Saturday, June 3, 2017

ሁለት የኢትዮጵያ ሴት ሯጭ ስፖርተኞች በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያሳዩት ጋጠወጥ ባሕሪና ፖለቲካዊ ምርጫ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)


ሁለት የኢትዮጵያ ሴት ሯጭ ስፖርተኞች በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያሳዩት ጋጠወጥ ባሕሪና ፖለቲካዊ ምርጫ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)

 


ሴት ጀግኖቻችን (ከወደ ቀኝ የምትታየው የሐረር ወርቅ ጋሸው ነች)
ይህ ትችት የኔን ጽሑፍ በሚያስተናግዱ እንደሚለጠፍ ባውቅም፤ ለሌሎቹ ተቃዋሚ ድረገፆች በሙሉ ተልኳል። ቢያወጡት አስተማሪ ነው። ብዙዎቹ ግን እንደማያውጡት ጥርጣሬ አለኝ። ምክንያቱም የፖለቲካ መሪዎቻቸውና ድርጅቶቻቸውን ጨምሮ በዚህ ትችት ስለተካተቱ ወገንተኛነታቸው ከሉጓም በበለጠ ይስባቸዋልና። ለማንኛወም ለታሪክ ልኬአለሁ።

 

አሁን ወደ ርዕሱ ልግባ። በትግርኛ በምንመስለው ምሳሌ ልጀምር፡ {ዝፀገባ ደራሁስ ምስ ፀኻድም ማሕበር ይኣትዋ}  “የጠገቡ ዶሮዎች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር ይገባ”፡ ይባላል። ሁለቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች እውቅ ሯጮች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር መግባቱ ምርጫቸው አድርገዋል። ይሆናል።የጭልፊቶቹ እና የዶሮዎቹ ማሕበር የሚቆየው ዕድሜ አብረን የምናየው  ይሆናል።



ሰሞኑን በአጋጣሚ “ዩቱብ” ድረገጽ ላይ አንድ ማሕደር ለመፈተሽ  ጎራ ስል ድንገት ያላሰብኩበትን እና አስደንጋጭ አስገራሚ ነገር በዓይኔ ተመለከትኩ። “ገንዘቤ ዲባባ እና ወርቅነሽ ደገፋ” በሰንደቃላማችን ላይ ያሳዩት ፖለቲካዊ ጋጠወጥነታቸውን በወቅቱ የተመለከቱ ዜጎች ጉዳዩን ለማሳወቅ ‘በዩቱብ’ ላይ ለጥፈውት ለካ ኖሯል። እኔ ኣላወቅኩም ነበር።


ገንዘቤ ዲባባ ሰንደቃላማችንን ወደ መሬት ተመልሳ ስትጥል። Genzebe Dibaba demonizing Ethiopian flag.
Werknes Degefa demonizing Ethiopian flag


ወርቅነሽ ደገፋ ሰንደቃላማችንን ስትጥል


Sign Language Deciphered - Inverted Symbolism (pentagram) (Hugeieia pentagram) ሉሲፈራዊ የተወጠሩ ምስጢራዊ ማአዝናዊ የፍች ቁልፎች/ኮድ/


 ነገሩ እንዲህ ነው።ጌዜአቸውንና ገንዘባቸውን በመሰዋት ወደ ሜዳው በመግባት በአዩት ውጤት ደስታቸውን እና ድጋፋቸውን ለመለገስ ከተቀመጡበት መንበር ተነስተው ይዘውት የነበረውን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በሁለቱም ተጫዋቾች ላይ እንዲያሸበርቁበት ሲወረውሩላቸው ተቀብለው አገላብጠው ካዩት በየወራሪ ጣሊያኖች ሰንደቃላማ ይመስል ኤርትራኖች እንዳደረጉት፤ ወደ አፈር ጥለውታል። ከጥንት ጀምሮ ዓለምና አፍሪካኖች ያከበርዋትን ባለ ሦስት ቀለም የኢትዮጵያዊ ሰንደቃላማችንን ወያኔ እንደሚለው “የምንሊክ የነፍጠኞች አማራ እና የተዋሕዶ ቤተክርስትያን አርማ ነው”  ብሎ ወያኔ ባስተማራቸው አጉል ማስጠንቀቂያና ብረዛ ወደ አፈር መሬት  ወርውረዋታል። ይህ ይቅር የማይባል ታሪካዊ ወንጀል በታሪክ መመዝገብ ይኖርበታል። ይቅርታ ካልጠየቁ እኔ ራሴ በሚቀጥለው መጽሐፌ ውስጥ አንድ ርዕስ ሰጥቼ ፎቶግራፎቻቸው በመለጠፍ ድርጊታቸውን በታሪክ እንዲመዘገብ አደርጋለሁ።

 

በድረገጹ እና ‘ዩ ትዩብ’ ጎብኝቼ የተቺዎች አመለካካት ለመገንዘብ ሞክርያለሁ። አንዳንዶቹ እጅግ ተቆጥተዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ የሯጮቹ ጥፋት ይመሰል የወያኔን ስራ አላግባብ በእነሱ ላይ ተለጥፏል፡ ሲሉ ተከራክረዋል። ከነዚህ መሃል ዲሜጥሮስ የተባለ ኢትዮጵያዊ “ቦርካና” የተባለ ድረገጽ አዘጋጅ ወቀሳው ወያኔን እንጂ ሯጮቹ አይመለከታቸውም በማለት ከሐላፊነት ነፃ እንዲወጡ የተቻለው ያህል የዲፕሎማሲ ስራ ሰርቶላቸው አንብቤአለሁ። አዘጋጁ የግል አስተያቱ ባከብርም አልተስማማኝም። “ምርጫ የላቸውም” ነው የአዘጋጁ ክርክር። ይህ አመለካካት የብዙዎች ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እንዲህ ይላል። Editorial borkena Ethiopian News  February 10,2017 “Demonize not Ethiopian athletes for the flag” በሚል ርዕስ

On the part of the athletes, not using the historic and popular flag is not a matter of choice. The only context that it is a matter of choice is that it essentially comes down to whether they wish to return to Ethiopia or not, a decision perhaps with undesirable implication for their running carrier and their families, too.” ይላል ወንድም ዲሜጥሮስ።

ይህ ጥያቄ ለሁላችሁም ላርብ። ምርጫ የላቸውም፤ ምርጫቸው የወያኔ ሰይጣናዊ አርማ በሰንደቃላማችን ላይ የተጨመረበትን ከማክበርና ከመቀበል ሌላ ምርጫው ያ ብቻ ነው፤ ያን የወያነ  ተጽእኖ ላለመቀበል አገር ለመልቀቅ ዝግጁ ሆኖው መገኘት ሌለው አማራጫቸው ነው፤፡ምልባትም አገር ለመለቀቅ ዝግጁ ስላልነበሩና በቤተሰቦቻቸውም አደጋ ላለማስከተል የወሰዱት ምርጫ ነው ተብሎ የመከላከያ ምጉት ቀርቧል። ግሩም። ግን “ሃይማኖት፤አገር፤ሚሰት” በምርጫ የመሄዱ አይደሉም። ሁለቱ ሯጮች የሚከተሉት ሃይማኖት ትተው፤ ያገቡትን ወዳጅ/ባለቤት/ፍቅረኛ/ጓደኛ… ትተው ወያኔ የሰጣቸው ሃይማኖትና ወዳጅ/ባል/ (የትግሬ ፍቅረኛ/ልክ እንደ የወያኔው ሰራሽ ባንዴራ) አግቡ/ተከተሉ ካልሆነ…….. የተተነተነው የመከላከያ ምጉት ይከተላችሗል ቢባሉ፤ ምርጫ የላቸውም እና “ምርጫ ስለሌላቸው” ሃይማኖታቸው ወይንም ፍቅረኛቸውን መተውና ሩጫው መቀጥል ነበረባቸው?

አስቀደሜ እንደገለጽኩት፤ ስፖርተኞች ወይንም ሙዚቀኞች ስለሆንን ሕዝብን ማስደሰት ነው ስራችን እንጂ የማንም ፖለቲካ ደጋፊዎች አይደለንም ተብሎ የማምለጫ ምክንያት ተሰጥቶ የሚታለፍ ወንጀልም አይደለም። ስፖርተኞቹ ፖለቲካዊ የመወገን መብታቸው በዓለም ፊት በተግባር አሳይተውናል።የመወገን መብታቸውን አክብረናል። እኛም እንዳከበርንላቸው፤ የኛን ወደ አፈር ወርውረው በምትኩ የሚያከብሩትን በአፓርታይድ የትግሬ ጦረኛ ድርጅት የተቀረጸ ሉሲፈሪክ/ሉሰፈርያዊ/ ኮከብ ያረፈበት አርማ እና ይህ አርማ የሚያከብሩትንም አክባሪዎቹን የማውገዝ/የመውቀስ/ መብት አለን። ስለሆነም የሚዲያ አዘጋጆች “የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ” ምክንያታዊ መከላከያ እየሰጡ አትውቀስዋቸው የሚሉን “አገራዊ አርማን” የሚያክል አፈር ላይ የሚጥሉትን መከላከል ወያኔ ባሸናፊነት እንዲወጣ እና በአዲሱ ትውልድ ሕሊና የወያኔ ባንዴራ “እንዲለመድ” ማድረግ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ነው።

 

ይህ አርማ እያውለበለቡ በመመሪያ/በፖሊሲ/ የተነደፈ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ እቅድ ተግባራዊ በማድረግ የዚህ አርማ ባለቤቶች ነን ባዮች በ26 አመት ውስጥ ቢያንስ ከ5 ሚሊዮን ያላነሰ የአማራ ሕዝብ የዘር ማጽዳት ተፈጽሞበታል። ውጣ ተብሎ ተባርረዋል፤ ታምጸዋል፤ስጋቸው በሰው ጅቦች ተቀቅሎ ተበልቷል፤ እመጫቶች ከተኙበት መደብ ደማቸው እያንጠበጠቡ እየተጎተቱ ፤ለጅብ ተጥለዋል፤ እናቶችና አረጋዊያን እየተደበደቡ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጓል፤ህጻናት ከት/ቤት ገበታቸው እየተጎተቱ ተባርረዋል። ወዘተ…ወዘተ…. ይህ የተደረገው በቅርብ ነው። አንዳንዱ አንድ አመት እንኳ አልሞላውም (ቤንሻንጉል ውስጥ የተባረሩትን አማራዎች ስጋቸው የተበላ በቀርብ ነው)። በዚህ ወርም አዲስ የዘር ማጽዳት እየተካሄደ ነው።

 

ይህ የዘር ጽዳት ወንጀል ፈጻሚዎች የዚህ አርማ ባለቤቶች ነን በሚሉ ወገኖች የተፈጸመ ነው። አይደለም እንዴ?  በአግዳሚ መአዝናት የሚያልፉ የተጠላለፉ መስቀላዊ መስመሮች ጫፎቻቸው ላይ ሲደርሱ *የማይገናኙ* “ሉሲፈሪዊ ኮከብ” ቅርጽ የሚያመላክተው ባለቤቶች ተብለው የተቀመጡ “ጎሳዎች” (ብሔር/ብሔረሰብ/ሕዝቦች) በአፓርታይዳዊ ዲዛይን (ኤትኒክ ዲዛይን) እንደማይገናኙ/እርስ በርስ በጠላትንት እንደሚተያዩና፤ መጨረሻ ላይ አንደሚገነጣጠሉ የሚያሳይ ጥበባዊ የጠላቶች አርማ ነው። ይህ አርማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ማውገዝ ይጠበቅበታል። እየተጣለ ያለው ሰንደቃላማ የአማሮች የኦርቶዶክስ ነው ተብሎ ነው እየተወገዘ እና እየተጻፈበት ያለው። ስለሆነም ስፖርተኞችም ሆኑ የኪነት ሰዎች እንደ ዜግነታቸው የሚያሳዩት ውሳኔ ተጠያቂነት አለባቸው። ያለ ማወቅ ከወንጀል ነፃ ሊያደርግ አይችልም። ቅጣቱ ይለያይ እንደሆን እንጂ የዓለም አቀፍ ሕግ አርቃቂዎች የሚሉትም ይህንን ነው።

 


Haile Gebresilassie shading tears for his master Fascist Meles Zenawi's death
ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር መስርተው አቋማቸው ያሳወቁ የኪነት እና የስፖርት ሰዎች/ በፍርሃት የተጠጉ ዶሮዎች/ አሉ። መለስ ዜናዊ ሲሞት እምባቸው ያፈሰሱለት፤ አንድ ጥሩ መሪ አጣን ብለው ኑዛዜአቸው መለስ ዜናዊ ለገደላቸውና ለሚጠላቸው “ለአማራ ማሕበረሰብ” እና ለኦርቶዶክስ አማኞች በቴ/ቪዥን ሳያፍሩ እምባ-አፍስሰው-ነግረዋቸዋል። ፎቶዎች ለታሪክ ይናገራሉ። ሁለቱም ክፍሎች በወያኔ/በመለስ ዜናዊና በስብሓት ነጋ አንደበት “አከርካሪያቸውን” እንሰብረዋለን የተባለላቸው ጥቃት የተነጣጠረባቸው ናቸው (ሰንደቃላማው የአማራ እና የተዋህዶ ቤተክርስትያን የሁለቱ ክፍሎች ነው ስለተባለ) እንዴ!! እንዴት ነው ነገሩ ሃቅ አሃቁን እንነጋገር አንጂ? ለገንዘብ ሲባል ገዳዮችን እያመሰገኑ  የሚያለቅሱ ሞራለ ቢሶች ጥብቅና መቆም በየትኛው ሕግ? ? እነዚህ እስፖርተኞችእንደማንኛውም የኔ ብጤ ድሃ እና ያልተማረ ዜጋ ተሰድደው ችግር የሚገጥማቸው አይደሉም። ዓለም አቀፍ እስፖርተኞች ስለሆኑ በሚሊዮኖች ብር/ኢሮ/ዶላር የሚገዛ ውድ የተፈጥሮ ችሎታ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አማራጭ የላቸውም ተብሎ መከላከያ የሚቀርብላቸው አይደሉም።በተለይ እነዚህ ሁለት የሴት ሯጮች የሚሊዮኖች ልብ ያስሸፈቱና ያስጨበጨቡ ድንቅ ሯጮች ናቸው፤ ምርጫ የላቸውም ተብሎ ብዙ የሚደረደርበት ዲፕሎማሲያዊ ማምለጫ ተቀበይነት የለውም።

 

 ‘ሙዚቀኞች እና የስፖርት ባለሞያዎች’ እንደማንኛውም ዜጋ በተሰለፉበት የሞያ ዘርፍ’ መንግሥታዊ ሥርዓት በሚመራ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የማመስገን ወይንም የመቃወም መብቱ የተጠበቀ ነው። ሆኖም እኔ ከማንም ወገን አልወግንም የሚሉትንም ቢሆን፤ ከሃላፊነት/ተጠያቂነት ሊያመልጡ አይቻላቸውም።

 

ይህ ብልግና እና ቸልተኛነት ልምድ ሆኖ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምልክት ሰጪ የሆኑት የቅንጅት መሪዎች ለዚህ ሁሉ ብረዛ ተጠያቂዎች ናቸው። በሺዎቹ ሰልፍ ወጥተው ከአልሞ ተኳሾች ጋር በደንጋይ ገጥመው “ደምጻችን ተሰርቓል” ብለው ከወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮች ጋር “ጎዳና” ላይ ወጥተው ሲፋለሙ፤ መሪዎች የተባሉት ግን በየሆቴሉ ምሽግ ሰርተው ሲጠለሉና፤ ሲሸሹ፤ መጨረሻም “ባላደረጉት ወንጀል ጥፋት ፈጽመናል ብለው “ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ሲወጡ” ነው፤ ሰንደቃላማውም ፤ዜጋውም፤ ማጎንበስ የጀመረው። ሰለሆነም “ምርጫ የለንም” ተብሎ “ሽንፈትን” እንደ ፋሽን ተወስዶ አትሌቶች እና የኪነት ሰዎች (ጥቂቶችን አይጨምርም) ሰንደቃላማን በማርከስ ስራ ላይ የተጠመዱት።


ተቃዋሚ ድርጅቶች ስለ ሰንደቃላማ ምን ዓይነት ባሕል ለአትሌቶች ፤ለኪነት ሰዎች እና በጠቅላላ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምን የዓዕምሮ አጠባ (የሳብቨርዥን/የክለሳ/ብረዛ/) ትምህርት አስተማሩ ብለን ብንጠይቅ፤ ትልቁ የውድቀት ድርሻ የወሰዱት እነሱ ናቸው። በስዕላዊ ገለጻ በሚከተለው ማስረጃ ላሳያችሁ።  “ዩ ዲ ጀይ” (አንድነት) በተባለው ልጀምር። በሰልፋቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ካያችሁ ፈልጉና አሳዩኝ።

አሁን ደግሞ ወደ ሳማያዊ ፓርቲ እታች ያለውን ጉድ እንመልከት

ከዚህ በታች ያለውን ወደ እስላም ተቃዋሚዎች ካርታን እንመልከት፤ እውጭ አገርም ሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ማውለብለብ ሃጢያት መስሎ እስኪታይ ድረስ ነው የሚከተለወን እንደሌሎቹ ቁርጭራጭ ጨርቆችን ያውለበለቡት፤

 

በዛው ቀውጢ ትግል ውስጥ ሆነው “ሰንደቃላማችን” ይህ ነው ብለው አንገታቸውን ለቢላዋ የሰጡ የ “መ ኢ አ ድ” ድረጅትአባሎች ግን ይህ ታሪካዊ ገድል ፈጽመዋል አንመልከት። እነዚህም እሳት ውስጥ ሆነው ነው “ሰንደቃላማችን እና ሃይማኖታችን እኩል እናስከብራለን ብለው የወያኔ አርማ ጥለው አርበኞች የተዋደቁባት፤ጣሊያኖችን ያስደነገጠች፤ አፍሪካኖች የሚያውቋት፤ዓለም የሚያውቃት ሰንደቃላማችን በማውለብለብ ታሪክ ሰርተዋል። ከወያኔ ጋር ስለሰንደቃላማ ጉዳይ እስከ ፍርድ ቤት እየተጓተቱ ምን ዓይነት ትግል እንዳካሄዱ ታስታውሳለችሁ።


መጨረሻም በተመሳሳይ ወደ ሲያትል ልወሰዳችሁ። እዚህ አሜሪካ በምንኖርበት ወያኔ በማይቆጣጠረው አገር ሆነው “የኢትዮጵያ አንድነት” በሚል ስም የተዘጋጀ በቅርቡ ሲያትል ውስጥ በአፍቃሬ ግንቦቶችና በገለልተኞች በኩል የተዘጋጀው የስብሰባ አዳራሽ ካለፈው ትምህርት የተማሩ ቢመስሉም፤ (ደጋግሜ ስለሲያትል ጉባኤዎች ስለ ሰንደቃላማችን ጉዳይ ያደረጉት የሚያዋርድ ተግባር መፈጸማቸውን መዘገቤ ይታወሳል) አዳራሹ ልክ ወያኔ እንደሚያደርገው ዓይነት በኦነግና ኦብነግ ባንዴራ “የተዘነቀ” ሳይሆን በብሔራዊ ሰንደቃላማችን ማሸብረቁ ምስጋና ቢገባቸውም፤ ያው በታጭቦ ጭቃ ጎዳና በመራመድ፤ በሰገነቱ መነጋገሪያ /ፖድዮም/ ላይ የተለጠፈው የኢትዮጵያ ካርታ ግን የባሕረ ነጋሽ መሬታችንን የላካተተ ወያኔ የቀረጸላቸውን ብርሃኑ ነጋ በመጽሐፉ ያከበረውን እና ግንቦት 7 የተቀበለውን የወያኔ ካርታ ነበር በሕዝቡ ፊት ለጥፈው ብረዛ (ሳብቨርዥን) ያካሄዱ.-ምስሉን-ተመልከቱ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የሞትለትንና ያወረስዋቸውን ዓለማ የካዱና የከዱ……..” ሲሉ አድማጫቸውን ሲያስተምሩ፤  ይህንን ንግግር ሲያደርጉ የቆሙበት የመነጋገሪያ ሰገነት/ፖዲየም/  ላይ የተለጠፈው ካርታ  “አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የሞትለትንና ያወረስዋቸውን መለክአ ምድራዊ/ ካርታ ያላካተተ/የካደ/ ወያኔ የቀረጸው ሉዓላዊ የኢትዮጵያን መለክዓ ምድር ያላካተተ ካርታ ነው”። ለዚህ ነበር ስብሰባው የግንቦት 7 አዘጋጆች ስብሰባ ነው ተብሎ የተነገረው። ስለሆነም የሰንደቃለማ እና ሉዓላዊ መሬቶች ብረዛ ተቃዋሚዎችም ትልቅ ሴራ በማካሄድ የወያኔን ትልቁ ድርሻ እየተወጡ ነው እያልኩ ለብዙ አመታት ለማስገንዘብ የጣርኩት። ስለሆነም ስፖርተኞች እና የኪነት ሰዎች ይህንን ሲያደርጉ የብረዛ ትምህርቱን የቀሰሙት ከወያኔ ብቻ ሳይሆን ከብዙዎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ጭምር መሆኑን ላስገነዝብ እወዳለሁ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)  getachre@aol.com

 
Ethiopia: ገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ በሰበረችበት ውድድር ኮኮብ የሌለው ባንዲራ ሲወረወርላት የሰጠችው ምላሽ ይመልከቱ!! 


Ethiopia : Reaction of Athlete Worknesh Degefa to Ethiopian opposition flag in Dubai Marathon 2017


አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay getachre@aol.com