Tuesday, August 9, 2016

በአማራው ኮለኔል ስም የአንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ያሸበረቀበት የዲሲው ሰልፍ ጌታቸው ረዳ (Editor Ethio Semay)



በአማራው ኮለኔል ስም የአንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ያሸበረቀበት የዲሲው  ሰልፍ
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethio Semay)

አማራው ዛሬም በስሙ እየተነገደበት ነው። ግልጽ ግልጹን እንነጋገር! እኔ ዘንድ ማማት፤መለማመጥ፤ማድበስበስ የሚባል ነገር ብዕሬ ውስጥ ቦታ የላቸውም።  ቢቆጠቁጣችሁ፤ ቢጎረብጣችሁ ምክንያቱን ፈልጎ መፍተሄ መስጠት ይጠበቅባችል።  የምንነጋገረውና መስዋእት ከፍለን አገራችን እና ቤተሰቦቻችን እንዳናይ ለዘመናት እራሳችን መስዋዕት የከፈልንበት ምክንያት እዚህ አገርም የቀረንበት ምክንያት፤ የዜጎችን መብት በፋሺስቶችና በሴረኞች በተገንጣዮችና ተባባሪዎቻቸው ምክንያት ተነጥቋል። ስለሆነም መስዋዕት እየከፈልን ነው። የአማራ ሕብረተሰብ ስቃይ፤ ስቃያችን ነው። የአማራን የሰሞኑን መብረቃዊ አብዮት በሴራ ለመጥለፍ የሚ

The spectacular hero Colonel Demeke Zewde
ሞክሩትን ሁሉ እንቃወማለን።
ሰሞኑን ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ “ጸረ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንገተን ዲሲ ውስጥ” የሚለውን ከዚህ በታች ያለው ርዕስ ‘You Tube ’ ላይ የተለጠፈው ጉጉል ብታደርጉት ( Protests against the TPLF in Washington Dc https://youtu.be/WdwTvU7TxiI ) የምንነጋገርበት ርዕስ ትረዱታላችሁ።

Andargachew Tsige instead of Colonel Demeke
ተሰላፊዎቹ አሸብርቀው የተሰለፉበት ያገራችን ሰንደቃላማ እጅግ የሚያኮራ ቢሆንም፤ አማራውና የአማራውን አስደናቂ ትግል ክርቢት ጭሮ ያደመቀው ጎንደሬው ጀግናው ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ስሙም አልተነሳም፤፤ፎቶግራፉም ይዞ የተሰለፈ ሰልፈኛ አልነበረም፤ ገድሉም አልተወሳም።  በምትኩ የግንቦት 7ቱ መሪው በነገዴ ‘ኦሮሞ’ ነኝ ብሎ የነገረን የኢሳያስ አፈወርቅ አወዳሽና ጸረ አማራው “የአንዳርጋቸው ጽጌ” ፎቶግራፉ በተደጋጋሚ ከፍ ብሎ በካሜራ ሲቀረጽ ነበር

በዛው ሳይወሰኑምን ታመጡተብሎለዓይናችን ድፍረትየግንቦት7  የበላይ ተቆጣጣሪ የሆነው የኢሳያስ አፈውርቂ ባንዴራ ከኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ጋር ሲያፎካክሯት ውለዋል። (ሰልፈኞቹ ላገራቸው ሉአላዊነት ቆመናል የሚሉ ከሆነ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ማንኛቸውም የድርጀቶችም ሆኑ የመሳሰሉ ምልክቶች፤መፈክሮችና ባንዴራዎች ከሰለፋቸው ላይ ለምን እንዲታደጉ እንደማየደርጉ ለኔ አይገባኝም) ካሜራውም፤ ብዙ አመራዎችና ትዮጵያዊያን ሲገደሉ የተውለበለበች የሻዕቢያን ሰንደቃላማ ልክ  እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ለዓናችን እይታ ደጋግሞ ሲቀረጽልን ውሏል።

the Narrow Nationalist Bekele Gerba photo Replaced Colonel Demeke  in Wshington Ethio protest

Shaabiya flag contaminating our flag
ይህ ብቻ እንዳይመስላችሁ። አሜሪካ ውስጥ በኢሳት ቲ/ቪ ቀርቦ “አማራው የኦሮሞን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት” ብሎ በድፍረት የምላሱን ቆሻሻ ተጸዳድቶብን የሄደው ጠባብ ብሔረተኛው በቀለ ገርባም በተደጋጋሚ ፎቶግራፉ አሸብርቆ እንድናየው ካሜራው የተቻለውን ያህል ጥረት አድርጓል።

ይህ ሁሉ ጉድ ስመለከት ንዴቴም የልቤን ትርታ ሸሚዜን ቀድዶ ለመውጣት ትግል ገጥሞ ነበር። ራሴን ለማበርድ ብሞክርም፤ ያው የአማራው አብዮት የአንዳርጋቸው እና የበቀለ ገርባ፤ እንዲሁም የሻዕቢያ ባንዴራ እንዲውለበለብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለታሪክ እንዲቀር ሆን ተብለው የታሪክ ጠለፋ ተፈጽሟል።  የፈጸሙት ኦነጎች/ሻዕቢያዎች ቢሆኑም፤ የሴራው ግምባር ቀደሙ ተዋናዩ ‘ግንቦት 7’ መሆኑን ስለማወቅ ንዴቴ አልብርድ ብሎ ከኔው ጋር ሲታገል ቆይቷል።

ሕዝቡ የምናውቀው በስሜት የተበረዘ፤ አገራዊ እሴቶች ተጠልፈው በኢትዮጵያ ሰልፎች ውስጥ በሴራ በጥናት “ሳብቨርስ”/ሲበረዝ፤ ከመጮህና ከመጨፈር፤ከማንጨብጨብ አልፎ እማሃላቸው ውስጥ የሚውለበለቡ የጠላት እሴቶች እና ምልከቶች፤ ባግባቡ ለብረዛ የተደረጉ ሴራዎች መሆናቸው ሊረዳቸው ያልቻለ ማሕበረሰብ ነው። 

ይህ ነገር አንድ ነገር አስታወሰኝ። በውጭ አገር ጸሐፊ ተጽፎ “በዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ደሳለኝ አለሙ” የተደበቀው ማስታወሻ በሚለው (የጣሊያን እና የኢትዮጵያዊያኖች ጦርነት የዘገበ ታሪክ ነው) መጽሐፍ ውስጥ “የግርማዊ ጃንሆይ ቀ.ሃ” አርቆ አሳቢነትን ሲያደንቅ፤ እንዲህ የሚለውን አስታወሰኝ፤

“ይህንን አደጋ በደምብ ተረድተው የነበሩት የመጨረሻው ንጉሥ ነበሩ። ሰዎቻቸውን ለማስረዳት፤ ለማስገንዘብና የነበረውንም ሁኔታ ለማሻሻል ሞክረው ነበር። ነገር ግን አንድ ብቸኛ በሰውነት ደቀቅ ያለ ሰው ከአሥራ አምስት ሚሊዮን ስንፍና የተሞላበት አንጎል ጋራ ምን ፋይዳ ማምጣት ይቻላል? ላመሻሻል የነበራቸውን ብርቱ ምኞትና ፍላጎት አጡ።” ይላል ስለ ጦርነቱ ሁኔታ በሰፊው ጦርነቱ ውስጥ ተካፋይ ሆነው በዓይናቸው ያዩት ደራሲ ዶ/ር ሀረልድ ናየስተሮም (ካልተሳሳትኩ ደራሲው ስዊዲናዊ መሰሉኝ)።

እውነት ነው። ደራሲው እንዳሉት ደጋግመን ለብዙ አማታት ግንቦት 7ም ሆኑ የተለያዩ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎችና ሻዕቢያዎች፤ በከፍተኛ ጸረ አማራ ባሕሪ የሚሰቃዩ የጥላቻ በሽተኞችን መሆናቸውን ደጋግመን በማስረጃ ብናስረዳም፤ የአማራን ሰው በራሱ ላይ የሚፈርዱበትን ያለፉትም ሆኑ የመጪው ዘመን መከራ የሚያቅዱለት ድርጅቶችን ለይቶ መገንዘብ አልቻለም (ጎንደር ይሁን በባሕር ዳር? ላይ አማራን ነፍጠኛ እያለ የሚሳደብ ድርጅት (ግንቦት 7) ሲመራ የነበረው አንዳርጋቸው ጽጌ እና እንዲሁም የበቀለ ገርባን ፎቶግራፍ ታቅፈው ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ በቪደዮ ተቀርጾ አይቻለሁ)። በኮለኔሉ እና አብረውት  በእሰር ላይ ያሉ የወልቃይት ኮሚቴ መሕበረሰብ ጅግኖች ምትክ የእነ ኣንዳርጋቸውና የነበቀለ ገርባ ፎቶ ጎልቶ አንዲታይ ብረዛ እንዲከናወን ጠለፋው ባስገራሚ ሜላ ተከናውነዋል። ሕዝቡስ ግንዛቤ አለው? ይህ በማን አቀነባባሪነትና ሴራ አንዲተከናወነ ለኔ ግልጽ ነው። ህዘቡ እሰካልነቃ ድረስ ጠለፋው የሚያቆም አይደለም። 

ሕዝቡ ግንዛቤውን ለማዳበር እራሱን እና አካባቢውን እንዲፈትሸ ከስሜት እንዲርቅ አውነተኛ ግንዛቤ እንዲያድርበት ያለውን ሁሉ መረጃ አቀብለናል፤ ፤ጽፈናል፤ ተከራክረናል። ከዚህ ወዲያ ተደጋጋሚ ሰንፍና እየተመላላሰ የሚነዳው ከሆነ፤ በሚሊዮን ስንፍና የተሞላበት አንጎል ጋር እስኪበቃን ድረስ በንጽፍም ምን ፋይዳ ማምጣት ይቻላል? ተመልሶ ወደ ጭቃ መግባቱ አይቀሬ ነው።

ያለ ምንም ጥርጠር የሰሞኑ አብዮት አማራው ባስደናቂ ሕዝባዊ አብዮት ዋኝቶ ማንነቱን አስመስክሯል።በጠመንጃ ጠላቶቹ ጋር ተጋጥሟል። ለዛው አመርቂና ጀግንነት ፈጠሪውና ተዋናዩ ማንም ሳይሆን  አማራው እራሱ ነው! መብረቃዊው ብልጭታው ወደ ነጎድጓዳማ ዝናብ ተለውጦ ሞገደኛ ጎርፍ በመፍጠር ወያኔዎችና መሰል ጠላቶቹ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ  ከትቶ ደምብረው በየአቅጣቻው እንዲሸሱ አድርጓቸዋል። ኦነጎችም ወደው ሳይወዱ፤ ግንቦት 7ም ወዶ ሳይወድ “አማራን ነፍጠኛ” እያሉ ‘አማራ’ ለማለት ሲጸየፉት የነበረው ‘መስተጻውእ’  “አማራ” ብለው እንዲጠሩት ባስገራሚው አብዮት አስገድዶአቸዋል። 

አማራው በስንቱ ተዋርዶ፤ ተስድቦ፤ ተገድሎ፤ ተዘርፎ፤ ተባርሮ ያየነው ታሪክ እንዳይበቃ ፤ዛሬ ደግሞ እራሱ የለኮሰውን አብዮት መሪዎቹ እኛ ነን እያሉ ግንቦት7ም ሆነ “አስመራ” ውስጥ  የመሸገው “አማራ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ” ብሎ ራሱን የሚጠራ ጅላጅል “ግምባር ቀደም ሆነን እየመራነው ያለነው እኛ ነን”  ሲል በዘሐበሻ /ሕብር ራዲዮ ላይ የተለጠፈውን “አውድዮ” አድምጠነዋል። ባሕር ዳር እና ጎንደር ውስጥ ለኢሳት ደውለው “ብርሃኑ ነጋ” አስመራ ውስጥ  መሽጎ ምን እየሰራ ነው? ዛሬ ካልረዳን መቸ ሊረዳን ነው? እኛ እንኳ ባዶ እጃችን እየተጋፈጥን እነሱ ጠመንጃ ታቅፈው አስመራ ውስጥ ምን ይሰራሉ? ብለው ነው ደውለው የገዛ ጣቢያውን እውነታውን የነገሩን። ሁሉም የዚህ ሕዝብ አብዮት ለመጥለፍ ያልተደረገ ሴራ የለም።ዛሬ ይባስ ብሎ ዲሲ ውስጥ የተደረገው ሰልፍ ስንመለከት እኔ እና ወዳጆቼ እጅግ አስገራሚ ሆኖ ነው ያገኘነው።

አስገራሚው ነጐድጓዳው “የአማራው አብዮት” ክርቢት እንዲለኮስ ግምባር ቀደም ምክንያት የሆነው የኮለኔል ደመቀ ዘወዴን መስዋእትንትና ጅግንነትም ሆነ ፎቶግራፍ ለታሪክ ሳይቀርብ ሆን ተብሎ በግንቦት 7 መሪውና በጸረ አማራው በቀለ ገርባ ፎቶ ግራፍ ተተክቶ እንድናይ መደረጉ ልባችን ቆስሏል።

ምፅዋ ላይ ደራሲ ‘ታደሰ ተሌ’  ጀኔራል ተሾመ ተሰማ “የጀግናውን የአፄ ቴድሮስን ዕድል በማግኘቴ እደለኛ ነኝ” በማለት ሽጉጣቸውን ጠጥተው በጀግነት መቃብራቸው በቀይ ባሕር ውስጥ ማድረጋቸው ባስገራሚ ብዕሩ ነግሮናል። ዛሬም “ዘራፍ! ዘራፍ!የጐንደር ልጅ! ጎንደር ተወልጄ፤ከቴዎድሮስ አጥንት ወጥቼ፤ እጄን ለፋሺስት አምላኪ አልሰጥም” ብሎ ጀግንንት አሳይቶ ተኝቶ የነበረውን መላው የአማራ ሕዝብ ባስገራሚው ማዕበላዊው ውቅያኖስ እንዲዋኝ ምክንያት የሆነው ደመቀ ዘወዴን በማንኛውም ሕዝባዊ ስብሰባና ሰልፍ መርሳት እጅግ አስነዋሪ ድርጊት መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ። 

ማገዶ ሆነው የአማራን ሕብረተሰብ ውርደት እንዲያከትም ለዳግም መወለድ ምክንያት የሆኑትን እንደ እነ ደመቀ ዘወዴ ያሉት ከሕዝብ የወጡ ያልተጠበቁ፤ያልታሰቡ ሕዝባዊ ጀግኖች ብቅ ብለው ወደ መድረክ ሲወጡ እንደገና “እንዲቀበሩ” የሚያደርጉ ሴረኞችን እንቃወማለን።

 አማራው በራሱ አብዮትና ትግሉ እራሱን ከከበቡት ጠላቶቹ እያስተዋለ እራሱን ነጻ ያወጣል! በዝውቹ ጽሑፎቼ በ welkait.com ድረገጽም ስለሚታተም እዛውም ብዙ ሰነዶች ስለሚለጠፉ ድረገጹን ተከታተሉት።

አመሰግናለሁ!

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ/ Ethio Semay) getachre@aol.com