Monday, December 31, 2018

የቀድሞ የ ኢንሳ ሓላፊ ወያኔው ተ/ብርሃን ወ/አረጋይ አጋአዚያንን በማጠናከር የተቀመጠበት ስብሰባ የፎቶ ማሕደር ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)


የቀድሞ  የ ኢንሳ ሓላፊ ወያኔው ተ/ብርሃን ወ/አረጋይ አጋአዚያንን በማጠናከር የተቀመጠበት ስብሰባ የፎቶ ማሕደር
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

በዚህ የፎቶ ትንተና ዝርዝር ዘገባ እየሰራሁኝ ስለሆነ ለጊዜው ጠብቁኝ እና ፎቶግራፎቹን ብቻ ለዛሬ አቅርብላችሗለሁ። ለaan media ምሳጋና አቀርባለሁ።
ስብሰባው የተካሄደው መቀሌ ውስጥ ሲሆን ከግራ በኩል የታዩት አንዳንዱን በፎቶግራፍ የሚታዩት፤-የፋሺሰት ወያኔ መንግሥት የኢንሳ ሓላፊ የነበረው ተ/ብርሃን ወ/አረጋይ፤በጸረ አማራነት የሚታወቀው የትግሬዎች ፋሺሰት ንቅናቄ አስተማሪው ሽማግሌው መምሕር ገ/ኪዳን ደስታ፤ እመሃል ፊት ለፊት የተቀመጠው ደግሞ የሆርን አፈይርስ ኦን ላይን ማገዚን አዘጋጅ ትግርኛ ቋንቋ የማይናገር አዲስ አበባ ያደገው ወያኔው ዳንኤል ብርሃኔ እና የመሳሰሉ ወያኔዎች ሲሆኑ፤-

ወደ ቀኝ በኩል የሚገኙት ድግሞ በእንግሊዝ አገር የሚኖር የዋናው የአጋአዚያን ክፍል መሪው እዮብ በርሔ (ቅጽል ስሙ ተስፋጽዮን በማለት ራሱን የሚጠራ) ነው። ይህ ሰው በመላ ዓለም የሚገኙ እንዲሁም በዋናነት ደግሞ  እስራል አገር እና በመሳሰሉ አገሮች ውስጥ የሚገኙ በጸረ እስልምና እና በጸረ አማራ የተደራጁ ኤርትራኖች እና ትግሬ ክርስትያነችን ይመራል። ድርጅቱ የእስራሎች ማሕተም በማዳበል የቤተክርሰትያን አናት ላይ የሚተከል የአክሱም ጽዮን መስቀል ቅርንጫፎች ምስል ያለበት ነጭ እና ቀይ አንዲሁም ሰማያዊ ቀለም የተሰመረበት የራሳቸውን የአጋዚ ባንዴረ እና ማሕትም አዘጋጅተው የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ እና የትግራይ ክርስትያን ትግርኛ ተናጋሪ ማሕበረሰቦች (ትግራይ ትግርኚ) ንቅናቄ ቅርንጫፎችን ይመራል። እንግሊዝ አገር በሌብነት ተይዞ ነበር የሚባልለት እዮብ ገብረስላሴ በቅጽል ስሙ “ተስፋጽዮን” በሚል በየ ዩቱብ ላይ ማድመጥ ትችላላችሁ። ይህ የአጋዚያኖች ሙላሕ የትግራይ ትግርኚ የታሊባን ሕሊና ርዕዮት በማካሄድ “የራሱ ካልቶችን” በማደራጀት ጸረ እስላም እና ጸረ አማራ አክራሪ ሃይላትን በብዛት በመመልመል የሚገኝ አደገኛ ሰው ነው።

አብረውት በቀኝ በኩል በመደዳ የተቀመጡት ደግሞ ከውጭ አብረውት የመጡት እና ከውስጥ ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ጸረ  አማራ እና ጸረ እስላም አክራሪ የአጋዚ አባሎች እና አመራሮች ናቸው። ስብሰባው የተካሄደው ያው ወያኔዎች በመደቡላቸው ባጀት እና መስተንግዶ ትግራይ ውስጥ ነው የተካሄደው። ሰፊውን ዘገባ እየሰራሁበት ስለሆነ ዘገባው ሲጠናቀቅ አቀርብላችሗላሁ። በስብሰባው ውስጥ ሰብ ሕድሪ የተባለ ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀስ  “ፋሽስት ንቅናቄ” ሕጋዊ እና በዓለም ውስጥም ተገቢ ሥድራውን እየያዘ የሚገኝ ማደግ ያለበት እንቅስቃሴ ነው ብሎ በግልጽ  የሚሰብክ እጅግ አክራሪ ወጣት ክፍል ያቀፈ አማራን ለማጥፋት እና ኢትዮጵያን ለመበተን በግሃድ በአውራምባ ታይምስ ዩቱብ ሚዲያ መልእክቱን የሚያሰራጨው አደገኛ አክራሪ ድርጅትም አለበት።

አስቀድሜ አንደገለጽኩት ደጋግሜ ካሁን በፊት የሰጡሁት ሰነድ ስለሆነ ያንን ያልተመለከታችሁ ካላችሁ ዛሬም በድጋሚ ማስረጃውን ለማየት አጋዚያን ማለት በወያኔ ማኒፌስቶ መሰረት ወደ አክሱም ተሰድደው የመጡ ከዓረብ ዓለም የፈለሱ የዓረብ ዘሮች ማለት ሲሆን ወያኔ የፈለፈላቸው የዛሬዎቹ ወያኔ ጫጩቶች ደገግሞ ፤አጋዚያን’ ማለት “ትግርኛ ቋንቋ የሚናገሩ ኤርትራ እና ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪ እስላሞች ሳይጨምር ትግርኛ የሚናገሩ ክርስትያን ትግሬዎች አጋዚያን ይባላሉ” የሚል ትርጉም ይሰጡታል።

ስለሆነም በወያኔ ማኒሰፌስቶ ሜይ 1983 ኣጋዚአን እነማን መሆናቸው ሲነግረን እንዲህ ይላል

     “The people of Tigray have a rich history of thousands of years. In the past, they were Known by various names such as Axumites, Habeshas, etc. Before 1000 BC, present day Tigray was inhabited by Nilotic and Hametic peoples of African origin, who led a primitive communual life…..the tribes of South Arabian origin known as the Sabean, Agazeans, Habeshats, and Himyarites began to cross the Red Sea and settle in the areas which are todayTigray and Eritrea. These tribes were at a more advanced stage of development than the indigenous people. / People’s Democratic programm of TPLF, May 1983) “

የአዶሊሱ ንጉሥ በሃውልቱ ላይ ጽፎ የተወው ጽሑፍ ደግሞ አጋዚአን  የመሳሰሉትን በውግያ አስገብሮ እንደያዛቸው ይናገራል። እነዚህ አጋዚአያን የሚባሉ በወያኔ ማኒፌስቶ እና በአዱሊሱ የንጉሱ ሃውልት የተጠቀሱት ናቸው።  የዛሬ ትግሬዎች ማንነታቸው ፍለጋ ወደ ላ በመሄድ እራሳቸውን ወደ ጭለማ ዓለም በማስገባት የሕሊና ቀውስ ውስጥ በመሄድ ‘የፋሺት’ ንቅናቄ በማካሄድ ተንሰተው የምናያቸው ምክንያት በማንነታቸው ውስጥ የሚረብሻቸው የበታችነት ስሜት ወይንም የሚረብሻቸው “የበላይነት ፍላጋ” ወደ ላው ወደ ጭለማው ዓለም የሚያስገሰግሳቸው አንዳች ነገር እንዳለ አመላካች ነው። ፋሺስቶች በዚህ በጣም የታወቁ ናቸው። ወደ ላ ቁፋሮ በመሄድ ያልሆኑትን ለመሆን የሚጥሩ የበላይነት ነበራችሁ እንዲባሉ ከውስጥ ስሜት የሚጋፈጣቸው አንዳች ነገር ለማምለጥ ሲሉ የማይፈነቅሉት የታሪክ መረጃ የለም።  ስለ የወያኔ አጋዚያን በሚቀጥለው ሳምንት ስለምንመለስበት እዚህ ላቁም እና ስለ ሌሎቹ የወያኔ ጫጩቶች አንድ ልበል እና ልደምድም።

ብዙ ሰዎች ዓረና ስለተባለ የወያኔ ጫጩት ያልገባቸው ነገር ስላለ አንድ ነገር ልበል።

ከዚህ አያይዤ ልገልጽ የምፈልገው ዓረና እንዲህ አለ ወያኔን ተጋፈጠ ወዘተ…..እያላችሁ እራሳችሁ የምታታልሉ የሚዲያ አውታሮች ዓረናን ከማቆላመጥ ታቀቡ። ዓረና ማለት ብዙ ህይወት ያጠፉ የወያኔ አንጋፋ መሪዎች የነበሩ አሁን ከዚህ ድረጅት ውስጥ ያሉበት፤ በዘመነ ወያኔ ተወልደው አድገው በወያኔ ሕሊና አስተሳሰብ የታጠቡ ወያኔ በዕንቁላልነታቸው ቀፍቅፎ ያሳደጋቸው የወያኔ ጫጩቶች ናቸው። ይህንን ካለመናችሁ ከመሪያቸው አብርሃ ደስታ ጀምሮ የሚሉትን መፈተሽ አለባችሁ።

አብርሃ ደስታ፡
“ከመለስ ዜናዊ ይልቅ ለኔ ጠላቴ ምኒሊክ ነው”።

ስለተፈላጊ የወያኔ ወንጀለኞችም ሲናገር እንዲህ ይላል፦

በትግርኛ
አሕሊፍና አይክንህቦምን፤ ክገዝኡና ግን አይክነፍቅደሎምን! 

አማርኛ ትርጉም

 አሳልፈን አንሰጣቸውም  ሊገዙን ግን አንፈቅድላቸውም (አብርሃ ደስታ በፌስ ቡክ ያስተላለፈው የህወሓት ወገንተኛነቱን ጋሃድ ሲያደርግ)።
      
ኪዳነ አመነ (የዓረና ሥራ አስፈጻሚ አባል) -

 ይህ ወጣት ከተፈለፈሉት ታዳጊ የወያኔ ጫጩቶች አንዱ ነው። በትግራይ ግራ አክራሪ ፋሺስዝም ቅኝትም የተቀኘ ወጣት ለመሆኑ አትጠራጠሩ።

 እንዲህ ይላል፤-

“…በፖቲካ ካልኩለሽን (ቅመራ ማለቱ ነው) ሰለክቲቭሊ (ያነጣጠረ ሴራ ማለቱ ነው) ደክዩመንትሪ ፊልም (የፊልም ዘገባ ማለቱ ነው) በትግራይ ሕዝብ ላይ ተሰርቷል። ይህም ከሁለት ብሔር የተመረጡ ከአማራ ክልል እና ከኦሮሞ ክልል ታሳሪዎች ‘ትግርኛ ተናጋሪው እንደዚህ አደረገኝ እንዲሉ ተደረገ” ነው።”

በመቀጠል እንዲህ ይላል   በፊልም ዘገባ የታዩ ስቃይ ደርሶብናል ባዮቹ አጥፊውን ማለትም የኢሕአዴግ ሥርዓት እንደዘህ አደረገኝ፤ ማለት ሲገባቸው፤ አንደዚያ ማለት ካልቻሉም ህወሓት ነው እንዲህ ያደረገኝ፤ ከህወሓት ውስጥም እገሌ የተባለ ሰው ነው አንዲህ ያደረገኝ ማለት ሲገባቸው፤ “ትግርኛ ተናጋሪ ነው አንዲህ ያደረገኝ   እንዲሉ ተደረገዋል። የዓረና አባላት ከነዚህ በላይ ግፍ የደረሰባቸው አሉ። “

 በማለት እጅግ ነውረኛ የሆነ እንዲሉ ተደርጓል” የሚለው ዓይን ያፈጠጠ የውሸት ውንጀላ እና አሳባቂ ምስክርነቱን አስደምጦናል። ያለ ማፈር ደግሞ ግብረሰዶም የተፈጸመባቸው እና ጎሳቸው እየተነሳ ሽንት በላያቸው ላይ የሚሸናባቸው፤ ወንድ እስረኞችም ሆኑ ሴት እስረኞች፤ ሌላ ቀርቶ “በድብዳባ የተሰቃየ ባለው እስረኛ ፊት ላይ ቀመው ልብሳቸውን አውልቀው እራቁታቸው የሚሻፍዱና የሚያንቋልጡ” ነውረኛ ሴት መርማሪዎች በዓረና ታሳሪዎች ተፈጽሟል የሚል ከሆነ ማስረጃው አላሳየንም። ኪዳነ አመነ የዓረና አባላት ከነዚህ በላይ (አርሱ ትግራይ ሕዝብ ለመወንጀል “ትግርኛ ተናጋሪ ነው አንዲህ ያደረገኝ   እንዲሉ ተደረገዋል።  የሚላቸው የአማራ እና የኦሮሞ ታሳሪዎችን (ትግርኛ ተናጋሪ ነው በሉ ተብለው ተመርተው/ተሰብከው ነው) እያለ እየወነጀላቸው ያለው ግፍ የተፈጸመባቸው ዜጎቻችን) ዓረናዎች ከዚህ በላይ የበለጠ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል የሚል ከሆነ ማስረጃውን ለማውጣት ማን ከለከለው። ዩ-ትዩብ- እና ፌስ ቡክ ሚዲያው ክፍት ነው!! አደለም እንዴ?

የሚገርመው ደግሞ “አብይ  አሕመድ ጸረ ትግሬ ነው”፤የአማራ ሚዲያ ጋዜጠኖች ጸረ ትግሬ ናቸው” ሲል ይወነጅላቸዋል። ለዚህ ነው ዓረና ማለት ወያኔ የቀፈቀፋቸው የወያኔ ጫጩቶች ናቸው የምላችሁ።  

አብርሃም አስራት፡
ይህ ደግሞ አንድነት ፓርቲ ምናምን እያለ ሲሸውዳችሁ የነበረ ነው። እልም ያለ ጸረ ምኒሊክ ነው። መ ኢ አ ድ ን የሚኒሊክ ናፋቂዎች ይላቸዋል። በላፈው ኤል ቲ ቪ በተባለ ከኪዳነ አመነ (ዓረና) አረጋዊ በርሔ፤ አበበ ተ/ሃይማኖት እና እርሱ ለውይይት ተጋብዘው በነበሩበት ወቅት እንዲህ ይላል፡-

“የድምበር እና የማንነት ኮሚሽን” ጸረ ሕገ መንግሥት ነው፡ ሕገ መንግሥቱን ይጻረራል። ሕገ መንግሥቱ መከበር አለበት” ይላል።እንግዲህ የታያችሁ - ሕገ መንግሥት እያለ ያለው ፋሺሰቶች የመሰረቱት የአፓርታይድ ሕገ መንገሥትን ነው። ይህ ሕገ መንግሥት ለ27 አመት እልቂት አምጠቶብናል ብሎ ሕዝቡ እንዳልጮኸ ሁሉ አብርሃም አስራት ሕገ መንግሥት ተጥሷል ይላል። ወያኔዎች እና ጸረ አማራው ወንጀለኛው ኦነግ ያረቀቀው ሕገ መንግሥትን ነው “ይከበር” እያለን ያለው። ሕገ መንግሥት ይከበር የሚሉት ደግሞ አስገራሚው “ትግሬዎች እና ኦነጎች ብቻ ናቸው/በብዛት”።  ‘አማራዎችም ሆኑ “ዜጎች” (ብሄር፤ብሔረሰቦች ሕዝቦች የሚለባሉትን አላልኩም) ሕገ መንግሥቱ አያውቃቸውም። አይወክላቸውም፤ሲፀድቅ አልነበሩም፤አልተጠየቁም። ብሔር የለኝም ለሚል ዜጋ መብቱ የት አንደሚሆን አይታወቅም።

አብርሃም አስራት የሚባለው ጉደኛ ነው፦ይህ ብቻ እንዳይመስላችሁ- ባለፉት ወራት ወያኔ ባዘጋጀው የትግራይ ምሁራን ሰሚናር፤ “ትግራይን ለማስገንጠል እንዲመቻቸው” ትግራይን ማእከል ያደረገ ትኩረት አድርገን ምጣኔ ሃብታችንን እንዴት ወደ ትግራይ አምጥተን ማሳደግ ይቻላል የሚል ስብሰባ ሲደረግ አብርሃም አስራት የሰጠው አስተያየት “አዲስ አበባ ብዙ በትግራይ ማሕበረሰቦች የተገነቡ በሚሊዮኖች የመያወጡ ፎቆች እና የንግድ ተቁዋሞች አሉ። እነሱን ከዚያ አስመጥተን እዚህ ትግራይ ውስጥ በመትከል ትግራይ እራስዋን እንድትችል ማድረግ ይቻላል”። ይላል። ኢትዮጵያ ሰላም የለም ትግራይ ሰላም አለ፤ ስለዚህ ባለ ሃብቶቹ ሃብታቸው ይዘው ወደ ትግራይ ይምጡ” ሲል ተናገሯል። ይህ የትግራይ ትግርኚ ምስረታ አንዱ ምክር ነው።

 ከአውሮጳ የመጣው ጉዑሽ በርሄ የተባለ ሪሰርቸር ነኝ ባይ ለትግራይ አማራጭ (አንቀጽ 39 ለመጠቀም እንዲያስችል ለተሰብሳቢው ትምሕርት ሲሰጥ) እንደገለጸው “ትግራይ በምጣኔ ሃብት ትኩረታችን ካደረግን የቅርብ ክልሎች/አማራውን ሸቃይ በማድረግ/ወደ ትግራይ ኢንዳስትሪ ሥራ ፈላጊ/ በማድረግም ይሁን ሌሎች የትግራይ ቅርብ ጎረቤቶች የምጣኔ ምንጭ አከፋፋይ እንድንሆን፤ራሳችን እንድንችል ምሁራን ሃሳባችሁ ለግሱ ባለው መንገድ ነው “አብርሃም አስራትም” በህወሓት የቲ/ቪ ክፍለጊዜ ቃለመጠይቅ ሲደረግለትም ትግራይን የአፍሪቃ “ታይገር” እንዴት አንደሚቻል ሃሳብ የሰነዘረው።

ስለዚህ የትግራይ ኤሊቶች አጅግ በጣም በጣት የሚቆጠሩ ከተገኙ እንጂ ብዙዎቹ ከብሔረተኛነት ጭቃ ያልወጡ፤ከተረገረጉበት አሳፋሪ ታሪክ ለመውጣት የማይሹ ‘ታጥቦ ጭቃዎች” ስለሆኑ ተስፋችሁን ቁረጡ።

 ትግሬዎች ወያኔን መታገል አይፈልጉም ብለን ብዙ ጊዜ ተናግረናል። ወያኔ በትግራይ ልሂቃን የታቀፈ ፋሺሰት ነው፤ ስለሆነም ትግራይ ውስጥ ከባድ ጦርነት አስነስተው የትግራይ ሕዝብ ወደ እሳት ሊማግዱት ተዘጋጅተዋል ብለን ለበርካታ አመታት ተናግረናል። ይኸው እነ ተኽለብርሃን ፥ እነ ሙሉወርቅ ፥ እነ መሓሪ ዮሀንስ (የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነው፦ ይህ ወጣት ሳየው ጣሊያናዊው ወጣት ሙሶሎኒ ተመስሎ ይታየኛል። ባካባቢው ድንገት በታአምር ጤነኛ ፖለቲከኞች   ካሉ  ከወዲሁ እልባት ካልተደረገለት ወጣቱ  ያልተራ ወጣት ከመሆኑ የተነሳ ለሰው ልጆች ሕልውና እጅግ አስፈሪ እና “ለትግራይ እና ለአካባቢው ምናልባትም ለኢትዮጵያ በጣም አደገኛ አክራሪ ሊሆን የሚችል ወጣት ነው ብየ ስጋቴ ከወዲሁ ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ)። ከነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ እነ ደብረጽዮን እነ ስብሓት ነጋ እነ ገብረኪዳን ደስታ ትግራይ ትግርኚን ለመመስረት ተነስተዋል። በዚህ ሽፋን ብዙ የወያኔ ወንጀለኞች የወንጀላቸው መደበቂያ ሰበብ እየፈለጉ ነው ማለት ነው።

ለበርካታ አመታት ስነግራችሁ አናምንህም ብላችሁ “የትግራይ ሕዝብ የትግራይ ሕዝብ አይገነጠልም ስትሉ” ሕዝብ የሚባለው ማነው? ብለን ስንጠይቅ ገበሬው ትላላችሁ፡ ገበሬው በታሪክ ወሳኝ ሆኖም አያውቅም “ሊሂቁ” ነው ስንልም አትሰሙም። ሕዝብ ወሳኝ ሆኖ ከነበረ ከዛሬ የበለጠ ወያኔን ለመጣል  አመች ወቅት የት ሊገኝ ነው? መላው አገሪቱ ወያኔን በተቃወመበት ወቅት ዛሬ ድጋፍ እያላቸው ካልተነሱ መቸ ሊነሱ ብላችሁ ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?!!!!!!!!!!! ሕዝብ ለምትሉት ክፍል የምሰጋለት ነገር ቢኖር ካሁኑኑ የሚሻውን ጠነኛ መንገድ ካልፈለገ “ከዶፍ ዝናብ በኋላ ከለላ ፍለጋ እንዳይሆን ግን እሰጋለሁ”።
አበቃሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)