይሆን፣ ከሌሎች ነገድና ጎሣዎች በተለየ ሁኔታ ጉዳት ሳይደርስበት፣ ተጎዳን ብለው ብረት ነክሰው ጫካ የገቡ ልጆች ወላጅ የሆነ ሕዝብ፣ ለ23 ዓመታት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሲያጠፉ እንኳን በረሃ የሚገባ ድምፅ የሚያሰማ የጠፋው። መቼም ሁሉም ትግሬ ባንዲት የሥልጣን ወንበር ላይ አይቀመጥ። መቀመጥ የሚችለው ባለው የሥልጣን ተዋረድ ወንበሮች ነው። እነዚህ ወንበሮችም የተሞሉት በትግሬዎች ነው። (የዚህን ዝርዝር ሁኔታ ለማወቅ ለሚሹ «ሥልጣን ተሻሚ ትግሬዎችና የኢትዮጵያ አንድነት»፣ ታላቁ ሤራ የተሰኙትን መጽሐፍቶችና አቶ ገብረ መድህን አርአያና አቶ ጌታቸው ረዳ የሚጽፏቸውን ጽሑፎች እንዲያነቡ እጋብዛለሁ)።

ከነዚህ አጠቃላይ ዕውነታዎች ወጥቼ፣ በዘመነ ወያኔ አገዛዝ ትግሬው ሁሉ እንዴት እየተጠቀመ እንዳለ አንድ ሁለት ብዬ ነቃሾችን እንደሚከተለው ለፕሮፌሰር መስፍን ለማቅረብ እወዳለሁ። ከሁሉም በላይ አንባቢ ታሳቢ አድርጎ እንዲይዝልኝ የምሻው፣ ወያኔ የትጥቅ ትግል ሲጀምር፣ «ትግሬ ለችግርና ለስደት የተዳረገው ሥልጣኑን በዐማራ በመነጠቁ ስለሆነ፣ ተደራጅቶ የተነጠቀውን ሥልጣን በመረከብ፣ የበላይነቱን ሥፍራ በመያዝ ሁለንተናዊ ተጠቃሚ መሆን አለበት» ብለው፣ ነገዱን በአንድ ወታደራዊ ጠገግ ሥር አደራጅተው ለሥልጣን የበቁ መሆናቸውን ነው። በጨበጡት ሥልጣንም የሚከተሉትን ትግሬ ጠቀም ሥራዎች ሠርተዋል።
  
አንደኛ፦ 

ከወሎ አንድ አውራጃ (ራያና ቆቦን)፣ ከጎንደር ወልቃይትን፣ ጠገዴን፤ ጠለምትን፣ ሠቲትን፣ ላይና ታች አርማጨሆ ወረዳዎችን ነጥቀው ነባር ሕዝቡን ገድለውና አሰድደው ትግሬ አስፍረውበታል። በደረሰባቸው መሳደድ አገር ጥለው አውስትራሊያ ፐርዝ፣ ሜልቦርንና ብሪዝበን ነዋሪ የሆኑ የወልቃይት ጠገዴ ሽማግሌዎች ፣ ለዚህ ጸሐፊ ከ500 በላይ በወያኔ የተገደሉ፣ ሀብት ንብረታቸውን የተወረሱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ሰጥተውኝ በእጄ ይገኛል ።  ሽማግሌዎቹ የትግሬ ወያኔዎች ከ1972 ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ ፍጅት መጀመራቸውን በምሬትና በቁጭት ገልጸውልኛል።  የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በርትቶ ከወዲሁ ራሱን መከላከል ካልቻለ፣ ያገሩ፣ የንብረቱና የሀብቱ ባለቤት መሆን ቀርቶ መኖር እንደማይችል የተገነዘበው ተስፋዬ አጋዲስ የተባለ የወልቃይት ተወላጅ፣ ላካባቢው ሕዝብ እንዲህ ብሎ ማስጠንቀቁንም ይናገራሉ። «እነዚህ ከተከዜ ማዶ ያሉን ሰዎች ታግለህ ካልመለስክ፣ ቤትህንና ንብረትህን አሻግረህ ታያለህ።» ብሎ የተናገረው ዛሬ ዕውነት መሆኑን ያወሳሉ። ይህን ሰው አድነው እንደገደሉትም ያስረዳሉ። 

ይህም በመሆኑ፣ ከ1984-85 ባሉት ዓመታት ማይጭ እና ማዓዬ በተባሉት ቀበሌዎች ላይ 12000 (አስራ ሁለት ሺህ) ትግሬዎች  አሰፈሩ። ሁመራ እና ወልቃይት ዐማራው ተባሮና ተገድሎ ዛሬ ነዋሪው ከ95 % በላይ ትግሬ እንዲሆን ተደርጓል። ዳንሻ፣ ከትግራይ በሰፈራ መልክ በመጡ ትግሬዎች በመወረሩ ከነዋሪው 75% ትግሬ እንዲሆን መደረጉን በቁጭት ይናገራሉ። ሮዋማ፣ ሁመራ እና  ዳንሻ መገናኛ ላይ የሚገኝ ቀበሌ ነዋሪውን አፈናቅለው 25000 (ሃያ አምስት ሺ)  ትግሬዎች አስፍረውበታል። ትርካን ከሚባለው ቦታ 32000 (ሰላሳ ሁለት ሺ) ትግሬዎች አስፍረዋል። የአየር ማረፊያ ጣቢያም ገንብተዋል። ሰሮቃ፣ መተማ፣ አብደራፊ፣ አዲረመጽ፣ ቃፊትያ፣ አዲጎሹ፣ መዘጋ፣ ፀብራ፣ ማይገባ፣ ማይፀበል፣ ማይፀምሪ፣ የሚባሉት አካባቢዎችን ነባሩን የዐማራ ሕዝብ ተባሮ እና ተገድሎ፣ መቶ ለመቶ በሚባል ደረጃ በትግሬ እንዲያዝ መደረጉን  ያወሳሉ። መተማ ጥንት አንድም ትግሬ አይኖርበት የነበረው ወረዳ፣ ዛሬ በትግሬ ተወሯል። አብደራፊና አብረሃ ጅራ ትግሬ አልነበረም። ዛሬ ሱዳን በስደት የነበረውን ትግሬ አምጥተው ያሰፈሩበት እንደሆነ ምስክርነታቸውን ሰጥተውኛል። ዛሬ የኦነግና የኦሕዴድ አባሎች አዲስ አበባን ፊንፊኔ፣ ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረዘይትን ቢሾፍቱ ወዘተ እንደሚሉት፣ ወራሪዎቹ ትግሬዎች የወልቃይት እና ጠገዴን ነባርና ታሪካዊ ስሞችን እየለወጡ እንደሆነ አስረድተውኛል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን የወልቃይት ጠገዴ ሽማግሌዎች የሰጡትን ምስክርነት የሚያጠናክር መረጃ እንደ አውሮጳውያን ቀን አቆጣጠር ሜይ 27/ 2014 በላኩልኝ ኢሜይል እንዲህ ሲሉ ያጠናክሩታል። 

«ሌላው ቀርቶ ይግረማችሁ! ግንቦት 20 እያለ እያከበረ ያለው ለበዓሉ ዝግጅት ``የኢትዮጵያ አየር መንገድ`` ለትግሬ ተወላጆች ወደ አገር ለመብረር የበረራ ዋጋ ቅነሳ አድርጎላቸዋል። ማን ይሙት እስኪ ይህ መንግሥት የትግሬ መንግሥታ ባይሆን ኖሮ፣``ለትግሬዎች`` የአውሮፕላን ትኬት ቅነሳ ይደረግ ነበር? የትግሬ መንግሥት አይደለም እያሉ የሚከራከሩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በጀሮዬ አጋጥመውኛል። ለእኔም አነጋግረውኛል። ---- ትግሬ ቢጠቀምም ለወደፊቱ እንዳይጠቃ ``ተጠቅሟል አትበሉ`` ብሎ አንድ ፖለቲከኛ  በስልክ ነግሮኛል። እኔ ደግሞ፣ እሺ ተጠቅሟል ካላልን፣ የወያኔን ወንጀል እንዴት እንግለጸው? የወያኔን ወንጀል ደብቁ እያላችሁን እኮ ነው! አልኩት። ስለ ትግራይ ሕዝብ የመጪው ሁኔታ እየታሰበ አሁን ያለው፣ በሕይዎት እየተጠቃ ያለው ``አማራ ኅብረተሰብ`` ስትደርሱ ለምን ዝም ትላላችሁ? አልኩት። አማራውና ትግሬው ስታነፃጽሩ ስለትግሬው የወደፊት ዕጣ እየተከላከላችሁ፣ አሁን እየተጠቃ ላለው ኅብረተሰብ ጆሮ ዳባ መስጠት ``የወንጀሉ ተባባሪ መሆን ነው`` ብየዋለሁ።------የትግሬ ሕዝብ ባድሜ መሬቱ ተነጠቀ ብሎ፣ ሲጮህ፣ የወልቃይት የአማራ ሕብረተሰብ መሬት ተነጥቆ ወደ ትግሬ ሲሰጥ፣ አንቀበልም አላሉም። ወይም አልጮሁም። ለምን? ስለተጠቀሙ ነዋ! ታዲያ ተጠቅመዋል ማለት እንዴት ነው? የሰው ቤትና ርስት ገብቶ ሲያርስ እና ቤቱ ገፍትሮ እንዲኖርበት ከተፈቀደለት፣ መጠቀምን ስለሚያውቅ እምቢ አላለም። ታዲያ ፕሮፌሰር (መስፍን) ጥቂት የወያኔ ጀሌዎች ተጠቅመው ሊሆን ይችላል የሚሉን ጥቂት ስንት ነው? ሀው ሎንግ ኢዝ ሎንግ ይላሉ ፈረንጆች። ጥቂት ሲሉን ጥቂት ስንት ነው? እርሳቸውም ሆነ ተከራካሪዎቻችን በቁጥር ሊነግሩን አይችሉም። ሌላውን ጠቀሜታ እንተወውና በወልቃይት በመሳሰሉት መሬቶች እየኖረ ያለው ትግሬ በጣም በጣም ብዙ ነው። በወልቃይቶች አባባል መቶ በመቶ ትግሬ ብለዋል። ሁመራ ያለውን እርሻ ማነው እየተጠቀመበት ያለው? እኔ እኮ ትግሬ ነኝ። ግን ሐቁ መደበቅ የለበትም።» ብለዋል። 

በተመሳሳይ ሁኔታ ከወሎ በተነጠቀው መሬት ተጠቃሚው የትግሬ ገበሬ ነው። ይህ ደግሞ ፕሮፌሰር መሥፍን እንዳሉት ጥቂት የሚባል አይደለም። ብዙ፣ እጅግ በጣም ብዙ ነው። ባይገርማችሁ የራያ ሰው «ራያ እና ኢትዮጵያ» የሚሉ ስሞች ለንግድ መጠሪያነት እንዳይጠቀም መከልከሉን ብትሰሙ ምን ትላላችሁ? ፕሮፌሰር መሥፍን ተቃዋሚ የሚሏቸውን ትግሬዎች ለመጥራት ፈልገው አሥር ስላልሞሉላቸው «ምነው አሥር በሞሉልኝ» በማለት የቁጥራቸው ማነስ እንዳስቆጫቸው አልሸሸጉም። ያውም አረጋዊ በርሄና አስራት ገብሩ ተጨምረው። እንዴት ተሾፈ? በምን ታምር ነው የሕወሓት ዓላማ ጠንሳሾችና አጎልማሾች፣ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ገዳዮች፣ ይሙቱ፣ ይወገዙ እንኳ ባይባሉ፣ የወያኔ ተቃዋሚዎች ናቸው መባሉ? «ያልወልድኩት ልጅ አባባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ» ዓይነት ነው። ይህ በተቃዋሚው ማሾፍ ነው። የአዲስ ዘመን ጋዜጣ የአድማስ አምደኛ የግጥሞቹ ስንኞች የመጀመሪያ ቃሎች፣ የመጀመሪያ ፊደሎች ከላይ ወደ ታች ሲነበብ «ትግራይ እስክትለማ ሌላው አገር ይድማ» ሲል የጻፈው ግጥም፣ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚነቱን በጥበብ የገለጸበትን ማስታወስ የፕሮፌሰሩን ሀሳብ ውድቅ የሚያደርግ ነው።

ሁለተኛ፣ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ቅድሚያ ልማት ይሰጥ፦ 

ማንም የሽግግር መንግሥት ተብዬውን ቻርተር ያነበበና የሽግግር መንግሥቱን አመሠራረት ሂደት የተከታተለ ሰው ሊገነዘበው እንደሚችል፣ ወያኔ ራሱ በ17 ዓመት የትጥቅ ትግል ያወደማቸውን ተቋሞች እና ድልድዮች፣ መልሶ ለመገንባትና አዳዲሶችም ለመሥራት እንዲያመቸው በቻርተሩ ውስጥ «በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ቅድሚያ መልሶ ግንባታ» ይሰጥ የሚል ሕግ አጸድቆ ለስድስት ዓመት ያላንዳች ጠያቂ የአገሪቱ በጀት፣ ከእርዳታና ለጋሽ ድርጅቶችና መንግሥታት በኢትዮጵያ ስም የመጣን መዋዕለንዋይ ለትግራይ ክልል እንዲውል አድርርጓ። ይህ አሠራር ሁሉንም ትግሬዎችን ጠቀመ ወይስ ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ጥቂት የሚሏቸውን? አንባቢ ዕውነታውን በጥልቀት ለመረዳት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት «ዕውን እንደሚባለው በወያኔ አገዛዝ ትግሬዎች ተጠቃሚዎች አይደሉም?» በሚል ርዕስ ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ቃል በአባሪነት ቀርቧልና ይመልከቱና ፍርደዎን ይስጡ።

ሦስት፣ የትምህርት ሥርጭት፦ 

 ለአንድ አገር ሕዝብ ዕድገትና ሥልጣኔ የሰው ኃይል ልማት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የትግራይ ትውልድ በኢትዮጵያ ላይ የዘር አገዛዙን የበላይነት ጠብቆ ለመጓዝ እንዲችል አድሏዊና ፍፁም ዘረኛ በሆነ የሀብት አከፋፈልና የበጀት ድልድል አድርጓል። በዚህም የትግራይ ሕዝብ ሠፊ የመማር ዕድል እንዲኖረው እያደረገ ነው። በ2002ዓም ላይ የትግራይ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳኘው አይጠገብ የተባሉ ሰው ወይን በተሰኘ በሬዲዮ፣ በሰጡት መግለጫ፣ የክልሉ የትምህርት ዕድገት በሚከተለው መንገድ ገልጸውታል። በ1984ዓም ላይ ወያኔ ሥልጣን በጨበጠ ባመቱ በትግራይ ክልል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት 103፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት 13፣ የተማሪዎች አጠቃላይ ብዛት 83000 (ሰማኒያ ሦስት ሺ)፣ የአጠቃላይ መምህራን ብዛት 2300 (ሁለት ሺ ሦስት መቶ) እንደነበር አስረድተዋል። በ2002ዓም ላይ፣  የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 1995፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 132፣ የአጠቃላይ ተማሪዎች ቁጥር 1000000 (አንድ ሚሊዮን) ከፍ ማለቱን ብቻ ሳይሆን፣ ዕድገቱ በብርሃን ፍጥነት የተጓዘ መሆኑን በሚያመለክት መልኩ   ገልጠውታል። (ይህ እንግዲህ የሥልጠና፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶችን ሳይጨምር ነው) ጥንት ያልነበሩ፣ ሁለት ኮሌጆች፣ ሦስት ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸውንም አስረድተዋል። የትምህርት ሥርጭቱ ዕድገት በሚከተለው መልክ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል። ማነኛውም ለትምህርት የደረሰ የትግሬ ልጅ ከቤቱ በዘጠኝ ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያገኛል። ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቀና ቀጣዮቹን ከዘጠኝ እስከ አሥር ያሉትን ትምህርቶች ለመከታተል እያንዳንዱ የትግራይ ተማሪ በአሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ትምህርት ቤት ያገኛል። ለመሰናዶ ማለትም ለአሥራ ሁለተኛ ክፍል ለመማር ከቤቱ ወደ ትምህርት ቤቱ መጓዝ የሚጠበቅት ርቀት 19 ኪሜ ብቻ ነው። ይህም ማለት የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች በትግራይ የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች በ19ኪሜ ሬዲዬስ ክልል ተቋቁመዋል ማለት ነው። በትምህርት የሚገኘው ጥቅም ደግሞ ለጥቂት ትግሬዎች ተብሎ የሚገልጽ አይደለም። ሁሉንም ትግሬ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። የትምህርቱ ጥራት ከማንኛውም ክልል በበለጠ የሚሰጥ መሆኑን አንባቢ ልብ እንዲሉልኝ እሻለሁ።

በሌላ በኩል የትግራይ መንግሥት መረጃ እንደሚለው እኤአ እስከ 2006 ባሉት (ማለትም ወያኔ ሥልጣን ከጨበጠ 1991 እስከ 2006) ባሉት አሥራ አምስት ዓመታት ውስጥ 113 መዋዕለ ሕፃናት፣ 1598 አንደኛ ደረጃ፣ 64 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 54 ኮሚኒቲ ኮሌጆች፣ 3 ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸውንና አግልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸን ያስረዳል። ይህ በክልሉ በግል የተቋቋሙትን 51 የአንደኛ ደረጃና 13 የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሳይጨምር ነው። በአጠቃላይ በመማር ማስተማር ሂደት ሕዝቡ በነቂስ ተጠቃሚ የሆነ መሆኑን የመንግሥቱ መረጃ እንዲህ ሲል ያጠቃልለዋል። «በአንደኛ ደረጃና በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአዲስ ተመዝጋቢዎች ቁጥር በ482 ነጥብ 6 ፐርሰንት አድጓል ይላል። በዚህ ተጠቃሚው ጥቂቶች ወይስ ብዙኃኑ?

አራት፣ የጤና ተቋሞች ሥርጭት፦ ለአንድ አገር ሕዝብ የኃያልነትና የጥንካሬ መገለጫዎች ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል ሁለቱ የሕዝቡ ጤንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅና  የሕዝቡ የአንድነት ስሜት የጠነከረ መሆን እንደሆነ ይታመናል። በዚህ ረገድ ወያኔ የትግራይን ሕዝብ በፀረ-ዐማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪክና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ስሜት ላይ የተመሠረተ የጠባብ ብሔርተኝነት  ሥነልቦና በሕዝቡ ውስጥ አስርጿል። ይህ ሥነልቦና የኋላ ታሪክ የሚስብ በምድጃ ዙሪያ የሚቀነቀን «ከሥልጣን ማዕከሉ በዐማራ ተነጠቅን» ከሚለው ሐረጉን ይስባል። በዚህ ሥነልቦና ላይ ተመሥርቶ ወያኔ «ሥልጣን ከዐማራው» ለመንጠቅ በርሃ ገባ። በትጥቅ ትግሉ ዘመንም በኃይል በታገዘ የ17 የፋኖ ዘመን የትግራዊነትን ሥልቦና በውድና በግድ በሕዝቡ መሀል አሰረጸ። በ23 ዓመታት የሥልጣን ዘመኑ ደግሞ፣ ባሳየው የሁሉም የበላይነት ስሜት ከእኛ በላይ ላሳር ነው የሚል የትግራዊነት ብሔርተኝነት ስሜትን ሰማይ ጥግ አጎነው። ቀደም ሲል «ለድህነት፣ ለበሽታ፣ ለስደትና ለልዩ ልዩ ችግሮች የዳረገህ ዐማራው ነው» በሚል ብሦትን መነሻና መድረሻ ባደረገ ያላቋረጠ ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡ ከኢትዮጵያዊነት ስሜቱና እምነቱ ወጥቶ፣ ትግሬ ነኝ፣ ከኢትዮጵያ በፊት ትግሬነት ብሎ በማመን በቋንቋ የጠበቀ አንድነት እንዲመሠርት አደረገ። በኋላም «ልጆችህን ገብረህ የጨበጥከውን ሥልጣን ሊነጥቁህ ነው፤ ዐማራ ሊያጠፋህ ነው፣ መጡብህ ነቅተህ ጠብቃቸው» ከሚለው ፕሮፓጋንዳ በተጨማሪ፣ ሕዝቡን የፖለቲካውና የኢኮኖሚው የበላይ በሚያደርገው ድርጅታዊ አሠራሩ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ በሆነ መንገድ የቁሣዊ ሀብት ተጠቃሚ በመሆኑ፣ ፕሮፓጋንዳው ቁሳዊ መሠረት እንዲይዝ ከመደረጉም ባሻገር፣ አንድ ለአምስት አቧድኖ ወታደራዊ ዲስፕሊን በተላበሰ መልኩ አንድነቱን ነፋስ ሊያስገባ በማይችል ሁኔታ አጠናክሮታል። ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ነገድና ጎሣዎች መካከል እንደ ትግሬው አንድነቱ በኅሊናዊና ቁሳዊ መልኩ የጠነከረ  ፈልጎ ማግኘት ይከብዳል። ይህ ኅሊናዊና ቁሳዊ አንድነት በጤንነቱ እንዲታጀብ ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ አድላዊ በሆነ መንገድ የጤና ተቋሞችን አስፋፍቷል።  ዓይናለም አዱኛ የተባሉ ሰው «የጤና ተቋሞችና አገልግሎቶች» በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ የትግራይ ክልል የሚገኝበትን የዕድገት ደረጃ እንደሚከተለው ገልጸውታል።

 የዓይናለም አዱኛ ጥናት እንደሚለው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ 131 ሆስፒታሎች፣ 7845 አልጋዎች፤ 3231 ክሊኒኮች፤ 723 የጤና ጣቢያዎች እንዳሉ ያስረዳል። በትግራይ 16 ሆስፒታሎች ተገንብተዋል። ይህም አንድ ሆስፒታል ለ285 323 (ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ ሦስት መቶ ሃያ ሦስት) ሰዎች ማስተናገድ ይችላል። የአገሪቱ የሆስፒታል ሕዝብ ጥምረት አንድ ሆስፒታል ለ553 990 (አምስት መቶ አምሳ ሦስት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና) ሰዎች ግልጋሎት ይሰጣል። ይህ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር፣ የትግራይ ሕዝብ በሆስፒታሎች የመገልገል መብቱ ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ፣ በግማሽ የተሻለ ወይም ብዙ ወረፋና ቀጠሮ ሳይኖረው የመገልገል ዕድሉ የሠፋ መኖኑን ያሳያል። ከሌሎች ክልሎች ትግራይ በሆስፒታል ተጠቃሚነቱ 20 ከመቶ ብልጫ እንዳለው የጥናት ውጤቱ አመልክቷል።

የሕክምና አገልግሎት ጥምረት በክልሎች፦  
ተራ ቁጥር
ክልል
ለአንድ ሆስፒታል ተገልጋዩ ሕዝብ ብዛት
ለአንድ የሆስፒታል አልጋ ተገልጋዩ ሕዝብ ብዛት
የሐኪሞች ሥርጭት
የጤና ሙያተኞች ሥርጭት
የነርሶች ሥርጭት/ ብዛት
የሕዝብና የነርስ ጥምረት
የሕዝብና የሐኪም
ጥምረት
1
ትግራይ
285 313
3222
59
163
2094
2180
70000
2
አፋር
72500
11877
10
16
208
6966
140000
3
ዐማራ
1 059 789
12468
133
273
1973
10206
140000
4
ኦሮሚያ
935 567
7989
149
522
3278
8562
180000
5
ሶማሌ
760 000
10459
53
23
476
9580
100000
6
ቤንሻብጉል ጉ
328 000
3200
6
18
397
1652
100000
7
ደ/ብ/ብ/ሕ ክ
787 250
8300
155
150
2143
7347
100000
8
ጋምቤላ
259 000
2590
4
10
156
1660
60000
9
ሐረሪ
52 250
294
41
11
277
755
5000
10
አዲስ አበባ
80 667
929
332
25
12583
250
10000
11
ድሬ ዳዋ
107 000
1845
31
8
226
1894
1500
973
1219
23811


Source: Aynalem Adugna, Health Institutions And Services (Lesson 13) እኤአ 2006/7
ከሠንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለው ትግራይ ውስጥ አንድ ሆስፒታል ለ285,313 ሰዎች፣ አንድ የሆስፒታል አልጋ ለ3,222 ሰዎች፣ አንድ ነርስ ለ2,180 ሰዎች፣ አንድ ሐኪም 70,000 (ለሰባ ሺህ) ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። በተመሳሳይ በዐማራው ክልል አንድ ሆስፒታል ለ1,059,789 ሰዎች፣ አንድ የሆስፒታል አልጋ ለ12,468 ሰዎች፣ አንድ ነርስ ለ10,206 ሰዎች፣ አንድ ሐኪም ለ140,000 ሰዎች አገልግሎት ይሰጣል። ልብ በሉ ይህን ከሌሎች ክልሎች ጋር ብታነፃጽሩት የምታገኙት ውጤት በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚው የትግሬ ሕዝብ ነው። በሕዝብ ብዛታቸው በሚያስገቡት ግብርና ታክስ፣ ባላቸው የተፈጥሮ ሀብት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ክልሎች የአገልግሎቶች ተጠቃሚ አይደሉም። ይህ አድልዖ አይደለም? በዚህስ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ አይደለም ማለት ይቻላል? ፍርዱን አንባቢና የእየለቱን ድርጊት በዓይኑ የሚያየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይስጥ።

የክልሉ መንግሥት መረጃ የሕዝቡን የጤና አገልግሎት ዕድገት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል። ከ1983 ዓም ጀምሮ ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ የታናናሽ ክሊኒኮች ቁጥር ከ100 ወደ 600 መቶ ማደጉን፣ ታናናሽ ሆስፒታሎች ደግሞ ከ10 ወደ 40 ማሻቀባቸወን፣ ማዕከላዊ ሆስፒታሎች ከ4 ወደ 13 መመንደጉን ያትታል። አንድ እጅግ ዘመናዊና ትልቅ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ (ሪፈራል) ሆስፒታል መገንባቱን ይገልጻል። በነዚህ ሁሉ ጥረቶች የሕዝቡ የጤና አገልግሎት ሽፋን ከ12 ወደ 70 ከመቶ መድረሱን ያረጋግጣል። ይህ ተጠቀመ ካላሰኘ ጥቅም በምን መልኩ ሊገለጽ እንደሚችል ማስረዳት ያለባቸው ፕሮፌሰር መሥፍንና የአባባላቸው ተጋሪዎች ናቸው።

በ2004(እኤአ) ከአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከተደመጠ ቃለ ምልልስ መገንዘብ የሚቻለው፣ በጤናው ዘርፍ የትግራይ ሕዝብ ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ተጠቃሚ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ማንም የትግራይን መልከዓ-ምድር አቀማመጥ የሚያውቅ ሰው ሊገነዘበው እንደሚችል፣ ከ60 እስከ 70 በመቶው የሚሆነው ሕዝብ የሠፈረባቸው ቦታዎች የወባ ትንኝ መራቢያ እንደሆነ ያውቃል። ጠዓመ ግደይ የተባለ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የተላላፊ በሽታዎች መከላከያ ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጸው፣ የትግራይን ሕዝብ ከሚያጠቁት ተላላፊ በሽታዎች መካከል አንዱ ወባ መሆኑን ገልጸው፣ በተደረገው በሽታውን የመቆጣጠር ብርቱ ዘመቻ፣ ከ2002(እኤአ) ጀምሮ ካመት ዓመት የበሽታው ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱን በዓለም ጥናትና በነርሱም ጥናት የተረጋገጠ ነው ብለዋል። በማያያዝም እኤአ ከ2008 ከነበረው የ2009 በግማሽ (50%) በሽታው መቀነሱን ወይም በቁጥጥር ሥራ መዋሉን አስረድተዋል። በ2002 (እኤአ)፤ 2003 ዓም፤ 2004ዓም በትግራይ ክልል ሲታከሙ ከነበሩት በሽተኖች 12% (አሥራ ሁለት በመቶው) የወባ በሽተኞች እንደነበሩ አስታውሰው፣ይህ ቁጥር በያመቱ እየቀነሰ መጥቶ በ2003 (እኤአ)ወደ 6% በ2004 (እኤአ) ደግሞ የወባ በሽታ ታካሚው ቁጥር ወደ 5% መቀነሱን አረጋግጠዋል። ማንም ልብ ያለው ልብ የሚል ከሆነ ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ ያገሪቱን የወባ መቆጣጠሪያ ድርጅት አፍርሶ መሣሪያዎቹንና ንብረቱን  ትግራይ መውሰዱን አናውቅም፣ አልሰማንም የሚል ሐቀኛ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብየ አላስብም።

በዚህ በያዝነው ዓመት (2006) ብቻ ለትግራይ ክልል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የሕክምና መሣሪያ «ዊተን ኢትዮጵያ» በተባለው የጀርመን ዕርዳታ ሰጭ ድርጅት ስም አይደር ሆስፒታል ገብቶ ሙያተኞች ስለአጠቃቀሙ እንዲሰለጥኑ ተደርጓል። መሣሪያው በቪዲዮ እየተደገፈ፣ ለቀዶ ጥገና፣ የልብ፣ የጨጓራ፣ የኩላሊት፣ የማሕፀን፣ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥና ለዚህም 30 ሐኪሞች ሰልጥነው ወደ ሥራ መሰማራታቸው ተረጋግጧል። ሰልጣኞቹ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ «ካሁን በፊት ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የነበሩ ታካሚዎች፣ ዛሬ ከክልላቸው ሳይንቀሳቀሱ መታከም ችለዋል።» ብለዋል። ይህ ጥቅም አይደለም ካልተባለ!

አምስተኛ፣ የኤሌክትሪክ መብራት ተጠቃሚነት፦ 

 ትግራይ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች (ክፍለ-ሀገሮች) ከተሞቿ ከኃይድሮ ኤሌክትሪክ በሚመነጭ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ አልነበረችም። ሁሉም ከተሞች በናፍጣ በሚንቀሳቀስ ጄኔሬተሮች የሚገለገሉ ነበሩ፣ ይህም በመሆኑ አብዛኞቹ ከተሞች የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚዎች አልነበሩም። ወያኔ ሥልጣን በያዘ ማግስት ሥራየ ብሎ የሠራው ሕዝቡን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ መብራት ተጠቃሚ ማድረግ ነው። በዚህም መሠረት ከባሕርዳር ደብረታቦር፣ ጋይንት እና ወልዲያ ከዚያም መቀሌ በተዘረጋ የኤሌክትሪክ መሥመር የትግራይ ዋና ዋና ከተሞች የመብራት ተጠቃሚ አድርጓል። አንባቢዬ ከዚህ ላይ ልብ እንዲልልኝ የምሻው፣ ከባሕርዳር መቀሌ የተሳበው መብራት ባለፈባቸው ከተሞች አገልግሎት እንዲሰጥ ያልተደረገ መሆኑን ነው። ይህን በተመለከተ የጋይንት ሕዝብ ለትውልድ መተላለፍ ያለባቸው ሁለት ቃሎች ተናግሯል። አንደኛው በላዩ ላይ የመብራት አስተላላፊ ሽቦ ተዘርግቶ፣ በእርሻው ላይ ምሰሶ ተተክሎ፣ የጥቅሙ ተካፋይ ባለመሆኑ በልቡ አዝኖ አዘኑን የገለጸበት ነው። እናም ለባድመ ጦርነት ልጅህን አምጣ ብለው ሲጠይቁት «እንደ መብራቱ እለፉን» ነበር ያለው። 

ሁለተኛው  በወያኔዎች ዓላማ ያልተደሰቱ ግለሰቦች የተተከለውን የመብራት ሽቦ ተሸካሚ ምሰሶ ባሳቻ ጊዜ ከጥቅም ውጭ ያደርጉታል። ይህ በተደጋጋሚ በመፈጸሙ የወያኔ ባለሥልጣኖች ቀጭን አስገዳጅ መመሪያ አዘጋጁ። መመሪያውም የመብራት ተሸካሚ ምሰሶ የተተከለበት ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ምሰሶዎቹን ሌት ተቀን እንዲጠብቅ፣ ካልጠበቀ የምሰሶውን ዋጋ በሦስት እጥፍ እንደሚቀጣ እና እንደሚታሰርም የሚያስገድድ ነበር። በዚህም የተነሳ የጋይንት ሕዝብ ሌት ከቀን በየምሰሶው ሥር ቁሞ ያድራል፣ ይውላል። በምሰሶዎች ሥር ሰዎች ለምን እንደሚቆሙ ምክንያቱ ያልገባው ተጓዥ፣ ካንዱ ምሰሶ ሥር ወደ ቆመው ሰው ጠጋ ብሎ፣ ምን እየሠራ እንዳለ ይጠይቀዋል። ምሰሶ ጠባቂውም «ትግሬን እራት እያበላሁ» ብሎ እንደመለሰት በስፋት ይነገራል። በዕውነትም የጋይንት ሕዝብ ትግሬን ቁሞ መብራት ይዞ ለዓመታት ራቱን አብልቷል። ይህ ጥቅም አይሆን ይሆን?

በዚህ ብቻ አልቆመም። ተከዜ ላይ የሚገነቡት የኃይድሮ ኤሌክትሪክ መብራት ማመንጫ እስኪጠናቀቅ አላስችላቸው ብሎ፣ ወይም ጎንደሬን ለመበቀል፣ በጣሊያን የደም ካሣነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከከፈለው አንዱ የሆነውና ለጎንደር ከተማ ከ50 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ የመብራት ምንጭ በመሆን ያገለገለውን ጄኔሬተር በደደቢት ሠራዊት ከተማዋን ለ3 ወር ከበው ነቅለው ብዘት ከተማ ተክለዋል። በዚህስ የተጠቀሙት «ጥቂት ትግሬዎች» ይሆኑ? ወይስ ድፍን የብዘት ከተማ ነዋሪ ትግሬ? 

ይህ ሁሉ ተደርጎ በትግራይ ለሚገነቡት ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ሆቴሎች፣ ለተስፋፉ ማኅበራዊ ተቋሞች ከፍተኛ የሆነ የኃይል ምንጭ በማስፈለጉ፣ ከፍታው 188 ሜትር፣ ዘጠኝ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ማቋት የሚችልና 300 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችል የተከዜ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ገነቡ። በዚህም በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የመሥፍን ኢንጂነሪንግ ብረታ ብረት ፋብሪካ፣ የመሰቦ የስሚንቶ ፋብሪካ፣ የዐድዋው አልሜዳድ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ፣ የአዲግራቱ መድኃኒት ፋብሪካ ወዘተ ተገንብተው ያላቋረጠ የኃይል ምንጭ እንዲያገኙ ተደርጓል። እነዚህ ፋብሪካዎች መገንባታቸውና ትግራይ ጠቀም መሆናቸው ባልከፋም ነበር። አሰዛኝ የሚያደርገውና ትግሬ ጠቀም የሚያሰኛቸው፣ አገነባባቸው፣ በአገሪቱ የተገነቡትን ተመሣሣይ ምርት የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን በሚያጠፋ መልኩ መዋቀራቸው ነው። በተሠራው የተከዜ ግድብ ከመብራት ኃይል ምንጭነቱ በተጨማሪ በዓመት 419 ቶን ዓሣ ማስገር የሚያስችል ሰው ሠራሽ ሐይቅም ተሠርቷል። (ምንጭ የትግራይ ክልል መንግሥት ድረ-ገጽ) እታዲያ ይህ ሁሉንም ትግሬን ጠቀመ ካልተባለ፣ ለትግሬ ሕዝብ ምን ቢደረግለት ተጠቃሚ ነው ሊባል እንደሚችል ማሳያ መሥፈርት ዐዋቂዎች ሊነግሩን ይገባል።

ስድስተኛ፣ የከተሞች ልማትና ዕድገት፦ 

 የድሮዋ ትግራይ ክፍለ-ሀገር 8 አውጃዎች እና 56 ወረዳዎች ነበሯት። ዛሬ የአውራጃዎቹ እና የወረዳዎቹ ቁጥር ከወሎና ከጎንደር የተነጠቁት ሲጨመር ከፍ ማለቱ የሚጠበቅ ነው። በዛሬዪቱ ትግራይ ዕድገታቸው የተፋጠነ፣ ዘመናዊ የከተማ መልክ ያላቸው፣ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መሠረተ ልማትና የማኅበራዊ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው አሥራ ሁለት ከተሞች አሉ። እነዚህም ከተሞች መቀሌ፣ አቢይ-አዲ፣ ዐድዋ፣ አዲግራት፣ ሁመራ፣ ማይጨው፣ ኩይሃ፣ እንዳሥላሴ፣ ውቅሮ፣ዛላንበሣ፣ አክሱም ናቸው። በከተሞቹ የተገነቡት ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፤ የተሠሩ አስፋልት መንገዶች፣ ሆቴሎች፣ መዝናኛ ቦታዎች፣ ወዘተ ከ23 ዓመታት በፊት እነዚህን ከተሞች የሚያውቅ ሰው፣ ዛሬ ቢያያቸው የሚያውቃቸው መሆኑን ለማመን ይቸገራል። አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ትውልዱ መቀሌ የሆነ፣ ከሁለት ዓመታት በፊት ትግራይን ጎብኝቶ ሲመለስ ያለኝ፣« በደሴ ወይም በጎንደር አድርገህ ትግራይ ክልል ስትገባ፣ ኢትዮጵያ ያለህ አይመስልህም። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። አውሮፓና አሜሪካ የገባህ ነው የሚመስልህ» ብሎኛል። ለዚህ ጓደኛየ ለነገረኝ የትግራይ «የአፍሪካ ታይዋን» መሆን «ሰሞኑን አዲስ» በተሰኘ ፕሮግራም ፣ኤደን ብርሃኔ በተባለች ሰው የተላለፈውን ዝግጅት ቪዲዮ በዩቲዩብ አይቸ ማስተማመኛ ሆኖኛል።

ዝግጅቱ መቀሌ ከተማ በ270 ሚሊዮን ብር የተገነባ ባለ5 ኮከብ «ፕላኔት» የተሰኘ ሆቴልን ለማስተዋወቅ የቀረበ ነበር። ሆቴሉ ላንድ ቀን አዳር ከ12ሺ እስከ 17 ሺ ብር የሚያስከፍል ነው። ይህ ሆቴል አሠራሩም ሆነ የውስጥ ዝግጅቱና አገልግሎቱ በዓለም ላይ አሉ በሚባሉት ከፍተኛ ሆቴሎች ደረጃ የተደራጀ መሆኑን ሥራ አስኪያጁና ሠራተኞቹ ሲናገሩ ይደመጣሉ። አካላዊ ገጽታውም ይህኑ ያረጋግጣል። 

ይህ ለመቀሌ ከተማ ማደግና እጅግ ዘመናዊ መሆን አንድ ማሳያ ነው።
ሌላው ነቃሽ በ2004 ዓም ሰኔ ወር ላይ በወይን ሬዲዮ የተላለፈ ዝግጅት ይህንኑ ይመሰክራል። የመቀሌ ከተማ ከፈጣን ዕድገቷ በተጨማሪ የተገነቡት መሠረተ ልማቶች ለሌሎች አገሮች አርያነት ያለው ሆኖ በመገኘቱ የአፍሪካ አገሮች የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት ማሳያ ሞዴል ሆና ተመርጣለች። በመመረጧም የበርካታ አገሮች የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜ ጎብኝተዋታል። ከተማዋን ከጎበኙት አገሮች መካከል የጋናና የኬንያ ባለሥልጣኖች ይገኙበታል። ከተማዋ በዓለም ባንክና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት በተደረገ ስምምነነት መሠረት፣ በተገኘ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በፈጀ ገንዘብ የተገነቡ የመሠረተ ልማት አውታሮችን 23 አባላትን ያካተተው የጋናና የኬንያ ልዑክ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የጋናው ልዑክ ሚስተር ዴሎ ፋንቺ የሚከተለውን ብለዋል። «በመቀሌ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮብል ስቶን ንጣፍ ለአፍሪካኖች ጥሩ ተመክሮና መከተል ያለብን ሞዴል ነው። የከተማው ጽዳት አጠባበቅ፣ የሕንፃ ግንባታ፣ በሥራው ላይ የታየው የሰው ኃይል ተሳትፎ፣ የሥራ አጥነት መቀነስ፣ ከሁሉም በላይ ሴቶችን በማሳተፍ የተከናወኑ ሥራዎች ከተማዋ የመልካም ዕድገት ምሳሌ ናት» ብለዋል።

የኬንያው የልዑክ ሚስተር ቪክርም፣ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ «በመቀሌ ከተማ እየተደረገ ያለው የዕድገት ግስጋሴ የአፍሪካ ምሳሌ» እንድትሆን ማስቻሉን በማውሳት፣ «በጣም ስባኛለች፣ እንኳን ደስ አላችሁ» በማለት የመቀሌን ከተማ ዕድገት በመገረም ገልጸውታል። መቀሌ ከክልሉና ከማዕከላዊ መንግሥት ከሚሰጠው በጀትና ከበጀት ተመላሽ ጠርቀም ያለ ገንዘብ ሌላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ለአካባቢ ልማት ሥራ አጥነትን ከከተሞች መጥፋት በሚል ዓላማ ተመሥርቶ ለከተሞች ልማት የሚውል ዕርዳታ እንደሚሰጥ ይታወቃል። በኢትዮጵያም ለ19 ከተሞች፣ በ6 ዓመት ውስጥ ሥራ ላይ የሚውል 302 ሚሊዮን ብር  ይመድባል። ከዚህ  ዕርዳታ ደጎስ ያለ ገንዘብ የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ያገኛል። በዕቅዱ መሠረት በ3 ዓመት ውስጥ አጥጋቢ ሥራ አከናውነዋል ለተባሉት አካባቢዎች የ150 ሚሊዮን ብር በጄት በተጨማሪ ድርጅቱ ሲመድብ፣ መቀሌ ተጨማሪ «አክሰሌሬትድ በጄት» (የተፋጠነ ዕድገት በጄት) ተቃሚ በመሆን 17 ሚሊዮን ብር የተጨመረላቸው መሆኑን ንጉሤ እና ጥዑመዝጊ የተባሉ የሥራ ኃላፊዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። የዚህ ዕድገት ተጠቃሚ በተናጠል የትግራይ ከተማ ነዋሪ፣ በጥቅሉ የትግራይ ሕዝብ መሆኑን እንዴት ማስተባበል ይቻላል?

ይኸው ድምፀ ወያኔ የተሰኘው ሬዲዮ እንዳስደመጠው፣ «የሥራ ማኅበሮች የለውጥ መሠላል ናቸው» በሚል መፈክር ሥር   በውስጣቸው 647485 (ስድስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አምስት) አባላት ያሉዋቸው አራት ሺህ ማኅበሮች «የገበያና የልማት ሥራ ማኅበር» በተሰኘ መጠሪያ የሚታወቁ በመላው ትግራይ ውስጥ መደራጀታቸውንና ድህነትን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሱ መሆኑን አብስሯል። አያይዞም የገንዘብ ቁጠባና ብድር አጠቃቀም ልምድ ለማዳበር 774 የቁጠባና የብድር ድርጅቶች ተመሥርተው በየገጠሩ የባንክ አሠራርን ፈለግ በመከተል ድህነትን በመዋጋት ላይ መሆናቸውን ገልጿል። በዚህም ከ97 ሚሊዮን ብር በላይ ከብክነት አድነው በቁጠባ መልክ ማከማቸታቸውን አልሸሸገም።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በዘጠኝ ወረዳዎች ብቻ፣ 11 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያላቸው ዘጠኝ የብድርና የቁጠባ ማኅበሮች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሰማራት ከባንክ የተበደሩትን በመመለስ ከድህነት ወደ ሀብታምነት መሸጋገራቸውን አስረድቷል። በወረዳ ደረጃ የተደራጁ 35 የማህበራት ኅብረት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በማከማቸት ፍራፍሬና ሌሎች ምርቶችን ለተጠቃሚው በማቅረብ ላይ መሆናቸው ተብራርቷል። በዚህና መሰል ተግባሮች ትግሬ አልተጠቀመም ከተባለ ማን ተጠቀመ እንበል?  

ወያኔ በዘር ተደራጅቶ ሰውን ብቻ ሳይሆን፣ ከተሞችን ጭምር ሊገድል ቁርጠኛ ሀሳብ ማድረጉን፣ የወያኔው የ12 ዓመት ሹመኛ የነበረው አቶ ኤርሚያስ ለገሠ በኢሣት መስኮት ብቅ እያለ ጉዱን እየነገረን ነው። ገና የሚዘከዝከው እንዳለውም በይደር ይያዝልኝ ብሎ ከአድማጮቹ ጋር ልብ አንጠልጥል ቀጠሮ ይዟል። እስከዚያው የነገረን ፍሬ ነገር ግን፣ የነፍጠኞች ከተሞች የተባሉት ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት እንዳይደረግ በፖሊሲ መወሰኑን ነው። በዚህም አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፣ ጅማና መሰል የዐማራው ነገድ ክምችት ይበዛባቸዋል የተባሉት የአገልግሎት ሰጪ ግንባታዎች እንዳይስፋፉባቸው፣ አዳዲስም እንዳይታሰብ፣ ነባሮቹም እንክብካቤ እንዳይደረግላቸው ዕድገታቸው የኋሊት እንዲጓዝ መወሰኑን የአካል ምስክርነቱን ሰጥቷል።

በወያኔ አመለካከት ሊለሙ የተፈለጉት ከተሞች አንድ ዓይነት ነገድ ይኖርባቸዋል የተባሉት እንደሆነ አቶ ኤርምያስ አስረድቷል። በዚህ ስሌት መሠረት ወጥ ቋንቋ የሚነገርባቸው ከተሞች በትግራይ ክልል ብቻ ያሉት መሆናቸውን አንባቢ ልብ ይበል። አንድ ነገድ በብቸኝነት የሚኖርባቸው ከተሞች ከፍ ሲል የዘረዘርኳቸው በትግራይ ክልል የሚገኙት ናቸው። የነዚህ ከተሞች ዕድገትም ከሌሎች እጅግ በተፋጠነ መንገድ ሊያድግ የቻለው፣ አድላዊ በሆነው የከተማ ልማት አስተዳደር በሚፈስ መጠነ ሠፊ ገንዘብ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይስተዋል አይባልም ። በዚህም የትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ተጠቃሚ መሆኑ የከተሞቹ ልማትና ለሕዝቡ የሚቀርቡት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች አፍ አውጥተው ይናገራሉ።

ሌላዋ ከተማ አዋሳ ናት። በከተማዋ ዙሪያ ሠፍሮ የሚገኘው የሲዳማ ነገድ እንደሆን ይታወቃል። ሆኖም ነገዱ በአኗኗር ዘይቤው የተነሳ፣ ወደ ከተማዋ በብዛት የገባ አልነበረም። በመሆኑም ነገዱን የከተማዋ ባለቤት ለማድረግና ባካባቢው ያሉትን ሌሎች ነገዶች ከከተማዋ ለማራቅ በታቀድ ስሌት፣ ለሌሎች ነገዶች ያልተሰጠ ዕድል ለሲዳማዎች በመስጠት፣ ለእያንዳንዱ የሲዳማ ተወላጅ ሦስት ሦስት የከተማ ቦታ በመስጠት ሁለቱን ሽጦ ባገኘው ገንዘብ ቤት እንዲሠራ ዕቅድ ወጥቶ የከተማዋ ቦታ ለሲዳማ ነገድ ተወላጆች በነፍስ ወከፍ መታደሉን ነግሮናል። አዋሳ ላይ ይህ ከተሠራ መቀሌና አዲስ አበባ ምን ሊሠራ እንደሚችል ልቦና ያለው ልብ ይበል።
ሰዎች ያልተገነዘቡት ሌላው ሐቅ፤ የኮዶሚኒዬም ቤቶች ግንባታ ዓላማ ነው። የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ግንባታ፣ የቤት እጥረትን ለመቀነስ ታስቦ የታቀደ አይደለም። የዕቅዱ መሠረታዊ ዓላማ የአዲስ አበባን ሕዝብ አሠፋፈር የነገዶች ስብጥር ሚዛን ወደ ትግሬ ያመዘነ እንዲሆን ለትግሬዎች መስፈሪያ የታለመ ነው። አንድ ትግሬ 57 ቦታ ያለው እንዳለ አውቃለሁ። በሙስና ተዘፍቆ የተያዘው የግምሩኩ ምክትል ኃላፊ እጅ ከፍንጅ ከተያዘው በሚሊዮን ከሚቆጠር ብር በተጨማሪ በርካታ የከተማ ቦታ ካርታ መያዙ የሚያመለክተው ትግሬዎቹ በቦታ ቅርምት ላይ መሰማራታቸውን የሚያመለክት ነው። በእያንዳንዱ ኮንዶ ሕንፃ የሚታዩት ትግሬዎች ብዛት የዚህ አባባል ማሳያ ነው። በዚህ ትግሬዎች አልተጠቀሙም ከተባለ ማን ተጠቀመ ልንል ነው? መቼም ዐማራ ተጠቀመ የሚሉ እንደሚኖሩ አልጠራጠርም።

ሰባተኛ፤ የአየርና የየብስ መገናኛ ግንባታ፦ መገናኛ ለአንድ አገር ሕዝብ ኢኮኖሚ የደም ሥር ነው። የመገናኛ አውታሮች መስፋፋት የሕዝቡን አንድነት ስሜት ይገነባል፤ የምርት ልውውጥን ያፋጥናል፤ የልዩነቶችን ግድግዳ ይሰብራል። ባንድ ቃል ለሁለንተናዊ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ በር ይከፍታል። በዚህ ረገድ፣ የትግራይ አውራጃዎች፣ ከአውራጃዎች፣ ወረዳዎች ከወረዳዎችና ካውራጃዎች፣ ገጠሮች ከከተማዎች መረብ መሰል በሆነ የበጋ ክረምት መንገዶች ተቆራኝተዋል። መኪና የማይገባበት የትግራይ ከተማ ቀርቶ የገጠር መንደር ፈልጎ ማግኘት ያስቸግራል። ከሁሉም በላይ ላሁኑ በኤፈርትና በትልማ ስም ተይዘው ያገሪቱን ከፍተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ፣ የእርሻና የማዕድን ምርቶችን ወደ ውጭ በቀላሉ ለመላክ፣ ወደ ትግራይ የሚገባውንም የኢንዱስትሪና የተግባር መገልገያ መሣሪያዎች በቀላል ወጭ ለማስገባት እንዲቻል ከመቀሌ ወልዲያ፣ ከወልዲያ ሰመራ፣ ከሰመራ ጂቡቲ (ታጁራ)፤ የሚገባ ከሁለት ሺ ኪሎሜትር በላይ የባቡር ኃዲድ እየተገነባ ነው። ለኋላም ለምትገነጠለው የትግራይ ረፐብሊክ፣ ከላይ ከተጠቀሰው ጥቅም በተጨማሪ  ብቸኛ የወጭና ገቢ ምርቶች ማመላለሻ እንዲሆን በተጠና መልኩ በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት በመገንባት ላይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከመቀሌ ወልዲያ ድረስ በመገንባት ላይ ያለው የ260 ኪሎሜትር የባቡር ኃዲድ ፣አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደፈጀና በመጭው 2007ዓም ሥራው እንደሚጠናቀቅ ድምፀ ወያኔ ይፋ አድርጓል።

ከባቡር ኃዲዱ ፣ ከአስፋልትና የጠጠር የመኪና መንገዶች ግናባታ በተጓዳኝ፣ ለአየር ትራንስፖርት አገልግሎትም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ግንባታዎች ተካሂደዋል። በዚህም መሠረት በአገሪቱ ታላላቅ የተሰኙና የዓለም አቀፉን መሥፈርት ያሟሉ ሁለት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያዎች አክሱምና መቀሌ ላይ ተገንብተዋል። እንዳሥላሴ፣ አቢይአዲና መሰል ከተሞች ለአገር ውስጥ በረራ ምቹ የሆኑ ጣቢያዎች ተሠርተዋል። ይህ እታዲያ የጠቀመው ጥቂት የሚባሉትን የትግሬ ነገድ አባሎችን ነው? ወይስ ሁሉንም የነገዱ አባሎች? ፕሮፌሰር መሥፍን እባከዎን መልሰዎን?

ስምንተኛ፤ በመንግሥት መዋቅር የተሠማራው የሰው ኃይል፦ በዘመነ ወያኔ የዘር አገዛዝ በየትኛውም የአገሪቱ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የኃላፊው ወይም የምክትሉ ቦታዎች በትግሬዎች የተያዙ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ይህን ማስተባበል ፈጽሞ አይቻልም።  ትግራይ ክልል አንድም የሌላ ነገድ አባል መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ተፈልጎ አይገኝም። የአገሪቱ የመከላከያ፣ የፖሊስና የደህንነት መዋቅሮች በትግሬዎች የተሞሉ ናቸው። አገሪቱ ካሏት በመከላከያ ሚኒስቴር ድርጅታዊ መዋቅር ካሉት ወሣኝና ቁልፍ ወታደራዊ የእዝ ጠገጎች ውስጥ 61ዱ የተያዙት በትግሬዎች ነው። ካሉት ጀኔራል መኮንኖች ውስጥ 57 ትግሬዎች ናቸው። የሌላ ነገድ ተወላጆቹ ሁለት ብቻ ናቸው። የሚገርመው ደግሞ ሁሉም ጀኔራሎች የዐድዋ አውራጃ ተወላጆችና ኤርትራዊ ደም ያላቸው መሆኑ ነው። ይህም ማለት የአገሪቱን ዓመታዊ የአስተዳደር በጄት የሚቀራመቱት የትግሬ ነገድ አባሎች ናቸው ማለት ነው። ለልጆቻቸው ሲዘንብ ለወላጆቻቸው አያካፋም ካልተባለ በቀር፣ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በረሃ ሲገባ፣ ልጆቹን እየመረቀ የሰደደ ወላጅ፣ በልጆቹ ጉልበት የተገኘው ጥቅም ተካፋይ አይሆንም ለማለት እንዴት ይቻላል? ዛሬ ሥብሃት ነጋ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የለውም ያሉት ኤፈርት፣ ትራንስ አፍሪካ ትራንስፖርት፣ ትግራይ ልማት ማኅበር፣ ደደቢት፣ ወዘተ የተሰኙት ኩባንያዎች የትግራይ ሕዝብ አንጡራ ሀብት መሆናቸውን እንዴት ማስተባበል ይቻላል? እታዲያ በዚህ ሁላ ተጠቃሚዎቹ ጥቂቶች ወይስ ነገዱ?

ዘጠንኛ፤ የነገዱ አባሎች በሌሎች ላይ የገነቡት ማኅበራዊ ሥነ-ልቦና የበላይነት ፦  በዚህ ጽሑፍ ማኅበራዊ ሥነ-ልቦና ስል አንድ ማኅበረሰብ ስለአንድ ነገር ያለውን ተመሳሳይ አመካከት ለመግለጽ የምጠቀምበት መሆኑን አንባቢዎቸ እንዲገነዘቡልኝ እወዳለሁ። በዚህ መሠረት ሁሉም ትግሬ፣ ያለው መንግሥት የትግሬ መንግሥት መሆኑን ያምናል ፤ይቀበላል። የደርግን መንግሥት ታግሎ የጣለ፣«የትግሬ ደመኛ ጠላት ነው ያሉትን የዐማራን የበላይነት» ያስወገደ፣ የኤርትራን ነፃነት በደሙ ያስገኘ፣ በሚለው ሁሉም ትግሬ ይስማማል። በዚህም የተነሳ ያሸናፊነትና የድል አድራጊነት ሥነልቦና የበላይነት ተጎናጽፏል። የዕለት ጉርሳቸውን በልመናል የመሠረቱ የሁሉም ነገድ አባሎች ባሉበት ቦታ፣ልብ ብለን ከሆነ፣ ከለማኞቹ ውስጥ  የመንፈስ የበላይነት ያለው ትግሬው ነው። ትግርኛ መናገር ብቻውን የልዩ ልዩ ጉዳዮች ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጎታል።

 ለምሳሌ ትግርኛ የሚናገሩ ሰዎች ከጉምሩርክ ዕቃቸው አይፈተሽም፣ ቤታቸው አይበረበርም፤ በኬላዎች ሳይፈተሹ ያልፋሉ፤ በማናቸውም ምርጫ ያለውድድር ያልፋሉ፤ ባሉት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሠሩ ትግሬዎች ካለቆቹ የበለጠ ይፈራሉ፣ ይከበራሉ፣ ድምፃቸው ይሰማል። ለዚህ በራካታ ምሳሌዎችን መደርደር እችላለሁ። አንድ ሁለት ግን ብየ ልለፍ። ወያኔ ከተሞችን ሲቆጣጠር በየቀበሌውና በየመሥርያቤቱ በታማኝነት ኃላፊነቱን በቅድሚያ የሰጣቸውና አሁንም የሚሰጣቸው ለትግርሬዎች ነው። ከዚህም አልፎ ትግርኛ የሚናገሩ የሌሎች ነገድ አባሎች የጥቃቅን ጥቅሞች ተቋዳሶች ናቸው።  «የሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ» ይባሉ የነበሩት እነማን እንደነበሩ ልብ በሉ። ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ካሰራቸውና ቤታቸው ከተበረበሩ ሰዎች ውስጥ መሆን የነበረብኝ ሰው ነበርኩ። ሊያስሩኝና ቤቴን ሊፈትሹም ግንቦት 22 ቀን 1983 ወደ ቤቴ መጡ። ባጋጣሚ ከቤቴ ትግሬ ሴት ነበረች። በሩን ሲያንኳኩ ወጥታ ምንድነው ብላ በቋንቋቸው/ በቋንቋዋ አነጋገረቻቸው። ምንም ሳይሉ፣ሰውየውንም እንየው ሳይሉ ተመልሰው ሄዱ። በኋላ ላይ እንደማነኛውም ሰው በአዋጅ ታሰረኩ። የትግሬዎች ቤታቸው አልተፈተሸም። በተቃራኒው ፈታሾች ነበሩ። ከውጭ ወደ አገር ቤት ሂደው የሚመለሱ ትግርኛ መናገር የሚችሉ ዕቃቸው ሳይፈተሽ፣ እነርሱ እንግልት ሳይደርስባቸው እንደሚወጡና እንደሚገቡ በይፋ የሚናገሩት ነው። ወደ ክፍለ-ሀገርም ሲሄዱ በየኬላው ችግር እንደማይገጥማቸውና ቋንቋው እንዳስከበራቸው ፣ይህም በሕዝቡ ላይ አድልኦ እየተሰራ መሆኑን ይመሰክራሉ። ሌላው ቀርቶ ከትግራይ ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች ሴቶች ባል ሊያገቡ ነው ሲባል፣ ቀድሞ የሚነሳው ጥያቄ ትግሬ ነወይ? የሚለው ነው። ትግሬ ካልሆነ ምንሊሠራላት እንደሚባል ይሰማል። ይህም የፖለቲካ ሥልጣኑ በወያኔ በመያዙ ነገዱ በጥቅል ያገኘው ጥቅም ነው። ይህስ ጥቅም አይባል ይሆን?

አሥረኛየወያኔ አገዛዝ ዘረኛ (አፓርታይድ) መሆኑ፦ የወያኔ አገዛዝ መሠረታዊ መመሪያ ዘረኝነት ነው። በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የፌደራል የመንግሥት አደረጃጀት፣ እየታየ ያለው የሥልጣንና የንብረት አያያዝ ይህኑ አፍ አውጥቶ የሚናገር ነው። ይህም በመሆኑ የወያኔ አገዛዝ ከደቡብ አፍሪካ የነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ጋር አንድ ነው። ነጮቹ በመካከላቸው የሀብት ልዩነት፣ የሚፈጥረው የመደብ ልዩነት እንዳላቸው ሁሉ፣ በትግሬዎችም ይህ ልዩነት አለ። ፕሮፌሰር መሥፍን መቀሌ ላይ የተገነባውን የወያኔ ባለሥልጣኖች መኖሪያ ሠፈር ሕዝቡ አፓርታይድ ብሎታል በማለት የትግራይ ሕዝብ የተቃውሞ መግለጫ እንደሆነ ያምናሉ። አፓርታይድ የተሰኘው ሠፈር የትግሬ ሕዝብ በማኅበራዊ መደቦች መከፋፈልና ክፍፍሉም  በያዙት የፖለቲካ ሥልጣን የተነሳ፣ የአገሪቱን ሀብት የዘረፉት ሰዎች ከቀረው ሕዝብ በኑሮ መለየታቸውን እንጂ፣ የሕዝቡን ተጠቃሚ አለመሆን የሚያሳይ አይደለም።  የደቡብ አፍሪካ ነጮች በአጠቃላይ፣ በጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ላይ ተመሣሣይ አመለካከት እንዳላቸው ሁሉ፣ ሁሉም ትግሬ በወያኔ ዓላማ፣ የኢትዮጵያን ሀብት በመዝረፍ እና ትግራይን በሌሎች ኪሣራ በመገንባት  ላይ ልዩነት ፈጽሞ የለውም። ወያኔ ትክክል ነው፤  ወያኔ የትግራይ ሕዝብ ልጅ ነው፤ወያኔ ደርግንና ዐማራን ተዋግቶ አሸንፏል፤ በመሆኑም ጀግና ነው፤ በዚህም የተነሳ የትግሬ ሕዝብ ጀግና ነው፣ ስለዚህም መግዛት አለበት ብሎ ከልቡ ያምናል።  ቅኝ ገዥዎችና የአፓርታይድ አገዛዝ የወጡበትን ነገድ፣ወይም ማኅበረሰብ ወይም ሕዝብ ጥቅም በጥቅሉ እንደሚያስጠብቁ ሁሉ፣ ወያኔም የወጣበትን ነገድ ሁለንተናዊ ጥቅም እያስከበረ ያለነው። ስለሆነም የትግራይ ሕዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች በዘመነ ወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ገዥ ነው።

የትግራይን ሕዝብ ተጠቃሚ መሆን፣ የጎጃም ገበሬ በ1982ዓም ጎንደርንና ጎጃምን እንደተቆጣጠሩ ባሳዩት የእህል እና የጋማ ከብት ሽሚያ፣ እንዲሁም የባሕርዛፍ ምንጠራ እንዲህ ሲል በተለመደ የብሶት መግለጫው ተናግሯል፤  
ከተተ በኬሻ፣
መዘነ በኪሎ፣
ጫነ በመኪና፣
ከጎጃም ነጭ ጤፍ፣
ከቤጌምድር ገብሱን እህል ጥራ-ጥሬ፣
ከደንቢያ  ማሽላ፣ ሽምብራ፣ በርበሬ፣
በልጆቹ ጉልበት ጠግቦ አደረ ትግሬ፤
ይህ ነው ሐቁ!

ፕሮፌሰር መሥፍን ይህን ሁሉ አያውቁም፤ አልሰሙም አይባልም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) የተሰኘ የሰብአዊ መብት ድርጅት አቋቁመው ለሕዝብ መረጃ ይረጩ እንደነበር አስታውሳለሁ። አውቃለሁም። ያ እርሰዎ ታረደ፣ ተገደለ፣ ንብረቱን ተቀማ እያሉ ይጮሁለት የነበረ ሕዝብ እኮ! ገዳዩም፣ አሳሪውም፤ ንብረት ቀሚውም ሕወሐት እንደነበር እንዴት ዘነጉት? ወይስ የሕወሓት ሠራዊትም እንደሚሉት ጥቂት ነው? ጥቂትስ ከሆነ ስንት ነው? ሕወሓት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ አብራክ ወጥቶ፣ የትግራይ ሕዝብ ባሕር፣ ወያኔ ዓሣ ሆኖ፣ እያንዳንዱ ትግሬ የወያኔ ዓይንና ጆሮ ሆኖ፣ ለድል የበቃ የፋኖ ድርጅት መሆኑን መቼም ያጡታል አልልም። ያ ሁሉ እርሰዎ የጮሁለት ተበዳይ ሕዝብ ፍትሕ ሳያገኝ፤ ለበዳዩ ነገድ አባል ያውም ለምን እንደሚለምን፣ የልመናውን ግብ በቅጡ ሳያውቁ፣ በመንገድ ላይ በደከመ ድምፅ የዕለት ተግባሩን ለመከወን ሲማጸነዎት፣ ልጆቹ፣ ወንድም እህቶቹ እና እርሱም ጭምር በሕዝባችን ላይ እያደረሱ ያለው ጥፋትና በደል ተረሳዎት? መቼም ወያኔ ተጠቅሞ መወርወር፣ «እንደ ሸንኮራ አገዳ መጦ መጣል» ባሕሪው ነውና፣ ይህንም ለማኝ ቄስ መሰል ሰው፣ ተጠቅሞ የወረወራቸው ሊሆኑ ይችላሉ። የአጋዚ አልሞ ተኳሽ ጦር አባል የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ወይም በዚያ መልክ እየለመኑ መረጃ እንዲሰበስቡ የተመደቡ ሊሆኑ ይችላሉ።

ለዚህ አባባሌ ተጨባች መረጃ ልስጥ። በ1982ዓም ላይ ደቡብ ጎንደርንና  ጎጃምን ለማጥቃት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ባሕርዳር በተለምዶ አጠራር መኮድ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ሠፍሮ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰልሉ የተመደቡት ሁለት ሴት ትግሬ ለማኞች  ነበሩ። ሁለቱም ጣና ዳርቻ ላይ ከቆሻሻ መጣራቀሚያ የፕላስቲክ ጎጆ ቀልሰው፣ የሬዲዮ መገናኛ በቡትቶ ውስጥ ደብቀው፣ ቀን ቀን ራቁታቸውን የጦሩን እንቅስቃሴ እብድ መስለው ሲሰልሉ በመዋል ማታ ማታ ያገኙትን መረጃ ያስተላልፉ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ጦሩ ለዘመቻ ሲንቀሳቀስ፣ አንዷ አውቆ አበድ መሆኗን በቅጽፈት ረስታ፣ አንዱን የጦር አባል «አይመልስህ፣ በሄድክበት ተደፋ» ትለዋለች። ጊዜው የውጥረት ብቻ ሳይሆን፣ የአለቃና ምንዝር ግንኙነት የላላበት፣ ሁሉም የፈለገውንና ያሻውን በፈለገው ጊዜ ማድረግ የሚችልበት ስለነበር፣ ወታደሩም በገዛ እጁ ፍርድ ሰጠ። በታጠቀው መሣሪያ ግንባሯን ብሎ ገደላት።

በዚህ ተንኳሽ ድርጊት አንቂነት ያችኛዋም ሰላይ ትሆናለች የሚል ጥርጣሬ በማሳደሩ፣ በተደረገ ክትትል ሌሊት በሬዲዮ መረጃ ስታስተላልፍ እጅ ተፍንጅ ከነመገናኛ መሣሪያው መያዟን አውቃለሁ። እናም ይህን የመሰለውን ጉዳይ በቅጡ ሳያገናዝቡ፣ የነዚያ በወያኔ ሠራዊት የተገደሉ፣ ቤት ንብረታቸውን ያጡ፣ ካገር የተባረሩ፣ ወላጆቻቸውን ያጡት የአያሌ ግፉአን በደልና ግፍ ከመቅጽፈት ከኅሊናዎ ተሰውሮ፣ የአንድ «ትግሬ ለማኝ ቄስ» ራበኝ ማለት «ትግሬ ሁሉ ርሃብተኛ ነው» ከሚል መደምደሚያ አደረሰዎ። ቢዘነጉት ነው እንጂ፣ ድሮም ቄስ ደብተራ ስለ ማርያም ብሎ ለምኖ ነው ትምህርቱን የሚማረው። የቄሱ ልመና ለዚህስ ቢሆን ምን ማረጋገጫ አለዎ? በሌላም በኩል የሰቆጣ አገዎች ትግርኛ ይናገራሉ። ድምፃቸውም የትግሬ ይመስላል። ይህ ቄስ የሰቆጣ አገው ሊሆኑ ቢችሉስ? አገዎች መበደላቸው ዕውነት ነው። ራያዎች መበደላቸው ሐቅ ነው። ዐማራው ሆን ተብሎ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በመርፌ እየተወጋ ሙትና ታማሚ እንዳደረጉት በርካታ መረጃዎች ያሳያሉ። ለኤድስ በሽተኞች ዕድሜ ማራዘሚያ ተብሎ ከዓለም ለጋሽና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጠው መድኃኒት ለዐማራው ክልል ሕዝብ የሚሰጠው እንክብል ከበሽታው ጋር ምንም ዓይነት ግንኑነት እንደሌለው በሙያው ጥናት ያደረጉ ሰዎች አረጋግጠዋል። ይህ ከማስጮህ አልፎ፣ ወኔው ቢገኝ እንደ ወያኔ ዱር ቤቴ ብሎ የጠላት ሆድ ቁርጠት መሆን ነበር። ባይሆን ለተበደሉና ለተገፉ ድምፅ መሆን ሲገባ፣ ጠግቦ ሲያገሳ ለሚያድር እሪታን ምን አመጣው። ወይስ «ከተራበ ይልቅ ለጠገበ እዘኑ» የሚለው ያባቶቻችን ባህል እሥረኛ ሆነው ይሆን? የፕሮፌሰሩ የትግሬ ተራበ ጩኸት «ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ» ሆኖባቸው ይሆን? ምክንያቱም፣ ከትግሬ ተጋብተዋል። ልጆቻቸው ትግሬዎች ናቸው። ወይም በደንብ የሚያውቋቸው እንደሚነግሩን ከሆነ፣ በዐማራ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ አላቸው ይባላል። ይህን አባባል በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጋራ ሀሳብ ሙዳይ መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 15 ሐምሌ 1992 ዕትም ላይ እንዲህ የሚል የዓለማየሁ ሞገስ የኑዛዜ ቃል አለ። የቀደስ ዓለማየሁ ሞገስ የኑዛዜ ቃል በከፊል እንዲህ ይላል፦

 «ለመሆኑ ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም የሚባል ሰው ማነው? ለሚል ጠያቂ፣ፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማርያም  የልከኛውና የዝነኛው ደራሲ አቶ አሥረስ፣ የደብረ ማርቆስ አውራጃ ልዩ ስሙ የዳ ተወላጅ ልጅ ነው። ወንድሙ ኮሎኔል ግርማ አሥረስና እሱን የሚመስሉ እህቶቹ አቶ አሥረስን የሚመስሉ ሁለት ሴት ልጆች አሁንም አሉ። እውነትን ለማወቅ የሚፈልግ አስተያይቶ ሊያረጋግጥ ይችላል። አቶ አሥረስ የሚያሳፍሩ ሰው አልነበሩም። የተማሩ ነበሩ፤ለምን እሳቸውን ትቶ መሃይሙን ወ/ማርያምን መረጠ ለሚል ጥያቄ» 

 ዓለማየሁ ሞገስ የሚሰጡት መልስ አለ። መልሱ ባጭሩ አባታቸውን መካዳቸውን የሚያመለክት ነው። ከላይ ጽሁፌን ስጀምር «ይህ ክህደት ነው» ብዬ ለደመደምኩበት ሀሳብ ማጠናከሪያ ነቃሽ እንዲሆነኝ ያቀረብኩት ነው። ትናንት የተጀመረ ክህደት ዛሬም በገሀዱ ዓለም የምናየውን ዕውነት ሲክዱ እያየን ነው። ይህ ሁሉ እርሳቸው በሕይዎታቸው የሚያስጠይቅና የሚያስተች ኃላፊነት ሳይወስዱ ሲተቹ የኖሩ በመሆኑ፣ ከመሸ ቢሆንም፣ ያላግባብ የሚቀርብ ትችት የሚመር መሆኑን እንዲቀምሱት ነው።
ፕሮፌሰሩ በሕይዎት ዘመናቸው ኃላፊነትን አጥብቀው ሲሸሹ የኖሩ ናቸው። ምክንያቱም ኃላፊነት የሚያስከትለው የተጠያቂነት ጉዳይ አለ። ኃላፊነትን የሚወስዱ ሰዎች በራሳቸው ላይ የማዘዝ፣ የግል ፍላጎትና ስሜቶቻቸውን ባሻቸው ወቅትና ሰዓት ለማድረግ አይችሉም። ኃላፊነቱ ይዞት የሚመጣ ተጠያቂነት አለ። ራስን ዘና አድርጎ ከፈለጉት ቦታና አካባቢ መገኘትን ያግዳል። ጥሩ ሲሠራ ከበሬታና ተወዳጅነትን ከማትረፉ ባሻገር፣ ትንሽ ስሕተት ሲገኝ የተራራ ያህል ገዝፎ ወቀሳና ትችት ያስከትላል። ይህን በመፍራት ይመስላል ፕሮፌሰር መሥፍን ኃላፊነትን ሲሸሹ የኖሩት። ለትችት ግን ቀዳሚ የላቸውም። ንጉሡን፣ ደርግን፣ የቅርብ አለቆቻቸውንና የሥራ ባልደረቦቻቸውን በመሞለጭ ይታወቃሉ። ይህ ቀረ፣ ያ ቀረ፣ እንዲህ መሆን ሲገባው እንዲህ አልሆነም ማለትን ያበዛሉ። ኃላፊነት ወስዶ የተጣመመውን ማቃናት፣ ያጠረውን ማስረዘም፣ የጎበጠውን ማረቅ፣ የጠፋውን መተካት ለፕሮፌሰር መሥፍን አስፈሪ ተራራ ነው። ለዚህም ነው  ከኃላፊነት ሲሸሹ የኖሩት።

በዚህ ትችታቸው የተሰላቹት ንጉሠ ነገሥቱ፣ እስቲ ገብቶ ይየው በሚል መልክ፣ በዚያን ጊዜ ከፍተኛ የሚባል ኃላፊነት ሰጧቸው። በወለጋ ጠቅላይ ግዛት የጊንቢ የአውራጃ ገዥ አደረጓቸው። እርሳቸው ግን አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ የፈለጉትን በፈለጉት ሰዓት እያደረጉ መተቸት እንጂ፣ ሠርቶ ማሠራት፣ ለሌሎች የተግባር አርኣያ መሆን፣ የሚሉት በአዕምሮአቸው ባለመኖሩ፣ በአማላጅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት አስረከቡ። ደርግም የኢትዮጵያ ችግር የብሔረሰቦች ነው የሚለው ጎልቶ የሚስተጋባበት ወቅት ስለነበር፣ ችግር ነው የሚባለውን አጥንቶ መፍትሔ ለመስጠት የአገሪቱን ምሑራን ጋብዞ ችግሩን እንዲያጠኑና የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያመነጩ ጥሪ ሲያቀርብ፣ አንዱ ጥሪ የተደረገው ለፕሮፌሰር መሥፍን ነበር። «አጅሬ» ግን ዛሬም እንደተለመደው አልሞከርም አሉ። ኃላፊነትን በድጋሜ ሸሹ። ራሳቸው በወሳኝ መሪነት ካደራጁት «የቀስተደመና» ፓርቲ በኃላፊነት ይቀመጡ ሲሏቸው አይሆንም አሉ። ለሦስተኛ ጊዜ ኃላፊነትን ሸሹ። በቅንጅት ምሥረታም ኃላፊነት እንዲወስዱ ሲጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። ሥራቸው ሁሉ ከኃላፊነት መሸሽ!

ይህ ሽሽታቸው ወህኒቤትም አብሯቸው ገባ። ማኪያቶ እየጠጡ፣ ሙቅ ከቀዝቃዛ እያማረጡ፣ የፈለጉትን በፈለጉት ቦታና ጊዜ የማድረግ ነፃነታቸውን ላጭር ጊዜ ሲነጠቁ ሌላ የሽሽት መንገድ መረጡ። «የወንድ በር»  የሚሉት። ዓላማ ላለው ሰው ሁለት ዓመት መታሰር ምንም ማለት አይደለም። ሁላችንም ቀምሰነዋል። ብዙዎችም እየኖሩበት እንደሆነ እናውቃለን። ይህ ግን ለፕሮፌሰር መሥፍን የሚቻል አልሆነም። መሸሻ መንገድ መፈለግ ነበረባቸው። መንገዱንም በአገር ውስጥና በውጭ ተወጥሮ ተይዞ፣ መተናፈሻ ይፈልግ የነበረው መለስ ዜናዊ ጠረገላቸው። ማንም የሽማግሌና የሽምግልናን ጉዳይ በሚገባ የሚያውቁ ሰዎች የሚስማሙባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ። ይኸውም የሽምግልና ዋና ተልዕኮው፣ አንዱ አጥቂ ሌላውን ተጠቂ የሚያደርግ ሳይሆን፣ ሁለቱም ወገኖች ከመጠቃቃት ስሜት ወጥተው፣ የድል አደራጊነት ስሜት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። ለዚህ ዕውነተኛ ስሜት መፈጠር ይረዳ ዘንድም፣ የአሸማጋዮቹ  ቁጥር ጎደሎ ሆኖ( ማለትም 5፣ 7፣ 9፣ 11 ) አንዱ ሰው በሁለቱም ተደራዳሪዎች ፍላጎት የሚከበርና የሚሰጠውን ውሳኔ የሚቀበሉት የሆነ በሰብሳቢነት፣ ሌሎቹ በተቃራኒው ወገን ተቃውሞ የማይቀርብባቸው ሆኖ፣ እያንዳንዳቸው የመረጧቸው ሰዎች በስምምነት የሚያቋቁሙት ባህላዊና ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው የፍትሕ ማኅበራዊ ተቋም ነው።

ከዚህ መሠረታዊ የሽምግልና አሠራርና የሽማግሎዎች አሰያየም ወይም አመራረጥ ስንነሳ፣ ሽማግሌዎች የሚመረጡት ሁለቱ ተሸማጋዮች የመረጡዋቸውና የተስማሙባቸው መሆኑ የማይታለፍ ጉዳይ ነው። ይህ ካልሆነ ጉዳዩ ሽምግልና ሳይሆን ዳኝነት ነው የሚሆነው። ያውም ፍርደ-ገምድል፤ በቅንጅት አመራሮችና በወያኔ መንግሥት መካከል የታየው «የሽምግል»ና ሂደትም ይኸው የፍርደ-ገምድል ፍርድ ነው። ለዚህ ፍርደ-ገምድል ሂደት መሳካት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የራሳቸውን ጉልህ ሚና ተጫውተዋል። የመጀመሪያው ሽማግሌዎች በጋራ ሳይመረጡ፣ በነርሱም ላይ የጋራ ስምምነት ሳይኖር፣ ሽማግሌ ብሎ መጥራት በራሱ ታላቅ ስሕተት ነው። በዚህ ረገድ ታሳሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ መላው ሕዝብ፣ በተለይም የመገናኛ ብዙኃን ሂደቱን የዘገቡበት ከዕውነታው እጅግ በራቀና ፍጹም ስሕተት በሆነ መንገድ ነበር። ሽማግሌዎች አልነበሩምና! በሁለቱም ወገኖች የተመረጡና የወል ስምምነት የተደረገባቸው አልነበሩምና!  እነዚህ መለስ ከገባበት አጣብቂኝ እና እየደረሰበት ካለው ዓለም አቀፍ ውግዘት መውጫ ቀዳዳ ለማግኘት ራሱ የመረጣቸውን ምልምሎቹን ሽማግሌ ብሎ መቀበልና ሀሳባቸውን ለማዳመጥ መከጀል በሁለት መልክ ክህደት ነው። አንደኛ የጋራ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ራስን አስገብቶ የሕዝብን ድምፅ ተቃራኒ ወደሆነ አቅጣጫ ማዞር ክህደት ነው። ሁለተኛ ነባሩን የሽምግልና ባህልና አሠራር የሚቃረን ክህደት ነው።

ፕሮፌሰር መሥፍን ለነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ዋጋ ሳይሰጡ፣ «የወንድ በር እንስጣቸው፣ እንሸማገል» በማለት ድምፃቸውን ለሽማግሌ ተብየዎቹ ቀድመው የሰጡ እንደሆነ፣ ካሸማጋዮቹ አንዱ የነበሩት ሰው፣ ከዚህ ዋሽንግተን ዲሲ መጥተው የልብ የልባችን ስንጫዎት አውርተውኛል። ይህ የእርሳቸው አባባልና ሀሳብ ገዥ ሆኖ፣ በሚያሳፍር ሁኔታ መለስ በፈለገው መንገድ  የቅንጅት አመራሮች «አጥፍተናል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ያድርግልን» የሚል ፊርማ ፈርመው፣ የሕዝቡን ትግል ስሜት አኮላሽተው፣ ራሳቸውን ለኅሊናዊ እስር ዳርገው፣ ከአካላዊ እስር ወጥተዋል። ይህን ሁኔታ ሳስብ አንዲት ባለቤቷ በሚያሳፍር ሁኔታ፣ አህያዋ ደግሞ ጀግኖች በሚሞቱባት አሟሟት የሞቱባት ሴት አንጎራጎረችው የሚባለው የኃዘን እንጉርጉሮ ትውስ ይለኛል፤ እንዲህ ነው፣
« የዘንድሮው ነገር የማይሆነው ሆነ ፣
የአህያዬ አሟሟት ለባሌ በሆነ፤» 

በፕሮፌሰር መሥፍን ፈር ቀዳጅነት በሌሎች ተከታዮች አጃቢነት የተቀነቀነው «የወንድ በር እንስጣቸው» ዜማ የማይሆነው እንዲሆን አድርጎ፣ ሕዝባችን ለተከታዮቹ ዓመታት ለሥቃይ እንደዳረገው አይተናል። ለዚህ ማስረጃ አምጣ የሚለኝ ያለ አይመስለኝም። እየኖረበት ነውና! Published on Ethiopian Semay (Editor Getachew Reda)