Thursday, July 14, 2016

አጭር መልእክት ለብርሃኑ ነጋ (የጎንደር አማራዎች አብዮት በሚመለከት) ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay )
አጭር መልእክት ለብርሃኑ ነጋ (የጎንደር አማራዎች አብዮት በሚመለከት)
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian  Semay )

ስለ ጎንደር ወልቃይት አማራዎች አብዮትና የትግሬዎችኢምፔሪያል ሄጀመኒፍጥጫ በሰፈዊው በሚቀጥሉት ሳማንታት ስለምመለስበት ለዚያ ላቆይና በርዕሱ የተመለከተው አጭር መልእክቴን ለሕዝብ ላስተላልፍ። በርእሱ የተመለከተው ጽሑፍ ጉዳይ በድረገጽ ለመለጠፍ አላማ አልነበረኝም ሆኖም፤ በዘሀበሻ ድረገጽ ላይተነሱ!..” – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋየሚል  የብርሃኑ ነጋ ጥሪ ለጥፎ ስለነበር። ከመግለጫው የሐበሻ ድረገጽ ሥር፤ኮመንትበሚለው ክፍል፤ ትንሽ ትችት ጽፌ ለመላክ ስጫን፤ Sucuri WebSite Firewall - CloudProxy - Access Denied ይልና የኢንተርኔት ማሺኔን  አይፒ ቁጥር ዘግቦበሎክድሆነሃል ስላለኝ መልእክቴን ማስተላለፍ ስላልቻልኩ ሌላ መንገድ ተጠቅሜ ለማስተላለፍ ወሰንኩ።እናም ይኼው።

 ይህ ለመጀመሪያ አይደለም፤ ከሦስት ሳምንት ወዲህ የጀመረ እገዳ ነው። ሐሳብን በነፃ መግለጽ፤መሪዎችን የመቃወም፤ የመጠየቅ፤የመጠራጠርና የመተቸት በግንቦት 7 ሚዲያዎችና ተባባሪዎቹ፤ እንዲሁምአብዛኛዎቹየዲያስፖራ ተቃዋሚ ሚዲያ በለቤቶች  ከወያኔ ላም በመጪው ሥርዓት የዜጎችየፕሬስ መብትአፋኞች እንደሚሆኑ ስነግራችሁ በእርግጠኛነት ነው (ይህ ቃሌ ሁሌም የምታስታውሱት ይሆናል!) ስለሆነም፤ ሆን ብሎ ድረገጹ ወዳጁ ብርሃኑ ነጋና ድረገጹ በገንዘብ የሚተባበሩት የኢሳትወፋፍሮች” (ፋት ካትስ) እየተከታተልኩ ሃጢያታቸውንና ድክመታቸውን ይፋ ስለማደርግ፤ ጽሁፎቼን ለማገድ ሞክረዋል። ስለሆነም ባለቤቱን ማነጋገር ጊዜ ማባከን ስለሆነ በሚተባበሩኝ ድረገፆች መልእክቴን እንደተለመደው ይኼየው ልኬአለሁ።

መልእክት ለብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 መሪ አስመራ/ኤርትራ
ተነሱ! በሚል በድርጅትህ ስም ከአስመራ ስላስተላለፍከው ጥሪ አድመጬዋለሁ። አጥብቄ የምጠይቅህ፤ ይህ ለአማራ ሕዝብ ያደረግከው ጥሪ ሆን ብለህ ይሁን ወይንም ሻዕቢያ አማክሮህ ይሁን፤ መልእክትህ እጅግ አደገኛ እና ለወያኔ ከሰማይ የወረደለት መና ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

መልእክትህን ልጥቀስ፡

አርበኞች ግንቦት 7 በየትኛውም የሃገሪቱ ክልል ለነጻነት ከሚታገለው ሕዝብ ጎን በቃላት ሳይሆን ባለው አቅም በቁሳቁስ አቅርቦት በሃገር ውስጥም ሆነ በተደራጁ አባሎቹ በኩል ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንደሆነ ለወዳጅመ ሆነ ለጠላት ማሳወቅ እንፈልጋለን!”

ይላል መልእክትህ።

ወድ አንባቢ ሆይ። ይህ መልእክት በትዕግሰት ስታነብቡት ብርሃኑ በግልጽ ወያኔዎችን እያላቸው ያለው፤ምንድ ነው ብላችሁ ትተረጉሙታላችሁ? አማርኛው ግልጽ ነው። ትርጉም አያስፈለገውም። ቀጥተኛ መልእክት ለወያኔ እየነገራቸው ያለው;
 
አርበኞች ግንቦት 7 በቁሳቁስ አቅርቦት በሃገር ውስጥም ሆነ በተደራጁ አባሎቼ በኩል ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንደሆነ ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ማሳወቅ እፈልጋለሁ!ይላል።

የፋሺስቱ ወያኔ መግለጫ ደግሞ ይህንን መግለጫ ተከትሎ የሚለውን አንብቡልኝ። ይኼው እንዲህ ይላል፤ ለእንግሊዚኛ አንባቢዎቹ የወያኔው አፈቀላጤዓይጋ ድረገጽየለጠፈውን ልጀምር። እንዲህ ይላል።

Federal and Regional Security Forces apprehended anti peace elements in Gonder area

“The Ethiopian anti terrorist task force and the federal police apprehend individuals alleged to have been working with terror groups stationed in Eritrea.According to authorities civilians as well as security officers were killed while servicing a court warrant to some of the wanted people living in the greater Gondar area and near the Amhara-Tigrai border area.”

ይህን ተከትሎ የፋሺስቱ ወያኔ መንግሥት መግለጫ ደግሞ፤ ወዶ ሳይሆን በግዱ እየቅለሸለሸውም ሆነእሬት እሬትእያለው የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማስረዳት የሚጠቀምበት አምርሮ የሚጠላው ቋንቋበአማርኛየሰጠው መግለጫ ደግሞ እንዲህ ይላል።

በኤርትራ ከመሸጉ ሀይሎች መመሪያ በመቀበል በአማራና ትግራይ ክልሎች ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 5 2008 (ኤፍ..) በኤርትራ ከመሸጉ ፀረ ሰላም ሀይሎች መመሪያ በመቀበል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደርና በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞኖች ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉና ዝርፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ኤርትራ ውስጥ መሽገው ከሚገኙ የፀረ ሰላምና አሸባሪ ሀይሎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠርና መመሪያ በመቀበል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ሶሮቃና ቁርቢ አካባቢ እንዲሁም ትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳ ደንሻና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።በአከባቢዎቹ በጦር መሳሪያ በመታገዝ ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ በአንድ ሰላማዊ ሰው ላይ ግድያ መፈጸማቸውን መግለጫው ጠቁሟል።…….” ይላል።

እንግዲህ ከዚህ "ጉራ" ከሚወድ "ምስጢር መቋጠር" የማይሆንለት ግንቦት 7 የተባለደደብድርጅት ወያኔ ከመና የወረደለትን ብትር ተቀብሎወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም። በትግሬዎች ተወርረናል፤ታፍነናል፤ ቋንቋችን ተነጥቀን በትግርኛብቻእንደንማር ተደርጓል፤ ስለሆነም፤ አፈናውና የመሬት ነጠቃው ይቁም፤ድመጻችን ይሰማ፤ግድያው፤ አፈናው፤ ዱላው ይቁም፤ መሬታችን ይመለስልን፤ እኛ ማሮች ነን፤ በግድ ትግሬዎች አታድርጉን……

 ብለው በሰላም ለተንቀሳቀሱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፤

በቁጥጥር ስር የዋሉትና አንቅስቃሴውን ያቀጣጠሉት ግለሰቦች ኤርትራ ውስጥ መሽገው ከሚገኙ የፀረ ሰላምና አሸባሪ ሀይሎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠርና መመሪያ በመቀበል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ሶሮቃና ቁርቢ አካባቢ እንዲሁም ትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳ ደንሻና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጸረ ሰላም አሸባሪዎች…….ናቸው…….’

በማለት ነው ሕዝባዊ የወልቃይት አማራ እንቅስቃሴ ለመቀልበስና፤ የገደላቸ ሰለማዊ ሰዎች ከተጠያቂነት ለመሸሽኤርትራ ውስጥ መሽጉ ሃይላት እርዳታና መመርያ ሲቀበሉ የነበሩ ናቸው" በማለት የብርሃኑ ነጋን ደደብ መግለጫ በመጠቀም ዱላወን ከብርሃኑ ነጋ ተቀብሎ በሰለማዊ ሕዝብ እንዲያሳርፍ ተጠቅሞበታል።

ለመሆኑ ኤርትራ ውስጥ የመሸጉ ሃይላት እየተረዱና እየተመሩ እያላቸው ያለውን እነማን ናቸው? ይህ ለመመለስ መኳተት አያስፈልግም። በግልጽ ብርሃኑ ነጋ አደባባይ ወጥቶ   
እኔ የግንቦት7 መሪ ነኝ። ብርሃኑ ነጋ እባላለሁ። ይህ መግለጫ ከኔ ነው። ሰሞኑነን በጎንደርም ሆነ በተቀሩት ክፍለሃገሪቱ ግዛት ክፍሎች ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለው  አብዮትበተደራጁ አባሎቼ በኩል ሙሉ ተሳትፎ እያደረገሁ እንደሆነ ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ማሳወቅ እፈልጋለሁ !” 

ሲል ለጠላት (ለወያኔ) እየነገረው ነው። አሃ!! አሃ!! ታዲያ ወያኔ ከዚህ ሌላ ምን መረጃ እና ሽፍንፍን ምክንያት ይፈልጋል? እራሱ ግንቦት 7 በተደራጁ አባሎቹ በኩል ተሳትፎ እያደረገ ቁሳቁስ/ጠመንጃ (?) እያቀበለ ንደሆነ እየነገረው?

 ይህ አደጋኛ ሰው፤ ካሁን በፊት ለጉራ እያለ ስሙን እና ድርጀቱን በሌለው አቅም ሰማይ እየሰቀለ፤ ምስኪን የከተማ አባሎችና ወጣቶች በወያኔ ጅቦች እንዲበሉ አድርጓል። ይህ ደግሞ ደጋግመን የገለጽነው ነው። እስር ቤት ሆነው ገና ዳቸው ለመስማትየመከላከያ ምስክርእናቀርባለን ብለው እሰር ውስጥ  ያሉ የዋህ የግንቦት 7 ሰለባዎች፤ ከስሜትና ከጭንቅ የተነሳ ለግንቦት 7 የጻፉትን ደብዳቤ በዘሐበሻ ይፋ አድርጎ ለመከራ እያጋፈጣቸው መሆኑን ካሁን በፊት ማውገዜን ታስታውሳላችሁ። አሁን ደግሞ የግንቦት 7 መሪዎች አማራን "በነፍጠነት" ሲዘልፉት እንዳልነበረ የተረሳ መስሎአቸው፤ካንገት በላይ” የሚወዱ አማራውን ሕዝብ/በተለይም ወጣት አማራውን ለማስፈጀት አንቅስቃሴው የኔ ተሳትፎ አለበትሲል ይፋ አዋጅ አውጇል።

 አማራዎች የዚህ ሰው መግለጫ በጥርጣሬ ማየት ይኖርባችሗል እላለሁ። በሰፊው እስክመለስበት ድረስ ውድ የወልቃይት ጠቅላላ የጎንደርና አማራ መላ ወገኖቼ ሆይ! የዚህ ሰው/የግንቦት7 መግለጫአደገኛእናለጠላት አጋልጦ በመስጠት፤እስራትና ለእንግልትእያጋለጣችሁ ስለሆነ፤ የጎንደር ሕዝብ ከዚህ ድርጅ ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው መግለጫ ማውጣት አለበት እላለሁ።ርካሽ ልታወቅ ባይነት/ፓብሊሲቲ/ የዚህ ሰውዬ ዐይነተኛ የተጠናወተው በሽታ ነውና ፤ከዚህ ድርጅት ንክኪ እንደሌላችሁ አውግዛችሁ ይፋ አድርጉ።

የጎንደር ወልቃይት/አማራ/አንቅስቃሴ ግንቦት 7 ከመፈጠሩ በፊት የነበረና የብዙ ትግልና መራራ ትዕግስት ውጤት ነው። ብርሃኑ ነጋ አስመራ ተቀምጦ እኔ ነኝ እየመራሁት ያለሁት ብሎ መዋዠቅ ብን ለማስጨፍጨፍ መሆኑን ይታወቅ።
 
ይህ አሁን ግንቦት 7 እየተጠቀመበት ያለው ጉዳይ፤ አሜሪካ ውስጥ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊሶች ላይ የወሰደው የግድያ እርምጃ፤ ቀኝ አክራሪ ሚዲያዎች “ገዳዩን” Black Lives Matter”ከሚለው የጥቁሮች እንቅስቃሴ ለማያያዝ ሲሞክሩ የእንቃሴው መሪዎች ግን “Black Lives Matter has nothing to do with killing police officers” ሲል ውንጀላወን እኛን አይመለከተንም፤ የለንበተም፤ ሲሉ በግልጽ ኮንነውታል። የፖለቲካ ብስለትና አንቅስቃሴ አብረው ካልሄዱ ለወንጃዮች “ሲሳይ” መሆን ነው።ባጭሩ የእንቅስቃሴው መሪዎች ውንጀላወን በእንደዚህ ያወግዛሉ፤-

“The goals and message of Black Lives Matter have nothing to do with harming police officers in any way. The movement is explicitly concerned with reducing the racial disparities found in the criminal justice system. None of its leaders have advocated for killing cops.” ይላሉ። 

የፖለቲካ ብስለትና የእንቅስቃሴ ስልት በብስለት መልስ መስጠት የሚችሉ የተካኑ መሪዎች ካልተሰለፉበት፤እንቅስቃሴው የጮሌዎች ስም ማስሪያና መነገጃ ሆኖ ይኮላሻል። የኛዎቹ የአስመራ ምሽግተኞች ደግሞ “አዎ! እንቅስቃሴው በተደራጁ አባሎቻችን የታገዘ ነው። ለወዳጅም ለጠላትም ለማሳወቅ እንወዳለን” ሲል የአማራን ሕዝብ ብሶትና እንቅስቃሴ ለመጥለፍና በጠላት አስሰልቦ ለማኮላሸት “እጁ እንዳለበት” ይፋ መግለጫ ሰጥቷል። አሁን ወያኔዎች የፈለጋቸውን ለማሰር “ግንቦት7” በር ከፍቶላቸዋል፤ ዱላውን አቀብሎአቸዋል። “ስፔኩሌት” ማድረግም የለባቸውም።

ጥቁሮቹ These facts are inherently contradictory. If there's no information about the motive, how can officials make any connection between the shooting and any movement, whether it's Black Lives Matter or something else? It's just blind speculation at this point.” 

 ሲሉ ነው የተሟገቱት። የግንቦት 7 መሪ ግን የአማራው ንቅስቃሴ ማን ነው እየመራውና እያገዘው ያለው የሚለውን ጥርጣሬ/ speculation/ ተውት እና  የእኔ እጅ አለበት፡ መረጃውም በዚህ መግለጫ እንድታወቁት ለወዳጅም ለናንተም (ለወያኔዎች) ይፋ አድረጌላችሗለሁ ሲል በቪዲዮ መልእክቱን ይፋ አድርጎላቸዋል።

 ፋሺስቱ ወያኔ ደግሞ በምላሹ፤-

በኤርትራ ከመሸጉ ሀይሎች መመሪያ በመቀበል በአማራና ትግራይ ክልሎች ሽብር የሚፈጥሩ ገለሰቦችን  እየለቀምኩ ነው። እንቅስቃሴው በኤርትራ ከመሸጉ ሀይሎች መመሪያ” እየተሰጣቸው መሆኑን ኤርትራ ከመሸጉት ሃይሎች አንዱ ግንቦት 7 በመሪው በኩል ይፋ አድርጎ ነግሮናል”

 በማለት 

ለመዋሸትና ወንጀሉን ለመሸፈን አመቺ በር ተከፍቶለታል። ለወያኔ ከሰማይ የወረደ መና ንዲህ ያለ አጋጣሚ ሰምቼ አላውቅም። ልብ በሉ የኦሮሞው እንቅስቃሴ ብዙ ሰዎች በጥርጣሬ ሊመለከቱት ያስቻለቻው ምክንያት “የጸረ አማራው የኦነግ ባንዴራ” እያውለበለቡ ሰለማዊ ሰልፍ ሲያካሂዱ ፤ወያኔ ምንኛ አንደተጠቀመበት ልብ በሉ። ዛሬም ብርሃኑ ነጋ፤ በደደብ ፖለቲካው ለፕሮፓጋንዳና ለጉራ ፍጆታ ሲል ሕዝብንና ትግሉን ለማኮላሸት፤ አለቆቹ አሜሪካኖች በሚሰጡት መመሪያ የትግሉን ፈር ለማሳሳት ንቅስቃሴው ቡሳቁስም ሆነ መመመሪያ የምመራው የኔ እጄ አለበት ሲል ለጠላት ዱላ አቀብሏል። ስለዚህም መወገዝ ያለበት። ርካሽ ፖለቲካና ሕዝብን ለጠላት የሚያሳጣ/ የሚያጋልጥ መግለጫ  አማራን በምትወዱና በምትደግፉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሁሉ መግለጫውን አውግዙት። 
 
ለምን የሚሉ፤በስሜት የሚነዱ፤ጮርቃ ስለት ያላቸው ሰዎች በርካቶች አሉ። እስኪ ለመደምደሚያ ይህችን ሌላኛዋ ንግገሩን አድምጡ
አንዲህ ይላል፡
“አርባ ምንጭ ውስጥ የተዋደቁትን የነፃነት አርበኞች ከጎንደር ሕዝብና ለጎንደር ሕዝብ አብረው እየታገሉ ባሉ  ጓዶቻቸው ተጋድሎ ይኮራሉ።” 

አምላክ ያሳያችሁ! እንዲህ አይነት ለወያኔ በትር የሚያቀብል መግለጫ ከየት ይገኛል? ጎንደር ውስጥ እያተገሉ ያሉ “የግንቦት 7 /የአርባ ምንጭ የተሰው ጓዶች ናቸው” እያለ ነው። አንግዲህ እንቅስቃሴው ግንቦት 7 እየመራው ነው ማለት ነው። ስለሆነም ወያኔ ፌስታው/ደስታው አይችለውም። 

ብርሃኑ ነጋ፤ እባክህን በምትወደው እንግሊዝኛ  ልንገርህ ;

You are adding more destructive than constructive agenda to the problem. It's about advancing your own agenda at the expense of others. Please stay out of it! Let my Hero, the people’s hero journalist Muluken Tesfaw talk about it and take the lead on it. Please stay out of it!

አመሰግናለሁ፡ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)getachre@aol.com