Saturday, June 11, 2016

ኦ! ሲሳይ አገና! ኦ! ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)

ኦ! ሲሳይ አገና! ኦ!
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)


ዛሬም ስለ ጉደኛውኢሳትስለ እሚባለው የሻዕቢያና የግንቦት 7 የፕሮፓጋንዳ  ማሰራጫሚዲያ እንመለከታለን። ዋነኛው ትችቴ ግን በሚቀጥለው ሰሞን የማነ ገብረአብ የተባለው ኤርትራን አፍነው ከሚያሰቃዩ ተጠያቂዎች አንዱ የሆነው በግንቦት 7 በኢሳት ራዲዮ ቀርቦ ከሲሳይ አገና ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ  የወሻከተውየኤርትራ ነፃነት ጉዳይአስመልከቼ “Revisiting the Eritreans’ mind & their Big Lies” በሚል ርዕስ የቆላማው እስላም ሊሂቅ  ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ያቀረበው ምክንያትዓረቦች ነንብለው የነደፉት ካርታ እና በደጋማው ክርስትያንም አይ ተመልምለው ኢትዮጵያን ለማፈራረስኮሎኒያል ኩዌሺንበሚል መሰረት የሌለው ውሸት ሕዝቡን አታልለው ለመጨረሻ ውድቀት የዳረጉት መስራቾቹ ከእነ ወልዳብ ወልደማርያም ጀምሮ ዛሬ በህይወት ያሉ እራሳቸው ለሐፍረት ያጋለጡ የዛሬቱ ሲኦላዊት ኤሪትራ መሪዎችና የኤርትራ ትግል፤ በኤርትራኖች ብዕር የተጻፈው አውነተኛ ማሕደር አቀርባለሁ።

(Eritreans’ voice in 1992)

እስከዛው ግን የማነ ገበረአብ ከሲሳይ አገና ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ  ባጭሩ እተቻለሁ።አስቀድሜ እንደገለጽኩት፤ የውጭ ጠላቶቻችን በሚያግዙት በግንቦት 7 በኩል የሚካሄደው ኢሳት የተባለው የፕሮፓጋንዳ ማዕከል የሚያሰራጫቸው የኤርትራን ወንጀለኛ መሪዎች በኢትዮጵያ ዓይን በበጎ እንዲታዩ የተክለሰውነት ፕሮፓጋንዳዊ ቀረጻ ዛሬም ቀጥሎበታል።

ትናንት -ሐበሻ የተባለው የግንቦት 7 ቅርንጫፍ አጋዥ ሚዲያ ስጎበኝ፤ሲሳይ አገና የኤርትራን ሕዝብ እያሰቃዩት ከሚገኙት የማነ ገብረአብ የተባለ የሻዕቢያ ድርጅት (እንደ የማነ ቃል አጠቃቀም) የፖለቲካ/ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሓላፊ ቃለ መጠይቅ ያደረገውን አደመጥኩ። ይገርማል!



አስቀድሜ እንደገለጽኩት የቃለ መጠይቁ ዋና ዓለማ ኢትዮጵያዊያኖች ስለ ሻዕቢያ ያለንን አመለካከት ለመቀየርና ፌርማ ለማሰባሰብ የተሞከረው ሙከራ ድጋፍ ለማግኘት ነው። አስገራሚ የሚያደርገው ግን ይህ ሚዲያ እርቃኑን ወጥቶ ስለ ሻዕቢያ መዶስኮሩ እጅግ ያስገርማል። የማነ ሲዋሽ ሲሳይ ዝም ብሎ ያልፈዋል: የማነ ኤርትራ ስደተኞች የሚባሉት አብዛኛዎቹኢትዮጵያዊያንናቸው ብሎ ሲዋሽ፤ ሲሳይ ይህ ውሸት ሳይጋፈጠው እንዳለ ‘’ሆን ብሎ” እያወቀ  እንዲለቀቅ አድርጓል።

እነ የማነ ቢዋሹ አይገርምም።፡ውሸት እየተመገቡ አድገው፤ ውሸት ተምረው፤አውነተ ገደለው፤ በውሸት ጎልበተው፤ለሕዝብ ዋሽተው፤ በውሸት ያረጁ ናቸው።ቢዋሹ አያስገርምም። ምክንያቱም፤ ለስደቱና ለሰብአዊ መብት ረገጣው ተጠያቂ ወንጀለኞች እነሱ ስለሆኑ፤ቢዋሹ አይደንቀንም።ሜዲተራኒያን ባሕር ገብተው የሚሞቱ፤ ሲናይ ምድረበዳ ውስጥ በበደዊን አረመኔዎች የሚያዙ ኤርትራዊያን አይደሉም እያሉ የሚወሹ፤ ሊቢያ በእስላማዊ አክራሪ ሃይሎች የታረዱ ብዙዎቹ ኤርትራዊያንኢትዮጵያዊያንናቸው እያሉ የሕዝባቸውን ህይወት በማራከስ ለወንጀላቸው መሸሸጊያ ምክንያት ቢሰጡ አላስገረመንም። ካሁን በፊት ይህንን ውሸትበድምጺ ሓፋሽራዲዮናቸው አስተላልፈውታልና አያስገርመንም።

ባድሜ አልወረርንም ብለው የሚዋሹ፤ ኢትዮጵያዊያኖች ባረንቱን ዘልቀው ወደ አስመራ ሲገሰግሱ፤ሽሬእንዳስላሴ ይዘነዋል ወደ መቀሌ እየገሰገስን ነው ብለው ለሕዝባቸው የሚዋሹ፤ ባሕሪያቸው ለምናውቅ ብዙም አያስገርምንም። አስገራሚ የሚያደረው ግን የግንቦት 7 ጋዜጠኛው እንደ ልማዱ ዛሬም የተለመደው ውሸት በሚዲያቸው ሲለቀቅ ያላንዳች ጠንካራወጣሪ”/ ቻለንጂንግ ጥያቄ የማነ የፈለገውን ውሸት ሲዋሽ እንዲዋሽ ዝም ብሎ ሲለቀው ከሚገርም በላይም እጅግ አስገራሚ ነው።

የማነ በለመደው ውሸታም ምላሱ የሱን ወንጀልኢ እየደበቀዌ ወደ ኦጋዴን፤ ወደ ሶማሌ፤ወደ ሰሜን…ያኦሮሞ እልቂት ሲያወራ፤ ሲሳይ ሆን ብሎ ሻዕቢያ በኩናማ፤ በዓፋርና በከበሳ  ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር =ፍጅት፤ሊያወሳለት አልፈቀደም። ለምን? እስኪ አንባቢዎቼ ጽሑፌን ስትጨርሱ ይህነን አጭር የተባበሩት መንግሥታት UN report: Massacre and mass graves of Eritrean Kunamas and Afars የሚለውን ዘገባ አንብቡ። http://hornaffairs.com/en/2015/06/10/eritrean-kunamas-afars-massacre-mass-graves-un-report/ስለ ኢሳት የሙያ ደካማነትና አደርባይ ውድቀት እኔ ከምገልጸው በበለጠ በጋዜጠኛ ወንደወሰን ገብረኪዳን ስለ ግንቦት 7/ኢሳት ጋዜጠኞችና ምንነት በግልጽ ያስቀመጠው አገር ውስጥ የሚኖረው ጋዜጠኛ ወንድወሰን ገብረኪዳን ኢሳት ጋዜጠኞችን እንዲህ ይገልጻቸዋል። (ዝርዝሩ ለማንበብ እኛ ቲቱሆያበሚል የጻፈውን (Ethiopian Semay) የተለጠፈውን ያንብቡ። እንዲህ ይላል። “ሚዲያ የግለሰብ ተቋም አይደለም፡፡ የህዝብ ነው፤ ህዝብ የማወቅ መብት አለው፤ ህዝብ ማወቅ የሚገባውን ነገር ማስተላለፍ አለበት፡፡ ፋሲል የኔዓለምና ጋዜጠኝነት የማይተዋወቁ ወይም ሊተዋወቁ የማይችሉ መሆኑን ነው፡፡ ጋዜጠኝነትና የሚዲያ ተቋማት ለፖለቲካ መሪዎች ልሣንነት ብቻ የቆሙ አይደሉም፣ ሙያውም ሁነ ተቋማቱ ለሥልጣንና ለባለስልጣናት አጎብዳጅ አይደሉም፡፡ ሊሆኑም አይገባም፡፡

 እኔ እስከማውቀው ድረስ ፋሲል የኔዓለም ይህ የነፃ ልሳንነት ልምድ የለውም፡፡ አዲስ ዜናጋዜጣ ባለቤት እናጋዜጠኛበነበረበት ወቅት አብረን በሰራንባቸው ጥቂት ወራቶች ውስጥ የታዘብኩት፣ የተረዳሁትና ያስተዋልኩት የፋሲል የኔዓለም አዳር ቀረሽ ውሎ ከዶ/ ብርሃኑ ጋር መሆኑን መሆኑን ነው፡፡ አልጋ የለውም እንጂ የቅንጅት ቢሮ ማደሪያው ሊሆን ምንም አይቀረውም፡፡ ካለ / ብርሃኑ ነጋ ፖለቲከኛ እንደሌለ የሚያምን፣ የዶ/ ብርሃኑ አምልኮ የተጠናወተው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ደግሞ የነፃ ልሳን ነፃ ጋዜጠኛ አይሆንም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ውስጥ አንዱማንኛውንም ሰው ጥብቅ ጓደኛህ አታድርግየሚል ነው፡፡ (ጓደኛ አታድርግ አላልኩም) ጥብቅ ጓደኛ ካደረግከው ከቀረቤታህ የተነሳ ይሉኝታ ማውጣጣት ያለብህን እውነት እንዳታወጣ ያደርግሃል፤ ከጥብቅ ቀረቤታህ የተነሳ እሱን በማመን የተሳሳተ መረጃ ሰለባ ልትሆን ትችላለህ ቀረቤታህ ገደብ ይኑረው የሚለው የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር፡፡

ጋዜጠኛ የፈለገውን ያህል ዕውቀት ቢኖረው፣ እንደማንኛውም ሰው አላዋቂ መሆን እንዳለበት ነው የሚታወነው፡፡ ተራ-ተርታው ሰው ማወቅ የሚፈልገውንተራጠይቅ ነው የሚለው፡፡ ፋሲል ግን ራሱን የበቃ የነቃ ዐዋቂ አድርጎ ስለሚያምን ለዚህ የሙያ መርህ ቦታ እንደማይሰጥ ነው የማውቀው፡፡ እሱ ከገባው ወይም የገባው ከመሰለው ለሌላው ሰው መረዳት ግድ የለውም፡፡ በዚህ ላይ ፋሲል ሌላ ሰው እንዲሞግተው አይፈልግም፤ የተደፈረ ነው የሚመስለው፡፡ እሱ ካለው በቀር ሌላው ሰው የሚለውን መስማት አይፈልግም፡፡ ከእሱ እምነት ውጪ እምነት የለም፡፡ ብላ ብላ ብላ፡፡ በዚህ እና በዚህ ምክንያት ነው ስለ 7D ሆነ ስለሌሎች ጉዳዮች ያላነሳው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ በመግቢያዬ ላይ የጠቀስኩትአስተካክሎ ከማይናገር መልዕክተኛ የማለዳ ወፍ ትሻላለች፤ ምነው ቢሉ መንጋቱን በትክክል ትናገራለችየሚለው የአለቃ ዘነብ አባባል::

ፍቺው ይኸው ይመስለኛል፡፡ እንደወፏ ያለ ጋዜጠኛና እንደ ወፏ ያለ የሕዝብ ተቋም ያስፈልጋል፡፡ ቲቲሆያ!!  ቲቲሆያን መሆን ያልቻለ ጋዜጠኛ፣ ቲቲሆያን መሆን ያልቻለ ተቋም ሕዝባዊነቱ ያከትማል፡፡ እንደጎረቤቴ እናትትሻልን ቀርቶ ትብስንያስመርጣል፡፡ የሕዝብን ልሳንነት የዘነጋና የሚዘነጋ ይሆናል፡፡

ካለ ኋላበመጨረሻ ስለ 7D ጥቂት ልበልይላል፡፡ 7D የሚባለው አካል ከዚህ ቀደም ያወጣውን መግለጨ የማየት እድል አግኝቻለሁ፡፡ ስለ 7D የአንባቢያንን አስተያየት እንዲሁ፡፡የወያኔ ተላላኪ ነውከሚለው አንስቶ፣ መሰረታዊ የሃሳብ ልዩነት በባንሳቱ ተገንጥሎ የወጣ ቡድን ነው እስከሚል አስተያየት ድረስ ታዝቤአለሁ፡፡

ግንቦት ስለ ዲሞክራቲክ ኃይል ህዳር 5 ቀን 2005 . ባወጣው ባለ 3ገፅ መግለጫ የተመድ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ አንቀፅ 19 ጠቅሶ ኢሳት (ESAT) በዚህ መሰረታዊ ሕግ ላይ እንደተመሰረተ ያስታውሳል፡፡ በመግለጫው ማጠቃለያምንም እንኳ መስከረም 21 ቀን2005 ዓም የላክንላችሁን መግለጫ ባታወጡትም በሕዝብ ተረድቶ ለሕዝብ አገልግሎት እሰጣለሁ፣ ለየትኛውም ወገን አልወግንም ብሎ ቃል የገባው ኢሳት አሁንም የሚለውን ሆኖ ይገኛል ብለን አናምንም፡፡….ራሳችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተዋወቅ እንድንችል በቃለ ምልልስ ይሁን በሌላ ጣቢያው ይመቸኛል ብሎ በሚያስበው… ” አስተናግዱን ይላል፡፡

ይኼ አባባል ድምፃችን ይሰማ ማለት መሰለኝ፡፡ ድምፅ ሁኑን ማለት መሰለኝ፡፡ እዛው ባሕር ማዶ ጣቢያውድምፅ ትሆናላችሁ ብለን አናምንምከተባለ፣ እንዴትና በምን መልኩ ቲቲሆያን ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይኼ ቀላል ጥያቄ ሊመስል ይችላል፡፡ ማነው የኛ ቲቲሆያ!?

እውነትም፤ ማነው የኛ ቲቲሆያ!? እነዚህ ናቸው ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀሮና ዓይን ነው እያሉ የሚዋሹን።ሲሳይ ከሻዕያም ይሁን ከግብፆቹ ለኢሳት ስራ ማስኬጃ ከሚወረወረው ገንዘብ እየተቆረጠ የሚወራብህን ወርሃዊው $4000 ደሞዝ በቀረብህ። ሲሳይ አገና! ! ሲሳይ አገና!

እስኪ በመጨረሻ ታሪክ ለማስታወስ አንዲመቻችሁ፤ አማርኛ የመጣብን ሃይለስላሴ ከገዛን በሗላ ነው የሚለውን የእነ ኢሳያስ አፈወርቂና የጀብሃዎች ውሸት “ከረኖች” መጀመሪያ ጣሊያን “ምድሪ ባሕሪን” ኤርትራ ብላ በቁጥጥሯ ስታደርግና የጣሊያን አስተዳዳሪ ስትሾምላቸው ከረኖች ፏሲስቶችን ሲቀበሉ “ሌጋው ሽቦ” እያሉ በአማርኛ ሲፎክሩና ሲጨፍሩ ማስረጃው ይኼው፤ ተመልከቱ። "Italy created Eritrea by an act of Surgery; by severing it's different peoples from those with whom their past had been linked and by grafting the amputated remnants to each other under the title of Eritrea (Trevaskis) ውሸት ላጭር ጊዜ እንጂ ለዘላለም ተሸፋፍኖ አይዘልቅም። ማስረጃውም በዩቱብ ይኼውና ተመለክቱት፡
Il Vicerè Graziani in visita a Cheren.
 መልካም ሌሊት/መልካም ምሽት/መልካም ቀን/ አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com