Friday, November 21, 2008

በሻዕቢያ መሪዎች ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ዛየር ተወስደዉ መረሸናቸዉን ያጋለጠዉ ሰነድ

 በሻዕቢያ መሪዎች ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ
ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ዛየር
ተወስደዉ መረሸናቸዉን ያጋለጠዉ ሰነድ
(ጌታቸዉ ረዳ)
ሰሞኑ የማቀረባቸዉ ጽሑፎች እየተከታተላችሁ እንደሆነ ከጎብኚዎች የቁጥር ብዛት መቁጠሪያ መገንዘብ ችያለሁ። በአንድ ኤርትራዊ ጸሐፊ ይፋ እየሆኑ ያሉት የምስጢር ሰነዶች ባለፈዉ ሰሞን ዋና ዋና ቁም ነገሮቹን እየጠቀስኩ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አቅርቤአለሁ። ዛሬ ደግሞ በክፍል 2 የቀረበዉ ሰነድ በወያኔዉ መለስ ዜናዊ መንግሥት የሚተዳደረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት መጓጓዣ ተባባሪነት፣ በኤርትራዉ የሻዕቢያዉ መንግሥት መሪ በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ ለአልማዝ ማዕድን ቁፈራ ከኤርትራ በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማመላለሻ ወደ ኮንጎ ተወስደዉ የቁፈራዉ ሥራ ካጠናቀቁ በሗላ፣ እነኚህ የኢሰፓ አባሎች ነበራችሁ ተብለዉ ተይዘዉ ዕድሜ ይፍታህ በኤርትራ በእስር ሲሰቃዩ የነበሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ አባላት (132 ዜጎች) እና የሻዕቢያ ኢዲሞክራሲያዊ አሰራር በመቃወም የታሰሩ የራሱ ታጋዮች 18 ኤርትራዉያን የመረሸኑ ጉዳይ እና ሌሎች ምስጢሮችን ኤርትራዊ ጸሐፊ “አቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ” የተባሉ ይፋ ያደረጉትን የምስጢር ሰነድ ባጭሩ ቀንጭቤ ያዘጋጀሁላችሁ ንባብ ቀርቧል። ከላይ የተዘገቡት ፎቶግራፎች በኢትዮጵያን ሰማይ ዌብ ሎግ የተዘጋጁ ናቸዉ።
ኤርትራዉያን ምሁራን የሻዕቢያን የተለያዩ ወንጀሎች በሚገባ እያጋለጡት ሲገኙ፦ አስከ ዛሬ ድረስ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በዓረብ እና በእስላም አገሮች ሴት እህቶቻችነን በጉቦ መልክ ለባዕዳን አገር ፖሊሶች በማቅረብ ተቃዋሚዉን ሲገድሉ/ሲያስገድሉ እና ሲያሳፍሱ እንደነበር ካሁን በፊት በመጠኑም ቢሆን ዘግቤዉ እንደነበረ ቢታወቅም፤ ድርጅቱ ነብሰገዳዮቹን በማሰማራት የሻዕቢያን ተመሳሳይ ድርጊት ይፈጽም እንደነበር የትግራይ ምሁራን ሳያዉቅት ቀርቶ ሳይሆን፡ በጣም አስገራሚ፤አሳፋሪና አስገማች በሆነ ቸልተኝነት ድርጅቱ ሲሰራቸዉ የነበረዉን በትግራይ ሕዝብ ያሳረፈዉ ግፍና በትር፤ እንዲሁም በየዉጭ ሀገሮች የአፈና፤የግድያ እና የሕገ-ወጥ ገበያ ድርጊቶቹን ከማጋለጥ ታቅበዋል።ለምን?
መልካም ንባብ፦
(“ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ ከ1973 (በፈረንጆች አቆጣጠር) ጀምሮ የመሳሪያ ሽያጭ እና የአልማዝ የጥቁር ገበያ/ኮንትሮባንድ ተሰማርቶበት የነበረዉን ህቡእ ሥራዉ ከረፈረንደሙ በሗላም ቢሆን ትላልቅ ሓይቅ አገሮች ተብለዉ ወደ ሚጠሩ አካባቢዎች ለምሳሌ ዛየር ዉስጥ ሎረንት ካቢላ ሲመራዉ ለነበረዉ የሽምቅ ተዋጊ ቡድንና የዛሬዋን ሩዋንዳ በመምራት ላይ ላለዉ ፓወል ካጋመ ሲመራዉ ለነበረዉ የሽምቅ ተዋጊ ሃይል ከደረግ ማርኳቸዉ የነበረዉን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት መጓጓዣ እየተጠቀመ መሸጥ እና ማስተላለፍን ቀጠለበት።
ከጥቁር ገበያዉ እንቅስቃሴ ዉጭ በኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት ስም ራሱን ሹሞ ለዓለም ያስተዋቀዉ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ “ወዲ ስኞራ” እና “ሰለሞን ሃይለ” (ራሻይዳ) በሚበላዉ ታጋይ የሚመራ አንድ መካናይዝድ ጦር እና የክፍለ ጦር አዛዥ የነበረዉ “ገብረ እግዚአብሔር ዓንደማርያም”/ዉጩ/ የሚመራ የኤርትራ ጦር ወደ ዛሬዋ ዛየር የድሮዋ ኮንጎ ሪፑብሊክ በመላክ ፕረዚዳንት መቡቱ ሰሲሴኮን በመቃወም ሲዋጋ ለነበረዉ ሎሬንት ካቢላን በማገዝ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዉግያ በማድረግ ካቢላን ወደ ሥልጣን ለማምጣት 29 ኤርትራዉያን መስዋዕት ከፍለዋል።
ለቅጥር ዉለታዉም ሎሬንት ካቢላ ወደ ሥልጣን ከመጣ በሗላ ከወረሳቸዉ ሰፋፊ የማዕድን ቦታዎች አንዱን ለኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት በባለቤትነት ለግሶታል።ለማዕድኑ ፍለጋና ቁፋሮም የሰዉ ሃይል ስላስፈለገ፤ደርግን በማገልገል የኢሰፓ አባሎች ነበራችሁ ተብለዉ “ናይዘጊ ክፍሉ” በተባለዉ የሻዕቢያ ታጋይ ተፈርዶባቸዉ ለዓመታት ሲሰቃዩ ከቆዩት ኢትዮጵያዉያንና ተቃዋሚ ተብለዉ ለእስር የተዳረጉ 18 ኤርትራዉያን ታጋዮች በድምሩ 150 ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን በሰንሰለት የፍጢኝ ታስረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማጓጓዣ አይሮፕላን ወደ ኮንጎ እንዲተላለፉ አድርጓል።
የአልማዝ ፍለጋ ቁፋሮዉ እየተካሄደ እያለም የተባበሩት መንግሥታት እና የፈረንሳይ መንግሥት ወደ ኮነጎ ሪፑብሊክ በመግባታቸዉ ጋር ተያይዞ ቁፋሮዉ ከቆመ በሗላ ምስጢሩ እንዳይታወቅበት በመስጋት በማዕድን ቁፋሮ አሰማርቷቸዉ የነበሩትን 150 ዎቹ ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን አስረኞች እንዲረሸኑ ተደርጎ በአንድ ጋጥ ጉድጓድ ተቆፍሮ ሬሳቸዉ በአንድነት እንዲቀበር ተደርጓል ። ይህነን አስመልክቶ ጀርመን ሀገር ሚታተም አንድ ጋዜጣ ድርጊቱን ይፋ በማድረግ ለሕትመት አድረሶት እንደነበር ይታወሳል።
ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አንዳንድ የዋሃን ወገኖች የትናንቱ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ-የዛሬዉ ህዝባዊ ግምባር ፍትህና ዲሞክራሲ- ንቅዘት የሌለዉ በብልሹ ስነ ምግባር እጁን ያልነከረ ጥንቱም ሲፈጠር ሆነ ዛሬ ገና ከመወለዱ በፊት ጻድቅ የሆነ እንከን የለሽ ቡድን አድርገዉ የሚገልጹልን የዋሃን አሉ።ሆኖም ሃቁ ከዛ እጅግ የራቀ ነዉ። እንደሚሉትም አይደለም።ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በትግሉ ጊዜ ጀምሮ የአልኮሆል መጠጦች፤የዕጸ-ፋርስ (ሓሽሽ) እና በመርፌ የሚወጉ ሕገ ወጥ መድሃኒቶች፤አልማዝና ወታደራዊ ንበረቶችን ወደ መሃከለኛዉ ምስራቅና የመሳሰሉ አገሮች በመሸጥና በማዘዋወር ሥራ ተሰማርቶ የነበረ ሃይል ነዉ።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ አህጉሮች ሕገ ወጥ ገንዘብ በማሸሽ እና በማካበት ድርጊት ተሰማርቷል። በዘህ ድርጊት ተሰማርተዉ ሲያገለግሉት የነበሩት አባሎቹ አንዱ የዛሬዋ የኤርትራ መንግሥት የአገር መከላከያ ሚኒስተር የሆነዉ የጀኔራል ስብሐት ኤፍሬም ታላቅ ወንድም ዳዊት ኤፍሬም ነበር። ዳዊት ኤፍሬም በሕገ ወጥ ተግባር ሓሽሽ እና አልኮሆል ጭና ስትጓዝ በነበረችዋ መርከብ በመያዙ የካቲት (February 1983) በኢጣሊያን መንግሥት ተይዞ የ5 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ሲያበቃ ሁኔታዉ ባልታወቀ ምክንያት እስራቱ ሳይፈጽም እንዲለቀቅ ተደረገ።
በመሳሰሉት ሕገ ወጥ ድርጊቶች የአልኮሆል የሕገ ወጥ መድሃኒቶችና የመሳሰሉት ገንዘብ ማስገኚያ ሕገ-ወጥ ገበያ ድርጊቶች ላማከናወን ካሰማራቸዉ ግለሰቦች -(ምንም እንኳን ከሚጠቀሱት ሰዎች ዛሬ በተላያዩ ምክንያቶች እስር ቤት ቢገኙም)፡ በድርጊቱ ተሰማርተዉበት የነበሩበት ቦታና ስም ዝርዝራቸዉ አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ያህል፦
(1) እስቲፋኖስ ሃይለ መኮንን (በዛየር-ኮንጎ) (2) ኤርሚያስ ደበሳይ/ፓፓዮ/ (በአዉሮፓ አገሮች) (3) ሰለሞን ሐድሽ (በሱዳን) (4) ደስበለ ተስፋጽዮን/ደሱ ወዲ ማዓሎ/ (በኤርትራ እና በመካከለኛዉ አፍሪካ) (5) ሙሴ በኺት (ሱዳንና በመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች) (6) ዳዊት መንግሥት አብ (አፍሪካ፤አዉሮጳ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ)መሓመድ አሕመድ ቓስም (መካከለኛዉ ምብራቕ) እና ሌሎች የመሳሰሉት ግለሰዎች በሚገኝበት ቡድን በኩል ነበር ሕገ-ወጥ ገበያዉ ሲያከናዉን የነበረዉ።
ድርጅቱ ከሕዝብ እና ከጠላት ማርኮ ያግበሰበሰዉ ዶላር ወደ ጎን ትተን ሕጋዊ ባልሆኑ ገበያዎች ያካበተዉ ሕጋዊ አስመስሎ በተለያዩ አህጉሮች በሚገኙ ባንኮች ሕጋዊ ሰነድ ከፍቶ ያስመዘገበዉ ገንዘብ 3.7 ቢልዮን ዶላር ነበረዉ። በጣም የሚገርመዉ በየባንኩ የተቀመጠዉ የገንዘቡ መጠን/አሀዝ ከኢሳያስ አፈወርቅ በቀር ማንም የሕዝባዊ ግመባር ባለስልጣን አያዉቀዉም።የገንዘቡ ባለቤትነትና መጠን የተመዘገበዉ በተለያዩ ግለሰቦች ሰም ስለተመዘገበ በባለቤትነት የተመዘገቡት ግለሰዎች በሕይወታቸዉ ላይ ቅራኔን በሚያስከትል የባለቤትነት አሰራር ዘዴ ነበር ሲጠቀሙበት የነበረዉ። ከኤርትራ ነፃነት በሗላ የንግድ ኮሚሽኑ ወደ ሚኒስቴርነት ሲሸጋገር የተቋሙ ሀላፊነት 09 እንዲረከበዉ ትዕዛዝ ተላለፈ።
ሐምሌ 1991 ደንጎሎ በተካሄደ ስብሰባ አስገራሚ ዜና ተላለፈ። ግምባር ማለትም ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ አዲስ በመቋቋም ላይ ለነበረዉ የኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት ለመቋቋሚያ በጀት የሚዉል 250 ሚልዮን ዶላር ማበደሩ ነበር። ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ መስከረም 1991 አጋማሽ ከጣልያን መንግሥት ጋር ባደረገዉ ግንኙነት በአለፉት 50 ዓመታት ፋሺስት ኢጣሊያ በኤርትራ ሕዝብና መሬት ላይ ላደረሰዉ ጉዳት በካሳ መልክ በራሱ አነሳሽነት ወደ 360 ሚሊዮን ዶላር ሊለግስ ዝግጁነቱ ካስታወቀ በሗላ፡ሊለግሰዉ የታቀደዉ ገንዘብ ለአየር ማረፊያ፤ለባቡር ሃዲድ መጠገኛ ለዘመናዊ መጓጓዣ እና መገናኛ መንገዶች ለመሳሰሉት እንዲዉል የመደበዉ ቢሆንም፡ ኢሳያስ አፈወርቅ ግን “ጥሬ ገንዘቡን በእጆችን ስጡን” በማለቱ ከተጠቀሰዉ ገንዘብ ከፊሉ እንዲሰጠዉ ቢደረግም፤ ጥያቄዉ ስላላስደሰታት፤ ለጋሿ ጣሊያን ላለመቻቸዉ የዕድገት ዘርፎች የማይዉል ከሆነ ብላ የተባሉት ዕቅዶች ሳይተገበሩ ልገሳዉ ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ።
የአሜሪካ መንግሥትም የህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ አካሄድ በቅርብ ሲከታተለዉ ከቆየ በሗላ ህዝባዊ ግምባ ሓርነት ኤርትራ በዓለማችን እጅግ አደገኛ ቡድኖች መካከል ከሆኑት አንዱ ብሎ ማህደሩ ዉስጥ ለመመዝገብ ጊዜ አልፈጀበትም። ይቀጥላል…………..”)
ማሳሰቢያ_
ወደ ጎነጎ የፍጢኝ ታስረዉ ወደ ኮነጎ ዛየር ማዕድን ቁፈራ ሲሄዱ ሃለፊነቱን የወሰደዉ ግለሰብ የህዝባዊ ግምባር የእስረኞች ጉዳይ ዋና መርማሪ የነበረዉ ወልደዝጊ ባህታ የተባለ ሲሆን በዉሳኔዉ ግምባር ቀደም ተዋናያን የነበሩ ባለስልጣኖችም ከሟቹ ዓሊ ሰይድ ዓብደላ ጀምሮ 9 ትላልቅ የሻዕቢያ ባለስልጣናት በዉሳኔዉ መሳተፋቸዉ ስምዝርዝር የገለጸ ሲሆን፤ ዛየር ኮነጎ ሄደዉ ማዕድን ቁፈራ ተሰማርተዉ ሲሰሩ እላይ በተብራራዉ ምክንያት የህዝባዊ ግምባር መሪዉ ኢሳያስ አፈወርቅ ምስጢሩ እንዳይታወቅ በማለት 150 ዎቹ እንዲረሸኑ ሲያደርግ ከነዚሁ 18 ኤርትራዉያኖች ሲሆኑ፤ የ18ቱ ስም ዝረዝር እና ምድብ ክፍላቸዉ፤ ዕድሜ፤ትዉልድ ቦታ እና የተማሩበት ትምርት ቤት እንደዚሁም በቁጥጥር የዋሉበት ዕለት እና ዓመተ ምሕረት በሰነዱ ላይ በዝርዝር ቀርቧል።-/-www.ethiopiansemay.blogspot.com