Getachew Reda feeding his birds |
-->
ወፎችን እየመገበ ያለዉ “እጅ” እኔዉ ራሴ ጌታቸዉ ረዳ ነኝ፤፤ ሚዲያ ለሰዉ ልጆች ምግብ ነዉ፤፤ከእኛ በታች በቁጥጥራችን ሥር ያሉት ምንም የማያዉቁ እንሰሳት እኛኑን ያምናሉ። ገዳያቸዉም ይሁን መድሃኒታቸዉ ስለማያዉቁት እኛ ወስነን በምንመግባቸዉ የሕሊና ፍርድ ተማምነዉ አምነዉን የሰጠናቸዉን ይመገባሉ፡፡ ለጥፋትም ለበጎም የዜና መጋቢዎች ከፍተኛ ሃላፊነት አለብን።ጌታቸዉ ረዳ መልካም ገና፤፤ መልካም ንባብ!
የይቅርታ መቋጠርያ ከረጢቶቻቸዉ ሲመረመሩ የሚሰጡን ምክንቶቻቸዉ
ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com -->
ምን እንደነካኝ ባላዉቅም ቆየትየት ብሎኛል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዬን የትግርኛዉም ሆነ የአማርኛዉን ክፈለጊዜ ካዳመጥኩኝ፣፣ብዙ እንደቀረብኝ ባዉቅም ሌሎቹ ጓዶቼ ስለሚከታተሉት ጀሮን የሚያስቆም ዜና ሲተላለፍ ተሎ ያስተላልፉልኛል እና ብዙም አላመለጠኝም ብልም አንዳንዱ ግን ያመለጡኝ ይመስለኛል፣፣ ካመለጡኝ መካካል አንዱ ባለፈዉ ሰሞን እንደምንም ብየ ድረገጻቸዉ ዘንድ ስጎበኝ የወያኔዉ ጦረኛ ስየ አብርሃ እና በወያኔ መንግሥት “የሃገሪቱ ፕረዚዳንት” ተብለዉ ሲጠሩ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቅዳሜዉ የእንግዶች ክፍለጊዜ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸዉን ባጋጣሚ ቁልፉን ስጫነዉ የሚመሰገን የጋዜጠኛነት ብቃትዋን ያሳየችበት የአዳነች ፍስሃየ ዝግጅት አገኘሁ፣፣ ሁለቱንም ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣኖችን በመወጠር አልተነፍስ ሲሉ ለማስተንፈስ ተጭና አልለቅ ብላ ስታስጨንቃቸዉ ያዳመጥኳት በጉግትም በአድናቆትም ነበር፣፣
መድረክ በተባለዉ ስብስብ ምን ሚና እንደሚጫወቱና ለምንስ እንዴትስ እንደተቀላቀሉ የመሳሰሉት ጥያቄዎች አቅርባ ያላቸዉን መልስ ከሰጡዋት በሗላ፣ ባለፈዉ የሥልጣናቸዉ ዘመን ባልሰራነዉ ነበር ብለዉ ዛሬ የሚፀፀቱባቸዉ የወስዷቸዉ ጎጂ ዉሳኔዎች ካሉ ዘርዝረዉ እንዲያሰረዱ ለጠየቀቻቸዉ ምክንያት ደ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ትላልቅ ወንጀሎች ከመናገር ቢቆጠቡም ጥቂቶች ቢሆኑም ከጓዳቸዉ ከስየ አብርሃ ባቀራረባቸዉ የተጸጸቱባቸዉ አንዳንድ ነገሮችን “አፍ ማስዘጊያ” ይሆን ዘንድ በተሻለ ሁኔታ ሲወረዉሩ በአንፃሩ አቶ ስየ አብረሃ ስህተት ሰራሁ ብሎ የሚፀፀትበት ካለ ያቺዉ ሁሉም ኢትዬጵያዊ ቀርቶ ዓለም የሚያዉቀዉን “የኤርትራ ጉዳይ” እንደ የማምለጫ በር ሲጠቀምባት ከማዳመጥ ሌላ ታላላቅ ስሕተቶች ሰርቻለሁ ብሎ እንዲህ እንዲህ የመሳሰሉት መጥፎ ምግባሮች/ሰብዓዊ ነክ እና ብሔራዊ ወንጀሎች ስሕተት ፈጽሜአላሁ/ፈርሜአለሁ/ተካፍያለሁ/አዝዤ ነበር፣ ነበር ወይንም እንዲከናወን ተካፍያለሁ ወዘተ ለማለት ከብዶት የተለመደዉ “ትዕቢቱ” አላስተነፍስ ብሎት የሰጣቸዉ ምክንያቶች “ያኔ ወጣትነት፣ ጮርቃነት፣ የአለመብሰልነት ሁኔታ…ስለነበር የተሰሩ ስሕተቶች ከነበሩ/ሊኖሩ ይችላሉ ከዛዉ አንጻር ነዉ…..ወዘተ…ወዘተ… በማለት “በጭረቅ” (ትንፍሽ) ላለማለት ለሕዝብ ያለዉ ንቀት ለስሕተቶች መፈፀም “ሎጋነቱን፣ወጣትነቱን፣አለመብሰሉን…” የማሳሉት እንደ ምክንያት ሲገልጽ ባደማጥኩበት ወቅት፣ የአቶ አሰፋ ጫቦ ብዕር ጆሮየ ላይ ድንቅር ብሎ “ሹክ” አለኝ፣፣
አቶ አሰፋ ከኢሕአፓዎች ጋር በተለይም ከሐዋርያዉ የዜናዉ ባሻገር ዘጋቢ ከአቶ መስፍን ታምራት (ከኪኒያ) ጋር ስሕተትን እና ይቅርታን በሚመለከት አንሰተዉ መልስ በሰጡበት ወቅት ያስነበቡንን ነበር የስየ አብርሃ መልስ ያስታወሰኝ፣፣ አቶ አሰፋ ጨቦ አንዲህ ሲሉ ጻፉ፣
“ከዛሬ 26 ዓመት በፊት የተደረገ ሥሕተት ቢኖር “አለ ብሎ የተቀበለ ግን አላየሁም!” ይቅርታ ማድረጊያ በቂ የታወቁ ምክንያቶች ይኖራሉ፣፣ ልጅነት…ወጣትነት…አፍላነት…የአብዬቱ እንግዳ ደራሽነት…የፖለቲካ ተሞክሮ አለመኖር… እያልን መሄድ ይቻላል፣፣ከ26 ዓመት በሗላ ፣አያት ከተሆነ በሗላ ያንኑ መልክ ያንኑ ‘ዉሃ ዉቀጥ” መደጋገሙ ምን ስም ሊሰጠዉ ይሆን? ይቅርታና ምክንያት መቋጠርያ ከረጢት ሁሉ ባዶ የሚሆን ይመስለኛል፣፣ ይልቁንም አንድ “ፍቅር እስከመቃብር” ላይ ያነበብኩትን አስታወሰኝ፣፣ አንድ ምራቃቸዉን መዋጥ የሚገባቸዉ ሰዉ ምራቁን እንዳልዋጠ ሰዉ ሲናገሩ ተደመጡ፣፣… ምና! ምና! ምራቃቸዉን የዋጡ ሰዉ ሁነዉ እንዲህ ይናገራሉ…! ተባለ፣፣ጉዱ ካሣ “…እንኳን ምራቃቸዉን ሊዉጡ ገና አልሰበሰቡም!” አለ፣፣ የአቶ ታምራት መስፍን ጽሑፍ ከዛሬ 35 ዓመት በፊት ያነበብኩትን “ፍቅር አስከመቃብር” አስታወሰኝ፣፣ (ጉግሣ መጽሄት ገጽ 8 መጋቢት 1993 ዓ.ም)፣፣
አቶ ስየ አብርሃ በስልጣን በነበረበት ወቅት ብቻ ተጠየቀ እንጂ ጫካ ዉስጥ በሰልጣን በቆየበቻዉ (ምናልባትም 17 አመት) ጊዜያቶች የፈፀማቸዉ ፣ግለሰባዊ እና ማሕበራዊ ወይንም ሰባዊ ነፃነት፣መብት፣ሕይወትን የሚመለከቱ ጥሰቶች ተናገር ተብሎ ቢጠየቅ በጋራ ዉሳኔም ሆነ በተናጠል የፈጸማቸዉ እርኩስ ወንጀሎች ዘርዝሮ ለመናገር እየዘገነነዉ እንደሆነ ሁላችንም የምናወቀዉ ጉዳይ ነዉ፣፣ ገብሩ አስራትም እንደዚሁ “ድሃይ” በተባለዉ የትግርኛ መጽሄት “በህወሓት ሥር ሆኜ ፈጸምኳቸዉ ስሕተቶች ሊኖሩ ይችሉ ይችሉ ይሆናለ ካሉም በድርጅቱ ሥር ሆኜ የፈጸምኳቸዉ እንጂ እኔ በግሌ ፈጸምኳቸዉ የሚጸጽቱኝ ጥፋቶች የሉም በማለት” አጉል መፈራገጥ/ሂፒክሪት በመግባት ለማምለጥ የሞከረዉ እንዳለ ሆኖ የትግራይ ክፍለሃገር “ፕረዚዳንት” ሆኖ ሕዝቡን ለ10 ዓመታት ሲጨቁን በነበረበት ወቅት ታጋዬቹ እሱ እና ባለደረቦቹ ጫካ በነበሩበት ወቅት የፈጸሙዋቸዉ ሰብአዊ ወንጀሎች በገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዲጠራላቸዉ ያመች ዘንድ “ልዩ አካል” እንዲቋቋምላቸዉ ሲጠይቁ “ለነፃነት ተብሎ የተደረጉ ጥፋቶች ስለሆኑ ጫካ ሆነን የሰራናቸዉ ጥፋቶች አያስጠይቁንም” ሲል በቴሌቪዥን መናገሩን የሚታወስ ነዉ፣፣ ስየም ሆኑ ሌሎቻችሁ እንደኔ እንደ እኔ ከሆነ የምለግሳችሁ ምዕዳን ቢኖር እንዲሁ በደፈናዉ “ስሕተት ፈጽመናል ተብሎ ነካ ነካ እያደረጉ ትላልቆቹን የጅምላም ሆኑ የነብስ ወከፍ ግድያዎች የተፈጸሙትን ወንጀሎች እያፈኑ ዓለም የሚያዉቀዉን ነጋሪ የማያስፈልገዉን የኤርትራን ጉዳይ “የይቅርታ መጠየቂያ የማምለጫ በር” አድሮ መሸወዱ እና “ወንጀል ብነፈፅምም “አፍላ ነበርን፣ ወጣቶች ነበርን፣ ብርካችን አልጠናም ነበር፣ ……..ወዘተ” የመሳሰሉ ምክንያቶች ያንኑ በየመድረኩ መደርደር “ዉሃ ወቀጣ” ከመሆን አልፎ የሚፈይደዉ ስለሌለ ይልቁንስ የማምለጫ ምክንያቶች የያዙ ከረጦቶቻችሁ ሁሉ ባዶ እየሆኑ ስለሚታዩ ራሳችሁን አጉል ባታስገምቱ እና ጨከን ብላችሁ “የኑዛዜዉን መንገድ!” ብትረግጡ በሰቀቀን ከመኖር ትገላገላላችሁ የሚል ነዉ፣፣በሰማዩም በምድሩም ምሕረት ታገኛላችሁ፣፣
የኢትዬጵአዊነት ሃይላት የገጠሙን ጠላቶች ለጊዜዉም ቢሆን (የለየላቸዉ የግንጠላ ፖለቲካን የሚያራምዱትን ወደ ጎን ትተን) በአገር ዉስጥ የሚኖሩ በዓረና ትግራይ እና በመድረክ ዉስጥ የሚገኙ ፋሺስቶች በሚልኩላቸዉ አሉባታ በመቀበል ያንኑን አሉባልታ በመኢአድ እና መሪዉ ላይ “ታርጋ” በመለጠፍ አሉባልታቸዉን ተቀባይ እንዲኖረዉ ለአልቧልታቸዉ ልዩ አምድና የዘመቻቸዉ ድምቀት በመስጠት ሰዉን ለማሳመን እየተሰራጨ ያለዉን በጣም ርካሽ የፋሺስቶች ባሕሪ ስንገምግም፣፣ ይህ ትንኮሳ እና አደረጃጀት “ከወያነ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ” ድርጅት ለሁለት መሰንጠቅ በሗላ በግልም በድርጅትም የተደራጀ ሃይል እየሆነ የመጣ ቢሆንም፣ በይበልጥ አፍጥጦ “ጸረ-አማራ” ኢላማዉ አድርጎ በአንድነት ሽፋን ስም የ1991 ዓ.ም ቱ የጥላቻ እና የነፍጠኛ ጥላቻዉ ዘመቻ ተቋርጦ ከተተወዉ ምዕራፍ ለመቀጠል እየተንቀሳቀሰ “አዲስ ግን ነባር ቡድን” ራሱን በሦስት ቦታ በመመደብ ፋሺስታዊ ባህሪ በተላበሰ ፖለቲካዉን ለመቀጠል እየተሯሯጠ ያለ ሃይል ብቅ እያለ ነዉ፣፣ እነዚህ ፋሺስታዊ እርምጃዎች/ባሕሪዎች ሲያካሂዱ የነበሩ የወያነ ትግራይ ፋሺስቶች ዛሬ እንደገና ወደ መድረክ ብቅ በማለት አንገታቸዉን እያንሰራሩ ያሉ ቡድኖች እነማን ናቸዉ?
1) የለየላቸዉ የወያኔ መሪዎች የነበሩ አሁንም ከወያኔ ሕሊና ያልተለዩ እነ ስየ እና እነ ገብሩ አስራት፣ (2) እነ ስየ እና ገብሩ ከወያኔ/መለስ መነጠላቸዉ በፊት በተለያዩ በዜና እና በጽሕፈት አዉታሮች፣ የፍትሕ፣ የዲፕሎማሲ ስራ እና የፖለቲካ እንዲሁም በጸጥታ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ተመድበዉ ሲያገለግሉት በየምክንያታቸዉ ከወያነ ትግራይ መንግሥት መንግሥትና/ድርጅት ሥር በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸዉን ያገለሉ፣የወያነ ትግራይ ብሔር በሔረስብ እና ሕዝቦች የሚለዉን የዉያነ ማኒስቶ ተቀብለዉ የነበሩ አንዴ ኢትዬጵያ አንዴ “ብሔር ብሔረስብ ሕዝቦች…” በሚለዉ ቅዠት የሚንገዋለሉ አንዳንድ “የተበረዙ ወያኔዎች” (3) በወያነ ትግራይ ዉስጥ ታጋዬች እና አመራሮች የነበሩ በተለያዩ ምክንያቶች ድርጅቱን ጥለዉ የወጡ አንዳንድ ግለሰዎች (4) አማራን ቀንደኛ ጠላት በማድረግ የአማራን ሕብረተሰብ ለማጥፋት የተቻላቸዉን ሁሉ የሞከሩ ኦኖጎችና የ ኦጋዴን ተገንጣይ ጂሃዲስቶች (5) የአማራን ጥላቻቸዉ ከኦነግ በማይተናነስ በ አማራ ላይ የዘመቱት የኤርትራ ሻዕቢያዎችና አሁንም በመለስ ዜናዊ ሥር የሚንቀሰቃሱና የሚታዘዙ (የሚቀለቡ) ኤርትራዊያን የጀብሃ ነበር ታጋዬች እና መሪዎች (6) “ሆሆ” ወዳደላበት ጭፈራ ዘለዉ የሚያዳምቁ “የስሜት መረዝ ያፈናቸዉ” እና (7)አዎ አይቀሬዎቹ የመለስ ዜናዊ የስብሓት ነጋ ተከታዬች፣፣ (8) በመጨረሻ ቅንጅትን አፍርሰዉ ብርቱካንን በሆሆታ አስክረዉ በማይሆን ስሜት አስጠምደዉ ለጨለማ ዳርገዋት የሸሹ የድሮ የቅንጅት አመራር እና አንዳንድ ጽንፈኛ ደጋፊዎቻቸዉ ይገኙባቸዋል፣፣
የእነዚህ ሰዎች ቅልቅል በሚሰራጭ ያሉባልታ የታርጋ ልጠፋ ሕብረተሰቡን እያወዠቀ ይበልጡኑ “ዘ አርት ኦፈ ላይንግ” ማለትም ፈረንጆች “ዉሸትን የማዘጋጀት ጥበብ” በሚሉት “የአሉባልተኞች ዓለም” በማዘጋጀት የሕብረተሰብን አስተሳሰብ በ“ዲስታቢላይዚንግ ፋክተር” (የሕብረተሰቡን ነፃ እይታ በመጫን) እያናጉ “ኢመጅ ሜኪንግ” (ራስን ወይንም የተወሰነ ሊሂቅ በፕሮፖጋንዳ ጭቃ አድቦልቡሎ በመቅረጽ የሌለዉን መልክ አቆነጃጅቶ በመቀባት “ከሰማይ የወረደ መድህን” በማስመሰል በታሪካችን ለመጀመርያ ጊዜ “ችግር ፈቺዎች” (ፐሮበሌም ሶልቭርሰ) እንደተገኙልን አድርገዉ መበስበክ “በመቅረጸ ዉሸት” ተዉበዉ ወደ “ፖለቲካዉ ገበያ” በመሰራጨት የቀረቡት ቅስቀሳዎች ስንመረምራቸዉ የማይጨበጥ ተአማኒነት ከማስተማር አልፈዉ ለዛች ሃገር ድሃ ህብረተሰብ በተለይም አጋር አጥቶ ሁሉም ከድቶት ለጥቃት ተጋልጦ ሲንገዋለል የነበረዉ የአማራዉ ሕብረተሰቡ ክፍል በማደራጀት የታገሉትን ታዋቂ ሰዎች ብያንስ ምሳጋናዉ ቢቀርባቸዉም ክብራቸዉን ጨምሮ እየተገፈፉ እንደሆነ እየታዘብን ነዉ፣፣ በቅርቡ የመኢአድ መሪዎች እነ መሃንዲሱ ሃኢሉ ሻዉል እና ብርሃኑ እንዲሁም ታየ እና ብዙዎቹ ስማቸዉ በማይገባ እየጠቆረ እንዳለዉ ሁሉ “በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት” ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምንም ጨምሮ ጭራሽኑ ወደ ጭራቅነት እና የወንጀለኛነት ባሕሪ እንዳላቸዉ በመቀባት አስነዋሪ ፈሺስታዊ ባሕሪያቶች ከመድረኩ እየተንጸባረቁ እያየን ነዉ፣፣
የፖለቲካ ልዩነት ሊኖረን ይችላል፣፣ ነገር ግን ጭራሽኑ ወደ ጭራቅነት እና አገር ሻጭነት አለፍ ብሎም በተራ ወንጀለኛ ባሕሪ እንዲገመገሙ እየተደረገ ያለዉ አስነዋሪ ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳ ኢትዬጵያዊነትን ስነምግባር የሚጻረር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፣፣ አሁን እየተደረገ ያለዉ በጣም አስገራሚ የታርጋ ልጠፋ እሽቅድድም ስንመለከተዉ ሃይሉም ሆነ ታየ ወልደሰማያት እንዲሁም (የፈለጋችሁ በሉኝ) በፕሮፌሰር መስፍን ላይም ጭምር እየተደረገ ያለዉ የስም ማጥፋት ጋጋታ በስታሊን ዘመን ትሮትስካይትን በአካል የመግድል ጥናት ብቻ ሳይሆን የትሮትስካይትን ስራዎችና. በጎ ስነምግባሮችን ሁሉ ከምድረ ሩስያ እና በዓለም የተሰራጩት ስራዎቹን ሁሉ “ዝናዎቹን የሚያጠቁሩ የአሉባልታ ታርጋ በመለጠፍ” ጭምር ጥረት አድረጎ ነበር ከታሪክ ተምረናል፣፣ አሁን እየተደረገ ያለዉ ከዚህ በምንም አይለይም፣፣
ተኮላ ሐጎስ በተባለ ድረገጽ ሰሞኑን ያነበባችሁ ካላችሁ፣- ለዚህ የ አሉባልታ ፋሽስታዊ ቅስቀሳ እየተሰራጨ መሀኑን መታዘብ ትችላላችሁ፣፣ ድረገጹ ማስረጃ ሳያቀርብ (ዉሸት ማስረጃ እንዲያቀርብ አይገደድም አና) የመሰል ዜናዊ ሚሰት ፓሪስ በአምባሳደርነት ሌሎቹም ትላልቆቹ የወያኔ ቁንጮ መሪዎች እንደዚሁ በየዓለማቱ በመመደብ በመለስ የተዘረፈዉን ገንዘብ ለመቆጠጣር እንዲያመቻቸዉ ሲመደቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ፕረዚዳንቱ ለሁለቱ የታወቁት “ማሃል ሰፋሪዎች/(የቤተመንገሥት ዉራጅ /የገረድ ልጆች)” (አማራዎች ለሚለዉ በፋሽስት አስተሳሰብ የዳበረ ጸረ አማራ/ሸዋ ሕሊና ባላቸዉ ጸሃፊዎች የተሰጠ ዘረኛ የጥላቻ ስም ልጠፋ የሚስጢር ስም /ኮድ ነዉ) ለእነ ሃይሉ ሻዉል እና ለልደቱ አያሌዉ እንደሚሰጥ እና ሁለቱ ‘መሃል ሰፋሪዎች” ብሎ ተኮላ ሓጎስ የሚጠራቸዉ ሁለቱ የድርጅት መሪዎች “ከሚሊዩኔሩ መለስ ዜናዊ” የተረፈ ርፍራፊ እንደሚቀራመቱ “አሉባልታን በማስራጨት” በየድረገጹ እና በየፓልቶኮቹ “የአሉባልታ ዘመቻ” በማካሄድ በተቃዋሚዉ ክፍል እየተለመደ የመጣዉ “የፋሺስታዊ ፕሮፓጋንዳ ባሕሪ” “ሰዎችን ነጥሎ” የማጥላላት ዕቅድ እና አይሁዶች በናዚዎች እንደ “ጠላት” ሲታዩ እንደነበረዉ “ለይቶ” የመነጠል ዘመቻ በተጠቀሱ ግለሰዎች እና ቡድኖች ቀስ እያለ በማደግ ላይ ያለ “ለዘብተኛ ፋሺስታዊ” የሚዲያ አጠቃቀም መድረኩ እያጣበበዉ በመምጣት ላይ ስለሆነ ‘በዚህ ተርም ኦይል” ማዕበል ዉስጥ እየዋኙ የሻገተ አሉባልታ እንደ ፖለቲካ መሳርያ ሲጠቀሙ የተለመደ ሆኖ ሲመጣ ሕሊናን ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግምንም ጭምር እያበላሹ ወደ አናርኪ እና አሉባልታ ዓለም ወደ “ዉሃዉ ወቀጣ” ባሕል እያስገቡን ስለሆነ፣ ነገሮችን ማጣመም እንደሚመች በሁላችን ዘንድ ማድረግ ያለ ቢሆንም፣ በተማሩ ክፈሎች እና መሪዎች አሉባልታ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ሲነዛ ግን አስነዋሪ ከመሆኑ አልፎ ህብረተስብን እና አገርን የሚያስወቅስ ስለሆነ፣ የተማሩ ሰዎች “ከብልግና/ከአብዩዝ ታቀቡ” እንላለን፣፣ መልካም ገና፣፣ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
--> -->