ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ ( ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com\
<አንዱ ሲቋጥር አንዲ ሲፈስበት የተቸገረው የጫካው መንግሥት
ጌታቸው ረዳ
የዘመናችን መንግሥት “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ይባላል። ይህ ከጫካ የተሰጠን መንግሥት አስራ ስምንት ዓመት ሙሉ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ የጫካ መንግሥትነቱ ጀምሮ ቢሰላ አንዱ ሲቋጥር አንዱ ሲፈስበት ከ34 ዓመት በላይ አስቆጥሯል።
ይህ ቡድን ሲመሠረት ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ዘመኑ የተከተላቸው ፍልስፍናዎቹ ብንመረምር ከግልብ የለውጥ ስሜቱ አንስቶ በወረቀት ያሰፈራቸው ከምስራቁም ከምዕራቡም ቦጫጭቆ በመለገብ ለሕዝባችን ያስለበሰው ቡቱቶ ፍልስፍናው ለዛሬው ኑሮአችን ብቻ ሳይሆን የነገውንም ስጋት ጨምሮብናል። ከጫካ ዘመኑ ጀምሮ ይህ ቡድን የተከተላቸው መንግዶች ከተራ የሽፍቶች ባሕሪ አልፎ በዓለም አቀፍ የተራቀቁ ምስጢራዊ የሽብር አሰራሮች ከተከተሉት የግድያ እና የሽብር እንዲሁም ሕገወጥ የገንዘብ ድለባ ወደ ማካበት የተሸጋገረ በዓይነቱ እጅግ የተለየ አፍሪካዊ ሽብርተኛ የሽምቅ ተዋጊ መንግሥት ለመሆን በቅቷል።
ሰሞኑን እየታዘብነው ያለነው የዋጋ ግሽበት በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቀርቶ ብዙ ዋሾ ካድሬዎቹ እና ሚዲያዎቹ በሚኖሩባት ትግራይ ውስጥም ቢሆን ከቅርብ ወራት በፊት አገሪቱ አደገች፤ገበያው ነፃ ገበያ ነው…በማለት ሲዋሹን እና በሕሊናችን ሲዛበቱብን እንዳልነበረው ሁሉ ዛሬ የሪፖርተር ዘጋቢ በትግራይ በተለይም በመቀሌ ከተማ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች በሥርዓቱ አገልጋዩች እየታሸጉ እንደሆነ ዘግቦታል።
እነኚህ ባለሃብቶች ተቋሞቻቸው የታሸጉበት ምክንያት የዋጋ ንረት ተከትሎ ሸማቹ/ተጠቃሚው ሕብረተስብ ፍጆታዎችን የመግዛት አቅሙ መግዛት ከማይችልበት አቅም በመድረሱ፤ ለዋጋው ንረት ተጠያቂው ነጋዴውን በማድረግ የሚሸጡበትን የዋጋ መጠን በማውጣት፤ትዛዙን የተላለፉ ነጋዴዎች “ትዛዝ ባለማክበር” እየወነጀለ ተቋሞቻቸው እንዲታሸጉ አድርጓል። ይህ ድርጊት ቀደም ብሎ አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ እንደታየ እና ውጭ አገር እዚሁ እኛ ጋር የሚኖሩ የሥርዓቱ ተከታዮች ልክ እንደጌቶቻቸው እኛኑን አንደዋሸን በመወንጀል በየዌብሳይቶቻቸውና በፓልቶክ ሸቃዮቻቸው አማካይነት የተመደቡበት ሃቅን የመሸፈን ተልዕኮ ሲያከናውኑ መደበቅ ከማይችሉበት ደረጃ በመድረሱ ይኸው ዛሬ ከአዲስ አበባ ተሻግሮ ችግሩ ወደ ትግራይም ጭምር በመሸጋገሩ የትግራይ ነጋዴም ሌሎቹ የቀመሱትን ጅራፍ መቅመስ ጀምሯል።በዚህ የውሸት ተልእኮ ለማካሄድ በትግራይና በውጭ አገር የተመደቡ የወያኔ የዜና ማሰራጫ ሸቃዮቹም አፍረው በመሸማቀቅ ይህ ካቅማቸው በላይ የተከሰተው ዱብ ዕዳ ዋሽተው እንዴት መከላለከል እንደሚችሉ አዲስ የውሸት ስልት ከጌቶቻቸው እየጠበቁ ይገኛሉ።
ወያነ ትግራይ የኮሚኒስቶች ፍልስፍና አነግቦ መሬት በቁጥጥሩ ሥር አስገብቶ ሸቀጡን፤የመገናኛ አውታሮችን፤ ባንኮችና ንግድ ቤቶች በአስመጪና ላኪ በዋናነት ሃብታም ነጋዴ ሆኖ ለጥቂቶች ገነት ለብዙሃኑ የጭንቀት ኑሮ የሆነ ሥርዐት መሥርቷል።ሸማቹና አምራቹ በወያነ ትግራይ ዋና ታጁርነትና ቁጥጥር ስለሚገራ የዚህ ታጁር ተመፅዋች እና ትዕዛዝ አክባሪ ከመሆን አላለፈም። ታጁሮቹ ካቅም በላይ በሚጋብሱት ሃብት ሲተፉ ስለሚያድሩ ትፋታቸው የገባየው ዓየር በክሎታል።ምሕረት የለሽ ነጋዴ ቢፈጠርም የተማረው ከሥርዓቱ ነውና ተወቃሹ ነጋዴው ሳይሆን በዋናነት ሥርዓቱ ነው። በዚህም የተነሳ የገበያው ንረት ሲታወክ ስርዓቱን የሚመሩት ጥቂት ወረበሎችና አማካሮቻቸው “ደርግ” ሲያደርገው እንደነበረ የዋጋ ቁጥጥር ስልት ተከትለው ይኸው ዛሬም የዋጋ ንረት መነሻ ምክንያቱን በነጋዴው ላይ በማመካኘት አንዱን ሲቋጥሩ አንዱን ሲፈቱ ይታያሉ። ሥርዓት በዘመናዮቹ የወያኔ ትግራይ ያዲሱ ትውልድ የመሳፍንቶችና ጫካ በቀል ከብረቴዎች ስበስብ የሚመራ ስለሆነ እነኚህ መሳፍንቶች የሚከተሉት ሞራላዊ እሴት ቅጥፈት ሲሆን፤- “ቅጥፈት ደግሞ“ በአገራችን ሞራላዊ እሴት ብቻ ሳይሆን የሥርዓተ መንግሥቱም ዋልታና ማገር ሆኗል። (In our country the lie has become not just a moral category but a pillar of the state) (ሰውነት መልካሙ) የዓለም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚና የቀድሞ ሶቭየት ሕብረት ሥርዓተ -መንግሥት ነቃፊ ከነበሩት አለክሳንደር ሶልዘንስቲ ንግግር የተወሰደ።)
<ስለሆነም ከትግራይ ጫካ የተሰጠን መንግሥት የሚከተለው ሞራላዊ እሴት “ቅጥፈት” ስለሆነ ቅጥፈትም የሥርዓቱ ዋልታና ማገር ስለሆነ በፖለቲካውም ሆነ በምጣኔ ሃብቱ በኩል በሕዝቡ ላይ የሚደረሰው የስቃይ ንዳድ ሲጨምር ሥርዓቱ የሚይዘውና የሚጨብጠው እያጣ አንዱ ሲቋጥር አንዱ ሲፈስበት ተጨንቆ ይታያል። አንዱ ሲቋጥር አንዱ እየፈሰሰበት ተቸግሮ ያለው ይህ ዝርክር ሥርዓት በተቃዋሚ ሃይሎች መወገድ አልቻለም። ይህ ከጫካ የተሰጥን መንግሥት የሚወገደው ዕጣ ፈንታችን ሆኖ “ባንድ አጉራ ዘለል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እንደሚሆን” ስጋቴ እየጨመረ ሄዷል። ሰላም እንሰንብት። ጌታቸው ረዳ Getachew Reda editor Ethiopian Semay www.ethiopiansemay.blogspot.com
Tuesday, January 25, 2011
Subscribe to:
Posts (Atom)