Wednesday, May 26, 2010

ወያነ ትግራይ የሞት ሞቱ ያየበት የዲሞክራሲ ፌስታ! ጌታቸዉ ረዳ (ግንቦት17/2002) June 26/2010 http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

የወያነ ትግራይ ወንጀል ፋይሎች ክፍት ናቸዉ። ትንንትም ዛሬም ለነገም ክፍት ናቸዉ። ሞልቷል፤ተትረፍርፏል። ወያኔ ዘንድሮም በለመደበት ዉሸት እና ወንጀል በተካነበት ዘራፊ ባህሪዉ ስልቱን በመዘርጋት የዘንድሮዉንም ምርጫ ሳያሸንፍ አሸንፍኩ በማለት “የጠላቶቻችን ተቀጣሪ”-የሆነዉ መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ/አብዬት አደባባይ ተብሎ በሚጠራዉ በአዲስ አበባ የሕዝብ መሰብሰብያ ሜዳ ዉሸቱን ባደባባይ ሲዘላብድ በጆሮቸዉና በዓይናቸዉ ለማየት የተገኙና እንዲሁም “ለእሱ ያደሩ ታጋዬች እና ቤተሰቦቻቸዉ፤ከያቅጣጫዉ ያሰባሰባቸዉ በጎሳ ፤ባምቻ ጋብቻ በቋንቋ ፤በቆዳና በክልል መተዳደር የመረጡ ጠባብ ብሄረተኞች ፤ እና በተለያዩ ዘርፎች ያደሩለት አገልጋዬቹና እንዲሁም ሲያስነጥሰዉ መሃረም የሚያቀብሉት አፍረተ ቢሶች በመሰብሰብ” የዘላበደዉን የአሸነፍኩ ዉሸቱን ለማዳመጥ በተጠራዉ የዉሸት መድረክ በተናገራቸዉ ነገሮች ላይ በተከታታይ ሰሞኑን ስለምንሄድበት ለዛሬ አንድ የምላችሁ አግራሞቴን የሳበዉ በሚቀጥለዉ የምንመለከታቸዉ ንግግሮቹ ላይ ይሆናል።የዚህ ሰዉ ሕይወት ስገመግም ሰዉ ከሚገባዉ በላይ ረዢም ዕድሜ ይኖራል ያለዉ የጁልየስ ቄሳር አባባል ያስታዉሰኛል ።በትግርኛዉ “እግዜሔር ዝፈንፈኖ” (እግዚአብሔር አልወስድህም /አልገድልህም ብሎ ለመሬት ስቃይ የተወዉ” እንደሚሉት ነገር። ዕባብ አከላቱ ተቆራርጦ ወገቡ ተቆርጦም ቢሆን ሲንቀሳቀሱ እናያለን፤፡ አዎን እኛ አበሾች ወይንም ማን እንዳለዉ አላዉቅም በዛሬዉ አነጋገራችን “አምባገነኖች እንደ ድመት ዘጠኝ ህይወት አላቸዉ”የምንለዉ ነዉ ሮማዊዉ ጁልየስ ሴዛር “ሰዉ ከሚገባዉ በላይ ረዢም ዕድሜ ይኖራል” ለማለት የፈለገዉ። ሰዎች ከወንጀላቸዉ ብዛት (በስልጣን ከለላ ፤በጉልበት፤በሕዝብ ስም ተጠልለዉ ለሰሩት ወንጀል ሳይጠየቁበት)ወይንም ከሚበዛባቸዉ ስቃይ ምክንያት መኖር የሚገባቸዉን ህይወት መቀጨት ሲኖርባት (የአልጋ ቁራኛ ሆነዉ በድን አካል ይዘዉ ትንፋሻቸዉ ብቻ መተንፈስ የቻለች)የምታቃስት ህይወት መሞት ሲገባት ከሚገባት በላይ ትኖራለች ማለቱ ነዉ። የወያኔ መሪዉ ትናንት በዛዉ አደባባይ የተናገረዉ የቱልቱላ /ፕሮፓጋንዳ ንግግሩ ላዳመጠ “ጤነኛ ሕሊና”ላለዉ አድማጭ የሚደርስበት ግምገማዉ ቢኖር “ይህ ሰዉ ለሰራዉ ቅጥፈት እና ወንጀል ዉስጣዊ ሕዋሳቱ ምንኛ እየተፈታተነዉ እና እየተሰቃየ እንደሆነ ካዘጋጀዉ ጽሁፍ ከሚያንብባቸዉ የዉሸቶች ዓረፍተነገሮች፤መዋሸት ከሚገባዉ በላይ እየዋሸ በድን አካላቱ ተወጥራ መኖር ከሚገባዉ በላይ እየኖረ እንደሆነ ከአንደበቱ ከሚያ’ሰማዉ ሲቃ መገመት ይቻላል”።መለስ ዜናዊ በእንዲህ ዓይነት ዉሸት ተከብቦ ሲደመጥ የምንደመድመዉ አጠቃላይ ግምገማ ምንድ ነዉ? መለስ ዜናዊ ከሚገባዉ በላይ እየዋሸ እንደ “ሞሶሎኒ”በትምክህት ተወጥሮ በቆለለዉ ዉሸት መዳከሩ የሚያመላክተን ነገር “ሕይወትን ስለወደዳት ሳይሆን፡ ከእዉነት እየሸሸ “ሞትን/ቅጣትን”መፍራቱን ያመላክታል”። ትናንት ከአነበበዉ ወረቀት የተደመጠዉን እስኪ እንመልከት፦ “ይሁንታችሁን ያልሰጣችሁን ዜጎች ቅር ያሰኘንበት ምክንያት አጥንተን ለማስተካከል እንደምንረባረብ፤ በሚቀጥለዉ ጊዜ ይሁንታችሁን ለማግኘት ሌት ተቀን እንደምንጣጣር እስከዛዉ ድረስ ደግሞ የምናቋቁመዉ መንግሥት የመረጠንን ህዝብ ብቻ ሳይሆን እናንተንም በእኩልነት እንደሚያገልግል በድርጅታችን መላ አባልት እና ሰማዕታት ስም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።” (መለስ ዜናዊ ከተናገረዉ ያደባባይ ዉሸቱ “ከአዲስ አበባ የቀጥታ ስርጭት”በሚል በወያኔ ጋዜጠኞች የተላለፈዉ የድምፅ ቅጅ ምርጫ ግንቦት 17 2002/ በፈረንጅ May 25/2010)።ይህ ዉሸት መለስ ዜናዊ የሚዋሸዉ ዉሸት ብቻ ሳይሆን ከሱ ጋር የነበሩት የወንጀል ድርጊት ተጋሪ ግበረ አበሮቹ ዛሬ በአንዳንድ ምስኪኖች “መሪዎች እና ተቃዋሚ” የሚል ስም የተሰጣቸዉ እነ ስየ አብርሃ፤ገብሩ አስራት፤አረጋሽ አዳነ፤ ነጋሶ ጊዳዳ፤ እና ወዘተ…ሰልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሲለፍፉት የነበረዉን የዉሸት ባህሪ ነበር የደገመዉ። ሁሉም በጭንቀት በጭንቀት ዓለም ተወጥረዉ እንደሚኖሩ እናዉቃለን። ይህ በድርጊት የማየተረጎም “እኩል እናገለገልሃልን” ቱልትላ የሚያሳየን ባህሪ እነ መለስም ሆኑ ከላይ የተጠቀሱት የድሮ የመለስ ጃንደረባዎቹ የፈጸሙትን የወንጀል ድርጊት ከባድ በመሆኑ “በይፋ ተገልጦ እንዳይወጣ እጅግ ይጠነቀቃሉ”፤ ይፈራሉንም። እነኚህ ሰዎች ቅጣንና ሞትን የሚፈርዋት መሆናቸዉ በዉስጣቸዉ ፍርሃትን ያነገሰበት አንደበት ከሚሰነዝሩት የንግገር አንደበት ማወቅ ይቻላል።በጣም የለሰለሰ፤ ለሕዝቡ አክብሮት ያለዉ የሚመስል ግን “በድርጊት የማይፈጸሙት” እንደሆነ በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነዉ። መለስ በተቃዋሚዎች ላይ ያስሰማዉ ንቀት፤ማንቋሸሽ፤የተጠቀመበትን “ከዚህ ተማሩ፤ ኑ እናስተምራችሁ…”ፍጸማዊነት እና የትምክህት አንደበት የሚያመለክተዉ ነገር ዉስጣዊ መንፈሱ የተረበሸ አንደሆነ ይጠቁማል። ሁሉም ማለት ይቻላል (እነ ስየ፤ እነ ብርሃነ ፤እነ ገብሩ..ጨምሮ ) በዛች አገር ሕዝብ እና ሉዓላዊነት ለሰሩት ወንጀል ዘርዝሮ ላለመናገር፤ላለመናዘዝ፤ያዩትን ወንጀል ላለመጠቆም በስልጣናቸዉ ቀንብር ስር “ማን ምን”-ግፍ እንደደረሰበት እና እንደተከናወነ፤ለፈጸሙትና ላስፈጸሙት ላለመግለጽ “ ይከሱናል ፤የቀዋሙናል፤በሕግ ይፋረዱናል”የሚሏቸዉን ክፍሎች ዝናቸዉን በማጥፋት/በማንኳሰስ ታጥረዉ የራሳቸዉን ስዕል ላለመግለጽ እጅግ ይጠነቀቃሉ። እያድበሰበሱ ለመሸሽ ይጥራሉ። ለነሱ ያደሩ፤በመንገዳቸዉ የተጓዙ ወይንም ህልናቸዉ በቀላሉ በሰሜት ተገዝቶ የሚታሉ ግለሰቦችን በመሰብሰብ/በማደራጀት ከሚፈርዋት ሞትና ቅጣት ይሸሻሉ። በእንደዚህ ያለ ስልት የመጓዙ ችሎታ ያወቀበት መለስ ዜናዊ ብቻ ሳይሆን መድረክ ዉስጥ የታቀፉት ጃንደረባዎቹም ጭምር “ብዙ የዋህ፤ብዙ ተላላ ኢትዬጵያዊ”-በየዓለማቱ ተስፋ ቆርጦ መሪ አጥቶ የሚያንቀራፋ ማሕበረሰብ እንዳለ እና እንደሚከተላቸዉ ከትግሉ በፊት ጀምሮ የሕዝቡን ደካማ ብልቱን ስላጠኑት በሕልም እያቃዠ ከሚያባርራቸዉ ከሕሊናቸዉ ብቻ “እየሸሹ”በጋሃድ ግን “እዉነትን እየተከተሏት”እንዳሉ እያታለሉ የሞት ሞታቸዉን ሲሞቱ በቁም እየታዘብናቸዉ ነዉ።ከላይ የታዘብነዉ የመለስ ዜናዊ ዉሸት እና ቃል ኪዳን እዉነትን ምንኛ በዉሸት ቢላዉ እየቆራረጠ እየጣላት እንደሆነ ነዉ። ያልመረጠዉ ሕዝብ እንዳለ አዉቋል። ቅር የተሰኘ ሕዘብ ደግሞ በራሱ የድምጽ ማጭበርበርያ ሰንጠረዡ ከመቶ ሕዝብ ምናልባት “ነጥብ አንድ”-እንበለዉ “አንድ-ብቻ”-ነዉ ቅር የተሰኘዉ እና ያልመረጠኝ ብሎናል (.1%)። እንግዲህ ከመቶ ሰዎች አንድ ሰዉ ብቻ በወያኔ የክህደት እና የወንጀል የገበና ማህደር ቅር ከተሰኘ “መለስ ዜናዊ ልጆቻቸንን ከበረሃ ጀምረህ ከግብራበሮችህ ጋር አሁን አስካለህበት ጊዜ ድረስ ገድለሃል፤ አሰገድለሃል፤ብሔራዊ ወንጀል ፈጽመሃል፤በስልጣን ባልገሃል፤ገንዘብ መዝብረሃል፤እንዲመዘበር አስደርገሃል፤ፈጽመሃል፤አስፈጽመሃል፤በሌላ ፍጡር ጉዳት እንዲደርስ አስደርገሃል፤አገሪቷን ለጠላት ክፍት በማድረግ ብዙ ሕይወት እንዲያልቅ ምክንያት ሆነሃል፤ብዙ እናቶች ባንተ ትዕዛዝ እንባቸዉ አቅርረዋል፤….እና ተጠየቅ!.”የሚሉ ክሶች እንድንመሰርት እንችል ዘንድ ተደጋግሞ ለ18ዓመት የጠየቅነዉን “አንተ እና መሰል ባልደረቦችህ ተከሳሾች መንግስትህና ድርጅትህ የማይቆጣጠሩት “ልዩ” ገበና ፈታሽ እና የፍርድ መድረክ፡ እንዲቋቋም ፈቀደኛነትህ አረጋግጥልን”ቢባል መልሱ ምን እንደሚሆን ለናንተ ግልጽ ይመስለኛል። እንኳንና መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ያለዉ ቀርቶ ከወያኔ ስልጣን የተለዩት እነ ስየ እነ ገብሩ ደም በታጠበዉ እጃቸዉ እና ገበናቸዉ “እየሰጡት ያለዉን የመሸሽያ መልሳቸዉን”መገንዘብ ትችላላችሁ።
ዓለም በዉሸት ጎዳና መራመድ ለምዷታልና ምድሪቱ በዕዉነት ጎዳና እንዳትጓዝ ብዙ “ዉሸተኞች” መድረኩን በመቆጣጠር ሕዝቡ ከዉሸት ጎዳና እየሸሸ” ጉዞዉን ቀይሮ “በዕዉነት ጎዳና”-እንዳያደርግ ብቻቸዉን እንዳይቀሩና እንዳይጋለጡ በዉስጣቸዉ ፍርሃት ያነገሰዉን ዉሸት አየዋሹ ዛሬም በዛዉ የዉሸት ጎዳና ሲሮጡ ልባቸዉ አስሬ ሲመታ ይደመጣል። ለዚህም ነዉ መለስ ዜናዊ በዛዉ ፍርሃት ባነገሰዉ ዉስጣዊ ፍርሃቱ በአገርና በሕዝብ ላይ በፈጸማቸዉ እጅግ ከባድ፤ ከባድ ወንጀሎች እሱ እና በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉት ጃንደረባዎቹ አንድ ቀን ለፍርድ መቅረቡ እንደማይቀርለት ስለሚያዉቅ “አሁንም ሕዝባችንን ቅር የሚያሰኙ በርካታ መሠረታዊ ጉድለቶች እንዳሉብን በጥልቀት እንገነዘባለን”-ሲል ጃንደረባዎቹ በተቃዋሚ ጎራ ሆነዉ እየተናገረዉ ያለዉን የድላ ቃላት በቃል ብቻ እነሱም እንደሚደሉሉን ሁሉ እሱም ያንኑ መደለያ “ሕዝብችንን ቅር ያሰኙ በርካታ ጉድለቶች. እንደፈጸመን በጥልቀት እንገነዘባለን” ሲል ተጠያቂነት የሌለዉ የድለላ ቃል ትንናት “የዲሞክራሲ ፌስታ”-ብሎ በሚወዳቸዉ የልብ አማካሪዎቹ በጣልያኖቹ ቋንቋ በሰየመዉ “ፌስታ” *መሠረታዊሲ ወንጀሎች* እንደፈጸመና “ጉድለት ብሎ የጠራዉ ወንጀሉን *በጥልቅ እንደተገነዘበዉም* በኑዛዜ መልክ የተናዘዘዉን አስደምጦናል።ሕዝባችንን ቅር የሚያሰኙ በርካታ መሠረታዊ ጉድለቶች እንዳለበት በጥልቀት ከተገነዘበ ማድረግ ያለበት “የሕዝቡን ቅሬታ ለማጥናት እና ቅሬታዉን ለማዳመጥ በሰማዕታት ስም ቃል ገብቻለሁ” በማለት በለመደበትን የወያነ የዉሽት ባህሪ “ትሬድ ማርክ/መለያ” ከመፏከት መጀመርያ ማድረግ ያለበት “ይህ ይህ ወንጀል እኔ እና ጓዶቼ እንዲፈጸም አድርገናል፤ ዛሬ ተምረናል፤ ለዚህ ደግሞ ተገቢዉ ቅጣታችን ለማግኘት በደል ያደረስንባት አገር እና ሕዝብ፤ሰዎች እና ድርጅቶች በሚፈቅዱት ፍትሕ ሰጪ አካል ተምርምረን ቅጣታችንን ለማግኘት ዝግጁነታችን በሰማእታት ስም ቃል የገባንበትን ዉል ይሄዉ ሕይወታችን በናንተ ላይ ጥለናታልና ኑ ፍረዱን”፡ -ማለት ነበረበት። ነገር ግን እሱም ሆነ ግብረ አበሮቹ በወንጀል፤ የሺሕ ነብሳት ሕይወት እንድትጮህ ያደረጉ ፤ ነብሰ ገዳዬች እና እርኩስ መናፍስት ናቸዉና፤ ሞትና ቅጣትን ስለሚፈሩ “ዛሬ ወይንም ነገ ባጭር ለምታልፈዉ ሕይወት”ለእዉነት ሲል “ሞትና ቅጣትን”የማይፈራ ፍጡር አንድም (አስገደ ገብረስላሴ እና ገብረመድህን አርአያን ሳይጨምር)ከማሃላቸዉ ስለሌላቸዉ ትናንትም ዛሬም ነገም ዉስጣቸዉ ፍርሃት ባነገሰዉ ዉሸት መዋሸትን መምረጣቸዉ የሚያመላክተዉ ቢኖር ዛሬ መለስ ዜናዊ በ99.9%ድምፅ ተመርጫለሁ ሲለን ወያነ ትግራይ የሞት ሞቱ ያየበት ይህ የመጨረሻዉ የፍርሃት ጠርዝ የነካበት ወቅት መሆኑን ላሰምርበትእፈልጋለሁ።/_/-/-/http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com