Wednesday, July 9, 2014

እውነት ኮበለለች (አንዳርጋቸው ጽጌ ካሰቃያቸው አንደበቶች)


እርማት፤

ባለፈው ጽሑፌ የአማራ ሕብረተሰብ ስቃይ በማስመልከት ጋዜጠኛ አበበ ገላውን እና  ታማኝ በየነን  ሁለቱም  የጐንደር የአማራ ነገድ ናቸው ብዬ ጽፌ በነበረው አስመልክቶ ጋዜጠኛ አበበ ገላው “እኔ ጐንደር ውስጥ አልተወለድኩም፤ ወላጆቼም ጐንደሬዎች አይደሉም። ማንም ልሁን ምን፤ (…) ሳይሆን መጠራት የምፈልገው “ኢትዮጵያዊ” ነኝ። ነገዴ ከዚህ ነው ማለት ጠባብ የፖለቲካ መስመር መከተል ነው ብሎ ስላለኝ እና ቅሬታው ስለገለጸልኝ። ምንም አንኳ ቆየት ብሎ የደረሰኝ መረጃ ፤አበበ የጎንደር ሳይሆን የወሎ ሰው መሆኑን ቢነገረኝም፤ በነገድ መጠራት “በጠባብ የነገድ ፓለቲካ መጓዝ ነው” ብሎ  ስለሚያምን፤ ይህ አስገራሚ ክስተት ብቻውን ሳይሆን በርካታ ሰዎች በዚህ ስለሚያምኑ፤ ይህ የተሳሳተ “የነገድ ፎቢያ” እና ““ትርጉም “ዕምነታቸውን  ሳከብር፤ ከወዲሁ ደግሞ ነገዴ ትግሬ፤ነገዴ አማራ፤ነገዴ ኦሮሞ ..ነገር ግን ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ማለት “የጠባብ ብሔረተኝነት ፓለቲካ” አራማጆች ብለው እኛን “በጠባብነት” የሚከሱ ሁሉ መብታችንም እንዲያከብሩ ከወዲሁ ጥሬየን አቀርባለሁ። በዚህ የተሳሳተ “የነገድ ፎቢያ” እራሱ “ያልተሰመረበት የመጥፎነት ፎቢያ” ባሕሪ ቢሆንም ወደ ጠባብነት የሚያዞሩት “ኢትዮጵያዊ  ነገዶች” ሌላ ጊዜ በዝርዝር ስሕተታቸውን ለማረም እመለስበታለሁ።  ብቻ ለእርማቱ ይኸው።  ጋዜጠኛ አበበ ገላው ጎንደሬ ወይንም ወሎየ ወይንም  “አማራ” ወዘተ.. ሳይሆን  “ኢትዮጵያዊ” ነው። በዚህ እርማት አድርጌአለሁ ። ነገዳቸውን መጥራት እየተጠየፉ  “ኢትዮጵያን”  መክዳት መስሎ የታያቸው ወገኖች፤ እባካችሁ ከእገሌ ነገድ ነኝ የመጣሁት ብሎ ለሚል ነገዱን የሚጠራ ዜጋ ጠባብ እያላችሁ ራሳችሁን ከማመጻደቅም ተቆጠቡ።         

ወደ ሁለተኛው ሓተታየየ ላምራ፡

እውነት ኮበለለች (አንዳርጋቸው ጽጌ ካሰቃያቸው አንደበቶች)

ከአዘጋጁ- ሓተታ፡ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የኔን የጌታቸው ረዳ አጭር ሓተታ ካነበባችሁ በሗላ፤ አንተነህ ጌትነት የተባለው ወጣት፤ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል እያለ ራሱን ወደ ሚጠራው የአንዳርጋቸው እና የብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 ን በመቀላቀል “ኤርትራ ድረስ ሄዶ” የተቀላቀላቸው፤ በሗላ የአንዳርጋቸው ጽጌ ምንነት ከተመለከተ በሗላ ድርጅቱን በማውገዝ፤ ያየውን የታዘበውን  እና የደረሰበትን “ጉድ’ ካሁን በፊት በሰፊው ዘግቦታል።

ታሪኩን ለመመልከት ግንቦት 7 ለሁለት ከተከፈለ በሗላ ግንቦት 7 ዲ በማለት ሌላ ድርጅት በመመስረት http://www.ginbot7d.org/ የሚል ድረገጽ ይመሰረቱትን ይጎብኙ። ዛሬ ባጭሩ እሳትን እና ብርሃኑ ነጋን ለክርክር በመጋበዝ በማንኛውም ሚዲያ እና በሚዲያቸውም ጭምር ጉዳቸውን ለማጋለጥ ጥሪ ያደረገበት እና፤ ሚዲያዎችንም እሱን ለማቅረብ እና ለመከራከር  እውነታውን ላለመጋፈጥ “እየተሸማቀቁ” ለምን እንደፈሩ እና እያፈገፈጉ አንዳሉ ይጠይቃቸዋል።

 የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባ የነበረው ወጣት አንተነህ ጌትነት  እውነት ኮበለለች  በማለት አብዛኛዎቹ ግንቦት 7ን በማገልግል ሥራ የተጠመዱትን የዲያስፖአራ ተቃዋሚ ድረገፀችን “ኢትዮ-ሚዲያ”፤ “ኢሳት” “ዘሓበሻ” ፤ “ቋጠሮ”፤ “አቡጊዳ”…ወዘተ..ወዘተ… ን ጭምር የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባዎችን ደምፅ ለሕዘብ አንዳይደርስ “በማፈን” እውነት እየሸፈኑ የሕዝባዊ ሃይል ታጋዮችን “ሄሊኰፕተር” ተብሎ በሚጠራ የኤርትራኖች የቶርች ስታይል፤ በመከተል አንዳርጋቸው ሲያሰቃያቸው የነበሩትን የአንዳርጋቸው ሰለባዎች አንዱ የሆነው “አውነት ኮበለለች” በማለት አነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ድረገፆችን አሳፋሪ ተግባራቸውን ወጥሮ ይጠይቃል። ኬኒያ ድረስ የኢሳቱ ጋዜጠኛ እና የግንቦት 7 አባል አቶ ከፋሲል የኔ ዓለም ጋር ምግብ ቤት ገብተው የሆነውን ነገር ይነግረናል።
 

አንተንህ ጌትነት  ጋዜጤኞችን "ጠያቂዎች ብቻ መሆናችሁን አታስቡ ተጠያቂዎችም እንደሆናችሁ አትዘንጉ።"  ይላቸዋል።

ዝርዝር ታሪኩን ከማንበባችሁ በፊት የኢትዮጵያን ሰማይ ሐተታ እነሆ፡           

      እኔም አንዳርጋቸው  ነኝ! እኔም ግንቦት 7 ነኝ!  ካሁን በሗላ ግንቦት 7ን ተቀላቅያለሁ” በማለት ካሁን በፊት ኩፉኛ ሲዘልፋቸው የነበሩትን የግንቦተ 7 መሪዎች እና የድርጅቱ “መለከት እና እምቢልታ” የሆነው “ኢሳትንም” ጭምር የወረፋቸው ያህል ፤ ዛሬ “በድንገት አንዳርጋቸው ነኝ ማሉቱ”  የዲያስፖራ ፖለቲከኞች ገጸ ባሕሪ ምንነት፤ ለምናውቃቸው ወገኖች ባያስገርምንም፤ አንዳንድ የዋሃንም “አርበኛቸው አንዳርጋቸው” ጽጌ ብዙ አበበ ገላውን ወደ ጫካ የሚያስኮበልል አጋጣሚ መገኘቱ የተደሰቱ ሊኖሩ ይችላሉ።

በዚህ ጉዳይ በሰፊው በሚቀጥለው ሰሞን በሰፊው ስለምተነትነው ላዘሬ ግን እስኪ አበበ ገላው እና ኢሳት ፤አበበ ገላው እና ግንቦት 7 መሪዎች እንዴት ይመለከታቸው እንደነበር ከምስጢር  አፈተለከ ተብሎ የተገኘው የጋዜጠኛው  የአበበ ገላውን እሮሮ (ኮምለይንት) መለስ ብለን እንፈትሽ። ኢሳት የማን ነው እያለ ብዙ የዋህ ይጠይቃል፤ ሆኖም አበበ ገላው ግን  ኢሳት “የድርጅት ሎሌ እና ልሳን” አንደነበረ ይነግረናል። እንዲህ ይላል።

በኢሳት ላይ ያለኝ አንዱ ትልቅ፤እኔ ብዙ ቅሬታ የለኝም ግን የድርጅት ልሳን ሆኖ ለድርጅት ሎሌ መሆን ደግሞ አልፈልግም፡፡እኔ በበኩሌ፡፡ይሄ ሲሪየስ {serious} የሆነ ኢሹ ነው፡፡እኔ ይሄ ሚዲያ ኢንዲፐንደንትራን {independently run} መሆን አለበት፡፡ይደብርሀል!  ራሱ መስራቱም ማገልገሉም፡፡እኔ ማገልገል የምፈልግው ማንን ነው? ግንቦት ሰባትን አይደለም ማገልግል የምፈልገው፡፡ወይም ግንቦት ዘጠኝን አይደለም ወይም ግንቦት20ን አይደለም፡፡እኔ ሰርቭ {serve} ማድረግ የምፈልገው የኢትዮጵያን ህዝብ ነው፡፡”

ወደ ጫካ የመኰብለል ምርጫውስ “አንዳርጋቸው ነኝ” ብሎ ሰሞኑን ግንቦት 7ን ከተቀላቀለ በሗላ፤ ምርጫው ሊሚትድ ይሆን ወይስ የአንዳርጋቸው ቦታ ይተካ ይሆን? አንዳርጋቸው ነኝ ማለት ምን ማለት ይሆን? እስኪ አበበን ወደ ሗላ እንፈትሽ፦ አንዲህ ይላል።

“እኔን መ ደል የሚፈልግ  መዓት ሰው  አለ፡፡ ህንን ንም  ነግረኝ አያስፈልግ ም። እኔ ራሴ  ውቀዋለሁ። ህንን ካወቅ ይሄንን በምን አይሁኔ ነው  የምትቋቋመው?  መጋፈጥ  ው? ወይስ ሄጄ  ሽጉጥ  በመግዛት? ነው   ወይስ  ጫካ በመግባት?  ምርጫህ ሊሚትድ ነው።” ይህ ተናገረ የተባለው ቈይቷል።ዛሬስ ጫካ ውስጥ የመግባቱ ዕድል ሊሚትድ ይሆን? “አንዳርጋቸዎችን”  አብረን የምናያቸው ይሆናል።

አሁን ወደ አንተንህ ጌትነት ትችት “አውነት ኮበለለች” ጽሑፍ እንግባ፡

                    እውነት ኮበለለች                                                                          
ጊዜውን ለውጠው አረጉት ባለጌ፣
ጀግና ሲባል ሰማን አንዳርጋቸው ጽጌ
ጊዜ ተሸርሽሮ እውነት ተሸርሽሮ አለኝ እጅ እጅ፣
አወጁ አሉ ባንዶች የክተት አዋጅ።
አወይ የጅል ጊዜ ባንዳ ጀግና ተብሎ ታሪኩ ሲውሳ፣
ሻቢያ ያፈነው አንበሳው ታደሰ ታሪኩ ተረሳ።
እውነት ኮብልላለች ሄዳለች ፍልሰት፣
የጋዜጤኞች ውሸት ስለመረራት።

“አንድ ሰው ህይወቱን መስዋዕት ስለደረገ ብቻ የሞተለት ዓላማ የግድ እውነት ነው ማለት አይቻልም።” ለምሳሌ ህ.ወ.ሃ.ትን መውስድ አንድ ተጨባጭ ምስክር ነው። በግለሰቦችም ደረጃ የኮሌኔል ታደሰ ሙሉነህንና የአንዳርጋቸው ጽጌን ማንነትና ምንነት እንመርምር የትኛው መስዋዕት የሆነለት ዓላማ ትክክል ነው? መልሱን ለአንባቢያን እተዋለሁ።

እጅግ ደግሞ የገረመኝ አንድ ጋዜጤኛ ተብዬ  የመን ሰነዓ ሆኖ ያስተላለፈው መልክት ቃል በቃል እንዲህ ይነበባል” ግንቦት7 እያለ ራሱን የሰየመውን ድርጅት መቃወም ማለት የአንዳርጋቸው ጽጌን የዘማናት ጀግንነት መካድ ማለት እንደሆነ እያንዳንዱ ስሜታዊ ፖለቲከኛ ሊረዳው የሚገባ ጉዳይ ነው።” ወንድሜ ግሩም ተ/ ሃይማኖት እስኪ ልጠይቅህ?

፩ኛ/ የአንዳርጋቸውን የዘመናት ጀግንነት ልትዘረዝርልኝ ትችላለህ? እኔ ግን የማውቀው ታሪክ ለወያኔ አድሮ ብዙ ወራዳ ስራ እንደሰራ ነው። ብንራሳ ብንረሳ በፕሮፌሰር አስራት ላይ ያደረገውንና በአማራው ላይ የፈጸመውን እንዲሁም ከግንቦት7 ጋር በአማራው ላይ እየሰሩ ያሉትን ደባ እንዴት የኢትዮጵያ ህዝብ ይረሳዋል ብለህ ብታስብ ነው የዚህን ያህል የዘመናት ጀግና ያደረከው። ምን አልባት አንተ ስለአማራው ከማይገዳቸው ወገኖች በመሆንህ አልፈርድብህም።

፪ኛ/ አንዳርጋቸው እኮ የግንቦት7 ሁለተኛ ሰውና እኔ ከወሰንኩ የኔን ውሳኔ ግንቦት7 ሊለውጠው አይችልም የሚል ፈላጭ ቆራጭ እንዴት ከግንቦት7 ለይቶ ማየት ይቻላል? ይህንን አንዳርጋቸው ስለ ማለቱን የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ በጆሮዬ የሰማሁት ሃቅ ነው።
አንዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲያኮቦክብ ከወራቶች በፊት የወያኔ ጉጅሌዎች ሊያስገድሉኝ ሞከሩ፣ በሰልክ ተነጋገሩ ጅኒ ጃንካ ቢልም ከግንቦት7 ህዝባዊ ኃይል ከሚባለው ባዶ በስም ብቻ ትልቅ ከሆነው አምልጦ ነፍሱ ያትረፈው የወሊሶ ልጅ የሆነውና ከአዲስ አበባ ዩንቭርሲት የመጀመሪያ ድግሪ ያለው ትግስቱ ብርሃኑ ይህ የአንዳርጋቸው ወሬ ፈጠራ ስለመሆኑ እማኝነቱን ሰጥቷል። 

እንግዲህ ይህ ማኮብኮቢያው የነበር ሲሆን አሁን ደግሞ የስማነው ከየመን ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ እንደተወሰደ ነው። እኔ እጅግ ያልገባኝ ነገር የጋንቤላ ፕሬዝዳንት የነበረውና የኖርዌይ ዜግነት ያለው የወያኔ ደህንነቶች ያፈኑት በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ሲሆን አንዳርጋቸው ደግሞ ጋዜጤኛ ግሩም እንደነገረን ከዋና ከተማዋ ሰነዓ ከ50 ኪ.ሜ የማይበልጥ ርቀት ላይ ጦርነት እየገጠመ ያለው የሁቲ መሪ እና ተዋጊዎቹ በዋናዋ ከተማ ባሉበት ያልተረጋጋ ሀገር ሄዶ ተያዘ የሚለው ነገር እንቆቅልሽ ሆኖብኛል።

 የመን ደግሞ ከኤርትራ ጋር መልካም ግንኙነት የላትም። ይህ ደግሞ ያሳየኝ ነገር አስቀድሞ ሲያኮቦክብ የነበረው አሁን ደግሞ በረረ የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል።ይህ በአጋጣሚ ቢሆን እንኳን አንዳርጋቸው ችግር ደረሰበት የሚባለው በአማራው መፈናቀል እና ስቃይ በጨምረበት ወቅት እና በተለያዩ የዜና አውታሮች ሰፊ ትኩረት በተሰጠበትና የህዝብ ቁጣ ባየለበት ጊዜ በመሆኑ ደግሞ ሌላ እንቆቅልሽ ፈጥሮብኛል። ሁሉንም ዕድሜ ይስጠው ለዕድሜ የምናየው ይሆናል።

አንዳርጋቸው ማነው የሚለውን ለማወቅ ከግንቦት7 ህዝባዊ ኃይል በስንት ጭንቅ አምልጥው ሱዳን እንደ አይጥ ተደብቀው መከራቸውን የሚበሉትን እነ ትግስቱ ብርሃኑ፣ ሽታው ሺፈራው፣ ማስረሻ፣ እና ሌሎቹ በግንቦት7d ቃለመጠይቅ የሰጡትን ማዳመጥ የአንዳርጋቸውንና የብርሃኑ አውሬነት በሚገባ ሊረዳ ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የጌታቸው ረዳን ብሎግ ማየት የነዚህንህ አውሬዎች ማንነት እንዲረዳ ያደርገዋል።

www.ethiopiansemay.blogspot.com ኢትዮጵያን እንወዳለን የሚል ሁሉ ይህንን ያንብብ። እውነትን ወደጎን በመተው አንዳርጋቸው ጀግና ነው ማለት ኢትዮጵያን ከመካድ አይተናነስም።

“ አንድ ሰው ህይወቱን መስዋዕት ስላደረገ ብቻ የሞተለት ዓላማ የግድ እውነት ነው ማለት አይቻልም።” እንዲህ ከሆነማ ወያኔ መስዋዕትነት መክፈሉ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን የሞተለት ዓላማ ኢትዮጵያን የማጥፋት ሴራ መሆኑ አይካድም። ታዲያ ግንቦት7 በኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ኤርትራ ሆኖ መታገሉ አንዳርጋቸው ጀግንነት እንዴት እንዳደረገው አልገባ ብሎኛል። “ አንድ የጥሞና ሰዓት ከአንድ ዓመት አጉል ህልም ይሻላል።” ኤርትራ ታግዬ ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ ማለትም ከአጉል ህልምነት የዘለለ አይደለም። ከልብ ማፍቀር ራስን ያስጠላል። ሀገራችንን ስናፈቅር ከራሳችን በላይ አድርገን መሆን እንዳለበት የሚያሳየን አባባል ነው።

እኔን እጅግ ያሥፈራኝ የአዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ መወሰድ ሳይሆን በየጊዜው የግንቦት7፣የኦነግና የኦብነግ አባል እየተባሉ በሌሉበት ስንቶቹ መከራ እየበሉ እንዳሉ የምናውቀው ሃቅ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ህብረ-ብሄር ድርጅቶች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እያገኙ በመሆናቸውና የምርጫ ሰዓቱ እየተቃረበ በመምጣቱ የግንቦት7 መረጃ ከአንዳርጋቸው አገኘን በማለት እውነተኛው ሀገር ወዳድ ታጋይ ለመግደልና ለማሰር መንገድ የሚያመቻች መሆኑ ደግሞ እጅግ አሳስቦኛል።  ከዚህ በተጨማሪ ሥርዓት የሌለው መግለጫ ማውጣት ደግሞ ሀገር ውስጥ ያለውን ሀዝብ ለወያኔ ጥቃት ለመዳረግ ካልሆነ በስተቀር ምንም ፋይዳ የሌለው ነው ?

 ከግንቦት 7የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና የመጀመሪያ እርከን ተግባሪዊ የትግል ጥሪ

 ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!

ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓም

በየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።

አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ምን ማለት ነውአንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።

ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶች ጋር ንቅናቄዓችን ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ የቻለ መሪ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ለወያኔ የጉሮሮ ቁስል የሆነበት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ጋር ግንቦት 7 የፈጠረው ጠንካራ ትብብር ነው። በትህዴን ጋር በመሆን አቶ አንዳርጋቸው ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ጀርባ መንጠልጠል እንዳይችል አድርጎታል። እናም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ከዘረኝነት ፀድቶ መገኘት ማለትም ጭምር ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት በኢትዮጵያዊያን እኩልነት እና እኩል ባለመብትነት ከልብ ማመን እና ለእኩልነት በጽናት መታገል ማለት ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን የግድ የግንቦት 7 አባል መሆንን አይጠየቅም። አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን ለመልካም ዓላማዎች መሳካት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀትን እንጂ የግድ ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር መወገንን አይሻም። ያም ሆኖ ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የሆነ ሰው በጠንካራ ድርጅት የታገዘ ትግል አስፈላጊነት ይረዳል።
በመጨረሻም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ኦኪሎ ኦኴኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እዚህ ዘርዝረን ልንጨርሳቸው የማንችላቸው ጀግኖቻችንን ሁሉ መሆን ማለት ነው።

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነንዘመቻ ትኩረቶችን በየጊዜው የምንገልጽ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል ያለበት የዓለም ዓቀፍ ዘመቻው የመጀመሪያ እርከን ትኩረቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።

የዘመቻው የመጀመሪያው እርከን ትኩረቶች
ይህ የመጀመሪያ እርከን ሶስት ቦታዎች ላይ ያተኩራል፡- የመን፣ ብርታኒያ እና ወያኔ ተብሎ የተከፈለውን አንብቡት ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ። ይህ ጥሪ አንዳርጋቸው እውነት ታስሮ ከሆነ እሱን ለማስፈታት እንደሆነ እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃ ለማውጣት ያለመ አልመስል አለኝ። እውነት አንዳርጋቸው ኤርትራ ያሉትን የጎሳ ድርጅቶችን አስማምቷል? በጭራሽ ከአርበኞች ድርጅት ጋር እንኳን መቀራረብ ያለቻለ እንደሆነ እኔ እራሴ ምስክር ነኝ። ጋዜጤኞችን ጠያቂዎች ብቻ መሆናችሁን አታስቡ ተጠያቂዎችም እንደሆናችሁ አትዘንጉ።

በመጨረሻ የማስተላልፈው መለዕክት ኢትዮጵያን ለማዳን የቆምን ዜጎች ሁሉ አንድ እንሁን። ተነጣጥሎ ትግል ውጤቱ ውድቀትና ለውጥ አልባ መሆኑን በ23ቱ የወያኔ አገዛዝ  ያየነው ሃቅ ነው። የተናጥል ትግልን የሚፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያን ከመበታተን ለማዳን የቆሙ ሳይሆኑ በተቃራኒው የቆሙ ናቸው።
“ ሰላም በኃይል አትገኝም፤ልትጠበቅ አትችልም፤ልትገኝ የምትችለው በመግባባት ብቻ ነው።” ግንቦት7ቶች ህዝብን አክብሩ!ህዝብ በሚፈልገው መንገድ ተጓዙ! ከእውነት አትሺሹ ወደ ሂሊናችሁ ተመለሱ!!!

Email: yqobadishegala@gmail.com  ውድ አንባብያን በዚህ ኢሜሌ የሚሰማችሁን ሁሉ  ብትልኩልኝ ለመወያየት ዝግጁ ነኝ።  ኤርትራ አለው ስለሚባለው የግንቦት7 ወታደርና አንዳርጋቸው አለ ስለሚለው ትግል ውሸት ስለመሆኑ በቀጥታ ለህዝብ በሚተላለፍ ኢሳት ቲቪ ለመወያየት ዝግጁ ነኝ ። ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በግንቦት7 ኤርትራ በረሃ ስልጠና ወስጄ የነበርኩና ስለአንዳርጋቸውና ግንቦት7 የማውቅ እኔ ብቻ በመሆኔ የማውቀውን እውነት ለማስረዳት ዝግጁ ነኝ። በተደጋጋሚም  ለኢሳት ብልክም መልስ አጥቻለሁ። ዝግጁ ከሆናችሁ ምን ጊዜም ዝግጁ ነኝ።
“ክደት ቅስም የምሰብር ሀይለኛ መጥረቢያ ነው!!!”
አምላክ ለኢትዮጵያዊያን ሰላምና ፍቅር ያድለን!!!
አንተነህ ጌትነት ( የሶማው ከባዕድ ሀገር ከአውስትራሊያ)  
      ሐምሌ 30-2006   Posted @ Ethiopian Semay (getachre@aol.com)