Monday, April 17, 2023

የአመቱ ምርጥ ጀግና አዲሱ ደረበ! ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/17/23

 

የአመቱ ምርጥ ጀግና አዲሱ ደረበ!

ከጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/17/23

ወደ ትንታኔየ ከመግባቴ በፊት ጀግናየሚባለው ቃል ትርጉም ልስጥ።  ጀግና ማለት ከተራው የሰው ልጆች እርምጃ ውጭ ለማሕበረሰቡ ሲል የማይሞት ትውስታ ሰርቶ የሚሄድ ሟች ማለት ነው። ሲሞቱ የማይሞቱ ትውስታዎችን ለዘላልም ትተው በማሕበረሰቡ ሕሊና ውስጥ በአማልክት ገጽታ የሚመለክና የሚተረክላቸው ሥራ ሰርተው የሚያልፍ ኢትዮጵያዊያን በታሪክ መዝገብ እየተመዘገቡ አልፈዋል።

በአገራችን የጥንት ታሪክ “ባንዳ” የሚባለው የውጭ አገር ሴራ ተባባሪ “ቅጥረኛ” በቁጥር ጥቂቶች ነበሩ። በነዚህ በ32 አመት ውስጥ ግን በሚገርም ሁኔታ የባንዳዎች ቁጥር በመቶዎች ሳይሆን “በሚሊዮኖች” ተባዝተው የአገሬው ሕዝብ ወደ ስቃይና ብካይ ለውጠዋታል።  ሆኖም እንደ ባንዳው ብዛት ሚሊዮን ጀግኖች ባይታዩም የማይሞት ትውስታ ሰርተው ያለፉና ዛሬም በየጫካውና እስርቤቶች የሚገኙ አምበሶችና አምበሲቶች እያየን ነው።

ጨለመ ሲባል መብራት ይዞ ብቅ የሚል ብርሃን አብሪ ከዚህም ከዚያም የሚታይ ክስተት እንደሆነ በዚህ የ32 የመከራ አመት ውስጥ አይተናል። እነ አሳምነው ጽጌ የማያልፍ ታሪክ አስመዝግበው አልፈዋል፤ስማቸው የማላውቃቸው በርካቶችም እንዲሁ አልፈዋል። በህይወት ያሉ እንደ እነ እስክንድር ነጋም አሉ። እስር ቤት ውስጥ የታጎሩ በርካቶች አንሰትና ተባዕት ጀግኖቻችን ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ።

ዛሬ ድግሞ ጫካ ወጥተው ጠመንጃን በጠመንጃ የመመከት ሥራ ለመሥራት ቃላቸው በግብር እያስመሰከሩ ካሉት ብዙ ጀግኖች ውስጥ ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ የዚህ ዓመት ምርጥ ጀግና አድርጌ መርጨዋለሁ። የናንተው ተራስ መቸ ነው?

 ብዙዎቻችሁ በየፌስቡክ ውስጥ ተወዝፋችሁ መቀመጫችሁ ያወፈራችሁ ሴቶችና ወጣት ወንዶች የዚህ የውጭ አገር ምቾት ትታችሁ በየፌስቡክና በዩ-ትዩብ እየወጣችሁ ዐብደት በሚመስል በተግባር የማይታይ የፉከራ ቃላት አቁማችሁ “አገር ወዳድነታችሁ” ለማስመስከር ለጥቂት ወራትም ቢሆን እስኪ እምደምትፎክሩት ወደ አገር ቤት ጫካ ውረዱና እንደ እነ አዲሱ ብረት ታጥቃችሁ የአብይ አሕመድንና የፋሺሰቱ ወያኔ ሴራ ለማስቆም እስኪ በፍንጃል የምትለካ ላብ ጠብ አድርጉ። የተማሪው ዘመን ለመጥፎም ለደግም እኮ ብዙዎቹ ጫካ የገቡት ውጭ አገር ሲኖሩ የነበሩ ወጣቶች ናቸው። በእናንት ዘመን ሲደርስ ለምን ቆመ? አሁን ጫካ የወጡት ጀግኖች እናንተ ካልተቀላቀላችቸው በግራም በቀኝም እንደ አሸን የፈላውን ጠላት ብቻቸውን እንዴት ይታገሉት?

የኦነግ ታጣቂዎች እኮ ወጣቶች ናቸው፤ የወያኔ ታጣቂዎች እኮ ወጣቶች ናቸው፡ እናንተ ወላጆቻችሁ እየታመሱ ሕጻናት እያማረሩና እያለቀሱ ነብሰጡሮች እየታረዱ፤ እየተፈናቀሉ “የወንድ ሃሞት” በሚጠይቀው ጫካና ተራራ ላይ ተገኝታችሁ ሴረኞቹን ጠመንጃ በጠመንጃ ካልመከታችሁ፤ ስቃዩ እንዴት ይቆማል ብላችሁታስባላችሁ?

አባቶቻችሁ እና ዘመዶቻችሁ ዕርዱን ሲሉዋችሁ ከርሳችሁ ወድዳችሁ ከዚያች የፌስቡክና መኪናችሁ ላይ ተቀምጣችሁ ከምታስተላልፉት የዩቱብ “ምክርና ፉከራ” ወርዳችሁ ጫካ ውስጥ እስኪ ለጥቂት ወራትም ቢሆን ወጣትነታችሁን ሞክሩት?  

“እኔ ዘመነ ካሴ ነኝ! እኔ አዲሱ አበረ ነኝ! እኔ መሰረት አበራ ነኝ! እኔ ወዘተ..ወዘተ…. ነኝ!” እያለችሁ ፌስቡክ ከመጻፍ እናንተ እነሱ ከሆናችሁ እነሱ ባሉበት ቦታ ላለመገኘት ለምን ወደ ኋላ ኣላችሁ ?

እስኪ  ውሸታችሁን አቁሙ! እኛ አገር ውስጥ እያለን ትከሻችን የሚሸከመውን ያክል ጥቂትም ብዙም ይብዛም ይነስም ጠመንጃ ተሸክመን የወያኔን አገር አፍራሽነት አስቀድምን ስላወቅን ጠመንጃን በጠመንጃ ሞክረነዋል። ደርግን በፓርቲ ሳንደራጅ በግል አይበገሬነት በይፋ ሕዝባዊ አዳራሾች ላይ እስራትን ሳንፈራ ተጋፍጠነዋል። ብዙ ጊዜ ታስረን ለስቃይ ተጋርጠናል። ዛሬ ተራው የናንተው ነው። እስኪ ከውሸት ዓለም ውጡና ራሳችሁን ሞክሩሩት! ክብር ለጀግኖች!

The AMHARA

https://www.youtube.com/@theamhara6399

እስኪ የዚህ ጀግና ምርጥነት ሼር አድርጉ? ያም ሊከበብዳችሁ ነው፤ ግን ሞክሩ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)