Wednesday, June 12, 2024

የንጉሡ የልጅ ልጆችና የልዑል ራሥ መንገሻ ልጅ አዲሱ የወያኔ ቡቃያ ከ ኢሕአፓነት ወደ ወያኔነት! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ) 6/12/24

 የንጉሡ የልጅ ልጆችና የልዑል ራሥ መንገሻ ልጅ አዲሱ የወያ ቡቃያ ከ ኢሕአፓነት ወደ ወያኔነት!

ታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay አዘጋጅ) 6/12/24

ሁለት ርዕሶች አሉኝ፡፡ አንደኛው በርዕሱ የተጠቀሰው ጉዳይ ሲሆን ( እስቲፋኖሰ መንገሻኔ ወያኔ የበረሃ ትግል ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ልሳ በርሐ (የወያኔ ድርጅት ዋና መሪ  የአረጋዊ በርሐ እህት) ካናዳ ወሰጥ የወያኔ ህዋስ አባል ሆኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ፡፡ልጅ ጃልየ መንገሻ ድሮ ኢሕአፓ ከዚያም በጦረነቱ ወቅት ከወያኔ ጋር ሲተሻሸ የነበረ፡፡ ሁለቱም የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም (ለወያው መሪ ለአቦይ ስብሐት “ነጋ” ወንድም) ልጆች  ናቸው፡፡ የአጎታቸው ደርጅሆነው የወያ ሥርወ መንግሥት መቀላቀላቸውን እንመለከታለን፡፡ ሁለተኛው “ሰለ የሚዲያዎች” የቆየ በሽታቸው በድጋሚ ማገርሸቱን እንመለከታለን፡፡

 ባለፉት ሁለት ወራት ብዙ ሺ አንባቢዎች ጽሑፎቼን አንብባችኋል፡፡ለዛም አመሰግናችኋለሁ፡፡ካታ የሚዲያ ሰዎች እባካችሁ አንብቡን እያልን ስተሰሙን ዘመን አለፎናል፡፡ የምንለምንበት ምክንያት መጣጥፎች እንደ ዩቱበሮቹ የገንዘብ ጥቅም የሚገኝበት ሳይሆን አብዛኛው’ ወጣቱ ትውልድ ግብዝ በመሆኑበተሰለበ’ ሕሊና ስለሚዋኝ  ከየት መጥቶ ውድየት እየተጓዘ እንዳለ ባለማውቁ የሚረከባት አገር ተፈረካክሳ አገር አልባ ሆኖ እንዳይቀር በሚል ስጋት ነው፡፡

ስለዚህ ካነበቡኝ ውስጥ አገራዊ ቁጭት በማሳደር ጥቂት የሚቆጫቸው ሰዎች ካገኘሁ በእነዚህ ጥቂቶች ሕሊና ውስጥ ካደረ ሌላውን እያስተላላፉ በጠላቶችና በባንዳዎች የተዳከሙትና የተፋቁትን የወላጆቻችን ቅርስም ሆኑ የተነጠቅናቸው የወደብ ባሕሮቻችንና በመጠቃት ላይ ያለው ሰንደቃላማችን ከመርሳት ማዳን ያለብንን ትላልቅ ማንነታችንን ሊያሳድሱት ይችላሉ የሚል የእምነት ተሰፋ ነው

ወቅቱ ውርደትን የተከናነብንበት ወቅት ነው፡፡

ወቅቱ የዓለም አከራሪ እሰላሞች በዙ ተከታይ እያገኙ ዓለምን በሸሪዓ ለማስተዳደር መትጋት አለብን የሚሉበት ወቅት ነው፡፡ በአብይ አሕመድ የሚመራው አደገናኛው በማእራባዊያን የሚመራው ''የፖቲካ ጤውም'' የእስላሞቹ ያህል  አዳዲሰ አባላት እየመለመለ ዓለም በተለይም ሰፊውን አፈሪካ በብዛት አዳርሶታል፡፡ ኢትዮጵያንም እንደ ጉንዳን ወረርሺኝ ሰገጦ ይታል፡፡ ኦርቶዶክስ ለ33 አመት ሙሉ ፍዳውን እያየ ነው፡፡ በመለስ የትግዎች አገዛዝ ዘመን የነገሥታቶቹ የልጅ ልጆችም ለንብረታቸው ሲሉ አንዳንዶቹ አዲሰ አበባ ደው የወላጆቻቸው ሆል ተረክበው ፤የመለስ ናዊ ሥርዓት እጅ ነሺዎች ሆነው ሥርዓቱን በመፍራት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች “የሰበሰባ አዳራሽ” ሲከለክሉና ለሥርዓቱ ሲጎነበሱ አይተናል (በዚሀ ላይ ታሪከ የዘገበው ዋቢሸበ ባለት የሆነው የለዑል መኮንን ልጅ የሆነው ልዑል በዕደማረያም ነው)፡፡

 እነኚ የነገሥታት ዘሮች ከወያ ጋር መሞዳሞድ ከለመዱ ዓመታት ሆንዋቸዋል (ልዑል ራሥ መንገሻም ያው ናቸው ፤ስለሳቸው ከወያ ጋር የነበራቸው ቀረታ የጻፈኩትን አሰታወሱ) ስወልቃይት የተናገሩትን ሁለት ምላሳቸውንም አትርሱ፡፡ በቅርቡ ደግሞ ልጃቸው የሆነው የልዑል ራሥ መንገሻ ሥዩም በተማሪ ዘመን ድሮ  የኢሕአፓ ፓርቲ አባል የነበረ ደግሞ ከአከራሪ ወያነ አባላት ጋር ሲሞዳሞድ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

 “ትግራይ ትወት” (ትግራይ ታሸንፋለች) በሚል የገንጣዮች (የሃገረ ትግራይ) መርሃ ግብር ማለትም ከጦርነቱ በፊት “መከታ” (በትግርኛው “መኸተ” ) ለሚለው አክራሪ የወያን ተከታይ መሁራን ሲያሰባሰቡት በነበረው <ለጦረነቱ ዝግጅት አጋዥ> ወፈር ያለ ገንዘብ ካዋጡት አንዱ የወያነ አዲሱ ቡቃያ ሆኖ ብቅ  ያለው “ጃልየ መንገሻ” መሆኑን ገንዘብ ካዋጡት ስም ዝርዝር ስመለከት እውነትም  ሕልውናችን ተቃውሶብናል ያሰኛል፡፡

አገር በቀል የሆኑት እንደ እነ “ወያነ” እንደ እነ “የፖለቲካው ኦሮሙማውና “የፖለቲካ ንታል ኮስት” ሃይማኖት መሪው አበይ አሕመድ” እንዲሁም ጸረ አማራ ማሕበረሰብ አገር አፍራሹ “ኦነግ” የመሳስሉት የደከሙና ያበቃላቸው የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ (በቀውሰ ወሰጥ ቢሆኑም) ፡፡

<አድማጭ ያጣ ጩኸት> በሚል መጽሐፋቸው ፕሮሰር መስፍን (ነብስ ይማር) ይህንን አስመለክተው እንዲህ ይላሉ፡፟

<<አንዳንድ ሰዎች ወያ ያበቃለት ተልእኮው የከሸፈ የመሰላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን በማፈራረስ ወያ ርትራ በማሰገንጠል የጀመረው ፈጥነን ካልገታነው የሚቀጥል ይመሰላል፡፡ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልእኮ ገና ከጥንስሱ የወያ ብቻ አይመስልም፡፡የሎች ፈላጎትም እቅድም እንጂ፡፡

ሰለዚህ አንድ ማሳያ ብንወሰድ...

አንድ ኣባቱ በተ መንግሥት ጸጥታና የደህንነት አባላት ተይዞ የታሰረበት ወጣት ከወላጅ እናቱ ጋር አብረው ወደ አሪካ አምባሲ ሰለ ሰውየው መታሰር ለመንገር ይዳሉ፡፡ በመርጫ 1997 ዓ/ም ለማስታረቅ ወዲያ ወዲህ ስትል የነበረች ዲፕሎማትም  ስለ አባትየው ደህንነት ደህና መሆኑ እና ምንም እንደማይደርስበት ካረጋገጥችለት በላ እንዲሀ ትለዋለች ፦

“ኢትዮጵያ በቅርቡ አመታት ወስጥ አራት ቦታ ተከፋፍላ አራት የተለያዩ  አገራት  ልትሆን እንደምትችል ግምት መኖሩ ነግራው ታሰናበታቸዋለች፡፡ በእርግጥም ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ግምቶች መኖሩ ከመርጫ 97 በፊት ሰምተን ነበር፡፡>> ያሉት የፕሮሰር  መስፍን ወ/ማርያም ጽሑፍ ላስታወሳችሁ እፈለጋለሁ፡፡

ሰላማዊትና የነገድ ፍትግያ ችግር የለባትም ሰትባል የነበረቺውን ሱዳንን ምን እያደረጉዋት እንዳሉ ተመልከቱ፡፡ያገራችን ሕዝብ መከራ ጥልቀቱ ጥልቅ መሆኑን ይጠቁማል፡ (አስባችሁታል የልዑል ራሥ መንገሻ ልጆች የሃይለሥላ የልጅ ልጆች የወያ ተለሳላሾች ሲሆኑ? የውርደታችን መጠን ያን ያህል ነው፡፡

እንደ እኔ እምነት ኢትዮጵያ በአካል አትፈርስም ፤ ግን የስዎች ባሕሪና ባሕል ግን ይበላሻል (ባስፈሪ እርከንም ተበላሽቷል፤ የተበላሸ ባህል የሚኖርባት አገርና ሕዝብ ግን ልትሆን ትችላለች የሚል እምነት አለኝ፡፡) ይህ ግን “እንደ አገርና እንደ መኖር ሊቆጠር ይቻላል ወይ''? ነው አሳሳቢው ነገር (አሁን ትግራይ ውስጥ “ሃንግ” ተብለው በሚጠሩ እንደ የ Guatemala “ማራስ”  የሚባሉት ዱርየ ጋንጎች ኗሪውን አላስኖር አላሰቅመጥ እያሉት እንደሚገኙት ጋንጎች ሁሉ በዚያ ባሕል አገር ተበሎ ቢጠራም መኖር ሊባል ነው ወይ? ነው ነገሩ)፡፡

መከራችን ዘርፈ በዙ ነው፡፡ሚዲያውም እንደነበረበት ቀጥሏል፡፡ ሁለተኛው ርዕሴም ሚዲያው ነው፡፡

 እኔ የምተቻቸው ን የምትከታተሉ እንደምታወቁት ፖለቲከኞችንና ሚዲያዎችን ነው፡፡ የተበላሸ መሪና የተበላሹ አከራሪ ፖለቲከኞችን ማሰጠጋት ማሽሞንሞን ድሮም አሁንም ያንን ባሕሪ ሰለቀጠሉበት ድግመን መነጋገር አለብን፡፡

የኢትዮጵያ ሚዲያ ተብየዎች ተንታኞች አድርገው የሚጋብዙዋቸው ሰዎችን ስትመለከቱ ትገረማላችሁ፡፡

ለምሳሌ ኦነጉና አከራሪው ጸረ አማራው ፤ ጸረ ኢትዮጵያ  የፕሮተሰታንቱ ፓስተር የጫት ሱስ ባገራችን ቀጣይ አስፈላጊነት  ሰባኪና ጫት  ቃሚው የወያነ ወዳጅ “ፕሮፌሰር እስቄል” ጋቢሳና ወያ“አሉላ ሰለሞንን” የመሳሰሉትን ነው፡፡

እጅግ አደገኛ ተምበርካኪ ሚዲያዎች የሆኑትን ፤ሕሊና የሚበርዙትን የምንቋቋምባቸው መንገዶች አንዱ የን የመሰሉ ሃሳብ ያላቸው ሚዲያዎችን የሚተቹትና የሚጽፉዋቸውን ማንበብ ነው፡፡ ጥይትና በእር የገድላሉ ወይንም ያድናሉ፡፡ አስቡት እስቲ የነገሥታትና የልዑላን  ቤተሰቦች “ለወያኔ ሥርዓትና አባሎቻቸው አጎብጓቢዎች ሲሆኑ”!!! ሚዲያዎች ኢትዮጵያን “ኢምፓየር” እያሉ የሚዘልፏት የፖለቲካ እብዶችን እየጋበዙ “ተንታኞች” አደረገው ሲጋበዙ አስቡት እስቲ???!!!

ሃይለየሱስ የተባለ የአብይ አሕመድ ብልጽግና አገለጋይ ሆኖ ተሹሞ የነበረ፤ አማራ ክልል ባሕርዳር ተቀመጦ ሲዘልፈን የነበረ፤ ሳልሳዊ አፄ ቴድሮስ ሆኘ አነግሣለሁ ሲል የነበረ የቀወሰ ሰው፤ ኤርሚያስ ለገሰ የተባለ ወደ ተፋቱ የተመለሰ ማፈርያም “ኮምፓስ” ሚዲያ  በሚል በሚያዘጋጀው ሚዲያ ላይ ሰሞነኛ ተንታኝ እድርጎ ሲጋበዘው፤ እሰኪ አስቡት!!!! ሚዲያው ምን ያህል እንደተበላሸ አሰቡት እስኪ፡፡

ነገን በዛሬ ይመሰረታል። ያኔ አገራዊ ነን ከሚሉ ሚድያዎች ጋር የሚተሻሹ የያኔ ድብቅና ያልተገለጡ ጸረ አገር ባንዳዎች ስቃወም የነገ ክፉ ውጤት አመንጪዎች ናቸው ስል የነበረው ውጤቱን ወያነ ከተወገደ በኋላ የነ ሌንጮ ባቲ የነ በርሃኑ ነጋ ወዘተ... ያያችሁት ጉድ ነው 

ያኔ ፖለቲከኞቹና ሚዲያዎች ሲንበረከኩ አገርም አብራ ተምበርካኪ ትሆናለች እያልኩ ብዙ ስጽፍ የተገነዘቡ ጥቂት ናቸው በተምበርካኪዎች ምክንያት የተነጠቅነውን ሁለቱ የባሕር ወደቦቻችን ምን ዕዳ እያስከፈለን እንዳለ ዓለም ያውቀዋል፤ እናንተም ትገነዘባላችሁ

ኢትዮጵያ  ዓለም ተዘግቶባት የሶማሊያ፤ የጅቡቲ እስላም አገሮች፤ የዓረቦች፤ የኤርትራኖችና የአሜሪካኖች ወዘተ…. ግብር ከፋይየቀይ ባሕር ባርያሆና  መቀጠልዋ ስትመለከቱ ስንቶቻችሁ እንደሚቆጫችሁ አላውቅም። በዚህ ባሕር ዕጦትና በውስጥ ጦርነቶች ብዛት ምክንያት ከጊዜ ብዛት ጭራሽኑም አገሪቱ ለባሕር ወደብ የምትከፍለው ዕዳ ሳትከፍል ብትቀር ምዕራባዊያንም ሆነ አረቦች ወይንም ግብጾች እንደማይወርሩን እርግጣኛ ሆኖ ዋስትና የሚሰጥ የለም።

እንደምታዩት አገሪቱ እየኖረች ያለቺው በልመና በሚገኘው ስንዴና ገንዘብ ነው። ትናንት 3 (ጁቡቲ፤ዓሰብና መፅዋ) ወደቦቻችንን አስረክበናል፤ ዛሬ ደግሞ የቆዩ ቅርሶችን እየፈረሱ ሃውልቶች እየተደረመሱ ለተመቻቸው ጥቂት ተሽሞንማኝ ሰዎች በፓርክና በተዋቡ ህንጻዎች እየተተኩ ናቸው፡፡ (የምትበላት ሳይኖራት የምትከናነበው አማራት!!! የሚባለው ነው እየታየ ያለው)

አብይ አሕመድ እያደረገው ያለ ይህ “የጮሌዎች ቁማር” የማሃይምና የየዋህ ሰው ሕሊና ለመስለብ እንደ ሥልጣን መግዢያ እየተጠቀመበት ነው፡፡ ሕዝብ በየመንገድ ተኝቶ በበሽታና በርሃብ እየተቆላ ባለበት አገር አዲስ አበባን የማሸብረቅ 'አታላይ ቁማር' የሚያስታወሰኝ አገር ድሆቻቸው በሕክምና እና በመኖርያ ዕጦት በየ ድልድዩና ጎዳናው ከውሾች ጋር እየተኙ ባሉበት በካፒታሊስት አገሮች (ለምሳሌ አሜሪካ) የታየና ያንን “ቅጅ/ኮፒ” አብይ አሕመድ እየተገበረው ስመለከት ሰውየው የሕጻን ጭንቅላት ያለው በሕዝብ ሕይወት የሚቋመር ቁማርተኛ ሰው ነው፡፡

ባለፈው ዓመት እኔን የመሰለ አንድ የሶቭየት ጻሐፊ ከታተመ 100 ዓመታት በኋላ የሆነው Pressenza የተባለው መጽሔትለህልም ፍላጎትየሚል ርዕስ አውሮጳ ውስጥ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ  ብቅ ብሎ ሕትምት ሲጀምር: በነ ጎርባቾቭ የመሳሰሉ ሶቭየት ሕብርትን ያፈራረሱዋት ባንዳዎች አንገታቸው ደፍተው የነበሩአገራዊያንምጽሔቱን ሲያነቡት የትንሳኤ ጨረር በሚል የግብረ-መልስ መልዕክቶች አጨናንቀውታል።

እነ ጎረባቾቭና እነ የልሰን ወደ ሥልጣን ሲመጡ የቆየውዓለም አቀፍ ድሆችና ሰራተኞች ተባባሩየሚለው ታግዶ የነበረው የጥንቱ የሶቭየት ሕብረት ብሔራዊ መዝሙር ፑቲን ወደ ሥልጣን ሲመጣ ታዋቂ የመዘምራን (ኳየር /ኦርኬስትራ) ሊቃውንት ሰብስቦ እንደገና እንዲዘጋጅ አድርጎ ብሔራዊ መዝሙር ሆኗል።

የሶቭየት ሕብረት ከተመሠረተ 100 ዓመታት በኋላ  Pressenza መጽሔት በጃንዋሪ 10 2023 ብቅ ብሎ ለሕትመት ሲበቃ የቀረበው ሰፊ ሐተታ ቢሆንም ከመርሳት ማዳን ያለብን ትልቅ ትውስታ ለሙዚየሞች ብቻ አይደለም: ነገር ግን ለሚመጣው አዲስ ቅኝትና ትውልድ እንደ ቁሳቁስ ገና ያልተሰራ ትልቅ ተግባር መስራት ላይ ማትኮር አለብን ይላል።

ፀሐፊው በመቀጠልም እንዲህ ይላል፤

 << ከጥቂት ወራት በፊት ከዚህ አለም በሞት ከተለዩት ታላቅ ሰው ልጅ የቼ የበኩር ልጅካሚሎ ጉቬራጋር በሃቫና እየተነጋገርን የሶቭየት ህብረትን በአለም ታሪክ ውስጥ ያለውን ሚና ለመተንተን ስንሞክር እንዲህ አለኝ፡-

(…) እያወራን ያለነው በሁሉም ጥርጣሬዎች ላይ ራሱን የቻለ እና አስደናቂ አብዮት ስላዳበረ ታላቅ ህዝብ ነው። የናዚ-ፋሺስት ጭፍሮችን በህዝቧ መስዋዕትነት አሸንፎ የሰው ልጅን በዋጋ የማይተመን ውለታ የሰራ ሕዝብ ነው። ሶቪየቶች የተለያዩ አይነት እና ስፍር ቁጥር በሌላቸው መስኮች ድንቅ ስራዎችን ሰርተዋል። ኢምፔሪያሊስቶች የውስጥ ተምበርካኪዎችን ይዘው ያን ታላቅ አገር ማፍረሳቸው እንዳይበቃ ሶቭየትን የመሰለ ታላቅ አገር የመሰረቱና የናዚ ጦርን ያሸነፉ ታላላቅ መሪዎች ሃውልት እንዲፈርስና ስማቸው ከታሪክ እንዲፋቅ ያደረጉ ባንዳዎች ስመለከት እጅግ ይከነክነኛል።….” አለኝ ይልል::

የውስጥ ተምበርካኪዎች በቆዩ ቅርሶች እና ታላላቅ መሪዎች ላይ የማጠልሸት ስራ ሲሰሩኢምፔሪያሊሰቶችአላመኑም ነበር።  እኔም እንደዚህ አይነት ነገር ይደረግ ይሆናል ብየ ካላመኑት  አንዱ ነኝ። ያም ሆኖ ቢደርግም እንዲህ ያለውን ግዙፍ ሥራ ለማጥፋት የሚያስችል ኃይል እንደሌለ ሁልጊዜ እርግጠኛ ነበርኩ።  ከስሜታዊነት ወይም ከርዕዮተ ዓለም ዝምድና ያልተያያዘ አገራዊ ዙፋን ማደፉን የሚቆጨው እንደ በአንድ እርሻ ላይ ጥሩ ቡቃያ በድንገት እንደሚበቅል ሁሉ እንዲያ የሆነ አዲስ ትውልድ እንደሚከሰትም አልጠራጠርም  ብሎኝ ነበር ይላል ጻሐፊው።

ካለ በኋላ ፊው፤

ያገራችን ታላቅነት ለማደስ ተነስተናል፤ እኛን ለመጨፍለቅ የሚገዳደሩም አይጠፉም፡ እየተያየን ነው። ዓለም ያለ ተገዳዳሪ አልተፈጠረችም ወይንም አትኖርምና አገራችንም የጥንት ታላቅነትዋን ለማስነሳት አንድ ጉዞዋን ጀምራለች። ከኢምፔሪያሊስቶች ተደናግጠዋል፤ ፑቲንም የወላጆቹን አርማ አንስቷል! ሲል ደምድሟል።

የተለያየ ስም ቢሰጠውም ጦርነት አወዳሚ ቢሆንም ላገር ክብር ሲባል እንደ አዲስ ቡቃያ አጋጣሚ ብቅ ብሎ ወደ ስልጣን የበቀለው ፑቲን ሩሲያኖች የቀድሞ ሉኣለዊነታቸውን እንዲያስታውሱ አድርጎ ምዕራባዊያኑን እያስጨነቀ ነው።

ይህ ልዩ እውነታ እኛ ኢትዮጵያዊያንም እንደ ፍጡራን ሰዎች ታሪካዊ ትውስታችን ይዘን እንድንቆይ ትልቅ ፍላጎት እንደሚሰማን ይነግረናል   ጥንታዊ የኢትዮጵያዊነት ፕሮጀክት ከብርሃን እና ጥላ ጋር ወደፊት የሚለው የቃል ተስፋ ሰንቀን  መሄድ አለብን እያልኩ ለ33 አመት ብናገርም በነዚህ 33 አመት የውስጥ ቅኝ ግዛት አሳዛኝ ገጠመኞች ማንነታችን ቅርሶቻችን፤ ወደቦቻችን ሃይማኖታችን እና ታላላቅ አርበኞቻችን ለውርደት በተጋለጠበት ዘመን፤

ታላቅ አገር የመሰረቱና የፋሺስት ጣሊያን ጦርን ያሸነፉ የታላላቅ መሪዎች ሃውልት እንዲፈርስና ስማቸው ከታሪክ እንዲፋቅ ካደረጉ ባንዳዎች ጋር አብረው የሚሞዳሞዱ ፤ እና የገንዘብ መዋጮ የሚያደረጉ አንዳንዶቹ የንጉሡ የልጅ ልጆች ማየት መራራ ቢሆንም ፡ አገር ወዳድ በሆኑ  በተራ ዜጎችዋ እና በማይምበረከኩ ልጆችዋ በማያቋርጥ ተከታታይ ንቃትየተከናነብነው ውርደታችንዘላለማዊ ሆኖ እንደማይቆይ በጊዜ ሂደት ሊቀለበስ እንደሚችል ከሩሲያ ፑቲን አገራዊነት የትንሳኤ ጨረር ተምረናል።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ