Saturday, June 13, 2020

ሳሞራ! ሳሞራ! ወደ አብይ መጣ! ትግራይ ውስጥ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ተነሳ! ቃለአጋኖዊ ጊዜኣዊ የስቃይ መስታገሻ! Saturday, June 12, 2020 ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay - ኢትዮ ሰማይ)ሳሞራ! ሳሞራ! ወደ አብይ መጣ! ትግራይ ውስጥ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ተነሳ! ቃለአጋኖዊ ጊዜኣዊ የስቃይ መስታገሻ!
Saturday, June 12, 2020
ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay - ኢትዮ ሰማይ)

እንደምን ሰነበታችሁ?  በኢትዮጵያዊያን ጀሮ ገብተው ሲያስደልቁ የሰነበቱት የዚህ ወር ሁለት ትኩስ ዜናዎች (1) የወያኔው ወታደራዊ አዛዥመሓመድ የኑስ” (ሳሞራ) ወደ አዲስ አበባ መምጠቱና ከፋሺሰቱ ኦሮሙማው መሪአብዮት መሐመድ” (አብይ) በመልካም ወዳጅነት ስለመገናኘቱ (2) ለኤርትራውያን ዘመዶቹ ወግኖ ምፅዋ ወደብና ሳሕል በረሃዎች ድረስ በመሄድ የወያኔ ተዋጊ ሃይሎችን ለውግያ በማሰማራት በሺዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ወታደሮችና ሰለማዊ ዜጎቻችንን የጨፈጨፈና ያስፈጀ፤ የተማረኩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት ለስቃይ የዳረጋቸው፡ ከጠላት ጋር የተባበረ፤ አረመኔው ጸረ አማራው በሟቹሓዲሽ ኣርአያ” (ሓየሎም አርአያ ) ስም የተሰየመፈንቅልየተባለ (አክራሪ የትግራይ ብሔተኛነትን አውቀውም ሳያውቁትም በኩራት የለበሱት መጠሪያፌስ ቡክ ላይ እየጨፈሩ ሲያስጨፍሯችሁ የሰነበቱትየተለያዩ የቃለ አጋ” (Exclamation) ቡድኖችትግራይ ውስጥ ድንገት ፈነዳ የተባለለትን መሬት አርዕድ ተቃዉሞእንዳጋጋልዋችሁ ታዝቤአለሁ።

በፈጠራቪዲዮውም በፎቶውምእየተደገፈ የስንቶቻችሁ ጀሮ እንደበጠበጠ ባላውቅም ከሚገባው በላይ ተለጥጦ ወያኔ አለቀላት እስከሚባል ድረስ ከተቃዋሚ የዜና ማሰራጫዎች እስከ የአብይ አሕመድኦሮሙማው እና መሰል ማሕበራዊ መገናኛ ድረገጾች ምራቃችሁ እስኪንጠበጠብ ድረስ ሲያስግቱዋችሁ ሰንበተዋል።
እነዚህ ሁለት ዜናዎች የሳምንቱ ዋና ርዕስ ሆነው ቆይተዋል።

ፈንቅል የተባለው የአብይ አሕመድ ደጋፊዎች የሚወራጩበት የቃለ አጋኖው ቡድን ዋና መዘውሩ ውጭ አገር ሲሆን፡ ትግራይ ውስጥ ተነሳ የተባለውመሬት አርዕድየተባለለት አብዮት፤ ካሁን በፊት የአማራ እና የኦሮሞ ቄሬዎች በዓለም ፊት በድምፅ ማጉልያ ይዘውወያኔይውደም የሚልመፈክርሳይሆን ለበርካታ አመታት የቆዩ የአስተዳደር ጥያቄዎችን የሚመለከት ነበር። እናነተ ጸረ ወያኔ ነው ማለት መብታችሁ ነው። ለመጃጃል ዲሞክራሲም ተዋናይ ነው።

ይህ ቃለ አጋኖ፤ እኔ የምለው ሳይሆን አዲስ አባባ ውስጥየዚህ እንቅስቃሴአማራር አባል የሆነ ከአጋር ወገኑ የቲ-- ተጠሪ ግለሰብ ጋር በቲ/ ለውይይት ተጋብዘው ስለ ጉዳዩ ሲያብራራ እንዲህ ነበር ያለው፡-

የሕዝቡ ጥያቄ በጣም ቀላል ነው። በቀላሉ የሚፈቱ እነዚህ ጥያቄዎች ወዲያውኑ መፈታት ሲገባቸው እየተጓተተ መዘግየቱ እንጂ በቀላሉ መፈታት የሚቻሉ ቀላል ጥያቄዎች ነበሩነበር ያለው።

የዜና ማሰራጫዎች ሲገልጹት ግን በተለይእኔ የምወደውኢትዮ 360 የተባለው ሚዲያ እነ ኤርሚያስ ለገሰና ሃብታሙ አያሌው እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ሁኔታው ሲገመግሙድሮም የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ አንድ አይደሉም ስንል ብዙ የተሰደብንበት አቋማችን ነው፤ ይኼው ዛሬ ማስረጃችን ይህ ነውእያሉ አጉል የቦተለኩበት መናኛ አቋማቸው አስደምጠውናል። በዚህ ወደ ሗላ እመለስበታለሁ።

አሁን ወደ ሳሞራ የኑስ ወደ አብይ መምጣት ጉዳይ እንመልከት።

በወያኔ ትግራይ ፖሊሲ ተቀርጾ በልኩ ተሰፍቶ እንዲለብሰው የተሰጠው የወያኔ ጨርቅ ለባሹአብይ አሕመድለቀድሞ አለቃው ሳሞራ የኑስን ከትግራይ አስጠርቶ በማይታወቅ ጉዳይ እንዲያማክረው ወደ አዲስ አባባ እንደመጣ እራሱ ሳሞራ ተናግሯል። ለምን እንደጋበዘው እስካሁን ድረስ ግልጽ ባይሆንም፤ በዜና ተንታኞች እንዳሉት ከሆነስለ ግብፅ እና አባይ ግድብእንደሆነ ይገልጻሉ።

እዚህ ላይ ብዙ ሰዎች ሲገረሙ አድመጬአለሁ። አብይን ሳሞራን በመጋበዙ ሲያደንቁት አደምጬአለሁ። ሁለት ነገሮችን እንመለክት ስለ ተባለው ግድብ እና የጸጥታ ጉዳይ ከሆነ፤ ሳሞራ ግብዣውን ለምን እንደተቀበለ ሊገርማችሁ አይገባም። ሁለት ነገሮች አሉ፡

አባይ ግድብ ሲመሰረት የአብይ አሕመድ ምላስ አስታውሱ። ምን ድነው ያለው? “ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ነበር የገነባውሲል አብይ ገና ወደ ሥልጣን ሲመጣ መናገሩን ታስታውሳላችሁ። ያንን የለመድነው እስስታዊ ምላሱን እራሱ ቀርጥሞ የግድቡ ተቆርቋሪ ሆኖ ቀረበ። ሳሞራን ያማከረበት ምከንያት አንደኛው ምክንያት፤ አባይ ግድብ የተመሰረተው በወያኔዎች ነው፡(በመለስ ዜናዊ) ወያኔዎች ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይልቅ ያንን ግድብ ለማስቀጥለና ለማስፈጸም የማይተኙበት ምክንያት በመሪያቸው በመለስ ዜናዊ ስለተጠነሰሰ ነው። አባይ ግድብ ሲነሳ የወያኔን ስም አብሮ ከግድቡ ጋር የተያያዘ ነው። ስለሆነም ሳሞራ ፈቃደኛነቱን ገለጸለት። የሚገርም አይደለም።

ሁለተኛው ምክንያት አብይ እና ሳሞራ የሚጣሉበት ምክንያት የለም።

የሚከተሉትም የሚያራምዱትምፋሺስታዊ አክራሪ ብሔረተኛነት ነው ስለዚህም አይጣሉም። የሚጣሉበት ወቅትአብይ እስካልነካቸው ድረስ ብቻ ነው” (ቀይ መስመራቸውን ካላለፈ!!!)።እስከዛሬ ድረስ ብዙዎቹ ወያኔዎችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው አልተነኩም (ስልጣን ላይ አሉ፤ ደሞዝም ይከፈላቸዋል) የሚሰጣቸው ባጀትበጉቦ እና ቁጣን ለማስታገሻመልክ ከአማራ ሕዝብ በላይ ከጋምቤላ ከሶማሊ ከወዘተ.. በላይ ለትግሬዎች አዳልቶ አለቆቹና ወዳጆቹ ለሆኑት የወያኔ ትግራይ መሪዎች ለሚያስተዳድሩት ለትግራይክልልለልማት ዘርፍ ከፍተኛ ሥራ ማስኬጃ እንደመደበላቸው አብይ እራሱ ኢፍትሃዊነቱን ሳያስበው ኑዛዜውን በፓርላማው ሳያፍር፤ሳይደብቅ አድላዊ መሆኑን ነግሮናል። (ትግሬዎች ድሮም ዛሬም ተጠቃሚዎች ናቸው የምንለው ለዚህ ነው)

በርዕዮተ ሓሳብም አንድ ናቸው። ሁለቱም ብልጽግናም ወያኔም አክራሪ ብሔረተኞች እና በአክራሪ ብሔረተኛነት የተቃኘው ፋሺስታዊው ሕገመንግሥት ተንከባካቢዎችና አስቀጣይ ናቸው። ስለዚህ ሳሞራ አብይ ጋር ወዳጅነት አለው፤ ወይንምአብይ ላይ መፈንቅለ መንግሥት እንዳካሂድ ተጠይቄ አላካሂድም አልኩኝአለ እየታበለ በአድናቆት እየተሞካሸ በዜና ማሰራጫዎች በተለይአለምነህ ዋሴየተባለው በዘሓበሻ ሚዲያ በጎረናው ድምጹ የቀረበው ቃለ አጋኖ ብታደምጡትእንዴት እያሳመረ በድምጽ ቅላጼ እንዳቀረበውስታደምጡ መስማት እጅግ የሚያሳምም፤በኢትዮጵያ ሉኣለዊነት እና ኢትዮጵያውን ነብስ የተጫወቱ የወያኔ አራዊቶችን ሰብኣዊ ባሕሪ ለማልበስየሚደረገው የዜና ማሰራጫዎች ትያትራዊ ቃለ አጋኖነት እጅግ ይገርማል። የእኛን (ኢትዮጵያን ያጠቁ/ያንበረከኩ/ለውርደት የዳረጉ/ወደባችንን የዘጉብን) ተሎ የመርሳት አባዜ ስንት ግዜ እየተጠቃን እንደምንኖር ለኔ ግራ ገብቶኛል።

አሁን መቸ ነው ሳሞራ (ወያኔዎች) እና አብይ የሚጣሉት? የሚል ጥያቄ ብታቀርቡ መልሱአብይ ወያኔን እንደናዚ ድርጅት ፈርጆ ከፖለቲካው ተሳትፎነትና ለሰሩት ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድግ ሲሞክር” (አያደርገውም ግን እንዲጥማችሁ ብየ ነው) ያኔ የአብይ አሕመድ መጨረሻ ይሆናል። ያንን ለማድረግ ወያኔዎች ወደ ደደቢት መሄድ አያስፈልጋቸውም! አብይን በደቂቃ ከብበው ማሰር የሚችሉ የወያኔ ታጋይ ወታደሮች ትጥቃቸውም ልብሳቸውም፤ የማዘዣ (የኮማንድ) ቀዳሚ መምርያዎች ሳይነጠቁ ከነማዕረጋቸው በወታደራዊ ስብሰባዎች የምታይዋቸው መኮንኖችና ወታደሮች ዛሬም የወያኔ ታጋዮች ናቸው። ለመለስ ዜናዊ ተንሰቅስቀው ከነመለዮቻቸውና ማዕረጎቻቸው አለም እያየ በቀብሩ ሰርዓትመሬት ላይ እየተንከባለሉ ያለቀሱወታደሮች ዛሬም አብይን እየወደዱት እንዳይመስላችሁ። የወያኔ ትግሬ ታጋዮች ተንኮል ማወቅ ብዙ መንገድና አመት ይጠይቃል።ወያኔነት ሃይማኖት ነው!! እንኳን ለትግሬዎችአባ ዱላ ገመዳእንዳለው ከኦነግ ይልቅ ወያኔዎች ለኦሮሞ ይቀርቡታልብሏል።

ስለዚህም አብይ አሕመድም ሆነ አማራን እንወክላለን የሚሉት 26 አመት ለትግሬዎች ያደሩዛሬም 2 አመት ደግሞለኦሮሞዎቹ በሎሌነት ያደሩት አማራ ነን የሚሉ (ብኣዴንም) ሆነ ወያኔዎችውስጣቸውን ደፍረው ማየት የሚያስችል ሓሞት ስለሌላቸው ሊለወጡ አይችሉም።፡አርከበ. ዕቁባይ .ወዘተ..እያላችሁ ቁጠሩ አብይ ጉያ ውስጥ ገብተው ወሬና እስትራተጂ የሚቀርጹ ሁሉም የተመደቡ የወያኔ ሰላዮች ናቸው። ወየኔን ለማታውቁ ሰዎች ይገርማችሁ ይሆናል።
ወያኔዎች በባህሪ ሊለወጡ ስለማይችሉመሸኘትከመጣ የሚለያቸው ሁኔታ ካለወያኔም፤አብይምአብረው ይሞታሉ። ሥብሓት ነጋ- “የኢሕአዴግ የቁልቁለት ጉዞበሚል የወያኔ አምላኪ የነበረው ባለሹመት ብርሃነ ፅጋብየተባለ በጻፈው መጽሐፉ እንዲህ ይላል።

ስብሓት ባንድ ስብሰባ ውስጥ እንዲህ አለ ይላል፡

ህወሓትምሆነኢሕአዴግእንደገና መፈጠር አለባቸው። ሕዝቡ በሚገባ አውቆናል። ሕዝቡ እያለን ያለውበዚህ ተሃድሶ ስብሰባቸውም ቢሆን ራሳቸውን ማየት ድፍረት ስለሌላቸው፤ ተቻችለውና የስቃይ መድሃኒት ውጠው ማቆያ አድርገውት ሊወጡ ይችላሉ፤ እያለን ይገኛል። እራሳቸው የምር ማየት ከጀመሩ እራሳቸው ይሞታሉ፤ እራሳቸውን ይገድላሉ እያለን ይገኛል።ሲል ስብሓት ይናገራል።

ደብረጽዮን እኮ አብይን ተአምራዊ ከሰማይ የመጣ ሙሴ አድርጎ ነበር ሲያሞግሰው የነበረው? የተለቀቀው ቪዲዮውን አድምጣችሗል አደለም? ወያኔዎች እስስቶች ናቸው፡ መያዣ የላቸውም። ስብሓትም ሆነ ሌሎቹ ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና መፈጠር እንዳለባቸው በተሃድሶ ስብሰባቸው ላይ ቢያሳስቡም እውን ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና ራሱን ፈጥሮ መሻሻል የሚያስችል ቁመናም ሆነ ድፍረቱ አለው ወይ? የሚለው መልስ ማግኘት ቀላል ነው። ሁሉም የወያኔ መሪዎች ለውጥ ያስፈልጋል ይበሉ እንጂ ራሳቸውን ማየት ከጀመሩ እራሳቸው እንደሚያከስሙ ስለሚያውቁ፤ ይኼው አብይ አሕመድ እራሱ መቀየር የማይችል ማስረጃ ነው።
አብይ እራሴን እቀይራለሁ ብሎ ቢነሳምእራሱን ማየት ሲጀምር አስፈሪ ሕዝባዊው ጥያቄ ከፊት ድቅን ሲልበትየሕገመንግሥቱ ጠበቃና አሞጋሽሆኖ በግልጽ በመናገርበስንት ታጋይ ደም የመጣ ሕገመንግሥታችንእያለ ባለፈው ሰሞንየወያኔና የኦነግ የፋሺቶች ሕገ መንግሥትንጥብቅና ቆሜ እሞታለሁ ሲል ፓርላማው ተቀምጦ ሲለፈልፍ መኖሩን ታስታውሳላችሁ።

ይህ የሚነገረን ነገር፤ ፋሺሰቶች በዲሞክራሲ የማጃጃያ ዘዴ የሚያታልሉ፤ እራሳቸውን መለወጥ እንደማይቸሉ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ሳሞራ መጣ፤ ወዲ ወረደ (ታደሰ ወረደ) አብይ ጋር አብረውምሳ በሉወዘተ…. ለቃለ አጋኖዊ ቡድኖች ግን እርካታ ነው።

አሁን የትግራይ እና የወያኔ ድርጅት አንድ ነው አይደሉም ክርክር፤ በሚቀጥለው በሰፊው ባቀርብ ለዛሬ ግን እነዚህን ጥያቄዎች ላቅርብላችሁ_ እነሆ፤-

ወያኔ እና ህወሓት አንድ ነበሩ? አንድ ከነበሩስ መቸ አመተምሕረት ተለያዩ? የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ሲከተል የፈቀደበት (አስገዳጅነት ከሚለው ሌላው ምክንያት) የተቀበለው ምን ነበር? የድርጅቱ መነሻ ጥያቄ ምን ነበር? የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ዲሞክራሲ ነበር? ዛሬም ዲሞክራሲ ነው ለምትሉ ሰዎችዛሬም ትግሬዎችበጎሳ ፌዴራሊዝምያምናሉ፤ይቀበላሉ። አይደለም እንዴ? ታዲያእውን ፌደራሊዝም፤ በዲሞክራሲ ያምናል? የትግራይ ሕዝብ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምን ያምናል ወይስ አያምንም? አዎ የምንል ከሆነ፤ የማንን ርዕዮት እየተከተለ ነው ልንል ነው? የወያኔ!! አይደለም እንዴ? በቋንቋ መተዳደር ያመጡት ጣሊያኖች ናቸው- ታዲያ ትግሬዎችና ወያኔ አንድ ካልሆኑ ወያኔ ጣሊያንን የሚያመልክ ወያኔ ያስተማራቸውን በቋንቋ የመስተዳደር ትግሬዎች ለምን ዛሬም አፓርታይዱን ተቀብለውት እስከመጨረሻ እንታገልለታለን ይላሉ?

ይህንን ልጨምርላችሁ___-

አጅግ አምርሮ ኢትዮጵያዊነት የሚጠላ የትግራይ አዲስ ትውልድ ተፈጠሯል ወይስ አልተፈጠረም? ብዛቱስ ስንት ይሆናል? ወያኔ ኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እያወረደ የወያኔ ባንዴራ እንዲይዙ ሲደረጉ ዛሬም ያንን ተቀብለው በዓለም ፊት ይታያሉ፤ በየገጠሩ በክብር ተውለብልቦ በሙዚቃ ስትታጀብ ይታያል፡ ታዲያ ትግሬዎች እና ወያኔዎች አንድ አይደሉም? 42 አመት ሙሉ የትግራይ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ ቆይቷል ለምትሉ ከዶ/አሰፋ ነጋሽ የቀረበላችሁ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡

1967 . ወያኔዎች የካቲት ወደ ደደቢት በረሃ ከሄዱበት ጀምሮ የተወለደ ትውልድ ስንመለከት በአማካኙ 1- 12 አመት ዕድሜ ጀምሮ ያላቸውን ህጻናት በወቅቱ የነበሩትን ስንመለከት ጸረ ኢትዮጵያነት እና ጸረ አማራነትን (ጎቦታት ትግራይ መቓብር አምሓራይ! (የትግሬ ተራሮች የአማራ መቀበሪያዎች) እያሉኣምሓራይ ፤አድጊ፤ ዑዎሽ በሎ እዚ ኣምሓራይ) በሚል ጥላቻ እየተመረዘ ካስተማራቸው ከዚያ አመት ማለትም ዕድሜአቸው 12 ጀምረው የነበሩ ታጋዮችም ሆኑ ሰላማዊ የትግራይ ህጻናት ወጣቶች ዛሬ ዕድሜአቸው 46 ሲሆን በጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአማካኝ 92% (ዘጠና ሁለት ከሞቶ) ዕድሜአቸው 52 እስከ 56 ዕድሜ በታች ሆኖአቸዋል ማለት ነው (ትግራይን የሚጨምር ማለት ነው) ይህ 92% በወያኔ አስተሳሰብተላቅጦ፤ተቦክቶ የተፈጠረ ትውልድ ነው ባጭሩ ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አማራ አመለካካት ተሸካሚ ነው። አሁን ጥያቄው፤ ባንዴ ሊፈወስ የቻለ ከወያኔ እሴቶች/በረከቶች/አስተሳቦች/ ጋር እንዴት ተላቀቀ የሚል ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?

ስለዚህ በዚህ ሃይል ድጋፍ ነው ወያኔ ይወድቃል ስንባል የነበርነው። ደርግን የሚያክል ስርዓት ታግሎ ከጣለ፤ ዛሬ ከወያኔ እራሱን ማውጣት ለምን አልቻለም?
ካናዳ ውስጥ ኗሪ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ ባለሞያ የሆነው ተክሌ የተባለው (ኢሳት ውስጥ እንደ ጋዜጠኛ ሆኖ የነበረ)- ጌታቸው፤ ማሰረሻ፤ ወዘተ የሚሉ ስሞች በሓጎስ፤ በዲሳሳ በነገዎ.. ስም ተተክተው በሥልጣን ፊት ለፊት መግባት አለባቸው፡ጌታቸው ..ማስረሻ..” የሚሉ አማራ ስም ያለቸው አማራዎች ስልጣን ይበቃቸዋል፤ በመንበረ ሥልጣን አመራር ከሗላ እንጂ ከፊት መቀመጥ የለባቸውም ሲል አማራን አጥብቆ የሚጠላማፈሪያየሆነ ግለሰብ ይህንኑ በትግራይ ተሸንፈናል ፤በትግሬዎች እንድናለን ሲል ነበር። ዛሬ የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ራሳቸውን ነጻ ማውጥት አልቻሉም። የወያኔ ተቃዋሚ የሚባሉትም ግማሹ ትግራይ ለማስገንጠል የቆሙ ግማሹ ደግሞ የአብይ አሕመድ የርዕዮተአለም አስፈጻሚኩሊዎችሆነዋል። ወየኔ ሄደ በወያኔ ተተካ!!

ታዲያ በማአከላዊ መቶኛ ማለትም 92% የሆነው ትግራይ ውስጥ 42 እስከ 54 ዕድሜ ያለው ከላይ የተዘረዘሩትን የወያኔእሴቶች በሙሉይቃወማል ወይስ ይቀበላል? አይቀበልም ካልን ማስረጃችሁን ንገሩኝ።የወያኔ ትግራይ መመስረትስ ዛሬም ህያው ሆኖ ያከብረዋል ወይስ አያከብረውም? አዎ ከሆነ ለምን? ወያኔነት ኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስደፈረ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ ያስቀረ፤ አማርኛን በላቲን ፊደል እንዲተካ በሕግ የደነገገ (ትግራይም ጭምር (ኩናማም ዓፋሮችም..ወዘተ..) የመከራችን ፈጣሪ ከሆነ- ከወያኔ ትግሬ ጋርብዙዎቹ ትግሬዎችዛሬም ግንቦት በመጣ ቁጥር ለምን ትግሉን ያከብሩታል?
አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)