Sunday, June 25, 2023

ለወዳጄ ለገብረመድህን አርአያ ማስታወሻ ባለህበት ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 6/25/2023


ለወዳጄ ለገብረመድህን አርአያ ማስታወሻ

 

ባለህበት

 

ጌታቸው ረዳ

 

(Ethiopian Semay)

 

6/25/2023

ጤናህ እንደተጎዳ ከወዳጄ ሰምቻለሁ። አምላክ ምህረቱን ይስጥህ እያልኩ ኢትዮጵያዊያን አርበኛንና የትግል ባለውለታዎችን የማስታወስ ችሎታም ሆነ የማክበር ባሕሪ የላቸውም። ውለታህ የተረሳ ሆኖ ስለታዘብኩ፤ ሰው የረሳህም መስሎ ስለተሰማኝ ፤ ትዝ ቢላቸው ብየ የተወክልንን  የወያኔ ወንጀል የታሪክ ላስታውሳቸውና ባንተው ንግግር ጥቅስ ልጀምር፡

በሕይወት ከቆየሁ፤ ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ ስትወጣ ለሚመለከተው በመምራት የጅምላ መቃብሩን ቦታዎች አሳያለሁ።” ገብረመድህን አርአያ (የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ታሪክ እንወቀው የወያኔ ፋሽስት ስርዓት በኢትዮጵያ’ ከሚለው የላክህልኝን ሰነድ።

እስኪ አንባቢዎቼን እንዲያስታውሱህ ስለ ወያኔ የግድያ ሱስ እና ወንጀል ምን ብለህ ነበር? ልጥቀስ፤

<< አንድ ወንድ ወይም ሴት ከመገደላቸው በፊት በምርመራ ሰቆቃ ይደርስባቸዋል። የምርመራው ሂደት፤እስረኛው ሁሉ በቶርቸር ማሰቃየትም ሆነ መግደል ከታች ተዘርዝረው ያሉትን መሰቃያ ዘዴዎች መሆን እዳለበት በዝርዝር በመወያየት ያፀደቁት 1 ስብሃት ነጋ 2 ግደይ ዘራፅዮን 3 አረጋዊ በርሄ 4 አባይ ፀሃየ ሲሆኑ ህዝብም ያለቀው በዚሁ አሰቃቂ ቶርቸር ነው ።

1.     ጎማ በለበሰ ብረት ጭንቅላትን፤ ብልትን እና ሆድን መቀጥቀጥ፤

2.    ሴትን ደግሞ ብልቷ ላይ የፈላ ውሃ በማፍሰስና ጡትን መግረፍ፤

3.    በጋለ ብረት ማቃጠልና እንጨትና ገለባ እሳት አቀጣጥሎ የተመርማሪውን ገላ መለብለብና እስትንፋሽ ማሳጣት 

4.    የፈላ ውሃ ጭንቅላት ላይ ማፍሰስ፤

5.  24 ሰዓት ሙሉ እርቃን አድርጎ በግንድ ላይ በማሰር   ለፀሃይና ለብርድ ማጋለጥ፤

6.  ቀኑን ሙሉ በገመድ ዘቅዝቆ መስቀል፤

7.  የወንድ ብልት ላይ 10 ኪሎ አሸዋ ማንጠልጠል፤

8. በምግብና በውሃ ውጥ መርዝ መጨመር፤  በብዙ ጨውና ላምባ (ናፍጣ) የተነከረ እንጀራ መስጠት፤ ምግብና ውሃ ለሳምንት መከልከል የመሳሰሉት ናቸው።

ይህ ጭካኔ አገር ውስጥ መንግሥት ከሆኑም በኋላ ቀጥለውበታል።

ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ብዙውን ጊዜ የሚፈጽሙት፤ እነዚ ገዳዮችም በስብሃት እና  በግደይ ሰልጥነዋል ። ዋና ዋናዎቹ ገራፊዎችና ርሽና ሲያካሂዱ የነበሩ የሚከተሉት ናቸው

1. አለምስገድ ኢንቺ

2. ብስራት አማረ

3. ድለዊ

4. ሙሉጌታ አለምሰገድ  

5. ክንፈ ገብረመድህን

6. ሃሰን ሽፋ

7. አበበ ዘሚካኤል

8. ወዲሻምበል፤

9. ሙሉጌታ( ወዛም)ፀጋይ

10. ህቡር ገ/ኪዳን

11. አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቤ)

12. ሃይሉ በርሄ (ሃይሉ ሳንቲም)

13. ዘርአይ ይህደጎ

14. ታደሰ መሰረት ናቸው። (የነዚህ አወቃቀር ፈለግ ተከትሎ ብዙ ገዳይ መርማሪዎች በየገጠሩ ተሰማርተው ነበር)

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በምርመራ በጣም የታወቁ  ጨካኞች ነበሩ። አበበ ተ/ሃይማኖት ማለት በወያኔ ዘመን የአየር ሃይል ሃዛዥ የነበረ፤ አቶ ገዛኢ ረዳ የተባሉት እና ሌሎች አዛውንቶችንና ወጣቶችን በእሳት እያቃጠለ ሲመርምር የነበረ አረመኔ ነብሰገዳይ መርማሪ ነው።

ከዚህ ሳንወጣ ግን ‘ሓለዋ ወያነ’ በአካባቢው የፈጸማቸውን የጅምላ የመቃብር ቦታዎችን እንመልከት፤

1. ጻኢ ሓለዋ ውያነ

2. ወርዒ

3. በለሳ ማይ-ሃማቶ  

4. ዓዲ ጨጓር

5. ዓዲ በቅሎ

6. ሆያ እገላ

7. ጻዕዳ ምሸላ - ዓዴት

8. ቡምበት

9. ሱር

10. ቃሌማ ገሃንብ

11. ባኽላ  

12. ጂራ ዓዴት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ምስክርነትን በተመለከተ፤ ኗሪው ሕዝብ፤ መሬቱና እኔ፤ የዚህ ጽሑፍ ደራሲ ገብረመድህን አርአያ፤ ሁሉንም ቦታዎች ስለማውቅ፤ በሕይወት ከቆየሁ፤ ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ ስተወጣ ለሚመለከተው በመምራት የጅምላ መቃብሩን ቦታዎች አሳያለሁ።>>

ይላል ወዳጄ ገብረመድህን። ሆኖም ኢትዮጵያ ከወያኔ ፋሽስት አገዛዝ ነፃ በትወጣም ሌላ የወያኔ አገልጋይ የነበረ ኦሮሙማ አብይ አሕመድ ተተክቶ ሁለቱም በሕግ ላለመጠየቅና በጦርነት ሰበብ ዕድምያቸው ገፍቶ ሳይጠየቁ ሞተው ያልሞቱትም በቀጠርዋቸው በፈረንጅ አገሮች በፖሊካ ስደተኛ ስም ተመዝግበው “በሰላም” እንዲኖሩ ጦርነት በመክፍት ዕድመያቸው እየገፋ ማምለጫ አድርገውታል እና አንተም ባለህበት አውትራሊያ ጤናህ እንዲመለስ ጸሎቴ ነው።

የምን ግዜም የጥንቱ የጥዋቱ አብሮ አደግ ወዳጅህ ጌታቸው ረዳ ከአገረ አሜሪካ!!

Ethiopian Semay