አቻምየለህ ስለ ጋጠወጡ ሺመልስ አብዲሳ (ኢትዮ ሰማይ)
በነዶክተር ዳኛቸው አሰፋና ዳንኤል ክብረት ስለ ኢትዮጵያዊነቱ የተመሰከረለት
ሺመልስ አብዲሳ ዛሬ በዐፄ ዳዊት መዲና በበረራ/አዲስ አበባ ያስተጋባው ንግግር በኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ላይ ያለውን ጥላቻ ብቻ ሳይሆን ስለ ብአዴን ያለውን ንቀትም ያሳየበት ነው። የአማራውን አከርካሪ ሰብረን ትክሻውን ለእስክስታ ብቻ አስቀርተነዋል ያለው የቀድሞው ባለጊዜ መለስ ዜናዊ ነበር። የመለስ ዜናዊ ዲቃላው ሺመልስ አብዲሳ በዐፄ ዳዊት መዲና ላይ ሆኖ «የነፍጠኛን አከርካሪ ሰብረን ለዚህ በቅተናል» ያለው መለስ ዜናዊ ባለጊዜ ሳለ የተናገረውን በመድገም ነበር።
እነ ሺመልስ ለመንግሥትነት የበቁት በጎንደርና ጎጃም፣ በወሎና በሸዋ በተደረገው የአማራ ተጋድሎ ወያኔ በመሸነፉ፤ የብአዴን መሪው ደመቀ መኮንን የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነቱን ቦታ ለዐቢይ ሰጥቶ ብአዴን በሙሉ ዐቢይን እንዲመርጥ በመደረጉ ነው። በዚህ ሁሉ የአማራ ትግል ተደግፈው ለመሪነት የበቁት እነ ሽመልስ ዛሬ ግን የሚናገሩት ለሥልጣን የበቁት ሕወሓትን ከአማሮች ጋር በመሆን በጋራ ታግለው ሳይሆን የአማራን አከርካሪ ሰብሮ እንደሆነ አድርገው ነው። ይህ የሺመልስ ንግግር ኦሕዴድ ዛሬም ትግሉ ከነፍጠኛ ጋር መሆኑን በግልጽ ያሳየበት ነው። የአማራ ልጆችን መስዕዋትነት መና አስቀርተው ለሥልጣን ላበቋቸው ለብአዴኖች ቢያንስ ትንሽ ክብር ቢኖረው ኖሮ ሕወሓትን በጋራ ታግለውና አሸንፈው ለሥልጣን በቅተው ሳለ እነ ሺመልስ ግን ለሥልጣን የበቃነው የአማራን አከርካሪ ሰብረን ነው ብሎ በአደባባይ አይተፋም ነበር። ባጭሩ አማራውን እያሰደበው፣ ርሥቱን በሌላው እያስወሰደበት፣ እያስናቀውና
ጠላት ያደረጉት
እንዲያዋርዱት እያደረገው
ያለው ብአዴን ነው።