ባሕርዳር ውስጥ አንዳንድ ቤት አከራዮች
ትግሬዎችን በማሳሰር የነበራቸው ጸረ ትግሬ ሱታፌ የአማራ ሕዝብ እንዲያወግዛቸው መልዕክቴ እነሆ
ጌታቸው ረዳ
EDITOR ETHIOPIAN
SEMAY
2/11/2022
እንደምታውቁት እኔ በትግሬነቴ ለአማራ ሕዝብ ሰላም በመቆም በደሉን በምጽሐፍም
በሙግትም በቃለ መጠይቅም አዲስ አበባ ከሚታተሙ መጽሔቶች ጀምሮ ውጭ አገር ከነበሩት ጋዜጦችና መጽሄቶች ጽሑፎቼን ለሕዝብ በማስተላለፍና
በተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ኤምባሲዎች ስለ አማራ መጎዳትና ጉዳቱም እንዲቆም የበኩሌን አስተዋጻኦ ማድረጌንና
ሲያንቀላፋ ለነበረው አማራ ምሁርም እንቅልፉ አንዲባንን መድረጌና አሁን አማራ ላለው የአማራ መነቃቃት ደረጃ የኔ ድርሰሻ እንዳለው ታሪክ የዘገበው እውነታ ነው።
አማራ የተባለ ከፋኖ መሪ እስከ እስከ ያለው ምሁርና ጠቅላላ ወጣት እኔ ስለ አማራ መጎዳት ስጮህ ከግንቦት 7 እና ከወያኔ ጋር ወግኖ ጊዜው ሲያባክን የነበረ ነው። ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ የኔ ዘመዶች በአንዳንድ አማራዎች እየተጠቃ ሳይ እጅግ ይገርመኛል። ያም ሆኖ “ዛረስ” ከነዚህ ቂመኞች መማር አልቻልክም? ዘመዶችሁ ሲያሰቀይዋቸው ዛሬም ስለነሱ ወግነህ ትጮሃለህ፤ “ዕብድ ነህ’ ወይስ ምንድነህ”? እያሉ ብዙ ትግሬዎችና ወያኔዎች ይጽፉብኛል። ሁኔታው መራራ ቢሆንም ከትግሌ ግን አልተዛነፍኩም።
እርግጥ ነው፤ ለአማራ ሕዝብ በመቆሜም ትግሬዎች እኔን በጸረ ትግሬነት በጠላትነት ፈርጀውኛል።ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ። ቤተሰቤም አገሬም አንደሌሎቹ መጎብኘት አልቻልኩም። ለቀብርም አልደረስኩም። ዛሬም ሌላው ቁጥር 2 ወያኔ (ኦሮሙማው) ሥርዓቱን ተቆጣጥሮት እንኳን እኔን አገር ሊያስጎበኘኝ ቤተሰቦቼንም በሰላም ሊያኖራቸው አልቻለም። ያ ሁሉ ሳልበገር እስከ ትናንትናዋና እስካሁንዋ ድረስ ስለ አማራው ጉዳት መጪኼን አላቆምኩም።
ትግሬ ሁሉ ወደ “ማጎርያ በረት” መታጎር አለበት እያሉ ሳምናቸውና አብረውኝ ሲታገሉ የነበሩ የብዙ ዘመን ታጋዮችም ሳይቀሩ “የዘር ጭፍጨፋ አበራታቾች እና ግፋ በለው” ከሚሉት ጋር ዘመቻውን አበረታች ሆነው ሳያቸው የዘመኑ ብልሹነት ስመለክት “እጅግ ልቤ” ተሰበረ። ጊዜ ይለወጣል እያልኩ እታገላለሁ። አንዳንዴም ተስፋ እቆርጥና በቃኝ እላለሁ፤ ግፍ ስመለከት ደግሞ የሚታገለው ሰው ጥቂት ሆኖ ጸረ ኢትዮጵያ የሚያሾፈው ቡድን ሰፊ መድረክ አግኝቶ ሲያሾፍ ስመለከት አላስችል ብሎኝ በቃኝ ያልኩትን አጥፌ ልክ በማግስቱ እመለስና እታገላቸዋለሁ።
እንዲያም ሆኖ፤ “በጸረትግሬውና ጸረ አማራ የተቃኘው በሽተኛው “አብይ አሕመድ” እየተመራ በእነ ኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን (ኢትዮጵያዊው “ካቡጋ”) “ትግሬ ሁሉ ይጥፋ በግፋ በለው!” ዘመቻ ሲካሄድ ስሜቴን ተቆጣጥሬ በቀጣይነት ለአማራ እንደቆምኩት ሁሉ በትግሬነቴ ቤተሰቦቼ ላይ እየደረሰ የዘር ጥቃት ለመከላከልና ለማጋለጥ “የቤተሰብ፤ የታሪክና የሞራል ግዴታና ሐላፊነት አለብኝ።
ኢትዮጵያዊያን ነን ብለው በስራ ምክንያት ተዛውረው በዜግነታቸው ተማምነው በሰላም ሲኖሩባት በነበረቺው የባሕርዳር ከተማ ውስጥ ቤተሰቦቼ ላይ ዘግናኝ የሆነ ግፍ ደርሷል። ታስረው ተደብድበው የዘር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እንደገለጽኩላችሁ ይታወሳል።
እነሆ መላው የትግራይ ተወላጆች ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተናጠልና በጋራ ባጋለጥነው “የኦሮሙማ እና የአማሩማ-ኢንተርሃሙዌ” ጸረ ትግሬ የጥምር ዘመቻ አንዳንዱ ከአመት አንዳንዱ ከ3 ወር አሰቃቂ እስር እና ድብደባ በሗላ ከባሕርዳር “የኮንስንትሬሽን” (ማጎርያ በረት) ተለቅቀዋል።
2500 በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ባንድ ማጎርያ ቦታ ውስጥ ተሰብስበው ያለ ምንም የወንጀል ሱታፌና የፖሊስ መጥሪያ ወይንም የፍርድ ቤት ቀነ ቀጠሮ ከ12 አመት ጀምሮ እስከ 85 አመት ዕድሜ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ትግሬ “በመሆናቸው ብቻ” አብይ አሕመድ ባወጀው አዋጅ “እንደከብት” ከየመንገዱና ከሚኖሩባቸው መኖሪያቤቶቻቸው እየታፈሱ ወደ “ማጎርያ በረት” ታስረው እንዲራቡ፤ በበሽታ እንዲሰቃዩ፤ በምርምራ እንዲደበደቡ ከመደረጉም በላይ፤ሆን ተብሎ ትግሬ ያልሆኑ በአእምሮ ሕመም የተሰቃዩ “በርካታ ዕብዶችን” ወደ ማጎርያ ቤቱ በመቀላቀል በታሳሪዎች ላይ የሕሊና እና የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል። ይህ አደገኛ የዘር ማጥፋት ተግባር አብይ አሕመድና ደጋፊዎቹ ሓላፊነት ይወስዳሉ።
ጊዜና ሥልጣን ተጠቅመው ድርጊቱ እንዲፈጸም ያወጁ ከኦሮሙማው ጠ/ሚ ጀምሮ በየእርከኑ ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የመንግሥት ሓላፊዎች እየፈጸሙ ያሉት እየገረመን፤ ከዚህ ቡድን ጋር በመቀናጀት “በጋራ” (በኢንተርሃሙዌ መልክ) ተደራጅተው ለዘር ማጽዳት ዘመቻው የተባባሩ ባሕርዳር ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ቤት አከራዮች እጃቸው እንዳለበት ስሰማ እጀግ ነበር ያዘንኩት።
አማራዎች ከኦሮሞ እና ጉምዝ አካባቢ በጅምላ እየተገደሉ እና እየተፈናቀሉ ሲባረሩ፤ ባሕርዳር ከተማ የሚኖሩ “አንዳንድ” ቤት አከራይ “አማራዎች” በትግሬዎች ላይ አዋጁን በማስፈጸም ተባብረዋል።
ሌሎቹ ዘመዶቼ ለወደፊቱ በአከራይዎቻቸው ምን እንደሚደርስባቸው ባላውቅም ከነዚያ ውስጥ የኔ እህት በአከራይዎችዋ ሁለት ጊዜ የዘር መድልዎና ጥቃት ደርሶባታል።
ቤቴ ሳላውቅ ለትግሬ አከራይቻለሁ ይኼው እሰርዋት ብሎ ያሳሰራት አከረዩ ሲሆን፤ ዋናዋ ተከራይዋ እህቴ የ10 አመት ህጻን ልጅ ስላላት አብራ ስትኖር የነበሪቺው ዘመዳችን እርስዋም ገና “ቲን” ስለሆነች አከራዩ እስዋንም ለማሳሰር ጠቁሞ “ጎስታፖዎቹ” ለማሰር ሲመጡ ሀጻንዋን ይዛ ከሰው ቤት ተሸሽጋ ስትኖር ከመታሰር ድናለች።
ታስረው ከትናንት በስቲያ ሲፈቱ ይህ “በጥላቻ የሰከረ” አከራይ “ቤቴ ለትግሬ አላከራይም” ቤቴ ስለምፈልገው ለቅቃችሁ ውጡ በማለት ህጻናት ልጆች ይዛ የምትወድቅበት ቦታ በማፈላለግ ላይ ነች።ትግራይ እንዳይሄዱም መሄድም የማይቻል ነው። ይህ እንዳይበቃ ሥራቸው በሌሎች ሰዎች እንደተያዘ ተነገሯቸዋል።
ይህ የበደል በደል፤ የኢንተርሃሙዌው ሥርዓት ያለ ወንጀል ወንጀል እንደፈጸሙ ተደርገው ድብደባና እስር ደርሶባቸው ከእስር የተፈቱ ሰዎች አከራዮች በጥላቻ በቀል ተነሳስተው ንጹሃንን ተጨማሪ የዘር ጥቃት (ዲስክሪሚነሽን) ቢደርስባቸውም ይደግፈዋል እንጂ አይከፋወም።
በዚህ አጋጣሚ ባሕርዳር ያለችሁ የቴ/ቪዥን፤የራዲዮ/የፌስቡክ መላ “የአማራ ሚዲያዎች” በዚህ ጉዳይ አንድ ፕሮግራም በመስራት የህ በደል እንዲቆም እንድታደርጉና በሚዲያ ተሰራጭቶ የባሕርዳር ባለሃብቶች እና አነስተኛ ቤት አከራይ ባለቤቶች እንዲያደምጡት ቢደረግ “እንዳልታወቀ” መስሎአቸው ብቀላቸው እንዳይቀጥሉ ስለሚረዳ በዚህ ትብብር እንድታደርጉ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። በዚህ ላይ ጥሩ ስራ መስራት ይችላል የምለው አንዱ “አበበ በላው” እና አንዳንድ ሚዲያዎች ይህንን መልእክት እዛው ባሕረዳር ላሉ አማራ ሚዲያዎች ብታስተላልፉት ለአማራ እንደቆምኩት ሁሉ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ትግሬ ዘመዶቻችሁም እንደቆማችሁ ጥሩ አጋጣሚ ማሳያም ይሆናል።
ሌላው አደራየን የማስተላልፈው፤--
እኔ ስለ እናንተ ወገኖች እንደጮህኩት ሁሉ እናንተ ባሕርዳር ያለችህ እኔን
የምታውቁ ወገኖች ለባሕርዳር ወጣቶችና ፋኖ መሪዎች ይህንን መልዕክት እንድታስተላልፉ እና ቤት አከራዮች “በዘር መጠቃቃቱ” እንዲያቆሙ
፤ ካልቆመ ግን የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉንም እንደሚለበልበው እያየነውም ቢሆን ፤ ይህ መንግሥት በሚያውጀው የዘር ማጥቃት ዘመቻ የሚተባበሩት
አከራዮች ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ሕዝቡን እንድታስተምሩ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
EDITOR ETHIOPIAN SEMAY