Wednesday, October 12, 2022

እባቦቹ የሚተፉት ምራቅ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay 10/13/22)


እባቦቹ የሚተፉት ምራቅ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay

10/13/22)

የትግሬዎች ትግል ለብዙ አማታት እንደታገልኩት ኢትዮጵያዊነት የራቀው ጸረ አማራ መነሻ ያደረገ ፤ አማራን እንደ ማሕበረሰብ ለማጥፋትና እረፍት እና ሰላም ለመንሳት መነሳቱን ሳይሸሽግ ፤ሳይሰጋ በግሃድ የትግል ዋነኛው መነሻ እንደሆነ በበርካታ ማኒፌሰቶች፤ ጽሑፎች፤ ዘፈኖች፤ ግጥሞች እና በጦርነት ባሳየው የወረራ እና የጭፍጨፋ ማሕደሮቹ ግልጽ አድርጎ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ እየተጓዘ ነው።

ይህ ስንከራከርበት የነበረው ሃቅ በርካታ አማራዎች ተመልሰው እኛኑን መድረክ በመንፈግና አልፎም አማራውና ትግሬውን ማሕበረሰብ ለማጣላት ነው እያሉ ሲሰዘልፉን ኖረዋል።

ከስንት ትግል በኋላ እያንዳንዳቸው ቤትና ጎረቤት ማንኳኳት ሲጀምር የተከራከርነው እውነት ሆኖ የኛን ክርክር አምነው የነቁ አሉ። በንቃታቸው ቁጥር ግን ትግሉን አልገፉበትም። ይልቁኑ የማይረባ የስድብ መመላለስ ውስጥ ገብተው ትግሉን እያበላሹት ነው።  የሆኖ ሆኖ ዛሬ ለየት ያለ ሁለተኛው ምዕራፍ የያዘ ቪዲዮ  አቀርብላችሗለሁ።

 ቁጥር አንድ “አማራውን በናትህ በቃኝ፤በቃኝ፤ማረኝ አሰኘው !!!” እያሉ የሚዘፍኑት የጦር ሜዳ ዘፈናቸውን ባለፈው ወር ለጥፌ ተነጋግረንበታል።

በዚህ በለጠፍኩት ሁለተኛው ክፍል ቪዲዮ ደግሞ ዛሬም እነ ቴድሮስ ፀጋዬ (ርዕዮት ሚዲያ) ፤እነ አብርሃ በላይ (ኢትዮ ሚዲያ) እና ብዙ በርካታ የትግራይ አክራሪ ብሔረተኞች የሚደግፉት TDF (ቲ ዲ ኤፍ) ተብሎ የሚጠራ የወያኔ የፋሺስት ተዋጊ ሃይል ቀደምት ወላጆቼ የሚላቸው ወላጆቹ “አማራን እንዲጠላ” ባስተማሩት መሠረት ማሃለውን ጠብቆ ይሄው በግሃድ  ዓለም ሙሉ እንዲያደምጣቸው ቀርጸው በየፌስቡኩ እየተለጠፈ  ያለምንም ሓፍረትና ይሉኝታ እንድንመለከተው እየተሰራጨ ነው።

በዚህ ቪዲዮ የሚተላለፈው መልእክት ቀደም ብሎ በ17 አመት የትግራይ ፋሺሰቶቹ ትግል ዘመን ሲዘፈን የነበረ መላውን የትግራይ ሕዝብ በጸረ አማራነት እንዲሰለፍ ካደረጉት ዘፈኖች አንዱ ነው።

 ይህ የትግራይ “ኡር ፋሺዝም” ከጥንታዊ የባህል የካልት እምነት ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ፋሺዝም የተሸጋጋረ “ወልቃይት” መሬት ውስጥ በ21ኛው ክ/ዘመን በርካታ “የኦሽዊትዝን” ካምፖችን የመሰረተ እጅግ አደገኛ ፋሺስት ዛሬ ደግሞ ያ አልበቃ ብሎት  “በትግራይ መከላከል ስም” ያሰለጠናቸው የትግራይ ፋሺሰት የጥላቻ ጦረኞች “ያ ሞኝ አማራ እያባረርክ ፍጀው“ እያሉ ህጻኑን ሽማግሌውንም መነኮሳትንም ቄሱም ሁሉም እንዲጨፈጨፍ በዘፈን እና በአዋጅ ከበሮ እየደለቁ ጸረ አማራነታቸውን የትግል መሳሪያቸው እንደሆነ ዛሬም ቀጥለውበታል። አማራው ይህንን እየሰማም ምንም ሳይሰማው “እስክስታና መሽሞንሞን እስፖርትና ፕራንክ” እቃ እቃ እየተጫወተ እራሱ ወያኔና አብይ አሕመድ ወዳዘጋጁለት “የኦሽዊትዝን” የመግደያ ካምፖች በረድፍ ተሰልፎ ያለ ማንገራገር እየተጓዘ ነው።

<<ቲ ዲ ኤፍ>>/ TDF/ እያለ ራሱን የሰየመ የናዚ ቡቃያ “አያታትና>> (ታላላቆቻችን) ከሚላቸው ፋሺሰቶች ያገኘው የጥላቻ ትምህርት በበለጠ በባሰ አቀራረብ እየተቃኘ ውጭ አገር ያሉት ከላይ የጠቀሱኩዋቸው የፋሺቶች ጠበል የተረጨባቸው የትግራይ አክራሪ ብሔረተኞች ልሂቃን አሁንም በዙሪያችን ሆነው ይህንኑ ቡቃያቸው እንዲያድግላቸው በመኮትኮት ላይ ናቸው።

በመጨረሻም

በቪዲዮው የምትሰሙት ዘፈን ትርጉም ካሁን በፊት በጻፍኩዋቸው መጽሐፍቶቼ ውስጥ ያሉት ጸረ አማራ የወያኔ ዘፈኖችና ግጥሞች ላስደምጣችሁና ቪዲዮውን ተመልከቱት።

በለጠፍኩት ቪዲዮ የምትሰሙት ፤ በትግራይ ሬዲዮ radio ለሕዝብ የሚተላለፈው የጥላቻ ትምህርት ነው::

ትግርኛው ግጥም

<<“ጎበዝ ተዓወት ተጋዳለይ ትግራይ

 አርኪብካ በሎ ነዚ ዓሻ አምሓራይ “>>

አማርኛው ትርጉም፡

<<ጎበዙ የትግራይ ታጋይ ሆይ

ድሉ ያንተ ይሁን  እያባረርክ በለው ያንን ሞኝ አማሃራ (ይ)>>

(ምንጭ ጌታቸው ረዳ ፤ ዘፈኑን ከዘፈነው የታወቀው

ሙዚቀኛ  ወያኔ አብይ ዓዲ/ተምቤን/ ውስጥ ወያኔ መኝታው ክፍል ገብታ የገደለቺው ገብረጻድቅ ወ/ዮሐንስ ከራሱ አንደበት የነገረኝ (የሙዚቃው ቡድን ተምቤን ሄዶ በነበረበት ወቅት በተዘጋጀላቸው ማረፊያ ሆቴል መኝታ ክፍሉ ውስጥ በውስጥ አርበኞች ትብብር ገብታ የገደለቺው ዘፋኝ ገብረጽዲቅ እንደነገረኝ <<ነዚ መድሓርሓራይ>>---<< ለዚያ አድሃሪ>>- የሚለው ቃል ከጊዜ በኋላ ኦሪጅናል ግጥሙ ተለውጦ ፤ “ነዚ ዓሻ አምሓራይ” <<ለዚያ ሞኝ አማራ”>>  ወደ እሚል መለወጡን ዘፋኙ መቀሌ ውስጥ በራሱ አንደበት ነግሮኛል ። ድርሰቱ የራሱ ይሁን አይሁን አልጠየቅኩትም። ወደ ወያኔ ከመቀላቀሉ በፊት ድሮ ስለምንተዋወቅ በውይይታችን ወቅት ይህንን የጥላቻ ግጥም እንዴት ሊለቀው እንደቻለ ጠይቄው የነገረኝን ታሪክ። ምንጭ - (የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? ደራሲ እኔው ጌታቸው ረዳ (ገጽ 431)

እንዲሁም”-

<<ይኽድ ንዓዱ>>

<<ወደ አገሩ ይሂድ>>

<<ሓቢርና ንሕሰብ ብዛዕባ ናብራና

ሎሚስ ይአኽለና ግዝኣት ናይ አምሓራ>>

<< ባንድነት እናስብ ስለኑሮአችን፤

ዛሬስ ይበቃናል የአማራ አገዛዝ >>

<< ናዓ ወሽ በሉዎ እዚ አድጊ አምሓራይ!!>>

<< ዎሽ በሉት! ወዲያ ሂድ በሉት ይኽ እህያ አማራ””

ምንጭ አስገደ ገብረስላሴ (ትግርኛ ቁ 2፤ጋህዲ ለካቲት 2001ዓ.ም) ትርጉም (ጌታቸው ረዳ - የወያኔ ገበና መህደር) (179)

በቪዲዮው ማሳረጊያ እንደምትሰሙት ታጋዮቹ <<“እኛ ላገራችን አማራ ለሆዱ”>> በማለት እያሾፉ ደምድመውታል። ከዚህ ሌላ በምን እናንቃችሁ?

Ethiopian Semay TPLF vowing to eliminate what it calls the Amhara the foolish Amhara

 

https://youtu.be/0nsN9c_rrTk

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)