Thursday, July 2, 2020

አድር ባይ የሃይማኖት መሪዎች እናንተን ሊወክሉ ይችላሉ እኔን ግን አይወክሉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Thursday, July 1, 2020

አድር ባይ የሃይማኖት መሪዎች እናንተን ሊወክሉ ይችላሉ እኔን ግን አይወክሉም
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
Thursday, July 1, 2020
ኢትዮጵያ ውስጥ ለ28 አመታት በፖለቲካ የተሾሙ የሃይማኖት መሪዎች ከስርዓቱ ጋር እየተሞዳሞዱ የቆዩ የአገሪቱ እሴቶች ሲናዱ  ዓይተው እንዳላዩ፤ አንዳንዴም ሰው እንዳይለኝ በሚል “በጽሑፍ ከማውገዝ አልፈው ጉዳቱን ላመስቆም ወይንም ሥርዓቱ ተጠያቂ እንዲሆን ጠበቅ ያለ ተከታታይ እርምጃ ሲወስዱ አልታዩም። እነዚህ የምታይዋቸው የሃይማኖት መሪ ተብየዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ለ27 አመት በወኔ ትግሬዎች፤ ዛሬ ደግሞ 2 አመት ሙሉ በኦነግ/ኢሕአዴግ/ኦሆድ (ብልጽግና) በሚል “የስም ለውጥ” ባደረጉ የኦሮሞ ፋሺስቶችና አሽከሮቻቸው የሆኑ የወንጀለኞች ጥምር መንግሥት “ስትቀጠቀጥ” ሰላም አጥታ ስትታመስ፤ ዛሬም አላባራ ያለው በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ሲፈጸም እንደ ሃይማኖት መሪዎች ማድረግ የሚገባቸውን ሃላፊነታቸው አልተወጡም፡ (ምናልበናት የካቶሊኩ መሪ በአንድ ወቅት የወያኔን ሥርዓት የወቀሱ ይመስለኛል (ማውገዝና መቃወም ግን ከወቀሳና ከመገሰጽ ይለያል)። ምናልባትም የፕሮተስታን መሪ ስማቸውን ረሳሁት “ኢትዮጵያ” ሲሉ የምወድላቸው፡ (ቄስ ጉዱና የሚባሉ ይመስሉኛል)። የተቀሩት ግን አይወራ ነው።

በትግሬዎች መንግሥት የተፈጸመው የአገር ክሕደት፤ አልበቃ ብሎ ዜጎች በነገዳቸው እየተለዩ መጨፍጨፍ፤መታሰር፤መገደል የደረሰው በደል እዚህ ለመዘርዘር ቦታ አይበቃውም። ሰላም ይመጣል ተብሎ ድጋፍ የተሰጠው “አብይ አሕመድ” የተባለ አደገኛ ሰው “አሳ ነባሪ” በሚል ከኢሳያስ አፈወርቅ የተሰጠው የምስጢር መለያ ተጠቅሞ የአገሪቱን ምስጢሮች “ለኦነግና ለሻዕቢያ” ሲያስተላልፍ የነበረ እምነተ ቢስ ግለሰብ ወደ ሥልጣን በመውጣት-  ከየ ቦታው የነበሩ ሁሉም ዓይነት አሸባሪዎችን ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ በማድረግ፤  “በተሰጠው አገር የማፍረስ አጀንዳ” መሰረት “አገሪቱ” አይታ ያላወቀቺው እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ጥቃቶች በሕዝብዋ ላይ አድርሷል።

ይህ ሲሆን እነዚህ የሃይማኖት መሪዎችም ዝምታን በመምረጥ “ተከታዮቻቸው ጥቃት ሲደርስባቸው”፤ “ተቋማቶቻቸው ሲፈራርሱባቸው” ሥርዓቱ እንደ መንግሥት እንዲሰራ ለማድረግ “መሬት አርዕድ” ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረግ ይልቅ ወደ አብይ አሕመድ ጽ/ቤት በመሄድ ሲሞዳሞዱለት አይቶ እሱም “ለሚደርስባችሁ ጥቃት እኔን ምን አድርግ ትሉኛላችሁ!! ሃላፊነቱንተ አልወስድም” ሲል እቅጩን ነግሮአቸው በወራቱ በርካታ ምዕመናን ሲገዱና ተቋማቶቻቸው ሲቃጠሉ፡ ጀሮ ዳባ ብለው ምዕመናኖቻቸውን ለተጨማሪ አደጋ እንዲጋለጡ ያደረጉ፤ አገሪቱ ወደ ጭንቅ ስትገባ ምንም ያልገደዳቸው “አድርባዮች ናቸው።

በሚገርም ሁኔታ ይህ ፋሺሰት መሪ በገጸ በረከት መልክ ከተዋህዶ ቤተክርስትያን ለባለቤቱ እና ለእርሱ “የወርቅ አልማዝ” የጣት ቀለበቶች ተሰጥቶታል።ብድራቸው ግን የተዋህዶ ምዕመናን እና ቀሳውስት ድያቆናት የአንገታቸው ማተብ እየተበጠሰ ሰንደቃላማቸው ከመስቀል እና ከጸናጽል ከከበሮ እየተቦጨቀ “አፈር ላይ” ተጥሎ እሱ በሚያስተዳድራቸው ፖሊሶች “በፖሊሶች ጫማ” ተረግጣለች። መሪ ተብየዎች  ግን “ዝም፤ዝም፤ ነው ያሉት”።

ከነዚህ አስመሳዮች በፊት የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች እራሳቸውን ለባንዳዎችም ሆነ ለባዕድ ወራሪ ላለመገዛት መስዋዕት እንደሆኑ እዚህ መዘከር ያስፈልጋል። መስዋዕቱ “አቡነ ጴጥሮስ” ባየች አገር እነዚህ “ነብሳቸውን የሚያስቀድሙ” በእኖር ባዮች አገር መመራት እጅግ ያማል።

መስዋዕቱ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በሕይወት እያለ ለእነዚህን አድርባይ የሃይማኖት መሪዎች የተናገረውን በወርቅ ቀለም የተጻፈ፤ እውነተኛ እና ወቅታዊ የአርበኛው ልሳን ጀሮአቸው ላይ ያስተጋባውን ደወል እዚህ ልጠቅስ ነው። ከመጥቀሴ በፊት ግን ጀኔራሉ ከነዚህ ነብሳቸው ከሚያፈቅሩ “መንፈሳውያን ነን” ከሚሉ መሪዎች በላይ ሃይማኖተኛ እንደነበር ሞረሽ ያሳተመው  ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያነበብኩትን በትንሽዋ ልጥቀስላችሁ።

“ ጄኔራሉን ዘጠኝ አመት በወያኔ ፅኑ እስር ቤት በእስራት የቆዩ፤ በእስር በነበሩበት ጊዜም አብረዋቸው ታስረው የነበሩት እነ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፆምና በፀሎት ስጋዊ ሰውነታቸውን ገትተው የሚኖሩ፤ የዚህ ዓለም ብልጭልጭ ኑሮ የማያታልላቸው መሆናቸውን ስለመሰከሩ፤ ጄኔራል ተፈራም  ”ጄኔራል አሳምነው በባህሪው ሃይማኖተኛ ነው።. ..በግሌ ለሃይማኖቱ በነበረው ቀናኢ ስሜት መንፈሳዊ ቅናት ያሳድርብኝ ነበር” በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ስለሰጡ፣ጄኔራሉ ከእስር ከተፈቱም ቀሪውን ጊዜያቸውን የዐማራን ሕዝብ በቅንነት ለማገልገል መወሰናቸውን ስለሚያውቅና በተግባርም ደፋ ቀና ሲሉ አማራው ጄኔራል አሳምነው ፅጌን እንደ ተራ ‘ነፍሰ -ገዳይ’ ወንጀለኛ ማየት ይከብደዋል።” ሲል ጠቅሰዋል።

አሁን ወደ እራሴ ትዝብት ልመልሳችሁ። ጀኔራሉ እውነተኛ የሃይማኖት ተከታይ ማድረግ ያለበትንና የተናገረውን በተግባር የተረጎመው “መስዋዕቱ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ” እነዚህ አድርባይ የሃይማኖት መሪዎች ከስርዓቶች ጋር ሲሞዳሞዱና ሲያቅማሙ 28 አመት ስለታዘባቸው ይህንን ታሪክ የማይረሳው በሕዝብ ፊት የተናገራቸውን ልጥቀስ።

እንዲህ ብሎ ነበር

“ አሁን እንዳለው ሁኔታ አይቀጥልም! አይቀጥልም!  አባቶቻችን ካሁን በኋላ የሽምግልና የድርድር ንግግር አታድርጉ፡ ሕሊናችሁ እና መሬት ላይ ያለው ለመናገር ሞክሩ፡ ከቻላችሁም እንደ አቡነ ጴጥሮስ ሁኑ!” ) ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ በሕዝብ እና በአስተዳዳር መካከል የተደረገ ውይይት ከተናገረው ንግግር የጠቀስኩት ጥቅስ።

ታዲያ አሁን የምናያቸው የሃይማኖት መሪዎች ይህንን የአቡነ ጴጥሮስን ቃል ኪዳን ለምን ጣሱ?  “ነብሰ ወዳዶች ስለሆኑ ? ወይንስ እየሱስ ክርስቶስ (ለክርሰትያኖቹ ነው አሁን የምለው) ስለ እኛ ሲል ስለተሰቀለ እኛ  መሞት የለብንም” ነው ማሳረጊያው?  “አባቶቻችን ካሁን በኋላ የሽምግልና የድርድር ንግግር አታድርጉ፡ ሕሊናችሁ እና መሬት ላይ ያለው ለመናገር ሞክሩ፡ ከቻላችሁም እንደ አቡነ ጴጥሮስ ሁኑ!” የሚለው ለምን ተግባራዊ ለማድረግ ፈሩ? ወይስ መሬት ላይ ያለው ሁኔታ “ሊታያቸው አልቻለም” ?

 ተቋማቶቻቸው እና ምዕመናኖቻቸው በቢላዋ ሲታረዱ ለማየት የሚያስችል ሕሊናቸው ያደነዘዘው “ስራይ” ምን ይሆን? መልሱ ልስጣችሁ ”አድርባይ/ ነብሰ ወዳድነት!” ነው። ግን ለምን? እኔ ተራው ዜጋ በአቅሜ ተወርቶ የማያልቅ ብዙ መስዋዕትነት ከፍያለሁ። እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ። የሃይመኖት መሪዎች ግን ከታች ያሉ በጣት የሚቆጠሩ “ባህታውያን” ካልሆኑ በስተቀር ትልልቆቹ ሃይማኖት መሪዎች ከፋሺሰቶች ጋር እየተሞዳሞዱ ልብስ እያሳመሩ 28 አመት እየተንፈላሰፉ እየኖሩ ነው። በደፈረሰው የፋሺስቶች ፖለቲካው ውስጥ ገብተውም ሲዳክሩ እያን ነው።

ትናንት እሮብዕ ቀን (7/1/20) “አጅግ የገረመኝ” ወደ 23 የሚያክሉ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ሲቪክ ተቋማት (ምሁራን ተብየዎች ጭምር) እነዚህን አድርባዮች እንደ ሃይማኖት መሪዎች አድርገው በመቀበል አብረው ያስተላለፉትን  መግለጫ ደግፈው አብረው መክነፋቸው የሚገርም ነው። እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ማድረግ የነበረባቸው 28 አመት ሙሉ “የሰው ደም እየጎረፈበት ካለው ከወልቃይ እስከ ሓረር፤ ከባሌ እስከ ጅማ ‘ ከከጅማ እስከ ጋምቤላ፤ ከምስራቅ እስከ ደቡብ ፤ከደቡብ እስከ ሰሜን” የአማራ እናቶች እርጉዞችና ዓይነስውሮች ከነ ነብሳቸው ወደ “እንቁፍቱ” ገደል እየተገፈተሩ ሲሞቱ አልሰሙም?

እስኪ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ነን ባዮች እና እነሱ ጋር አብረው እየከነፉ ያሉ ድጋፍ ሰጪዎችን ይህንን ላስታውሳቸው እና የሃይማኖት መሪዎቻችሁ ይህንን አልሰሙ እንደሆነ ላስታውሳቸው (እናንተንም ጭምር)፡

በገልባጭ መኪናዎች ሬሳዎች ወደ ጫካ ወስደው እንዴት ይገለብጥዋቸው እንደነበረ ተሸሽጎ ሲያይ የነበረ የዓይን ምስክር ላቀርብላችሁ ነው።

በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ከተደረጉት ጭፍጨፋዎች እንደ ገለምሶ ዕልቂት የሚያክል የለም። ለብዙ አመታት የቆየ በዐማራው ነገድ ላይ የተፈጸመ ግፍ ነው አሁን የማሳያችሁ። በገለምሶ አካባቢ ባሉ ወፊ፤ዳንሴ፤አንጫራና ገለምሶ ከተማ ዐማሮችና ክርስትያኖች እየተለቀሙ ተያዙ፡ በሀቡር ወረዳ “ጥርሶ ገደል” እየታረዱ ተጣሉ። የተገደሉት፤ እንዳሁኖቹ አሸባሪዎች የራስ ቅላቸው ከአንገታቸው ላይ በሜንጫ እየተቀላ ነው። አንድ ገልባጭ መኪና ሬሳዎች ከሌላ ቦታ አምጥተው ገለምሶ አውሳይድ ወንዝ አጠገብ ካለ ጫካ ሲገለብጡ ያየ ሰው ደግሞ ምስክርነቱን እንዲህ ይገልጸዋል።

“አውሳይድ ወንዝ አጠገብ ወደ ወፍቆሎ ጫካ ሲገለብጡት ተደብቄ እመለከት ነበር። ሙሉ ሽበት ያለበት፤ግራጫ የመሰለ፤አልፎ አልፎ ሽበት ጣል ያደረገበት፤ሙሉ ጥቁር የሆነውና ራስ በራ የሆነው ጭንቅላቶች ሲገለበጡ በዓይኔ አይቻለሁ። በእርግጥ የመኪናው የኋላ እቃ መጫኛ አልሞላም። ቢሆንም ግን ያየሁት “ጭንቅላት” ከሁለት ጆኒያ ይበልጣል።” ሲል የዓይን ምስክር “ምጽአተ አማራ” በሚል መጽሐፍ ተጠቅሷል።

እንዲህ ያለ የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት የሚያስንቅ የ28 አመት ያለተዘገቡ ጭፍጨፋዎች እና ወንጀሎች አገሪቱ ላይ ሲፈጸም፤ እነዚህ  እርቅና ድርድር እያሉ ከስርዓቶች እና ወንጀለኞች ጋር ሲደራደሩና ሲመዳሞዱ፤ እንዲህ ያለ ዕልቂት ግን ለማስቆም ምዕመናኖቻቸው አነሳስተው መንግሥትን እና ወንጀለኞችን ለማስቆም እግዚሃር የሰጣቸው “ሃሞት” ሊደፍር አልቻለም። ለምን? መልሱ ስጋን መውደድ ነው። (ልኑር ባይነት) ነው።

የሃይማኖት መሪዎች ሊከተሉት የሚገባ ሥጋዊ ባሕሪ ስለተጠናወታቸው ነው እንዲህ ያሉ ዘግናኝ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ሊያስቆሙት ያልቻሉት።እነ ባሕታዊ ፈቃደ ስላሴ እና የመሳሰሉ እጅግ የሚመሰገኑ ባህታውያን ኢትዮጵያ አብቅላ ነበር ግን ባለ ስጋ ወዳዶቹ በረትዋቸው።  የሙታኖች አጽም ዛሬም ወደ እግዚሃር እንጂ ወደ ሃይማኖት መሪዎች አይጮህም።ሩዋንዳና ኡጋንዳ የካቶሊክ መሪዎች ለሕዝብ ሲሉ ተሰውተዋል፡ ኢትዮጵያም አቡነ ጴጥሮስ እና አያሌ ሃይማኖታዊ አባቶች “አንገዛም” ምዕመናኖቻችንን አናስገድልም ብለው የተሰው አያሌ አባቶች አልፈዋል። እነዚህ ግን 28 አመት እንደ መዥገር ከገዢዎቹ ጋር እየተሞዳሞዱ አብረው እየተጓዙ ሕዝቡ ግን ወደ ማይቀረው ዓለም ባጭር እየተቀጠፈ በጋጠ ወጥ እና በመንግሥት ታጣቂዎች ጥይት እየተቆላ ላንዴና ለመጨረሻ ሕልፈቱ ያለፍትሕ ባሳዛኝ አገዳደል ሳይልፍለት እየተሰናበተ ነው።  እኛ  በሃይማኖት መሪዎቻችንም ጭምር ተከድተናል። 


ጌታ ሆይ የሃይማኖት መሪዎች ነብሰወዳድ ሆነዋል እና አንተው አቤቱ ምሕረትህን እና ዳኝነትህን ባስቾኳይ ስጥ!

Note :- to my facebook friends-
 አመሰግናለሁ፤፡ለኔ የምስጋና አውራ ጣት መስጠት ትረጉም አይሰጠኝም። ትርጉም የሚሰጠኝ ሃላፊነታችሁን ለመወጣት ለወዳጆቻችሁና አገር ላሉትንም አሳልፉት “ሼር” አድርጉት
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)