ንቀት ወይስ ቸልተኛነት-
ጥያቄየ ለባልደራስ አለቆች አዲስ አበባ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
በፋሺስቱ የኦሮሞዎች መንግሥት የሚታዘዙ ባለ ጊዜዎቹ የኦሮሞ ፖሊሶች፤ ከእስር ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዋስ ከተፈቱ
በሗለ፤ መንገድ ጠብቀው ተጠልፈው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ አድርገው
“መለስ አካዳሚ” በሚባል ጫካ ወስደው “ብልታቸው በገመድ ታስረው የኋሊት እየተጎተቱ ተደብድበው ለስቃይ እና አካል ጉዳት ተዳርገው
ሥራ አልባ የሆኑ የሁለት ህፃናት አባት ለሆኑት ዋና ሳጅን ምትኩ
ተሾመ እርዳታ እንድልክላቸው እንዴት እንደምልክላቸው ለሕዝቡና ለባልደራሱ አመራር በድረገጼ ማስታወሻ ብለጥፍም የባልደራስን አድራሻ፤ስልክ፤
ኢመይል የጠቁመኝ ሰው ባለመኖሩ ሲጨንቀኝ ከአመራሮቹ ጋር ትውውቅ
ያለው ሰው ይሆናል በሚል አቻምየለው ታምሩን በቴክስት መልእክት እና በስልክ ብደውልም እሱም እንደነሱ “ጀሮ ዳባ” ብሎ ከቁም ነገር
ባለመቁጥር “መልስ አልሰጠኝም”።
መጨረሻ ዋሺንግተን ዲሲ- ኗሪ የሆነው የባልደራስ አባል አቶ ሺመልስ _ለገሰ መልስ አግኝቼ “ቢዘገይም” (ሺመልስ ጥፋት
ሳይሆን አዲስ አበባ ባሉት ባልደራስ አመራሮቹ ቸልተኛነት) ከየጠቃቸው ከአንድ ወር በኋላ እርዳታ እንዴት እንደምልክላቸው ጠቁሞኝ 10, 210 ብር ($300) በባልደራስ
ዋና አመራር አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኩል ገንዘቡ ለሳጅን እንዲደርስ ላክሁኝ።
የገረመኝ ነገር፤ ድረገጻቸውን በሰው ጥቆማ ስጎበኝ፤ አቶ ስንታየሁ ቸኮል የሚከተለውን በግርጌ ጽሑፍ የ10 ሺህ 2 መቶ አስር ብር የገንዘብ አረካከብ እርዳታ
ለዋና ሳጅን ተሾመ ሲያስረክብ እንዲህ በሚል ጽሑፍ ነበር ለሕዝብ
የተለጠፈው “ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጭ ለዋና ሳጂኑ ምትኩ ከዚህ በፊት ካደረጉት የ 3ዐዐዐ ብር ድጋፍ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት የ10 ሺህ 2 መቶ አስር ብር የገንዘብ ዕርዳታ አድርገዋል::” ይላል።
እግዚሔር ያሳየችሁ። እኔ ዕርዳታ ሰጪው ጌታቸው ረዳ ለምን አልተጻፈም ሳይሆን
ቅሬታየ፤- ዕረዳታ ሰጪው “ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጭ” በሚል
ነው። እኔ የባልደራስ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጭ አይደለሁም!! ስለዚህ ለምን ድጋፍ ሰጪ ተባለ? ዕርዳታ የሰጠ እኔ እንጂ ባልደረስ ድጋፍ ሰጪ አይደለም።
በዚሁ ሳይወሰን “ሺመልስ እና ጓደኞቹ” ዕረዳታ እንደሰጡ ጽፏል።
እንዲህ ይላል ፡ “ታዲያ ይህንን ችግር ከግምት ውስጥ ያስገቡት የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጭ አባል የሆኑት አቶ ሽመልስ ለገሰ እና ጓደኞቹ ከዚህ በፊት ካደረጉት የ3000 ብር ድጋፍ በተጨማሪ የ10ሺ 2መቶ 10 ብር ድጋፍ ዛሬ አበርክተዋል።
የገንዘብ ድጋፉን ባልደራስ ዋና ፅ/ቤት ድርስ ባአካል በመምጣት የተረከብት ዋና ሳጅን ምትኩ እና ባለቤታቸው ለህዝብ የተደረገላቸው ድጋፍ ፓርቲውን ÷ አቶ ሽመልስንና ጓደኞቻቸውን
ምንም እንኳን መንግስት ያለደምወዝ ጎዳና ላይ ከነ ቤተሰቦቼ ላለፋት ወራት ቢጥለኝም እናንተ አንስታችሁኛልም ለዚህም ፈጣሪ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ዋጋውን ይከፈላችሁ በማለት ሳጅን ምትኩ ተሾመ ከልብ አመስግነዋል።”
አንባቢዎች እስኪ ይህንን ለትዝብት ውሰዱት፡ መጻፍ ላልቀረ ዕርዳታ ሰጪ የሆንኩትን የእኔ ስሜን መጻፍ ለምን አልፈለጉም?
ዕርዳታ ሰጪ እኔ ከሆንኩ የባልደረስ ድጋፍ ሰጪ ተብሎ በስሜ እንዴት ለሕዝብ እንዲነበብ ተለጠፈ?
ለማንኛውም እኔ ተርፎኝ ሳይሆን ከእጅ ወደ አፍ የምኖር ሰውዬ ከሳጅኑ ህይወት የኔ እንደሚሻል በማሰብ ከልቤ ያደረግኩት ዜጋዊ አስተዋጽኦ እንጂ የፖለቲካ
ድጋፍ ሰጪ ድርጅት እንዲሞገስበትአልነበረም። ለወደፊቱ ሰዎች እርዳታ
ሲሰጡ በስማቸው እንዲለጠፍ ማድረግና ዜጎች ለዜጎች የሚያደርጉትን ዕርዳታ ሌሎችም እንዲያበረታታ በስማቸው ማሳወቅ ያስፈልጋል። ስለዚህም
ከፍተኛ ቅሬታ ነው ያደረብኝ።
ለዚህ ቅሬታየም በድረገጻቸው አጭር ሂስ ብጽፍም ፤ከጉዳይ አላዩትም።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)