Thursday, July 6, 2023

የትግሬ ብሔረተኞች በሲኖዶሱ ይቅርታ ሲንጫጩ ዋሉ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/7/2023


የትግሬ ብሔረተኞች በሲኖዶሱ ይቅርታ ሲንጫጩ ዋሉ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/7/2023

የትግሬ ብሔረተኞች ስል “ትግሬ” የሚለው ቃል ትግርኛ የሚናገረው ክፍል ማለት በአመዛኙ እኛን የሚመለከት ስለሆነ ትግራይ ውስጥ ያሉ ሌሎቹ ንኡሳን ብሔረሰቦችን “ትግሬ/ትግራዋይ” የሚለው ቃል ስለማይመለከታቸው እነሱን አይመለከትምና በዚህ ተረዱልኝ።

ትናንት የፓትሪያሪኩ ጽ/ቤት ለትግራይ ሕዝብ ይቅርታ የጠየቀበትን መንገድ (ያንሳል ወይንም ሽወዳ ነው ይሉታል) በመኮነን የትግሬ ብሔረተኞች እነ ቴድሮስ ጸጋየ፤የካናዳው ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ እና በኢትዮጵያ ጥላቻ የተለወሰ ጭንቅላት ይዞ የሚምቦጫረቅ ዲያቆን ይመስለኛል “መምህር አብይ ሀይለ” የሚባል ሰው መግለጫውን ባነበቡት ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ (ቴድሮስ ጸጋዬ ‘ሚሊሽያው ጳጳጳስ’ የላቸዋል) ላይ የስድብ ውርጅብኝ ሲያዘንቡባቸው ውለዋል።

እነዚህ ገለሰቦች ጳጳሱን ለምን ዘለፉ አልልም፤ ምክንያቱም  እነ ቴድሮስ ጸጋዬ  የሚያብሩዋቸው እኔ ግን “አገር ለማፍረስ” በሚሰሩ በጳጳሳቾቻቸው ላይ አጸፋውን የዘለፋ ስድብ ስለማከናንባቸው በዚህ ቅር አይለኝም።

እኔን የገረመኝ ግን ወገንተኞች/ ዘረኞች መሆነቻውን ያሳየኝ በትግሬው ተወላጅ በአቡነ ማትያስ ይሁንታ የተፈረመው የይቅርታ መግለጫ መሆኑን እያወቁ ስድባቸውን ዘነቡት መግለጫውን ባነበቡት በአማራው አቡነ ጳውሎስ (አማራ ይሆናሉ ብየ እገምታለሁ) ለይ መሆኑን ያስገረመኝ።

እስከዚቺው ደቂቃ ድረስ ማስረጃ ማሳየት ያልቻለው በስማ በለው ተመርኩዞ  አቡነ ጴጥሮስን  “ትግሬ ብሆን ኖሮ ትግሬነቴን በሲሪንጅ የትግሬነት ደሜን መጥጬ አስወጣው ነበር” ሲሉ ከታማኝ ሰው ሰምቻለሁ” እያለ ስማቸውን ሲያጠፋ ሲያወግዝ የሚውለው ቴድሮስ ጸጋዬ ( ርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) አንድ ነገር ልለው እሻለሁ።

እሳቸውን ተውና አሁን ባለው ትግሬነት እኔው እራሴ ትግሬነቴን በስሪንጋ መጥጬ ማስወጣት ብችል ኖሮ አስወጣው ነበር ብልህ ትገረም ይሆናል።

 የ1989 የቻይና የሰራተኞች ማሕበር መሪ የነበረው Han Dongfeng እንደኔው ትግሬነቱን እርሱም  ቻይናነቱን እንዴት እንዳስጠላው ሲገልጽ ‘በ1989 ዓ.ም በቴነመን አደባባይ ተቃውሞ ላይ በተነሳው አድማ የቻይናው መንግሥት በሰራተኞች ላይ ያደረሰው በደል ሲዘክርና ታስሮ በነበረበት ወቅት በንዴት “ጭንቅላቱን ከግድግዳ ላይ እያጋጨ”  እየጮኸ እንዲህ ብሎ ነበር፤

“Those who can hear me just remember what I am saying; I will never be Chinese in my next life. Don’t be Chinese. It is too horrible to be Chinese, too sad.”

በማለት ቻይናነቱን እንዴት እንዳስጠለው የገለጸበትን ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ፡

እንዲህ ይላል፤-

“ለምትሰሙኝ ሁሉ፤ እያልኩ ያለሁትን አስታውሱ። በሚቀጥለው ሕይወቴ በፍጹም ቻይናዊ ልሆን አልሻም። ቻይናዊ አትሁኑ። ቻይናዊ መሆን በጣም አሰቃቂ ነገር ነው።ያሳዝናል! ” >>

ነበር ያለው ቻይናዊው የሰራተኛ ማሕበር መሪው Han Dongfeng:: አምና ባነበብኩት መጽሐፍ በገጽ 15 (The Coming Collapse of China (author Gordon G.Chang) The Dinner  Party page 15

 ስለዚህ “ጠበቃ ቴድሮስ ጸጋዬ” ጳጳሱን ተዋቸውና እኔ ትግሬው እንደ Han Dongfeng ሁሉ ትግሬ ሆኜ ለዳግም ውልደት እንደማልሻ ስነግርህ ትገረም ይሆን?

ሲኖዶሱ ያወጣውን የይቅርታ ደብዳቤ የሚለው ለአንባቢዎቼ ለግንዛቤ ያህል ያላዳመጣችሁ ስለምትኖሩ “አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ . 

አዲስ አበባ   

ኢትዮጵያ” በሚል የራሳቸው ፌርማ ያለበትን መግለጫ

እንዲህ ይነበባል፡

<<“በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም ባለመጠየቅዋ እና በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ እንዲሁም ለትግራይ ሕዝብ እሰጣለሁ ያለቺውን ዕርዳታ ባለመስጠትዋም ይቅርታ ጠይቃለች።”>>ይላል መግለጫቸው።

ይህ የይቅርታ መግለጫ በኔ በኩል ጭራሽ ሲበዛ እና መጠየቅም ያልነበረበት ነው። ምክንያቴን ከታች አስቀምጣለሁ።

መጠየቅም ከነበረበት አብሮ ሲኖዶሱ ማንሳት የነበረበትና ማውገዝ የነበረበት ከክሕነት አገልግሎታቸውና ከደሞዛቸው ጭምር መገለል የነበረባቸው የሚከተሉት የወያኔ ወረብ መቺ ፤ ቀሳውሰትና ቀዳሽ አስቀዳሽ ጭምር ሲኖዶሱ “የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ” ማስገደድ ወይንም መጠየቅ ነበረባቸው።

አለመታደል ሆኖ ሲኖዶሱ በገዛ እራሱ  ወደ አዘቅት በተለያዩ ውጥረቶች እያደፈቀ መሆኑን እያሁ ስለሆነ ይህንን አላደረም።

<< እየሃድጋ “አኸ!” እየሃድጋ  ለሃገሪትነ አባይ ትግራይ! >>  “ለታላቅዋ ሀገረ ትግራይ ፈጣሪ ይታደግ”  እያሉ የሚቀድሱ “የቤጃ ዘር” ያለቸው ጥንትም ኢትየጵያን (ዘመነ አክሱምን) ያወደሙ” ዛሬም “ጥንታዊትዋን ኢትዮጵያን በሃይማኖት ሥር ተወሽቀው ለማፍረስ ታቦት ተሸክመው ሕዝብን እየሰበኩ ላሉ ኢትዮጵያ ጋር ምንም ግንኙነት የለንም የሚሉ “የቤጃ ዝርያዎች” ምንም ያሉት ነገር የለም።

ወደ ታሪክ ስንሄድም ፤ በ1928 ዓ.ም ግራዚያኒን “ንሴብሆ” እያሉ እንደ ክርስቶስ በወረብ እያሸበሸቡ የተቀበሉ የትግራይ ካሕናትም በታሪክ መመዝገቡ እያሳዘነን ፤ ዛሬ ደግሞ የግረዚያኒና የሙሶሎኒ “የርዕዮተ ዓለም” ልጆች የሆኑት ወያኔዎች ኢትዮጵያ ትፍረስ እያሉ ታቦት ይዘው << እየሃድጋ “አኸ!” እየሃድጋ  ለሃገሪትነ አባይ ትግራይ! >>  በማለት ሌላ የጥፋት ዙር ሲደግሱ እያየናቸው ነው።

በሲኖዶሱ ይቀርታ ባልደሰትም አንድ ደስ ያለኝ እና ያመሰገንኳቸው ነገር ግን ፡አንዳንድ አገራዊያን ጳጳሳት ወደ ጦርነት ቀጠናው ሄደው ያስተላለፉት መልዕክት ያለመኮነናቸው ደስ ብሎኛል።

 

ምክንያቱም የወያኔ ጳጳሳት እና እነ እስታሊን ገብረስላሴ፤ እነ ቴድሮስ ጸጋዬ፤ እና የካናዳው ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ በየሚዲያቸው ሲያስተጋቡት የነበረው ውሸት ቀሳውስቱ ያስተላልፉት ንግግር አይገናኝም።

ለዚህም ሲኖዶሱ በገንጣዮቹ ግፊት ተነሳስተው እንኳን በስማቸው ይቅርታ አልጠየቁ በዚህ ደስ ብሎኛል።

ለምሳሌ ላስታውሳችሁ አንድ ብርቱ የሆኑ አገር ወዳድ ካሕን እንዲህ ማለታቸውን እናስታውሳለን፤

“ ከዚህ በላ እውነት ለመናገር ጳጳሳቱ ሁሉ መዝመት አለባቸው። ሲዘምቱ ግን “ሊተኩሱ ሊገድሉ አይደለም”፤ምክንያቱም ሃይላችን ምንድ ነው? መስቀል ነው! ሃይላችን እግዚአብሔር ነው! እና እኔ እና “አባ” እዚህ የተገኘነው እስከ መጨረሻ ድል እስኪገኝ ድረስ ወደ ስራም ወደ ት/ቤትም አንመለስም።>>

ይህ ድንቅ የሆነ አባታዊ፤መንፈሳዊና አገራዊ፤አርበኛነታዊ ምክር ነው። ይህችን ንግግር ጠመንጃ ይዘው ሰው ሲገድሉና ሲዋጉ ከነበሩ የወያኔ ቀሳውስት ጋር ሲነጻጸር የማይገናኝ ስልጡን መንፈሳዊ ምክር ነው። በጣሊያን ዓድዋ በ1888 ጦርነትም መስቀልና ታቦት ይዘው ነበር ገንጣይና አስገንጣይ ባንዳ ተባብረው ሲመጡ ያስቆሙት።

በእነዚህ እና በሲኖዶሱ ልዩነቱ ያለው ‘’ሲኖዶሱ ጦርነቱን እንዲቆም ያለመጠያቀቸው ይቅርታ ሲጠይቁ” አገራዊያን አርበኞች ቀሳውስቶቻችን ደግሞ “አገር ለመቁረስ፤ የአማራን እና የዓፋርን ሕዝብ መጨፍጨፍ፤ በመግደል፤ንብረት በመዝረፍ፤ገዳማት በማፍረስ፤ አየር ማረፊያ በማውደም፤ ባለትዳሮችን እና ሴት መነኮሳትንና አረጋዊያን እናቶችን በመድፈር፤ ሕዝብን ሲያስጨንቅ የነበረው ወራሪው ስድ የትግሬው ጦር ወደ አዲስ አባባ በመግባት ይበልጥ የተቀረውን የአማራ ሕዝብ እንዳይፈጅ የማስቆም መንፈሳዊ ግዴታ እና ሃገራዊ ግዴታ ስለነበረባቸው ጦሩ ጋር ሆነው ወራሪው ወደ ኋላ ወደ ክልሉ እንዲያፈገፍግ አድርገዋል።ይህ ይመሰገናል። ልዩነታቸው ይህ ነው።

አባ ማትያስ ግን ጦርነቱን እንዲቆም ባለመጠየቃቸው የትግራይ ሕዝብ እና ቤተክርስትያኒቱ ለነበረው አለመግባባት ይቅርታ ጠይቄአለሁ ብለዋል። አቁም መባል የነበረበት ትግሬው ነው ወይስ ማን ነበር?

 ይቅርታ መጠየቅ ለማን? ምን ማለት እንደሆነ ግራ ገብቶኛል?

የተጨፈጨፈው ጦር ተጨፍጭፎ ይቅር ነበር የትግራይ ሕዝብ ጥያቄና ከሲኖዶሱ ጋር የተከሰተው “አለመግባባት”?

ጦርነቱ የጀመሩት ትግሬዎች ናቸው (በወያኔዎች መሪነት ማለት ነው) አይደለም እንዴ? እንደው እንበልና ሲኖዶሱ ትግሬዎቹን ጦርነቱን አቁሙ ቢሉ ኖሮስ ይቆም ነበር ወይ?

የወያኔ ፋሺስቶች USA የሚል ጽሑፍ ያለበት ጩቤ በየቀበሌ ያለው ወጣት አስታጥቀው ብዙ ተሳቢ የጭነት መኪኖችን አዘጋጅቶ ካራ ፤ገጀራ፤ሚስማር የተመታበት ጣውላ እና በሠራዊቱ ዓይን ላይ የሚረጭና የሚበትን በርበሬ ይዘው በትግራዋይነት ፖለቲካ የሚነዳ ወጣት አዘጋጅተው በስሜት የጦዙ ወጣቶችን ሴቶችን እናቶችን ባለትዳሮችን የሚደፍሩ ፤<<አማራን ዋይ ዋይ! በቃኝ! በቃኝ! አሰኘነው>> ፤ << ሞኙን አማራን እያባረርክ በለው….”>> እያሉ ያበዱት የዚ ትግሬ ተዋጊዎችን እንዴት ማስቆም ይቻል ነበር?   ጥላቻቸውና ዒላማቸው “አማራ ላይ ነበር” አደለም እንዴ? እራሳቸው እየዘፈኑ እኮ ነግረውናል! ማን ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት?

ጦርነት እንዳይጀመር ቄሶች እና ሽማግሌዎች ተልከው መኖራቸውስ አባ ማትያስ አያውቁም  ኖርዋል? ወያኔዎች ለተላኩ ሽማግሌዎቹን ምን ይሉዋቸው እንደነበር ከሽማግሌዎቹ ትዝብት ምን እንደተባለ እንዴት ረሱት?

  ወገናዊነት  ነው? ወይስ ምንድነው? ፋሺስቶቹ ሆን ብለው የጀመሩት ጦርነት  ከትግራይ ውጭ  ያለዘራቸው አግብተው “ዘራችን አበላሽታችል” ተብለው የተገደሉ የወታደር ሚሰቶች አባ ማትያስ ወያኔዎችን በጥብቅ አወገዙ?

ጦርነቱ እንዲቆም ትግሬዎች ክልላቸውን ተሻግረው የአማራን ሕዝብንና የዓፋርን ሕዝብ ሲደፍሩ፤ሲጨፈጭፍና አብያተ ጸሎቶችን ሲያፈርሱና ሲዘርፉ አቡነ ማትያስ ይህንን አያውቁም ነበር? በከባድ የጭነት መኪና ተደፍጥጠው እየተጨፈለቁ ሆን ተብሎ በጭካኔ በአሰቃቂ አገዳደል የተጨፈጨፉ ሰማእት ወታደሮችስ አባ ማትያስ ያውቁዋቸዋል? ካወቁስ ለምን ለወገናቸው ብቻ በመወገን ለትግሬዎች ብቻ ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዱ? (እርዳታውስ ይቅር)

ለምን አንድ ወገን ብቻ የሚያስደስት ወገንተኛ ይቅርታ በማስሰማት በስማችንና በሃይማኖታችን ስም አማራንና ዓፋርን ሕዝብ ምንም ሳይጎበኙ ተሻግረው ወደ ትግራይ ሄደው ዕንባ እያቀረሩ ለወገናቸው ብቻ አሰቡ?  

የትግራይ ቀሳውስትና ጳጳሳት ህገ ወጥ ተግባርና ጦርነት ተሳታፊነታቸውን ከፍ ብሎም “አገር ምስረታ እስከመሄድ የደረሱ ካሕናት” ሳይኮኑኑና ከመንበራቸው ሳያስነሱዋቸው ሌላውን ወንጀለኛ (ጥፋተኛ) በማድረግ ለትግሬ ብቻ ይቅርታ መጠየቃቸው ነውር አይደለም ወይ?

 

ውድ አንባቢዎቼ ሆይ!

                  የትግራይ ቀሳውስት በተለምዶና በተግባር ያየናቸውና  የምናውቃቸው ቀሳውስት ሳይሆኑ ብዙዎቹ በጫካ የጠመንጃ ትግል ያለፉበአንድ ዘር ጥላቻ ያነጣጠረ የወያኔ ፖለቲካተቀብለው ሲሰብኩና ሲታገሉ የነበሩ በሚያሰዝን ሁኔታምየወያኔን ኮሚኒዝምአንቀበልም ያሉዲያቆናትንና ፤ቀሳውስትንሲረሸኑና ሲደበደቡ ከብቶቻቸው ሲወረሱ ምንም ያላሉ ወይንምተባባሪዎች የነበሩቀሳውስት ታጋዮች ትግራይ ውስጥ ዛሬ ነጭ ሽበት ሸብተው ሽማግሌ ሆነው ጳጳስና ቄስ ቢመስሉም ታጣቂ ታጋይ የነበሩ አያሌ ናቸው። እነዚህ የትግራይ የናዚ አገልጋይ ጳጳሳት የወያኔ ባንዴራ አውለብላቢዎች አማራን ያነጣጠረ ይጥላቻ ዘፈን አትዝፈኑ ብለው አንድ ቀን  አውግዘው ደናቁርት ዘፋኞችን ኮንነው ያውቃሉ?

ወይ-አለማፈር!

ትግራይ ውስጥ ያለው የዓጋሜው አውራጃ ተወላጅ የሆነው ወያኔው አቡነ ኤልያስ (?) አሁን በተ ጨዋ ሰው ቢመስልም 48 አመት በላይ ይህ ቄስም ሆኑ ሌሎቹ ሲያመልኩት የነበረው የወያኔ ፖለቲካ እና ሰንደቃላማ በመከተል ወያኔዎች ትዕቢት ወጥሯቸው አገር ለማፍረስ ጦርነት ከፍተው የሰሜን ዕዝ ሲጨፈጭፉት በተነሳው ጦርነት ከህወሓት ወታደር ( ኤፍ ይሉታል ባዲሱ መጠሪያው) ጎን ቆመው ፖለቲካ ሲሰሩ የነበሩ ቀሳወስት ዛሬ የኢትዮጵያ ቤተክረስትያን በትግራይ ላይ ጦርነት አውጃ በትግራይ ስለደረሰው የጦርነት ጉዳት አላወገዘችም የሚል ለግንጣላ ሽፋንቅብጥርጥሮሽምክንያት ፓርቲያቸውና ሰንደቃላማቸው ባዘዛቸው ውሳኔ መሰረትተገንጥለን ሃገረ ትግራይ መስርተናል”  ብለው ግንጠላን እና ለዳግም አስከፊ ብጥብጥ ጠንስሰው በየሚዲያቸው ሲሰብኩ የነበረው መቸው ?

የዚያ ውጤትም ነው በዚህ በለጠፍኩት ቪዲዮው ላይ እንደምታደምጡት << እየሃድጋአኸ!” እየሃድጋ ለሃገሪትነ አባይ ትግራይ! >> እያሉ የወያኔ ፋሺሰታዊ ባንዴራ የታቦታቸው መሸፈኛ እና ማድመቂያ በማድረግ በከበሮና በጸናጽል እየጨፈሩ   “የኢትዮጵያን ሕዝብ ረግመውእነሆ አቋማቸው አጠናክረው አቡነ ማትያስን  ይቅርታ እንዲጠየቁ አስደረጉ።

ለመሆኑ እነዚህዘረኛ ካህናቶችአማራ እና ዓፋር ውስጥ የትግሬዱርየ ተዋጊዎችገብተው መስጊዶች ቤተክርሰትያናት ፤ትምህርት ቤቶች፤ ሕክምና ቤቶች እና ላሊበላ ገብተው ሲዘርፉ ፤ሽንት ሲሸኑበት አየር ማረፊያን  ሲያፈርሱት (እራሳቸው አክሱም አየር ፖርት እንዳፈራረሱት) ልጃገረዶች ሲያምጹና ባለትዳሮች ሲደፍሩ፤ ቀሳወስት ሲደበድቡከብቶች እያረዱ ሲበሉ፤ በርበሬ፤ ሽሮ ፤ሳሙና፤ ዘይት ሲዘርፉ እነዚህ ተገንጣይ ጳጳሳት ተብየዎች አውግዘው ያውቃሉ? አላወገዙም!

አንዳንዱ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሠራዊቱን በመጨፍጨፍ የተካፈሉ መሆናቸው ማስረጃ አለን። ያውም <<የተከዳው የሰሜን ዕዝ>> ደራሲ ጋሻዬ ጤናውሰይጣን የሰፈረበት ሻሽ የጠመጠሙ ቄሰሶችና ንስሐ በመግቢያቸው ጊዜ ሐጢያት የናፈቃቸው የሠፈር ሽማግሌዎችይላቸዋል በጦርነቱ ወቅት ያሳዩት በሰይጣናዊው ወያኔ የሚታዘዙ የትግራይ ቄሶች ማሕደራቸውን እናውቃለን።

<<መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንበረ አክሱም >> የሚባል መንበር/ሲኖዶስ/ አክሱም ውስጥ በታሪክ እንዳልነበረ እያወቁ አሱን ወደ መንበሩ እናስመልሳለን እያሉ የዋሁን ሲዋሹት ነበር። አባ ማትያስ ይህንን ማውገዝ ሲገባቸው  በዝምታ አልፈውታል። ለምን?

የወዳጄ የሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አባባል ልዋስና

"የኦርቶዶክስንና የአማራን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርገን ሰብረነዋል!" ያለውን የዲያብሎስ አገልጋይ ፀረ ቤተክርስቲያንንወያኔን” በፍጹምትጋትና ታማኝነት” ሲያገለግሉ ኖረውና አሁንምእያገለገሉ ባሉበት ሁኔታ” በዚህም አገልግሎታቸውየቤተክርስቲያንን አከርካሪ” ያሰበሩ አጋንንት ሆነው እያለ ነው እንግዲህ (የትግራይ ቀሳወስት)ለቤተክርስቲያንና ለሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ መስለው” ሲኖዶስ ይቅርታ ይጠቀይ ቅብርጥስ እያሉ ሰው ለመምሰል ጥረት እያደረጉ የሚገኙት”>>

ስለሆነም <<…."ለሃይማኖታችን ቆመናል!" የምንል ትግሬዎች ካድሬ የትግሬ ጳጳሳትን "እረፉ አታጭበርብሩ! እያልን ያለነው”፣

"የኦርቶዶክስንና የአማራን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርገን ሰብረነዋል!" ያለውን የዲያብሎስ አገልጋይ ፀረ ቤተክርስቲያንንወያኔን” በፍጹምትጋትና ታማኝነት” ያገለገሉ ካድሬ የወያኔ ጳጳሳት አማራንና የቤተክርስቲያንን አከርካሪ ሰባሪዎች የሆነውን ሰንደቃላማ አውለብላቢዎች”  ስለሆኑ ለ47 አመት የበደሉትን የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ይጠይቁ እያልን፤ የተከበረው የሃይማኖት ታቦት ለወያኔ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ በማድረግ << እየሃድጋ! እየሃድጋ! ለሃገሪትነ አባይ ትግራይ! >> እያሉ ግንጠላና ብጥብጥ የሚያስነሱና ሚሰብኩ የትግራይ ካህናት ዛሬም እኔም በትግሬነቴ ሲኖዶሱ በነዚህ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተግባር ላይ ይፋ ውግዘት እንድያደርግ የተቃውሞ ጥሪ አቀርባለሁ።

እባካችሁ ጽሑፉን አዳርሱት! አንዝህላልነት ይብቃችሁ!

ጌታቸው ረዳ