Monday, February 27, 2023

ግራኝ አሕመድና የአብይ አሕመድ የአባት ስም መመሳሰል ብቻ ሳይሆን በግብርም አንድ ሆነዋል ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) February 27/2023


 የግራኝ አሕመድና የአብይ አሕመድ የአባት ስም መመሳሰል ብቻ ሳይሆን በግብርም አንድ ሆነዋል

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

February 27/2023

የምናስታውሰው ጸረ ወያነ ትግላችን ከባድ ነበር። ሊወገዱ የማይመስሉት አጋንንቶች ተወገዱና ሌላው ግራኝ አሕመድ የሚመስለው ኦሮማዊው ጋኔን ብቅ ብሎ ትግላችንን ጠልፎ እርሱና ተከታዮቹ ኢትዮጵያን ገነጣጥለው የራሳቸው አገር ለማድረግ እየሄዱበት ያለው የ5 አመት ጉዞ የብዙ አማራ ማሕበረሰብ እና የብዙ ኢትዮጵያውያን ህይወት በልቷል።

ይህ ከመምጣቱ በፊት አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ከጥቂት የትዝብት ቆይታ በላ “የጥገና ለውጥ እንጂ ሥር ነቀል ባለማካሄድ እራሴ አሸጋግራችኋለሁ” ሲል የሰውየው ዓላማ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሆነ በከፋ መልኩም የአእምሮ በሽተኛ እንደሆነ ስናስጠነቅቅ፤ የፖለቲካ መሃይሞች ከነ ዲግሪ እውቀታቸው በመደመር ሰበብ ሰክረው በሰውየው አሳሳች ምላስ መረቀኑ አንጨበጨቡ። ሌላ ቀርቶ ለጸረ አማራው ለግንቦት 7ም ለጃዋርም ጃኖ አለበሱት፤ የአብይ ፎቶ በደረታቸውም ሆነ በፌስ ቡካቸው ላይ አሸበረቁት። አማራውን ለማንቃት ስንጽፍ ከአማራዎቹ ወገን በግል የስድብ ናዳ በዚህ ፌስቡክ አስተናግጃለሁ። በዚህ ለውጥ ተብየው ወቅት የብዙ ዘመን ወዳጆቼ የአብይ ደጋፊ ሆነው ስላገኘሁዋቸው ከብዙ የረዢም ጊዜ ወዳጆቼ ተለያይቻለሁ። የኔ መስመር ልክ ነበር የነሱ መስመር የተሳሰተ በመኖሩ ቆይታችሁ ትነቃላችሁ ባልኩት መሰረት ብዙዎቹ ከዚያ ድጋፍ ወጥተዋል።ከማመስገን ሌላ ምንም አንልም።

በወቅቱ ወዳጆቼ አብይ ‘’አገር ወዳድ ነው፤ ዲሞክራቲክ ነው፤ሰላምና ፍቅር አንጋሽ ነው’’ ቢሉም ‘ማጠንጠኛው ግን” አብይ የሚመራው ሥርዓት “ቅኝ ገዥ እና ሽብርተኛ ነው” ስንል በምክንያት ነበር። እነሆ ተረጋግጧል።እሱ እየሄደበት ያለው መስመር በወያኔዎች መስመር ሆኖ ወያኔ  ያሰመረበትን የመገንጠል ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ነው። ኦሮሚያ የተባለ አገር ለመመስረት ዋና ከተማም “ሸገር” የተባለ የብድር ስም በመንጠቅ አዲስ ከተማ ለመመስረት ኦሮሞ ያልሆኑትን ዜጎች የመኖርያ ቤቶች በቡልደዘር እያፈረሰ ህጻናትን እና በሽተኞችን በሺዎቹ ወደ ጎዳና እየጣለ ይገኛል።  

ለብዙ ዘመናት ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል (እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ዛሬም ሥልጣን ላይ ናቸው)። ኦነጎች እና “የኦሮሞዎቹ ፖለቲካ” “ታጥቦ ሊጠራ አይችልም” እያልኩ ለብዙ አመታት ስከራከር የነበረበት ዋናው ነጥብ ይኼው ነበር። ዛሬ በተከታታይ ያያችሁት የኦሮሞዎች ፖለቲካዊ ፤ ስነ ኣእምሮአዊ እና የባሕሪ ስነምግባር ጥልቅ ማስረጃ አያሻውም። በአደባባይ ሰው ከመስቀል እስከ የአገሪቱ ሰንደቃላማ ከተሰቀለበት እያወረዱ መጣል እና አማርኛ ጽሑፍ በሚኖሩባቸው ከተሞች እንዳይታዩ በቀለም ማጥፋት፤ አሮሞ ያልሆኑትን ህጻናት ተማሪዎችን የኦሮሚያ መዝሙር እንዲዘምሩ ማስገደድ ሁሉ ያሳዩት ስነምግባር ስንከራከራቸው ለነበሩት የ30 አመታት ክርክራችን ሳይሸማቀቁ አረጋግጠውልናል።

ትንሽ ለትውስታ ወደ 4 አመት ወደ ሗላ ልጎትታችሁ። ኦነግ የተባለው በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ የፈጸመ የነበሰገዳይ ቡድን ሸሽቶ በጥገኛነት ተጠልሎ ከነበረበት የኤርትራ ምድር ለቆ 1300 ሰራዊቱን (ብዙውን ጊዜ ቶክስ ተካፍለው የማያውቁ ፤ በ40 አመት ትግሉ ያፈራቸው 1300 ተዋጊዎች ብቻ ናቸው እና) ይዞ በአጣዳፊ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄድ በኢሳያስ ትዕዛዝ በተሰጠው ማዘዣ መሰረት አዲስ አበባ ገባ።ከዚያም ዜናው ተሰምቶ ሊገባ ነው ሲባል ‘ቄሮ’ የተባለው በዱር ሕሊና የተበረዘ የኦሮሞ ወጣት የሪፖርትር ጋዜጣ ዜና ዘጋቢ ዮሐንስ አንበርብር 14 September 2018 የዘገበውን ዜና እንዲህ ያለውን ላስታውሳቸሁ፡-

በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል” ይላል።  በማቀጠልም

የፒያሳ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተረኛ መኰንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 700 የሚሆኑ ወጣቶች ጭነው የመጡት መኪኖች በአካባቢው ወጣቶችና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሪፖርተርም ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተገኝቶ፣ በአማርኛ መግባባት የማይችሉ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች የሕክምና ዕርዳታ ሲጠብቁ ለማስተዋል ችሏል፡፡”

በማለት በዜና የተዘገበውን ስትመለከቱ  አብይ አሕመድ የግራኝ አሕመድ ምስል በመላበስ እርሱና መሰል ተገንጣይ ጓዶቹ፤ ኢትዮጵያ መዳከምዋን ስለተመለከቱ ኢትዮጵያን ለመገነጣጠልና የሰላማዊ ዜጎችን ንብረት ለመዝረፍና ሰላም ለማወክ ጭፍራዎቹን በሚና አስጭኖ ወደ አዲስ አባባ በማስገባት የተጠቀሙበት ስልት ስንመለከት የተግማማው የኦሮሞዎች ፖለቲካ ለበርካታ አመታት ለተከታተልን ሁሉ አብይ አሕመድና እና ግራኝ አሕምድ የአባት ሰም መመሳሰል በቻ ሳይሆን በግብር መመሳሰልም አንድ ሆነዋል

አሕመድ ግራኝ ኢትዮጵያን በማዳከም የተጫወተው ሚና ጠባሳው ዛሬም እየታየ ነው። አብይን እንደ አሕመድ ግራኝ ሳወዳድር የሚገርማቸው ሰዎች እንደሚኖሩ አልጠራጠርም። አብይ አሕመድ እንደ ግራኝ ክርስትያንን ለማጥፋት የተነሳ እንደሆነ ባለፈው ሰሞን አሳይቶናል። የሚከተለው ሃይማኖት ጴንጤ ቢሆንም የመጀምሪያ ሃይማኖቱ የሥልጣን ጉጉት እና አገር ማፍረስ ነው። በደደቡብ ኢትዮጵያ እና ኦሮሞ ክልል የራሱ ተከታዮች ጴንጤዎችና መሰል የሃይማኖት አጭበርባሪዎች በሃይማኖት ስም የሕዝቡን ገንዘብና ቀልብ እየዘረፉ ሰልበውታል። ይህ እንዲሆንም ፈቅዶላቸዋል፤፡ አገር አፍራሾችም ቃል በገባላቸው መሰረት፤ ኢትዮጵያን አዳክሟታል። ከግራኝ አህመድ ዘመን ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የሰው ልጅ በአደባባይ ደብድቦ እንደ ክርስቶስ መስቀል፡ 11 ቤተክርስትያና ባንድ ቀን መውደም ቁጥራቸው ያልታወቀ ቀሳውስት እና ምዕመናን እንዲሁም አምሓራ የሆኑ የእሰላምና ተከታዮች በዘግናኝ አገዳደል ተገድለው የዘር እልቂት ተካሂዷል። የተከናወነውም በመደመር ስልት፤ወያኔዎች ከኋላ ሆነው በሚሊዮን ሕዝብ እንዲያልቅና እንዲፈናቀል፤ ህይቱ እንዲመሳቀል አድርገው አንደኛቸውም በዓለም አቀፍ ሕግ አልቀረቡም። ለዚህ ወንጀል ተጠያቂው አብይ እና ተከታዮቹ ናቸው የሚል ግን ለሕግ እስኪቀርብ ድሰር የሚቆም ክስ አይደለም።

ይህ አልበቃ ብሎ ‘በወንጀል መጠየቅ ያለባቸው፤ በዘር ማጥፋት መከሰስ ያለባቸው ነብሰገዳዮች ሁሉ ነብስ ባጠፉባት መሬት እንደገና ተመልሰው መጥተው ‘ዛሬም’ በድጋሚ እየጨፈሩ ባንዴራቸውን እያውለበለቡ ወንጀል እንዲፈጸም በር ከፍቶላቸው፤ያለ ምንም ሰቀቀን ሰው እየገደሉ፤ መሬትም ንብረትም እየዘረፉ ይገኛሉ።  አሸዋ ሜዳ ቡራዩ ከፋ እና አስኮ በተባሉ ኢዲስ አበባ ከተማ የከበቡ ቦታዎች በሚኖሩ የጋሞ እና አማራ ተወላጆች ላይ የንብረት ዘረፋ፤የድብደባ እና የግድያ ወንጀል በመፈጸም የተጀመረው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተጠናክሮ ወደ ወለጋ እና ጋምቤላ እንዲሁም በመሳሰሉ ከተሞችና ገጠሮች ቦታዎች አማራን እያደኑ በሺዎቹ ምናልባትም በሚሊዮኖች የዘር ማጽዳት ዘመቻ ተጠናከሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል። አብይ አሕመድ፤ (ኦሮሙማ ኢትዮጵያ ጠ/ሚ) ሽመልስ አብዲሳ (ኦሮሞ ክልል ሓለፊ)እና አበበች አዳኔ (ሕገ ወጥ አዲስ አባባ የኦሮሞዎች ወኪል ከንቲባ ተዋናይዮችና ተጠያቂዎች ናቸው።

ዳግማዊው ግራኝ አብይ አሕመድ አብይ የሚመራው ሥርዓት በነገዱ ኦሮሞ ባይሆንም ኦሮሞ ጠ/ግዛት ጅማ በሻሻ ኦሮሞዎች ጋር ስላደገ፤ ኦሮሞወ ተገንጣዮች የሚያራምዱዋቸው ማኒፌስቶዎች እና ምልክቶች እርሱም የሚጋራቸው ስለሆነ ለኦሮሞዎች የልብ ልብ ሰጥቶአቸዋል። አንዳንድ ጋዜጠኞችና ተንታኞች አብይ ኦሮሞ አይወክልም ሲሉ አድምጠናል፡ ሆኖም ያ ስሕተት ነው። አመጣጡን ማየት አስፈላጊ ነው፤፡ ታስታውሱ እንደሆነ አቶ በየነ የተባሉት ከኦሮሞ ገዳ መሪዎች አንዱ “አብይ ባይመረጥ እያንዳንዳችን ኦሮሞዎች ቢላዋና ገጀራ ይዘን ታጥቀን ተዘጋጅተን ነበር” ብለው ያሉት ማስታወስ በቂ ነው። ኦሮሞዎች ሥልጣኑ ሊቆጣጠሩት የተፈለገበት ዋናው ዐይነተኛ ምክንያት ኦሮሞዎች በወያኔ ዘመን የማይገባቸውን 3/4 ኢትዮጵያ መሬት በዋናነት እንዲይዙ እና ያልነበረና በታሪክ የማይታወቅ ስም በመስጠት “ኦሮሚያ” እንዲባል ጥቅም ያገኙ ቢሆኑም ፤ወያኔ በነበረበት ወቅት “ኦሮሚያ የሚባል አገር” እንዲመሰርቱ ስላልፈቀደላቸው፤ ዛሬ አብይን በሴራ እና በተንኮል ወደ ሥልጣን በማስገባት ኦንግን የሚያክል በጣም አደገኛ እና በዘር ማጥፋት የተከሰሰ ወንጀለኛ ቡድን ወደ አገር ገብቶ ፓርላማ ውስጥ በማስገባትና የሚኒሰትር ቦታዎች እና ወታደራዊ እርከኖች እንዲይዙ የራሳቸውን ባንዴራ እንዲያውለበልቡ እና አገር እንዲመሰርቱ ቀስ እያለ አብይ አሕመድ መንገዱን እየጠረገላቸው ነው።

ይህ አባባሌ የማይስማሙ ሰዎች ቢኖሩ አብይ እራሱ ከእስራል “ከነሴት” ፓርላማ ጋር በማነጻጸር የነገረንን ላስታውሳቸው። << ኦሮሞም ሆነ ኦጋዴን ሶማሊ እንዲሁም ትግሬውም ሆነ ሌሎቹ ልገንል የሚል ጥያቄ አቅርቦ ወደ ፓርላማ ማመልከቻ ካስገባም ሆነ የመገንጠል መሪ አላማውን ለማሳካት ወደ ፓርላማ ባለሁ ካለ ፓርላማ ውስጥ ገብቶ ሕዝቡ ዘንድ ሄዶ የማስገንጠል አጀንዳውን አስመዝግቦ በሬፈረንደም ማስገንጠል ይችላል>> ያለውን አስታውሱ። “አብይ ግራኝ አሕመድ” የትግራይ ወንጀለኞችን የኦሮሞ ወንጀለኞችን የጉራጌ የወላይታ የሶማሌ ወንጀለኞችን ወዘተ… ሁሉ እንደ መርከብ ኖህ ባንድ መርከብ አሽጎ ከግብጽ ከአሜሪካ ከአስመራ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ በማስመጣት በሕዝባችን ላይ ዳግም ወንጀል እና የዘር ማጥፋት እንዲፈጽሙ በማድረግ ይኼው ከግራኝ አሕመድ ወዲህ ያልታየ የሰው ህይት ጭፍጫፋ እየተካሄደ ነው።

አናርኪው አብይ አሕመድ በሚያስቅ አነጋገሩ “ፓርቲዎች ሳይሆኑ አሸናፊው ሕዝብ ነው” የሚለውን ንግግሩ ኮሚኒስትነቱ እና አናርኪስትነቱን ያልለቀቀው መሆኑን ደምበኛ አመላካች ንግግር ነው። ማወቅ ያለባችሁ ሕዝብ የሚባል የለም። ሕዝብ የግለሰቦች ስብስብ ማለት ነው። ግለሰቦች ደግሞ ዛሬም ቤቶቻቸው ውስጥ የንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ቤተክርስትያኖቻቸው ውስጥ እንዳሉ የሚገደሉበት የሚዘረፉበት ፤ባደባባይ እንደ ክርስቶስ የሚሰቀሉበት ሥርዓት እና ዘመን ውስጥ ባለበት ወቅት ሕዝብም ሆነ ግለሰብ አሸንፏል ብሎ መናገር እንደ “አናርኪስቶች” አብይ እና ለማ መገርሳ እንደ ዳውድ እና እንደ እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲሁም እንደ የሁሉም ቤት ወጥ ቀማሹ ታማኝ በየነ የመሳሰሉት በሕልማቸው የሚቃዡት ቅዠት ነው። ታማኝ ኢትዮጵያዊነት ነው እንጂ አማራነትን መደራጀቴን አልወደውም ይል እና ኦሮሞዎች መንደር ሲሄድ ደግሞ የኦሮሞዎች ሰንደቃላማ የተጣፈበት ልብስ ለብሶ ያሸበርቅ እንደነበር ይታወሳል።ዘመኑ ዘመነ አናርኪ ነው የምለውም ለዚህ ነው። በርካታ አድርብ ባይ እና ነብሰ ገዳይ ሁሉ መንገዱ ጨርቅ ሆኖለታል። መደመር ሌላኛው የአናርኪ (ስርዓተ ድብልቅልቅ) ስም ነው። 

እንደምታውቁት ‘ኦሮሚያ” የሚባል መሬት በታሪካችን አይታወቅም!!!!!!! ኦሮሞ ብለው ራሳቸውን እየጠሩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው ተዋልደው እየነሩበት ያለውን አሁን ያሉበት ቦታ ከግራኝ ዘመን ወዲህ ከገናሌ/ባሌ ወንዝ አካባቢ ተሻግረው ጋሎች የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ነገዶች ሲኖሩበት የነበረውን መሬት ነው ዛሬ ኦሮሚያ ብለው እየጠሩት ያለው። ቆየት ብለው ደግሞ በጣሊያን ማኒፌስቶ የሚያምኑ የወያኔ ትግሬዎች በ1983 ኦነጎች በሰጡዋቸው የወረራ ካርታ (3/4) አጽድቀውላቸው ኦሮሚያ ብለው አስፍተው እንደገና ሰጥዋቸው። ካልሆነ ኦሮሞ የሚባል ቦታ ከግራኝ አሕመድ በፊት የሚታወቅ ምንም ቦታ በኢትዮጵያ መልክዓ ምድር አይታወቅም። ነብሳቸውን ይማር ፤ ወዳጄ እና መምህሬ የተከበሩት ታላቁ የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴን በማስረጃ ላቅርብ።

We have the irrefutable contemporary Portuguese testimonies, such as the historic map of Alvarez enumerating all the provinces of pre-ኦሮሞ Ethiopia in 1520. There is no ኦሮሞ-land mentioned anywhere. More importantly we have the chronicle of Shihab ad Din, the biographer of Gragn Ahmed who has recorded in his "Futuh al habasha"(the Conquest of Abyssinia) (1519-1539) where the conquered Ethiopians are described village by village, a work which has been translated with enormously useful and instrumental foot-noting by the well known French scholar Rene Basset. And no where do we see a reference to the ኦሮሞ..”

 ከላይ የተጠቀሰው ጥቅስ “ጋላ” የሚለው በራሴ “ኦሮሞ” እያልኩ ለውጨዋለሁ (የደራሲው መብት በመጋፋቴ እየጠየቅኩ) “ጋላ” አትበሉን እኛ “ጋላ” አይደለንም “ኦሮሞ” እንባላለን ባሉት መሰረት “ኦሮሞ” እያላችሁ ጥሩን ባሉት መሰረት እንጠራቸዋለን። ለኛ ግብር አንጂ ስም ልዩነት ግድ የለንም። ‘ከ500 አመት በፊት “ዜናሁ ለጋላ’ በሚል ርዕስ የያኔው “የጋላ ታሪክ” የጻፉ እና ለዛሬዎቹ ኦሮሞዎች ትውልድ በዝርዝር ጽፈው ትተውላቸው የሄዱት የጋሞ ጎፋ ሰው የነበሩት ‘አባ በሕርይ’ የተባሉት የገዳም አስተዳዳሪና የዘመኑ ሊቅ በፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ እና በዶክተር አለሜ እሸቴ መካከል በነበረው የቅጅ ባለቤትነት (ኮፒ ራይት) አለመግባባት አስመልክተው “ለኔ ጌታቸው ረዳ የተላከ” በሚል የኢሜይል መልእክት ከላኩልኝ የተገኘ ምንጭ ነው)።

ኦሮሞዎች የራሳቸው ጽሕፈት እና ፊደል ስለሌላቸው አባ ባሕሪ በግዕዝ ጽፈው የተውላቸውን የትውልድ ሐረጋቸው፤አስተዳደራቸው ኑሮአቸው እና ታሪካቸው ከማመስገን ይልቅ ሲዘልፏቸው ማድመጥ እጅግ የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው። ዛሬ ኦሮሞዎች “ቄሮ” ‘ሜሮ’  ምናምን እያለ ሰውን ባደባባይ አንደ ክርቶስ ከነነብሱ እየሰቀለ ያለ ‘አናርኪ’ ሁላ ከ30 አመት በፊት “ኦሮሚያ” የሚባል መሬት ነበርን የሚለው ጥያቄ ሊመልሱት አይቻላቸውም። ይህንን ውስጣቸ ቁት ያንን ኢ- ሕጋዊ የቦታ መቀራመት ሕጋዊ ለማስመሰል ያለነበረ ባንዴ በመፍጠር የማንነት ችግር ያለበት ኦሮሞ ያልሆነው አብይ አሕመድ አጀንዳቸውን እያቀላጠፈላቸው ይገኛል።

የአብይ አሕመድ ግራኝ ዘመን “ኦሮሚያ፤ኦሮሚያ፤ኦሮሚያ፤ ያም የኔ፤ ያም ኬኛ፤አንደ ህጻን አሁሉንም የኔ ነው ብሎ ማግበስበስ” እያየንበት ያለው አስገራሚ ዘመን በኢትዮጵያ ጫንቃ እየተፈጸመ ነው።

 ዛሬ ወያኔዎች በኢትዮጵያዉያን ቁጣ ልክ ቢገቡም፡ አብይ ብቻውን እየሆነ እየተገፋ ሲሄድ እንደገና የወንጀል አጋሮቹ ወያኔዎች ጋር አብሮ ለመስራት እየጣረ ባለበት ወቅት  ይህ የግራኝ አሕመድ ዲቃላ መሳይ በሽተኛ ከሥልጣን ለማስወገድ ሕዝቡ ማድረግ የሚገባውን ድርሻው እያደረገ ስላልሆነ ሕዝቡ አገሩንም ሆነ እራሱ ጨርሶ ከማለቁ በፊት ደግመን ደጋግመን የምናደርገው ጥሪና የማንቃት ተግባር በማጠናከር አብይ አሕመድ ባልነበረበትና ባልተወለደበት ዘምን የተከናወነውን የአፄ ምኒልክ የዓድዋን ድል መሪነት “እኔ የመራሁት ነው እያለ ለመሻማት” እያደረገ ያለው አስደንጋጭ የሆነ “የሕሊና በሽተኛነት ምልክት” ስለሆነ አገራችን ከዚህ በሽተኛ ግለሰብ ነፃ ለማውጣት ትግላችሁ ዛሬም “ኢትዮጵያ ወይንም ሞት! የምትሉ ‘ኦሮሚያ ወይንም ሞት’ ከሚሉ ፋሺስቶች መሆን እንዳለበት የብዙ አማታት ትግላችን ዛሬም ህያው ትግል ሆኖ መቀጠል አስፈላጊነቱ እየጎላ በመምጣቱ ያንን ተግባራዊ ላመድረግ ሕዝቡ ተኝቶበት ካለው ከባድ እንቅልፍ እንዲባንን ዛሬም በድጋሚ ጥሪያችን እናስተጋባለን።  

ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian seamy)