የኢሕአፓ ዘረኝነትና ዛቸው!
ጌታቸው ረዳ
ነብሱ
ይማረው በገጣሚ ሃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) ግጥም ጽሑፌን ልጀምር።
በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል
ህይወት
የምንለው እንደ ጥሬ እህል
በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ
ቢማሰል
የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል!!
(ገጣሚው
ገሞራው)
አሁን ትልቅ አገራዊ ርዕስ በመጻፍ ላይ ስለሆንኩኝ፤ ጊዜ ላለመሻማት ስል ሌላ ቀን በሰፊው እስክመለስበት ጊዜ፤ ሰሞኑ ኢሕአፓዎች በድረገጻቸው በአሲምባ ላይ ስለ እኔ የለጠፉትን ‘ዘረኛና አግላይ ካርቱን” አማራና ኦሮሞን በማናከስ ዘርን ከዘር ለማጨራረስ በወንጀል የሚከሰሰው ኤርትራዊው ተስፋዬ ገበረአብ ጋር እኔን በማነጻጸር “እኝህ ሰው ምን ነካቸው ከአማራ በላይ አማራ! የከለላ ታሪክ ፤ጋጋታ ምን የሚሉት?” በማለት፤ “ትግሬው ለትግሬ” እንጂ ስለ አማራው አያገባውም፤ ሌላው ስለ አማራ የመጨነቅ፤ የመቆም መብት የለውም!’ ከማለታቸው ሌላ፤ እጅግ አስገራሚ ካርቱናቸው ደግሞ “የከለላ ታሪክ” በማለት እኔን ለአማራው ሕብረተስብ እንደ ባዕድ ወገን አድርገው በመሳል፤ ለሰሚው እጅግ አሳፋሪና ዝቃጭ የሆነ የመንደር ብስለታቸውን ለማንጸባረቅ ሞክረዋል።
በፓልቶክ ስሙ “ፋኖ” በመባል ወይንም “አደባባይ” በመባል
የሚታወቀው እዚህ ሳንሆዜ ከኔ ጋር የሚኖር ምስኪን የኢሕአፓ ካልትም ሳይቀር፤ “አማራ፤ አማራ ፤የሚሉ ፡ስለ አማራ፤
ስለ ሞረሽ የወገኑ ሰዎች” አማራዎች ሳይሆኑ ከሌላ ጎሳ የተወለዱ የወታደር ልጆች ናቸው” ሲል ከኤርትራዊያን በባሰ
መልኩ የዘቀጠ “ዘረኛነቱን” ሲያነበንብ የተደመጠውን በአውድዮ ቀድተው ወዳጆቼ የኢሕአፓ ‘ጉድ አደምጥ” ብለው የላኩልኝም አደምጬ ሰዎቹ ጭልጥ ብለው ወደ ዘር ቆጠራ መግበታቸው
አጅግ አዘንኩላቸው።
ኢሕአፓዎች ስለ አርበኛቸው ስለ ማርክሲስቱ ዋለልኝ መኮንን እና ስለ ድርጅታቸው የተቸሁትን
ተገቢውን መልስ ጽፈው መከራከር ሲገባቸው፡ የነቁ፤የበሰሉ መስለውኝ የነበሩት ሰዎች ወደ ዘረኛነትና ወደ አሉባልታ ሲገቡ ማየቴ
በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ እጅግ የወረዱ፤ ቢቆሉ፤ቢቆሉ የማይበስሉ መሆናቸውን ነው የታዘብኩት።
ስለ ኢሕአፓ በሰፊው ለወደፊቱ የምንነጋገርበት ሲሆን፤ ለአሁኑ ግን ለዚህ ዘረኛ እና
ዝቃጭ ብስለታቸው አሁንም በድጋሚ ያስታወሰኝ ነገር ቢኖር “ገዴዎን ለቪን” የተባለው እስራላዊው የሰው ልጆች ተሟጋች እና
ጋዜጠኛ “ሰለ ፍልስጢኤማዊያን ሰብአዊ መብት በመቆም እስራላዊያንን በመቃወሙ ምክንያት” ከእስራላዊያኑ የተሰጠው ስምና የካርቱን
ጥላሸት “ከፍልስጥኤማዊያን በላይ ፍልስጢኤማዊ” ሲሉ ካርቱን ለጥፈውበት የነበረውን አስታውሰውኛል። ይህ በኢሕአፓዎች
አልተጀመረም፤ ወያኔዎች ብለውኛል፤ ኦነጎች ብለውኛል፤ ዛሬ የአሲምባ ድረገጽና መሰል የኢሕአፓ ካልቶች የሚለፋደዱት ያንኑ
ከአቻዎቸው የቀዱትን ዘረኛና ያልበሰለ ጥሬ መልሳቸው፤ በማስረጃ ለጻፍኩት መልስ፤ በመረጃ አስደግፈው መልስ መስጠት ሲያቅታቸው፤
መልስ ይሆናል ብለው ከወንጀለኛውና “አገሬ ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም” ብሎ ኢትየጵያን ከከዳ ‘ከተስፋዬ ገብረአብ” ጋር
ያነጻጸሩኝን ካርቱናቸውን ለማዬት ትዝብታችሁን ለማኖር ክቡራን አንባቢዎቼ ድረገጻቸውን እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።
ከላይ የጠቀስኩት ፓልቶክ ውስጥ ሆኖ የጀገነ የኢሕአፓ ካልት ደግሞ “ድርጅቱ ድሮ
ሲያደርገው እንደነበረው የግድያ ሱሱን በኔ ላይ ለመጀመር የቃጣው ይመስላል”፤ ወጣቱን በማደራጀት “የድሮ ዶሚናንስ
ባሕሪያችን መመለስ አለብን” ይላል። በማርክሳዊያን ዓለም፤ ለዶሚናንት ባሕሪ መጓዝና መመኘት ምን እንደሚያስከትል እና
ምን እንዳስከተለ፤ አሁንም ምን እያስከተለ እንዳለ የምናውቀው ይመስለኛል። የዚህ ጉረኛ ሰው የተለፋደደበትን ስድብና የማስጠንቀቂያው
ዛቻ ወዳጆቼ እንዳደምጠው ቀድተው በአውድዬ ልከውልኝ፤አድምጬው፤ የካልት ድፍረት ምን ያህል ርቆ አንደሚሄድ አስገርሞኛል። ይህ
ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነው።
ኢሕአፓዎች ለማስፈራራት የተነሱበትን ሰው ማንነት አለማወቃቸው ይገርመኛል። ወያኔ
ዝቶ፤ዝቶ፤ዝቶ፤ ስሜን አጥፍቶ፤ጎሳየን ሰርዞ፤ ያልሆነለት፤ አሁን ምስኪኑ የኢሕአፓ ካልት “ኢሰፓ” ብሎ ሲወነጅለኝ፤ እንኳን ኢሰፓ
ልሆን ፤ ኢሰፓ ሲመሰረት አገሪቱ ባልነበርኩበት እና ትርጉሙ ምን
ማለት እንደሆነ እንኳን የማላውቀውን ሰውዬ፤ እኔን “ይሻለዋል” ብሎ ሲያስጠነቅቀኝ፤ ‘ተደራጁ እያለ የሚወተውታቸውን ወጣቶቹን
“አስልኮ” ነጭ ሽብር ሊያራምድብኝ ካልሆነ በቀር ምን ሊያመጣ አንደሚችል ገርሞኛል።
እነኚህ አርበኞች ናቸው፤ ተውአቸው እያልኩ ስከላከልላቸው ከስንት ወዳጆቼ
እየተቀያየምኩ፤ ስከላከልላቸው የነበርኩኝ ሰውዬ፤ ዛሬ ‘ቢቆሉ፤
ቢቆሉ፤ የማይበስሉ ሆኖው ሳገኛቸው፤ እውነትም ከዛው ከ70ዎቹ ምድጃቸው አሁንም እዛው አመዱ ላይ ተዘፍቀው መውጣት እንዳቃታቸው ለማየት ችያለሁ።አይጥ ለሞቷ የድመት
አፍንጫ ታሸታለች” ብሎናል ወዳጄ ገብረመድህን አርአያ ‘ እውነትም እኔን ለመጎነታተል አምሮአቸዋልና እሰየው! ምርጫቸው ነውና፤
አከብርላቸዋለሁ፤ ለሁሉም ኳሱም ሜዳውም እንሆ! እንፈታተሽ።ጥርሱ ያለቀበት ውሻ መጮህ እንጂ መናከስ አያውቅም፤ ኢሕአፓ
በዘረኛነት ቢጮህም “የእኔ ከአማራው ሕብረተሰብ መቆም” ሊያስቆሙኝ ከቶውኑ አይችሉም! “እንደ እናታቸው ጡት ያጡት እንደሆን
እንጂ ፤ “እኔ አማራም፤ ትግሬም አገውም፤ኦሮሞም፤ወላይታም፤ ሐረሪም ሶማሌም…..ወዘተ ወዘተ…. ነኝ” ኢሕአፓ “ባዕድ ነህ” ቢለኝም፤ ስለ አማራ የመቆም መብቴ ከተውኑ መንጠቅ
አይቻለውም። እንዴት ደፋር ነው ይህ ኢሕአፓ እባካችሁ? ድፍረቱ ሌላ ሰው ጋር ቢያደርገው እንዴት ባማረበት ነበር። ወይ
አለማወቅ!
ኢሕአፓ ‘የዜጎችን ህይወት ሲያደርገው እንደነበረው” መሪና ተመሪ ሳይታወቅ ወደ አናርኪ
ተለውጦ ህይወት በጥይት ሲቀስፍ እንደነበረው ሊቀስፍ ይችላል። ተጠያቂነትም አልነበረውም፤ እስካሁን ድረስ ተጠያቂነቱን
አልወሰደም፤ “ገደሉኝ እንጂ ገደልኩ አይልም፡ አጥፍቻለሁ ተጠያቂ ነኝ አላለም። ይህ ደግሞ የተጠቂዎች ዝምታ ወደ ስንፍና
ተተርጉሟል። እንግዲህ ማሾፍ ከቀጠሉ፤ አንድ የተቀናጀ ጥናት መደረግ አለበት እላለሁ።” የሰው ልጆች ህይወት በማርክሳዊ፤አናረኮዊና ፋሺስታዊ እርምጃው ሰውን
የመቅሰፍ መብት በገዛ እጁ ሊኖረው ይችላል። የኔን እና የዜጎችን ጎሳነትና የማንነት መብት’ የመንጠቅ ወይንም የመስጠት” መብት
አልተሰጠውም። ሊኖሮውም አይችልም።
ቢፈልግ ፓልቶክ ላይ እንደ እኩያዎቹ ዘረኛ ምላሱን ሊዘረጋ ሊሰበስብ ይችላል። ያንን
ዘረኛ መብቱን አከብርለታለሁ፤ ስለ አማራ ማሕበረሰብ መብት መከራከር መብቴን ግን ሊነጥቀኝ አይቻለውም።
ወያኔም፤ኦነግም፤ሻዕቢያም ሞክረውታል፤ ኢሕአፓም፤ ሊላላጥ ካልሆነ በቀር ከቶ አይቻለውም!
አላርፍ ካላሉ፤ “ኢሕአፓ በታጋዮቹ አንደበት” በሚል የማወጣው ሰነድ ይኖራል።ተከታተሉ፡
ይቀጥላል።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (Editor Ethiopian
Semay) getachre@aol.com