Thursday, November 4, 2021

ትኩስ መረጃ ከባሕርዳር! 11/4/2021 በአንዳንድ ከተሞች ሰላማዊ ትግሬዎችን በጅምላ ማሰር እና የመግደል እርምጃ ተጀምሯል ጌታቸው ረዳ Ethio Semay

 


ትኩስ መረጃ ከባሕርዳር!

11/4/2021

በአንዳንድ ከተሞች ሰላማዊ ትግሬዎችን በጅምላ ማሰር እና የመግደል እርምጃ ተጀምሯል

ጌታቸው ረዳ

Ethio Semay

የፋሺስቱ አብይ አሕመድ እየወሰደው ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ባንዳንድ የአማራ ከተሞች የትግራይ ደም /ዝርያ/ ያላቸው “ምንም የፖለቲካ ንክኪ የሌላቸው” “የጅምላ እስር ብቻ ሳይሆን “በጸረ ትግሬ” ጥላቻ በሰነቁ “አማራዊ ኢንትርሃሙዌ ገዳይ ቡድን” ትግሬዎች በከተማ” እየተገደሉ እየተገኙ ነው። በዚህ ምከንያት ትግሬ የተባለ በሙሉ ከቤቱ ሳይወጣ በፍርሃት ሞቱ እየተጠባበቀ ነው።

 ጸረ ትግሬው የኢንተርሃሙዌው ቡድን የግድያ ዘመቻው ጀምሯል። ኢትርሃሙዌው የአማራ ክልል መንግሥት መላ በቤተሰቦቼ ኣንድ በአንድ እየለቀመ በማሰር ላይ ይገኛል።

የኢንተርሃሙዌው ቡድን እየወሰደ ያለው እርምጃ እየተከታተልን ለታሪክ እንዘግባለን።

ኢንተርሀሙዌው መንግሥት ራሱን የጠቀመ መስሎት ንጹሃንን ሰብስቦ ባማሰር እንደ እኔ የመሳሰሉ 30 አመት ሙሉ ወያኔን እና አሁን ሥልጣን ላይ ያሉት የወያኔ አሽከሮች የነበሩትን ማፈሪያዎችን ስንታገል የነበርነው ጥቂቶች እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎች “ሳናስበው ድንገት በማስቆጣት”  በገዛ እራሱ  የሚቀበርበት የፖለቲካ መቃብሩ ሳይታወቀው በፍጥነት እየቆፈረ ነው። ወንድሜን ማሰር ሳያንሳቸው ዛሬ ደግሞ ትግርኛ እንኳን የማይችል የወንድሜን ልጅ (በጣም ወጣት) በትግሬ ጥለቻቸው አስረውታል።

ለማንኛውም አማራዊው ኢንተርሃሙዌው ቡድን ሰንቱን ገድሎ ስንቱን አስሮ ሥልጣን ላይ መቆየት ንደሚችል የሚታይ ይሆናል። 30 አመት ሙሉ አማራው ምሁር እና በድራግ የደነዘዘው ደደብ የአማራ ወጣት 30 አመት ሙሉ ተኝቶ ሰያንኮራፋ “ተነስ እያልኩ” ሰለ ተበደለው አማራ ጥብቅና ቆሜ ስቀሰቅሰው ቆይቼ ወያኔ እንዲወድቅ ብዙ ለፍቻለሁ። አሁን የራሴን ወገን ፍትህ አልባ በሆኑ ነብሰገዳዮችና ወንጀለኞች ሥልጣናቸውን መከታ አድርገው አንድ ሰው “ትግራይ ሆኖ በመወለዱ ብቻ” ማሰርና መግደል ከተጀመረ ቆሜ የማይበት ምክንያት የለኝም።

ዘንደሮ የሚለይልን ይመስለኛል። ወይ ኢንተርሃሙዌው መንግሥት ያሸንፋል ወይ ንጹሃን ያሸንፋሉ። ከሩዋንዳው ሁቱ እና ቱትሲ የዘር መጠፋፋት መማር ያልቻለ ካለ ቆይቶ የሚቆጨው ይሆናል።

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ)

Ethio Semay