Monday, October 17, 2022

ለገዳዩ የሚዘምር አሽቃባጭ የጎንደሬዎች መንጋ A herd of scornful goons singing to the Oromo fuhrer ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/18/22

 

ለገዳዩ የሚዘምር አሽቃባጭ የጎንደሬዎች መንጋ

A herd of scornful goons singing to the Oromo fuhrer

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

10/18/22

እርግጠኛ ነኝ አንዳንድ ጎንደሬዎች ትችቴን ደስ እንደማይላቸው እገምታለሁ (ካለኝ የብዙ አመት የጥናት ልምድ) ሆኖም “ዋጥ” አድርጎ ሃቁን መቀበል የጭዋ ባህሪ ነው። ትግሬዎች እስከሚበቃቸው ስነግራቸው አይወዱትም እናንተም እንዲሁ። ሆኖም ፖለቲካው መራራ ነው’ መዋጥ የግድ ነው።በጣሊያን ጊዜም ባንዳ የታየበት ነው ዛሬ ልዩ አይደለም።ሃቅ መቀበል የማይችል አንጀት ካላችሁ ከፖለቲካው መራቅ ነው። ዛሬ ደግሞ መሬታቸውን ለሱዳኖች ለሰጠው ሰውየየ ዕልል ኑርልን እያሉ ሲያሽቃብጡ ማየት የሚገርም ዘመን ነው።

 ብዙሃኑ “ለእውነት” ጥማታቸውን አሳይተው አያውቁም። ይላሉ የአእምሮ ጥናት ጠበብት። “ስሕተት ሆነው ቢታለሉም እንኳ፤ ስህታተቸውን ማምለክ ይመርጣሉ”። ስለዚህም  “የሕሊና ንህሎላ የሚሰጣቸው ሰው ሁሉ በቀላሉ  ይቆጣጠራቸዋል”። የኑህላለው ስሜት አመንጪዎቹ ደግሞ መንጋውን በመምራት ላይ ያሉት  ሰዎች ናቸው”። ይላሉ። በዚህ ሁሉ ጉዞ “ሀሳባቸውን ለመለወጥ የሚሞክር ቀና ሰው ሁሉ የሁሌም ሰለባቸው ይሆናል።” ይላሉ። ይህንን ሃሳብ የተናገረው ታዋቂው የአእምሮ ጥናት ጠበብት ጉስታቭ ለቦን ነው።

በቪዲዮው ላይ የምታዩት ንበሰገዳዩና የአባንቱስታዎች አፓርታይድ ግዛቶች መሪው አብይ አሕመድ ጎንደር ከተማ በገባበት ወቅት የጎንደር አሽቃባጮች ምን ያህል ቅሌታሞች መሆናቸውን ለታሪክ የሚቀር ትዕይንት እንደሆነ ከማሳያቱ አልፎ እነዚህ አማራዎች ናቸው ብየ እግምታለሁ፤ ወገናቸው እያሳረደ፤ እያሰረ፤እያፈናቀለ ፤ እያንገላታ እያሳደደ፤ ለ30 አመት ሙሉ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ግፍ እየሰራ ያለው  ሰርዓት በዕልልታና በጭፈራ እንዲሁም ነብሰ በላው እንደ ፈጣሪ ሲያሞግሱት ማየት የሚነግረን ነገር ካለ፤ ይህች አገር ገና ለ30 አመት መከራዋ የሚቀጥል እንደሆነ አመለካች ነው።

 

ብዙሃኑ “ለእውነት” ጥማታቸውን አሳይተው አያውቁም። የሚለን ጠበብቱ ጉስታቭ ለቦን ከዚህ ልምድ በማየት ነው።\ከበርካታ አመታት በፊት ወያነ ሥልጣን ላይ እያለ፤ ዛሬ የአብይ አሕመድ ድጋሚ ዐሽከር ሆኖ እያገለገለ ያለው ማፈሪያው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተባለ ግማሽ ወልቃየቴ ነኝ የሚል ሰውየ፤ ዛሬ አብይ ወደ ጎንደር ሄዶ ጎንደሮችን እንዳስጨፈራቸው ያኔ የዘመኑ ሹማሙንቶችም ጎንደር ሄደው ስያሽቃብጡላቸውና እንዲሁም እነ አያሌው ጎበዜና አዲስዩ ለገሰ፤ደመቀ፤ህላዌ ዮሴፍ ወዘተ.. የመሳሰሉት ወደ ውጭ አገር እየመጡ የጎንደር ማሕበር መረዳጃ፤ የንግድ ፤የብድር ምናምን እያሉ ውጭ አገር ያለውን ነሆለል ኢትዮጵያዊ ሲያኖሆልሉት ፤ ጥቂት የጎንደር ሰዎች ደግሞ ተቃውሞ በማሰማታቸው፤ ታዬ አጽቀስላሴ "Gondar ain’t your mama’s fool no more"  ጌኞ ሆይ “ጎንደር” ካሁን ወዲህ የናትህ ጎንደር አትሆንም” ሲል የስላቅ ጽሑፍ ኤኢጋፎረም ለጥፎ ነበር። እንዲያ ያሰኘውም፤ ብዙ ቸፋሪ ጎንደሬ ተከታይ አንዳላቸው የሚያመለክት ነበር። ዛሬም ያው አልተለወጠም። ማሽርገድ ባህል ሆኖ ዘልቋል።

ቀሳውስቱ ሓጂው፤ጡረተኛ ወታደሮች፤አዝማሪዎች፤ ሁሉ ነብሰገዳዩን ቅዱስ ሰው አስመስለው የፈጋ ፈገግታ እያሳዩ ሲያንቓልጡ ማየት በጣም ያስጠላሉ። ይህ የሕሊና በሽታ ነው።

የሰውነት በሽታ በሕዝብ ውስጥ ሊሰራጭ እና የወረርሽኝ መጠን ሊደርስ ይችላል” ልክ እንደ ኮረና ቫይረስ፡  ነገር ግን የአእምሮ በሽታዎችም እንዲሁ ብዙሃንን ይለከፋል።  ፈረንጆቹ የጅምላ ሳይኮሲስ/ የጅምላ መናወጥ ይሉታል። የጅምላ ሳይኮሲስ በጣም አደገኛ ነው። በጅምላ ሳይኮሲስ ሕዝቡ ጤነኛ መስሎ ቢራመድም ፤አጊጦ ቢለብስም ንክ ማሕበረሰብ ነው። እንደዚያ ሲሆን  እብደት በህብረተሰብ ውስጥ የተለመደ ነገር ይሆናል (ዕብደቱ ባንድ ሰው ብቻ ስለማይሆን)። ማለትም “እምነቶች” ያሳብዳሉ። እንደ ኢንፌክሽን ከሰው ወደ ሰው ይሰራጫሉ። በጅምላ የስነ ልቦና በሽታ የተለከፈው ማህበረሰብ  (መንጋ) ታሪካዊ እና ባህላዊ አውድ ውስጥ “ውትፍ ነቃይ” የሚሉት የድሮ ሰዎች” ተዋናይ ሆኖ  አፍራሽ ሆኖ አፍራሽ ሚና ይጫወታል። በኢትዮጵያችን በዘመናችን ትልቁ ስጋት የሆነው “የውትፍ ነቃይ” የጅምላ የስነ ልቦና ችግር ነው።

ለማጠቃለል፡ ጎንደሬው መከራ የደረሰበት መሆኑን ለበርካታ አማታት የጻፍኩበት ነው፤ ሆኖም ከዚህ በታች የተገጠመው በትሩን ላልቀመሱ ለአሽቃባጭ ጎንደሬዎች የተገጠመ ስለሆነ  ይህንን ብየ ልሰናበት።

አጼ ቴዎድሮስ በ1858 ዓ.ም አንጅባራ ከደጃዝማች ተድላ ጓሉ ተዋግተው ድል ካደረገ በኋላ በወቅቱ የተማረኩ ወታደሮችና እና የአካባቢው ኗሪ ወደ 20,000 እንደነበር ይገመታል፡ ቴዎድሮስም የተማረከው ሕዝብ እና ተዋጊ ሠራዊት በሰልፍ አስሰልፎ በጥይት እና በጎራዴ እየተደበደበ እንዲደገደል አደረገ።ጭፍጨፋው ከተጠናቀቀ በኋላም “ ጌታ ሆይ ጠላቶቼን እፊቴ ላይ እንዲወድቁ ስላደረግክልኝ ምስጋና ይድረስህ” ሲል መሬት ተሳለመ፡ ከዚያም አንዲት የጎጃም ሴት

     አንጠረኛው በዙ ከንጉሡ ቤት

     ባል አልቦ አደረጉት ይህን ሁሉ ሴት


 ሰትል ስትገጥምላቸው፡


ሌላ የጎጃም ሴት ደግሞ ፤-

 

“ልቤንም ገረፈው ለበሰው እረኛ

በሬየንም ነዳው አረደው ነፍጠኛ

እህሌን ዘረፈው በላው ቀለብተኛ

ንጉሥ የቀረዎ ጥቂት አማርኛ

ምነው ሆድ አይዘርፍ አረፈ እንደተኛ

አገሬን ዘረፈው እያለው ደስ ደስ

ሞኙ ቤጌምድሬ ፈንታው እስኪደርስ”

 (ምንጭ ሃለቃ ተክለየሱስ)፤

አሽቃባጭ እየበዛ መካች ሲታጣ ማነህ ባለተራ እያልን ለስንት ዘመን እንዲህ እንዝለቀው? ቪዲዮውን ለማየት ይህንን ይጫኑ።

https://www.facebook.com/100038936079701/videos/507559697893139/

 አመሰግናለሁ

ጌታቸው  ረዳ