Sunday, October 31, 2021

የኢሳት ጋዜጠኛው መሳይ መኮንን በንጹሃን ትግሬ ቤሰተቦቼ ህይወት ላይ ያስተላለፈው ለሁለተኛ ጊዜ የዘር ማጥፋት ጥሪ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) 10/21/2021

 

የኢሳት ጋዜጠኛው መሳይ መኮንን በንጹሃን ትግሬ ቤሰተቦቼ ህይወት ላይ ያስተላለፈው ለሁለተኛ ጊዜ የዘር ማጥፋት ጥሪ!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)

10/21/2021

ከትናንት በስትያ ጥብቅ መልዕክት ለመንግስት በሚል ርዕስ ያስተላለፈው የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን መልዕክት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ትግሬዎች የትም ይኑሩ የትም ገጠርና ከተማ እየተለቀሙ ወደ ማጎርያ እንዲገቡ ለመሪው ለአብይ አሕመድ እና በጣም በጭካኔአቸው ለታወቁ “ጊስታፖ” ፖሊሶች እና የደህንነት አባሎች ያስተላለፈው የዘር ጭፍጨፋ ጥሪ በየዜና ማሰራጫዎች በመጠኑ ማነጋገሪያ ሆኗል።

በጣም ጥቂት የሆኑ ትግሬዎች ያልሆኑ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በቁጭት እና በንዴት ጥሪውን አውግዘውታል። እጅግ አመሰግናለሁ። በተለይ እኔ  በቅርቡ በንጸሁ ወንድሜ የደረሰው ግፍ በኔ እና በቤተሰቦቼ ሕሊና ውስጥ ትውስታውና ስጋቱ አሁንም ስላልቀቀን በቋት ላይ ነን። እንዲህ ሆኖ እያለም ፤ በተቃራኒው እጅግ ጽንፍ የረገጡ የጀነሳይድ አባላት በየፌስቡካቸው የመሳይ መኮንን ጸረ ትግሬ አዋጅ የአማራ ወጣት እና ሕዝብ በንጹሃን ትግሬዎች ላይ እንዲበቀል ጥሪ እያስተላለፉ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ የማስተላልፈው መልዕክት “እንዲህ ያለ ቅስቀሳ የሚያሰራጩትን ፌስቡኮች እንደትመዘግቧቸው፡ጥሪ አቀርባለሁ።

አንዳንዶቹ የትግሬዎች ንብረት፤ሱቅ ቤቶች፤መኖሪያ ቤቶች እየገቡ እንዲሰባብሯቸው ሁሉ ጥሪ አቀረቡ እንዳሉ አይተናል።እንዲህ ያለ ጋጠወጥነት ያስታወሰኝ ጀርመኖች “Reich Christal Night” The Night of Broken Glass በመባል የታወቀው በዘመነ ሂትለር የናዚ ጀርመኖች “የ ኤስ ኤስ” (የሂትለር ቦዲ ጋርዶች) እና “ኤስ ኤ” (የድሮ ኮማንዶ ወታደሮች) በመናበብ በመላዋ ጀርመን በሚገኙ በአይሁዶች ቤቶች፤ንግድ ቤቶች ቤተጸሎት በምሽት እና በውድቅት ጥዋት ሰው በተኛበት ሰዓት በመግባት መስተዋቶችን በመሰባባር፤ ንብረት በመዝረፍ፤ የቤት እቃዎችን ወደ ደጅ  በመጣል እና በመግደል… እጅግ አደገኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የነበረውን አንብቤአለሁ። ይህ ወንጀል የተፈጸመው ሂትለር እራሱ ለጎቤል ባስተላለፈው የኮነሰንትሬሽን (ማጎሪያ) ካምፕ አዋጅ እና “የዘረፋ ጥቃት” እንዲፈጸም ባስተላለፈው ሰበብ በመጠቀም ያልታወጀውንም ወንጀል ጭምር በአይሁዶች ላይ ሲፈጽሙ እንደነበር ከመጻሕፍት አንብበናል።

ዛሬም በአንዳንድ ጽንፈኞች የሚተላለፈው አደገኛ መልዕክት ይህንን ወንጀል እንዲፈጸም ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። ለዚህ ተጠያቂው ጋዜጣኛ መሳይ መኮንን መሆኑን ካሁን እንዲታወቅልን ለመላ ጤነኛ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

 በ 5 ኣመት ውስጥ ሁለት (2) ጊዜ በመሳይ መኮንን የተላለፉ ሁለት ጸረ ትግሬ የዘር  ማጥፋት ወንጀል ጥሪው እንመልከት።

በሁለተኛው እና በቅርቡ ያስተላለፈው አዋጅ ልጀምር፡ ከዚያም ሁለተኛው እንመለከታለን።

ጥብቅ መልዕክት ለመንግስት ከ Mesay Mekonnen

==================================

ከህወሀት ጋር ግንኙነት የሌላቸውንም ሆነ ያላቸው የትግራይ ተወላጆችን በጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያዎች እንዲሰባሰቡ ስለ ማድረግ ይይተላለፈ ጥብቅ መልዕክት ለመንግስት  ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንደጻፈው አሁንም አልረፈደም ይላል::

እንደ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከሆነ የትግራይ ተወላጆችን፣ ከህወሀት ጋር ግንኙነት የሌላቸውንም ቢሆን በጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያዎች እንዲሰባሰቡ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ ተግባር አሁንም ቢሆን አለመርፈዱን ያስገነዝባል::

ጋዜጠኛ መሳይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተፈጸመን የአሜሪካን ልምድ በመጥቀስ እንዲህ ይላል::

"አሜሪካ ወደ ጦርነቱ ከመግባቷ በፊት በሀገሯ የሚኖሩ የጃፓን ዜጎችን በሙሉ ወደካምፕ አስገብታ ነው የጃፓን ወራሪንና የሂትለርን ጦር ማሸነፍ የቻለችው። ጃፓኖችን በብብቷ ስር ወሽቃ ወደ ጦርነቱ መግባት የሽንፈት መጀመሪያ መሆኑን በመረዳቷ እርምጃውን ወስዳለች.."

ኢትዮጵያንም ከዚህ ከዚያ የከፋ አደጋ ውስጥ ለማውጣት ጊዜው ያልረፈደ መሆኑን ጠቅሶ;

"የደሴው ግብግብ ዋና ተዋናይ ከህዝቡ ጋር አብረው የሚኖሩት የህወሀት ደጋፊዎች መሆናቸው በስፋት ይታመናል። እነሱን በጉያ ይዞ ጦርነቱን ማሸነፍ በፍጹም የሚቻል አለመሆኑን በማሳሰብ ለእነሱም ደህንነት ጭምር ሲባል እርምጃው በአስቸኳይ ሊወሰድ ይገባል!"

 በማለት ይመክራል ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን::

#MesayMekonnen

2) ካሁን በፊትም በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር September 4/ 2016 የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በትግሬዎች ላይ የዘር ማጽዳት ጥሪ “ዓሳን ለማስወገድ ባሕሩን ማድረቅ” በሚል በመላ የትግራይ 6 ሚሊዮን ሕዝብ የዘር ማጥፋት አዋጅ ጥሪ በኢሳት ቴ/ቪ ጣቢያ አንብቦ እንደነበር ይታወሳል። ይህንን ለታሪክ በመጽሐፌ ውስጥ ተዘግቧል። በወቅቱ ያላደመጣችሁት ሰዎች ብትኖሩ ቪዲዮው ሙሉውን አዋጅ እንድታደምጡት  ለጥፌዋለሁ። ዋና ዋና የሆኑትን የአዋጁ ፍሬ ነገሮች ባጭሩ አቀርባለሁ፡ ጥሪው በጎንደር አማራ ሕዝብ ስም ነው። እንዲህ ይላል፦

“ከጎንደር የአማራ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ”

“ይድረስ

 ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴ/ቪዥን ሳተላይት (ዲሲ አሜሪካ)፤

አምስተርዳም (ኒዘርላንድ)፤

ለኦሮሞ ሚዲያ ኔት ዎርክ (ዋሺንግቶን ዲሲ አሜሪካ)፤

 በሰላም ሊመለስልን ያልቻለውን ነፃነታችንን እርምጃ በተፈለገው የሃይል እርምጃ ለማስመለስ የቀረበ ጥሪ፤  

ወደድንም ጠላንም ምርጫው አንድ ብቻ ነው፡ እነሱ ወደ ፈለጉት የሃይል እርምጃ በመግባት ነፃነትን ማስመለስ!

  ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህ የጥፋት ዕቅድ የታቀደው ከ5 ሚሊዮን ሕዝብ ለ90 ሚሊዮን ሕዝብ ነው። ለዚህ ድግሞ……. >  <…የሚያሳዝነው ደግሞ 5 ሚሊዮን ቢበዛ ለ10 ፈላጭ ቆራጭና ቢበዛ በነሱ ዙርያ ላሉ 10 ሺሕ እንኳ ለማይሞሉ በመጠቀሚያ መደላደሊያ ለሚያገለግሉ ሰዎችም ጭምር ነው። < መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም እነዚህ መጠቀሚያ እና ለመዳላደሊያ የሆኑትን በተለይ ወገኖቹን የትግራይ ሕዝብ መካከል በተለያየ ጊዜ በመግባት ለሰላም እንዲታገሉ፤ካልቻሉ ብቸኛነታቸው እንዲያሳያቸው በተለያየ መንገድ ለምኗል። ይህንን ልመና ግን አልሞከሩም፤ ጭራሽኑ ይባስ ብለው፤ የነሱ ልጆች መንፈስ እንደሆኑ በመንገር የስነልቦና ጦርነት በማካሄድ ይስቁብናል፤ያዋሩዱናል። በመሆኑም ውርደትና እልቂት ብቻ ሆኗል።ይህ የ25 አመት ሰላማዊ ሰልፍ ውጤት እንደማያመጣ በኛ ተወካዮች ተነግሮናል።

.... ስለዚህ አሁን ምንድነው የምንጠብቀው? እንደዚህ እየነጣጠሉ እስኪጨርሱን፤ ካሁን በኋላ በንግግር መለስ መጠበቅ የዋህነትም ሞኝነትም ነው። ወደድንም ጠላንም ምርጫው አንድ ብቻ ነው። እሱም እነሱ ወደ ፈለጉት የሃይል እርምጃ በመግባት ነፃነትን ማስመሰለስ!  ’የተበላሸን ዓሳን ከባሕር ማስወገዱ አንዱ መንገዱ ነው፡ ‘የባሕር ውሃ ማስወገድ!”……..ስለዚህ በሚከተለው መሰረት እርምጃችንን ሰናመነታ በያለንበትበሚከተተለው መሰረት እርምጃችንን እንድንጀምር………>>

ይህ ጥሪ ትግሬዎች “ዓሳን ለማስወገድ ባሕሩን ማድረቅ” ሲል የዘር ፍጅት ፈጽሞብናል ብለው ደርግ ሲከስሱት የነበረው የወያኔዎች ትክክለኛ ቅጂ ነው ዛሬ በእሳት የተነገረው ጥሪ።“ዓሳን ለማስወገድ ባሕሩን ማድረቅ”

የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ ከበደ የዘር ማጽዳት ጥሪ “ዓሳን ለማስወገድ ባሕሩን ማድረቅ” (video source Ethiopian Semay September 4/ 2016) ቪዲዮ ስታደምጡ እና እንደገና ዛሬ ድጋሜ የዘር ጭፍጨፋ በመላ ትግሬዎች ሲያውጅ አሜሪካኖች በባንዳው ዲያቆን ክብረት የተንጫጩትን በኢሳቱ ጋዜጠኛ ኢሳት መሳይ መኮንን ላይ ሲያወግዙ አላደመጥንም። ምንልባት እውጭ አገር ያለነው ትግሬዎች ዝምታን ስለመረጥን ወይስ ምንድነው ነገሩ? ይህንን ለመታገል ያገባናል የምትሉ መላ ኢትዮጵያዊያንም ሆናችሁ ትግሬዎችም (ወያኔዎችም ብትሆኑ) ይህንን በዘር ጥላቻ የሰከረ “የኢሳት ጋዜጠኛ” ወደ ሕግ ለማቅረብ የምንችልበት ዘዴ ካለ የሕግ ባለሞያዎችም ጭምር ካላችሁ እንድንነጋርበት ጥሪ አቀርባለሁ።

በኢትዮጵያዊነታችን ለአማራው ማሕበረስብ እየጮህን እንደኖርን ሁሉ እናንተ ትግሬዎች ያልሆናችሁ ወገኖቻችንም በንጸሃን ትግሬ ዘመዶቻችን ህይት የዘር ጥቃት ጥሪ ሲደረግ ይህ ነውር በማውገዝ “ዛሬ ድርሻችሁን ለመወጣት” “ሼር” በማድረግ እንድትተባበሩ የምትፈተኑበት ጥሪ ስለሆነ መልዕክቱን በማሰራጨት እንድትተባበሩ ጥሪ አቀርባለሁ። “ሼር” አድርጉት!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ   watch the video attached below.

(Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)