Saturday, February 1, 2020

የአብይ ጩሉሌዎች በዲሲ ሕዝባዊ ስብሰባ በአርበኛው ሺመልስ ላይ ያሳዩት የዱርየነት ባሕሪ ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 2/1/2020


የአብይ ጩሉሌዎች በዲሲ ሕዝባዊ ስብሰባ በአርበኛው ሺመልስ ላይ ያሳዩት የዱርየነት ባሕሪ
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
2/1/2020
ፎሮግራፉ ላይ የሚታየው ባለ ቀዩ ቆብና እስኪ ቆብ የለበሰው ሌላኛ ማጉያውን  ከሺመልስ እጅ እንዴት እንደነጠቀው ተመልከቱልኝ


የግዕዝ ፎንት ጽሑፍ አልሰምር ብሎኝ ተቸግሬ ከመጻፍ ተቆጥቤ ነበር። ዛሬ ተሳክቶልኝ መጥቻለሁ። ዛሬ ድንገት ባንድ ፌስቡክ ወዳጅ ተለጥፎ ያየሁት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የኦነግ/ሻዕቢያው ቅጥረኛ “አብይ አሕመድን” ለመቃወም በተጠራው ስብሰባ ከወያኔ ሎሌዎች የባሱ ያገጠጡ ዱርየዎች “በአዘጋጂነት ቀርበው” በጀግናው የባልደረባው አባል “ሺመልስ” እጅ የድምፅ ማጉያ በመንጠግ ያስደነገጠኝና ካሁን በፊት አይቼው የማላውቀው ትዕይንት ማየቴ እንቅልፍ የምተኛ አይመስለኝም።

 ልብ በሉ ካሁን በፊት አይቼው የማላውቀው “የምላችሁ ምክንያት” ተቃዋሚ መስለው በአዘጋጂነት የቀረቡ ለአገዛዙ ያደሩ የአብይ አሕመድ አወዳሾች ያሳዩን “የተቃዋሚ ሰልፍ አዘጋጆች ሆነው የቀረቡ ለገዢው መደብ ያደሩ መልዕክተኞች” ባለፈው የወያኔ ጊዜም በፍጹም አይቼ ሰምቼ አላውቅም። ለዚህ ነው ይህንን ከዚህ በታች የምትመለከቱት ቪዲዮ በሰልፈኛው ፊት ላይ ቆሞ አብይን ሲያጋልጥ የነበረው ሁላችሁም የምታውቁት የውዲቷ አገራችን ሰንደቃላማ ከትክሻው ላይ የማይለያት ሺመልስ ሲናገር አዘጋጆቹ “የደምፅ ማጉያው” ከእጁ ነጥቀው “አብይን ጩሉሌ ብሎ መሳደብ አይፈቀድም” በማለት “ሺመልስ” ለተሸከመውን ሰንደቃላማ ክብር ሳይሰጡ የድምጽ ማጉያው ሲነጥቁት ሰንደቃላማችንን ከእጁ ሳይቀር ለማስጣል ሲንገዳገዱ አይተናል ። እነዚህ ሰዎች እንዴት አዘጋጆች ሆነው እንደቀረቡ በዚህ ጉዳይ የምታወቁ ካለችሁ እባካችሁ አስረዱን። በሎሌነቱ ‘መለስ ዜናዊን’ ያስናቀ የኦነግና የሻዕቢያ አሽከር አብይ ኣሕመድ እንዴት አስሰርጎ በተቃዋሚ አዘጋጅነት እንዴት እንዳሰለጠናቸው የሚገርም ሰው ነው። በዚህ ላይ ዲሲ ያላችሁ ዜጎች በስፋት ንገሩን። ቤጊዜው የሚፈልቁ አድርባዮች ካለፉት አድርባዮች እየሳሉ እንዴት እያስገረሙን እንደመጡ ተመልከቱልኝ። አብይ አሕመድ በሰደበን ቃል ተመልሶ ሺመለስ ጩሉሌውን “የጅማው ግራኝ አብይ አሕመድን ““ጩሉሌ” ብሎ ሲሰድበው መሪያችንን መስደብ አይፈቅም” ብለው አሜሪካ አገር እየኖሩ የመናገር ነፃነት ሲያፍኑ ይህንን አሳፋሪ የአብኢይ አሕመድ አገልጋይ የቅጥረኞች ባሕሪ ለታሪክ የተቀዱበት ቪዲየውን ይኼው ተመልከቱት፦

በአሜሪካ በተቋውሞ ሰልፍ ላይ ሌላ ተቋውሞ ተነሳ


አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ ኢትዮ